Wednesday, May 23, 2012

ማክሰኞ ጠዋት የቅዱስ ሲኖዶስ ውሎ


• (ሰበር ዜና) ማኅበረቅዱሳን ከሠንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መመረያ ሰር መመራቱ ቀርቶ ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ቤተክህነቱ ሥራአስኪያጅ እንዲሆን ተወሰነ፡፡
• የተሃድሶ አራማጅ ድርጅቶች ተወገዙ፡፡በህግም ይጠየቃሉ፡፡
• መ/ር እንቁ ባህርይ ተከስተ ጉዳይ እንደባለፈው ጥቅምቱ ሲኖዶስ ተደባብሶ ታለፈ፡፡


(አንድ አድርገን ግንቦት 15 ፤ 2004ዓ.ም )፡- በዛሬ ጠዋት በትናንቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ በተወሰነው መሰረት በማኅረቅዱሳንና በማደራጃ መምሪያው ስለተፈጠረው ችግር መላእከ ጽዮን ቆሞስ አባ ሕሩይ ወንድይፍራውና የማኅበሩ አመራሮች ምልዓተ ጉባኤ ቀርበው እንደሚያስረዱ ሲጠበቅ የነበረ ቢሆንም ምልዓተ ጉባኤው የማኅበሩን አገልግሎት እያደናቀፈው ያለው የመምሪያው ማኅበሩን የመምራት አቅም ማነስ በመሆኑ ማህበሩ ለጠቅላይ ሥራአስከያጁ ተጠሪ እንዲሆን ወስኗል፡፡ 
ምልአተ ጉባኤው የማኅበሩ አገልግሎት መስፋት፣ከጠቅላይ ቤተክህነቱ መምሪያዎች ጋር የሚተካከሉ የአገልግሎት ክፍሎች ያሉት በመሆኑ የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የመምራት አቅም ስሌለው ለጠቅላይ ሥራአስኪያጁ ተጠሪ እንዲሆኑ ወስኗል፡፡ በሊቀጳጳስ እንዲመራ መሆኑ የማኅበሩ አገልግሎት እንደሚያፋጥነው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤው ተስፋ አድርጎል፡፡ ማኅበሩ ከጠቅላይ ሥራአስኪያጁ ጋር ስለሚኖው አሰራር ለጥቅምቱ ሲኖዶስ ተጠንቶ እንዲቀርብ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ የማህበረቅዱሳን ጉዳይ በዚህ መልኩ እልባት ቢሰጠውም የመ/ር እንቁ ባህርይ ተከስተ ጉዳይ እንደባለፈው ጥቅምቱ ሲኖዶስ ተደባብሶ ታለፏል፡፡ “ማህበረቅዱሳን የመምራት አቅም እንደሌለው ከታወቀ፤ እንዴት የአትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሠንበት ት/ቤቶች መምራት ይችላል?” ተብሎ ቦታው ላይ እንዲቆይ ተድበስብሶ እንዲታለፍ መደረጉ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉትን ሁሉ አሳዝኗል፡፡ ይህን ተከትሎ የአዲስ አበባ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ተቃውሟቸውን እየገለጹ ነው፡፡



የተሃድሶ አራማጅ ድርጅቶችና ግለሰቦችን በተመለከተ በማሕበረቅዱሳን በኩል መረጃዎች ቀርበው፣ የሊቃውንት ጉባኤ አጣርቶ፣ ለሊቃነ ጳጳሳት ኮሜቴ ባቀረበው ሪፖርት መሰረት ቅዱስ ሲኖዶስ ማኅበራቱን አውግዟል፡፡በህግ እንዲጠየቁም ትእዛዝ አስተላልፏል፡፡

የማኀበራቱ ስም
1. የእውነት ቃል አገልግሎት
2. የቅድስት ልደታ ለማርያም መንፈሳዊ ማኅበር
3. አንቀጸ ብርሃን
4. የምሥራች አገልግሎት
5. ማኅበረ በኵር
6. ማኅበረ ሰላማ

በግለሰቦቹም ላይ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ተመሳሳይ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ቸር ወሬ ያሰማን!

1 comment: