Wednesday, May 16, 2012

የቅዱስ ሲኖዶስ ስድስተኛ ቀን ውሎ (አርእስተ ጉዳይ)

ኢትዮጵያ ውስጥ ብሎጋችንን ለማንበበብ ይህን ሊንክ ይጠቀሙ

/ ሲኖዶስ በፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አራማጅ ማኅበራትና ግለሰቦች ላይ የተዘጋጀውን ሪፖርት አዳመጠ

(ደጀ ሰላም፤ ግንቦት 8/2004 ዓ.ም፤ May 16/ 2012/ 
· ኮሚቴው ፍጹም ውግዘት የሚገባቸውን የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ እንቅስቃሴ አራማጅ ማኅበራትና ግለሰቦች ለይቷል - ማኅበረ ሰላማ፣ ማኅበረ በኵር፣ የምሥራች አገልግሎት፣ አንቀጸ ብርሃን፣ የቅድስት ልደታ ለማርያም መንፈሳዊ ማኅበር፣ የኢትዮጵያ መንፈሳዊ ተሐድሶ ኅብረት፣ አሸናፊ መኰንን፣ አግዛቸው ተፈራ፣ ጽጌ ስጦታው እና ግርማ በቀለ ይገኙባቸዋል

· “ሃይማኖቴ እንደ አባቶቼ ነው” ያሉት የአባ ሰረቀ እና “የቅን ልቦና የመንፈሳዊና የፈውስ አገልግሎትን ያቋቋምኹት ልጆቼን የማበላቸው ስለተቸገርኹ ነው” ያሉት የ‹ሊቀ ካህናት› ጌታቸው ዶኒ ጉዳይ ያለውሳኔ ሐሳብ ለምልአተ ጉባኤው ውሳኔ ቀርቧል
· አባ ጳውሎስ ከጥንተ አብሶ ጋራ በተያያዘ ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ንጽሕና እንዲመሰክሩ ሊጠየቁ ይችላሉ
· ሊቃውንት ጉባኤው ተደጋጋሚ ጥሪ አድርጎለት ያልቀረበው በጋሻው ደሳለኝ ዛሬ ጠዋት የሊቃውንት ጉባኤውን ሰብሳቢ በእጅጋየሁ በየነ አማላጅነት ሲለማመጥ ታይቷል፤ ሊቃውንት ጉባኤው “በአንድ ወቅት በራስ ቅል ኮረብታ ላይ ኢየሱስና ዲያቢሎስ ቁማር ተጫወቱ . . . ዲያቢሎስም በጨበጣ ገባ” የሚለውና ሌሎቹም ጥንቃቄ የጎደላቸው ንግግሮቹ ፍጹም ውግዘት የሚገባቸው እንደኾኑ አመልክቷል
· የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን አመራርና መዋቅር ይሻሻላል፤ በጠቅላላ ጉባኤና በቦርድ ይመራል፤ የኮሚሽኑ ሊቀ ጳጳስ የኮሚሽኑ ኮሚሽነር እንደሚኾኑ ተጠቁሟል
· የማኅበራት መመሪያ ረቂቅ ለውይይት ቀርቧል፤ አሁን ባሉበት አኳኋን ከቀጠሉ “ሌላ ሲኖዶስ ይኾናሉ፤ የፖቲካ ዓላማ ማስፈጸሚያ ይኾናሉ፤ በቀኝ ዘመምና ግራ ዘመም አቋም ቤተ ክርስቲያኒቷን ይውጣሉ/ይከፍላሉ” የሚል ስጋት የቀረበባቸው ማኅበራት ንብረት በአጥቢያ አብያተ ክርስቲያን መዋቅር ውስጥ ተጠቃልሎ እንዲተዳደር ሐሳብ ቀርቧል፤ የመመሪያውን ረቂቅ በጥንቃቄ የተመለከቱት የምልአተ ጉባኤው አባላት ጉዳዩ በይደር እንዲታይ አድርገዋል

ቸር ወሬ ያሰማን፤ አሜን

9 comments:

 1. haile michael zedebretsigeMay 16, 2012 at 11:50 PM

  የቅድሰት ቤተክርስቲያን የመጨረሻው የላዕላይ ሥልጣን ያለው ቅዱስ ስኖደስ እንደሆነ ይታወቃል :: ይህ ቅዱስ ስኖደስ የሚወስናቸው ውሳኔዎች በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ለቤተክርስቲያን የሚበጁ እንደሆነ ተግባራዊም መደረግ እነዳሉበት እሙን ነው::ነገር ግን ቅዱስ ስኖደስ የሚወስናቸው ውሳኔዎች በፓትርያርኩ እምብተኝነት በመንግሥት ከለላ ሰጭነት ተግባራዊ መደረግ ከተተው ቆይቶአል፡፡ ቅዱስ ስኖደስም ጥርስ የሌለው አንበሳ ሆኖአል ማለት ይቻላል፡፡ይህን በማየታችንም የቅድሰት ቤተክርስቲያን ልጆች በቁጭት ከመብገን ባለፈ መፍትሔ ማምጣት አልቻልንም፡፡ይልቁንም መፍትሔ ማማጣት ያለባቸው አባቶች ጳጳሳት ብቻ እንደሆኑ በማመን በአባቶች ላይ ያለንን ተስፋ እስከ መቁረጥ የደረስንም አለን፡፡ ይህንንም በደጀ ሰላም በአንድ አድርገን የጡመራ መድረኮች ከምሰጡ አስተያያቶች መረዳት ይቻላል፡፡  ስጀምር ስለ ቤተክርስቲያን ችግር እንደየሚናችን ሁላችንንም እንደሚያገባን መረዳት አለብን ፡፡አባቶች ድቁና ቅስና ልሾሙ እኛ ምእመናን የሚንመሰክርበት አሠራር መኖር አለበት፡፡ እርግጥ ነው ሊያሥር ልፈታ ልያጠምቅ ቀድሶ ልያቆርብ አንድ ሰው የግድ ቅስናና ከዚያ በላይ የክህነት ደረጃ ልኖረው ግድ ይለዋል ፡፡ ግን አንድ ሰው ካህን ስላልሆነ በአስተዳደር በገንዘብ አያያዝ ጉዳይ ወዘተረፈ አያገባውም ማለት አይደለም ፡፡  በእርግጥ አባቶች መሔድ ያለባቸውን ደረጃ እስከመጨረሻ ሔደዋል የሚል ድምዳሜ ባይኖረኝም ከአቅማቸው በላይ የሆነ ጉዳይ ያለ ይመስለኛል:: እንደ እኔ እምነት አብዘኞቹ አባቶች ስለቤተክርስቲያን ነፍሳቸውን እንኩዋን አሳልፈው ልሰጡ የተዘጋጁ ናቸው::ነገር ግን ነፍሳቸው አልፋ ሥራ መሠረት አለበት ::የደርግ መንግሥት ብሆን ገድሎ ስለምፎክር አባቶች ለሃይማኖታቸው ስሞቱ ምእመኑ ይሰማል ወደ ቀጣይ እርምጃም የሔዳል: አሁን ባለው ሁኔታ ግን ገና ከማሰባቸው ልገደሉ ይችላሉ:: በሌላ ምክንያት እንደ ሞቱም የውሸት ወሬ ወዲያው ይቀነባበራል ፡፡ስለዚህ አባቶች ሥራ የማይሠራበት ለምእመናን ስለ ሃይማኖታቸው ጥብዐት የማይጨምር ከንቱ ሞት ከምሆን ጊዜ ከመጠበቅ ወጭ ምንም ማድረግ አይችሉም፡ ታፍነዋል፡፡  መፍትሔው ያለው በምእመናን እጅ ነው፡፡

  1)ምእመናን በአንድነት መንግሥት በሃይማኖታችን ጠልቃ መግባቱን እንዲያቆም ይልቁንም ቤተክርስቲያኒቱን ለማዳከም ከሚሠራው ግልጽና ስውር ሤራ እንዲታቀብ መጠየቅ ፡፡ይህንን በግንባር ቀደምትነት በማስተባበር የሰንበት ትምህርት ቤቶች ትልቅ ሚና መጫወት ይችላሉ ፡፡ ምቹ ሁኔታ ያላቸውም እነርሱ ናቸውና ::

  2)በቤተክርስቲያን ጉዳይ ሁሉም ምእመን እንደሚያገበው መረዳት

  3)በየትኛው የቤተክርስቲያን አገልግሎት ማን መሳተፍ እንደሚችል ግልጽ ግንዛቤ መያዝ

  4)ሕግጋተ ቤተክርስቲያንና ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን ማወቅ

  ከላይ ከ2-4 የተጠቀሱትን ለማሳወቅ መምህራነ ቤተክርስቲያን ትልቅ ኃላፊነት አለባቸው፡፡

  የሰማን በማሰማትና በማስረዳት ዛሬ ነገ ሳንል መሥራት ያለብን ይመስለኛል፡፡ ምክንያቱም የቤተክርስቲያን ጉዳይ ከእጃችን ወደ መውጣት እየተቃረበ ነው፡፡

  ፓትርያርኩ ከውስጥ የተሐዲሶ መናፍቃን አርበኞችን ሲያደራጁ መንግሥት ከውጭ የሃይማኖት ነጻነት በሚል በፍርድ ቤት ቤተክርስቲያንን ለሁለት ለመክፈል እየቁዋመጠ ነው፡፡

  መንግሥት ቤተክርስቲያንን ለማዳከም ከመጀመሪያው አጀንዳ እንደ ነበረው ከዚህ በፊት በሰፊው ማንበባችንና ማስነበባችን ይታወሳል፡፡

  ይህ ስባል “እግዚአብሔር ያውቃል መጸለይ ብቻ……” የሚትሉትን ረስቼ አይደለም:: ግን እግዚአብሔር በሰው አድሮ እንደሚሠራ መረዳት ያለብን ይመስለኛል :: በእርግጥ ሁሉም በጎ ሥራ በጸሎትና በእግዚአብሔር ኃይል ነው የሚሠራው፡፡

  የቤተክርስቲያን ጉዳይ ሳይቃጠል በቅጠል እንዲሉ ከእጃችን ሳይወጣ ዛሬ ነገ ሳንል እንታደግ ፡፡

  ማላሰብያ ፡ምን አልባት ከዚህ በፊት ለብዙዎቻችን የሚመስለን የመንግሥት የመረጃ ደኅንነት ኤጄንሲ ማን ከማን ጋር ምን እንዳወራ ለመከታተል የሚችለው ስልክ ስንደዋወል ብቻ ነበር::

  ተንቀሳቃሽ ስልካችሁን አጥፍታችሁ ባትሪዉን ካላወጣችሁ ወይም ከስልካችሁ ተለይታችሁ ካላወራችሁ ባስተቀር ሳትደዋወሉ ተሰብስባችሁ ከማን ጋር ምን እንዳወራችሁ በቀላሉ የመንግሥት ደኅንነት መረጃ ቁዋት ውስጥ ልገባ ይችላል::

  ጾዳቤ(Email) ስትጠቀሙም ከስማችሁ ጋር ግኑኙነት የሌለውን account በመክፈትና password በመጠቀም አንድ ቦታ ወይም የግል ኮምፒዩተር ሳይሆን በተለያየ ቦታ ወይም ብዙ ሰው በሚጠቀምበት በመላላክ ስለ ቤተክርስቲያን መወያየት ትችላላችሁ፡፡

  ReplyDelete
 2. haile michael zedebretsigeMay 16, 2012 at 11:51 PM

 3. ሊቃውንት ጉባኤው ተደጋጋሚ ጥሪ አድርጎለት ያልቀረበው በጋሻው ደሳለኝ ዛሬ ጠዋት የሊቃውንት ጉባኤውን ሰብሳቢ በእጅጋየሁ በየነ አማላጅነት ሲለማመጥ ታይቷል

  ReplyDelete
 4. ጽጌ ስጦታው እና ግርማ በቀለ sint gize new yemiwegezut

  ReplyDelete
  Replies
  1. አስኪ በትዕግስት እንጠብቅ እንጅ አነዚህንማ ለማውገዝ የግዴታ የ ቅ/ሲኖዶስን ስብሰባ ጊዜ መሻማትም አልነበረበትም - ምክንያቱም በጣም የለየላቸው ናቸውና፡፡ ይልቁንስ የበግ ለምድ ለብሰው ያሉትንና ለመለየት ‹አስቸጋሪ. የሆኑትን ነበር በእንጭጩ ማስቀረት… የአባቶቻችን አምላክ ይርዳን!

   Delete
 5. የስለኩን ባትሪ ሳታወጡ እንዳታወሩ የሚለው ወሬ ህዝቡ ውስጥ ፍርሀት ለመንዛት የተቀነባበረ ሴራ ነው፡፡ አንዳንዴ የመንግስት ተቃዋሚ መስለው የተሳሳተ መረጃ ወደ ህዝቡ የሚለቁ አላስተዋዮች እንዳሉ ልንገነዘብ ይገባል፡፡ ቴክኖሎጅው ቢኖርም ሀገሪቱ አሁን ባለችበት ደረጃ መጠቀም አትችልም፣ ዋናው ነገር መወያየት ያለብን ነገር ለሀገራችን፣ለሀይማኖታችን እና ለአንድነታችን ጥሩ በሆኑ ርዕሰ ጉዳዮች ይሁን፡፡ ፍርሀት የምትነዙ እባካችሁ እናንተም ትሞታላችሁ ለቀጣይ ትውልድ ስትሉ ፍቅር፣ ሰላም፣አንድነትን ስበኩ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. haile michael zedebretsigeMay 17, 2012 at 4:29 AM

   Dear Abdisa ,
   It is not meant to frustrate .Just to remind to be careful so that they should not halt our objective of protecting our church from the very beginning, they way they have been frustrating individually.But even if it not on all mobile phones , I wanna assure u that they have reached to that level .
   So let us discuss and come to one point . Then let us express our opposition together . It should not be individually.

   Delete
 6. Dhugaasaa BaasaaMay 17, 2012 at 4:45 AM

  Actually, ene bizu mistir yalebet ayimeslegnim lebete kiristiyanachen kibir metebek menegagerina menager yalebin fitlefit newu egna ye silela woyim lela yepoletike ajenda yelenim.

  ReplyDelete