የቅ/ሲኖዶስ መደበኛ ስብሰባ ሦስተኛ ቀን የቀትር በኋላ ውሎ
- ቅዱስ ሲኖዶስ በቀጣይ ለሚኖረው አመራር የመላው ካህናትና ምእመናን ጸሎትና ሁለንተናዊ ድጋፍ እንዲደረግለት፣ የአባ ጳውሎስ ግብረ በላዎች በአባቶች ጽናት ላይ የሚፈጥሩትን ማንኛውም ጫና ለመቋቋም ዝግጁ እንዲኾን ተጠይቋል::
- በአባ ጳውሎስ፣ አባ ፋኑኤልና ኀይለ ጊዮርጊስ ጥላሁን ምክርና ኮሚሽን አድራጊነት የተጻፈው የዜና ቤተ ክርስቲያንጋዜጣ ርእሰ አንቀጽና ዘገባ በፈጠረው ቁጣ ሳቢያ የቅ/ሲኖዶስ ስብሰባ ተቋረጠ::
- የጋዜጣው ርእሰ አንቀጽና ዘገባዎች አባ ጳውሎስ በስብሰባው እንዲያዙላቸው የሚፈልጓቸውን አጀንዳዎች ከአባ ጳውሎስ “የፓትርያርክነት ዐምባገነንነት” ፍላጎት አንጻር የማብራራት ግብዝነት የሚታይበት ነው::
- አባ ጳውሎስን ከፓትርያርክነት ማዕርጋቸው በሚያወርዷቸው የቃለ መሐላ ጥሰትና የታማኝነት ማጣት ጉዳዮች ዙሪያ የጦፈ ውይይት ተጀምሯል::
- መደበኛ ስብሰባው ሰኞ ይቀጥላል::
(ደጀ ሰላም፤ ግንቦት 5/2004 ዓ.ም፤ May 13/ 2012)፦ ትናንት፣ ግንቦት 4 ቀን 2004 ዓ.ም ከቀትር በፊት በነበረው የቅ/ሲኖዶስ ስብሰባ ርእሰ መንበሩ አባ ጳውሎስ በምልአተ ጉባኤው ስምምነት የተደረሰባቸውን አጀንዳዎች ባለመቀበል ኾነ ብለው በያዙት ግትርነት የተነሣ ብዙኀኑ አባላት ከቀትር በኋላ ሌላ ሰብሳቢ መርጠው ውይይታቸውን ለመቀጠል ወስነው ነበር የተነሡት፡፡
የቅዱስ ሲኖዶሱ አባላት ከቀትር በኋላ ስብሰባውን ለመቀጠል ወደ አዳራሹ ሲገቡ የዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ በየመቀመጫቸው አንጻር ተቀምጦ ያገኛሉ፤ ፓትርያርኩም በኮሚቴው የተዘጋጁትን አጀንዳዎች እንደሚቀበሉ መስለው ተላስልሰው በመቅረባቸው ምልአተ ጉባኤው በእርሳቸው ርእሰ መንበርነት እየተመራ በተ.ቁ (2) ላይ የተመለከተውን የቅዱስ ሲኖዶሱን ዋና ጸሐፊ ብፁዕ የአቡነ ሕዝቅኤልን ሪፖርት አዳመጠ፡፡
ሪፖርቱ በንባብ ተሰምቶ ከተጠናቀቀ በኋላ ውይይት ከመጀመሩ በፊት ለሻይ ዕረፍት የተነሡት አባቶች ግን ጋዜጣው በያዘው ቁም ነገር ላይ መመካከር ያዙ፤ ምክክሩም አባ ጳውሎስ ከስብሰባው ቀደም ብለው ወደ አገር ቤት ከመጡት አባ ፋኑኤልና ኀይለ ጊዮርጊስ ጥላሁን ጋራ በማበር የጋዜጣውን አዘጋጆችና ጋዜጣው በሚዘጋጅበት መምሪያ ውስጥ በሓላፊነት የሚገኙ ሌሎች ግለሰቦችን በቅጥረኝነት በመጠቀም የሠሩት መኾኑን ይደርሱበታል፡፡
ከሻይ ዕረፍት መልስ የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ ስለ ዝግጅቱ ምንም እንደማያውቁና ሌሎች አጀንዳዎች ወደኋላ ቀርተው ምልአተ ጉባኤው በዚሁ ጉዳይ እንዲነጋገር ይጠይቃሉ፡፡ ከዚህ በኋላ በቤቱ የነበረው ድባብ በፓትርያርኩ እና በአባ ፋኑኤል ላይ ባነጣጠረ የተግሣጽ መአት የተሞላ ነበር፡፡ አባ ጳውሎስም ይኹኑ አባ ፋኑኤል የሠሩትን ያውቃሉና አንገታቸውን አቀርቅረው ተግሣጻቸውን ከመቀበል ውጭ የሰጡት ምላሽ አልነበረም፡፡
በተግሣጹ አባ ጳውሎስ ከተሐድሶ መናፍቃን ጋራ በግልጽ ስለማበራቸው የተነገራቸው ሲኾን አባ ፋኑኤልም “መወገዝ ያለብህ ሕገ ወጡ አንተ እዚህ እያለህ አንተ ብሎ ክህነት ያዥ” ተብለዋል፡፡
ሰኞ የስብሰባው አጀንዳ ይህና ይህ ብቻ እንደሚኾን ሁሉም አባቶች የተስማሙ ሲኾን ይህን ተከትሎ ስብሰባው ከተቋረጠ በኋላ ሁሉም አባቶች በየማረፊያ ቤታቸው እርስ በርስ መመካከሩን ቀጥሏል፡፡ በተለይም በአቡነ ፋኑኤል “ዶላር” ስፖንሰርነት፣ በኃ/ጊዮርጊስ መሪነት የታተመው “የዜና ቤተ ክርስቲያን” ጋዜጣ የዚህ እትም ቅ/ሲኖዶስ የጣላቸውን ጉዳዮች በማንሣት እና ትክክለኛ እንደሆኑ በመግለጽ ጸረ ቤተ ክርስቲያን አቋሙን ግልጽ አድርጎ አቅርቧል። የጋዜጣው ዝግጅት ቤተ ክህነቱ በአባ ጳውሎስ ዙሪያ በተሰበሰቡ ጥቅመኞች እና የተሐድሶ መናፍቃን ለመወረሩ ማስረጃ እንደ ኾነ የቅ/ሲኖዶስ አባላት በመግለጽ ላይ ይገኛሉ።
ጋዜጣው ምን እንደጻፈ፣ ስለምን እንደጻፈ ሊያውቅ እና ሲቆጣጠርም ይገባ የነበረው የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ ሊቀ ጳጳስ ስለ ዝግጅቱ አያውቁም፤ የጋዜጣው ዋና አዘጋጅም “በስሜ ተነግዶብኛል” እያሉ ሲሆን ጋዜጣው ከመሰራጨት እንዲታገድና አባ ጳውሎስን ጨምሮ አዘጋጆቹ በቅዱስ ሲኖዶስ እና በሕግ አግባብ የሚጠየቁበት ዝግጅት እየተደረገ ነው ተብሏል።
የጋዜጣው ርእሰ አንቀጽ አባ ጳውሎስ በሌላቸው ሃይማኖት እና ምግባረ ጽድቅ ሕገ ቤተ ክርስቲያኑን በማሻሻል የፓትርያርክነት ዐምባገነንነታቸውን ለማጠናከር እንደሚሹ በጉልሕ ያሳየ ሲሆን በብፁዓን አባቶች ላይ ደግሞ በሥርዐተ ሢመት፣ በሀብት ክምችትና በውጭ ዜግነት የጩኸቴን ቀሙኝ ክስና ግብዝነት የተሞላበት ጽሑፍ አቅርቧል፤ የጥቅምቱ ቅዱስ ሲኖዶስ “የውጭ ጉዳይ ተጠሪ ጽ/ቤት”የሚባለው ቅ/ሲኖዶስ ያልመከረበት መዋቅር እንዲዘጋ ከቃለ ዐዋዲውና ከሕገ ቤተ ክርስቲያን ጋራ እንደሚፃረር ያሳለፈውን ውሳኔ በመናቅ ነውረኛውን ኀይለ ጊዮርጊስ ጥላሁን “በሰሜን አሜሪካ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክን የውጭ ጉዳይ ተጠሪ ጽ/ቤት ባለሙሉ ሥልጣን ዋና ሓላፊ”በማለት ይጠራዋል፡፡ ከግማሽ ምእት በላይ በሰሜን አሜሪካ ሲከናወን የቆየውን የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት በመዘንጋት ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን ተላልፈው በሌሎች ሊቃነ ጳጳሳት አህጉረ ስብከት ክህነት በመስጠትና ማእከላዊ አሠራርን በመናድ የሚታወቁትን አባ ፋኑኤልን“በሰሜን አሜሪካ ሥራ አሁን ገና ሥራ እንደተጀመረ እና የታሪክ እመርታ እንደታየ” ይቀጥፋል፤ የዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ሀ/ስብከት ሥራ አስኪያጅ የኾኑትን ቀሲስ ዶ/ር መስፍን ተገኝን ‹በአሸባሪዎች አደራጅነት› በመክሰስ ሊቀ ጳጳሱ በሌላቸው ሥልጣን ላስተላለፉባቸው ውግዘት አጽድቆት ይሰጣል፡፡
ጋዜጣው በአቡነ ፋኑኤል ጉቦ እንደተዘጋጀ ምንም አላጠራጠረም። በተግሳጽ መዶሻ ሲወቀሩ ያመሹት አቡነ ፋኑኤልም አልካዱም። ጥያቄው ፓትርያርኩ እንዴት እንዲህ ያለ ነገር ሊፈቅዱ ቻሉ የሚለው ተመሳሳይ ጥያቄ ነው። ራሳቸው የሚመሯቸውን ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በጎን በጋዜጣ ማስደብደብ ምን የሚሉት “ፓትርያርክነት” ነው? ፓትርያርክነታቸውስ ለማን ነው? በ2001 ዓ.ም በቅ/ሲኖዶስ ጉባኤ የተቃወሟቸው አባቶች ቤታቸው በሌሊት ከመሰባበበሩ ጋር ያላቸውን ቁርኝት ይህ ሕገ ወጥ ጋዜጣ አዘገጃጀት ግልጽ አያደርገውምን?
ፓትርያርኩ ቅ/ሲኖዶሱን ባለመስማት ካመጹ ቆይተዋል። የዚህ ሕገ ወጥነታቸው ምልክት ደግሞ ቦሌ መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት የተደነቀረው ሀውልታቸው ነው። ቅ/ሲኖዶስ እንዲነሣ ቢወስንም በርሳቸው አምባገነንነት ይኸው እንደተገተረ አለ። ውሳኔያቸውን በተግባር ለመግለጽ ምንም አቅም ያጡት አባቶች ከዚህ በኋላ ለመናገር ፈቃደኛ ባይሆኑ ይፈረድባቸዋልን? የወሰኑትን ውሳኔ ቤተ ክህነቱ ለማስፈጸም የማይፈልግ ከሆነ ምእመናን ሊያግዟቸው አይገባምን? ይህንን ጣዖት መሰል ሕገ ቤተ ክርስቲያንን የጣሰ ሀውልት ምእመናን ነቃቅለው ሊጥሉ፣ አባቶቻቸውን ሊያጠቋቸው ከሚመጡ ወንበዴዎች እና “ዶላር-አምላኩ” የዲሲ ጆቢራዎች ሊከላከል አይገባውምን?
ደጀ ሰላም ባለፉት ዓመታት ስታደርግ እንደቆየችው ሁሉ በዚህ ዓመትም ስብሰባዎቹን “እንደወረደ” ሪፖርት ታደርጋለች። ይህንን የምታደርገው ግን “እገሌ እንዲህ አሉ፣ እገሌ እንዲህ ሠሩ” በሚለው እንድንዝናና ሳይሆን የሰማነውን ሰምተን ፣ ማድረግ ያለብንን ደግሞ እንድናደርግ ነው። ጎራው ለይቷል። ቤተ ክርስቲያን አፍራሾቹ፣ ጉበኞቹ፣ ዘራፊዎች እና የቤተ ክርስቲያን አጥፊዎቹን በግልጽ አውቀናቸዋል። ስለነርሱም ብዙ ብዙ ብለናል። አሁን ግን ይበቃናል። አባቶቻችን እየያዙት የመጡትን አቋም በመደገፍ “አይዟችሁ” ልንላቸው ይገባል። ከጎናቸውም እንቆማለን። መንግሥትም ቢሆን ይህንን ሕገ ወጥነት በመደገፍ ፖሊሱን እና ወታደሩን፣ ጥይቱንና ዱላውን የሚልክ ከሆነ ምእመናን ለሃይማኖታቸው መስዋዕትነት ለመክፈል የተዘጋጁ መሆኑንም ማሳየት ይገባቸዋል። ቅ/ጳውሎስ በፊልጵስዩስ መልእክቱ እንዳስተማረን “ይህ ስለ ክርስቶስ ተሰጥቶአችኋልና፤ ስለ እርሱ መከራ ደግሞ ልትቀበሉ እንጂ በእርሱ ልታምኑ ብቻ አይደለም” (1፥29)። እናምናለን፣ ስለ ማመናችን የሚመጣብንን መከራም በጸጋ እንቀበላለን። ከአባቶቻችን ጋር በመቆም ቤተ ክርስቲያናችንን እንታደጋለን። እግዚአብሔር ይርዳን።
ቸር ወሬ ያሰማን፣ አሜን
ቸር ወሬ ያሰማን፣ አሜን
ሪፖርታዡ ይቀጥላል፤ ተከታተሉን።
ooooooooooooooooooooo ahunes menlebel!!!
ReplyDeleteTesfa Atkuretu !
bertu ande adergenoche!
And Adrgen Bertu Bertu bertu bertuuuuuuuuuuuu
ReplyDeleteCher yaseman
geta hoy mihiretkn lak
ReplyDeleteብፁዕ ሊቀ ጳጳሳትን በእግዚአብሔር ስም እያመሰገን በዚህ እንድትቀጥሉ በእግዚአብሔር ስም እናሳስባለን:እኛም ከአባቶቻችን ጋር በመቆም ቤተ ክርስቲያናችንን እንታደጋለን። እግዚአብሔር ሃይሉን በረከቱን ይስጣችሁ:: ርትዕይት ሃይማኖታችንን አምላካችን ይጠብቅልን :
ReplyDeleteይህን ላልሰሙ ወገኖቻችንን እንዲሁም እህት ወንድሞቻችን እናት አባቶቻችን እንዲሰሙ እናድርግ እያልኩ አሳስባለሁ::
የጻርቃን የሰማዕታት የቅዱሳን ረድኤትና በረከት አይለየን!!! ቸር ወሬ ያሰማን ::
ገ/ስላሴ ከ HARAMAYA UNIVERSITY
This comment has been removed by the author.
ReplyDeleteebakachu semachehun keyerut,enanten belo ande adreregen!le mesenetatek yetefeterachu ye setan kurachoch,ye torenet awage be betekerestian seme ye metawegu defaroch,torenet kefelegachu betekerestiyanen tewet aderegachu andegnawen manenetachehun agaltachu wede medaw gebu hisabachehun tagegnalachu enante kehadi ye sabiya jelewoch esum mokero selakatew new be enante le metekem ye mimokerew,AYESAKALACHEHUM ENJI.
ReplyDeleteEinanite Shibiritegnochi Hayimanotawi Seine Migibari Yelelachihu !! mech newu bebetekirisitiyan sim meneged yemitaqomut? Qinigitoch Yaliteneqabachihu Mesiloachihula
ReplyDeletemehret and anonymous min abesachachihu? minfknachihu tesenakelebachihu ende? Egziabher eko betun ytebkal letekula asalfo aysetm. atbesachu minfiknachihun ketlu betekrstian gin tebaki alat. egzieabher lehulum lbona ystew frdunm yfred
ReplyDeleteWe have to STOP Fighting with each other, Fighting against our Patriarch. Now what our world need is someone who preaches peace.
ReplyDelete