Wednesday, May 16, 2012

የባቦጋያ መድሀኒዓለም የቦታ ውዝግብ ጉዳይ ቀጥሏል


ኢትዮጵያ ውስጥ ብሎጋችንን ለማንበበብ ይህን ሊንክ ይጠቀሙ  
http://www.andadirgen.blogspot.in

 • አቶ ጌታቸው ዶኒ እና የቦታው ባለቤትነት የተወሰነለት ሰው ቦታው ላይ የነበረውን መስቀልና የቤተክርስትያኑ ይዞታነትን የሚያረጋግጠውን የቤተክርስትያኑ ሙሉ ስም ያለበትን ከዓመታት በፊት የተሰቀለውን ሬክላም(ሰሌደ) ሲነቃቅሉ አርፍደዋል


በአቶ ጌታቸው ዶኒ አማካኝነት ተነቅሎ ጥጉን የያዘው የባህረ ጥምቀትና ታቦት ማደሪያ ሬክላም

(አንድ አድርገን ግንቦት 8 ፤ 2004 ዓ.ም)፡- የባቦጋያ መድሀኒዓለም ቤተክርስትያን ጉዳይ አሁንም መቋጫ አላገኝም ፤ ፍርድ ቤቱ ህዝቡ የወከላቸውን የቤተክርስትየን ቦታ ተሟጋቾች እናንተ የቤተክርስትያኒቱን ቦታ ለመጠየቅ አትችሉም ያላቸው ሲሆን ቦታውንም ለባለሀብቱ መወሰኑን ዘግበን ነበር ፤ የዚህ የቦታ ጉዳይ በሪዞርቱ ባለቤት እና በአቶ ጌታቸው ዶኒ አማካኝነት በህገወጥ የቤተክርስትያኒቱን የጥምቀት ቦታ ለማሳጣት የተደረገ ሴራ ሲሆን የአካባቢው ክርስትያኖች በጉዳዩ ያላቸው አቋም አንድና አንድ በመሆኑ ነገሮች ጌታቸው እንዳሰበው አልጋ በአልጋ ሆነው ሊሄዱለት አልቻለም ፡፡ በትላንትናው እለት 07/09/04 ዓ.ም አቶ ጌታቸው ዶኒ እና የቦታው ባለቤትነት የተወሰነለት ሰው ቦታው ላይ የነበረውን መስቀልና የቤተክርስትያኑ ይዞታነትን የሚያረጋግጠውን የቤተክርስትያኑ ሙሉ ስም ያለበትን ከ8 ዓመት በፊት የተሰቀለውን ላሜራ(ሰሌደ) ሲነቃቅሉ አርፍደዋል ፤ ከዚህ በተጨማሪ ከዚህ በፊት ህዝብ የወከላቸውንና በሴራ ያሳሰራቸውን ንጹአን ክርስትያኖችን ጉዳዩን ከአሁን በኋላ አናነሳም በሉና ፈርሙ ያለበለዚያ 6 ዓመት አስቀፈድዳችዋለሁ በማለት ሲዝትባቸው እንደ ነበረ ከቦታው የደረሰን መረጃ ያሳያል ፤ ለምዕመኑ እናንተን ለማሳሰር ሁሉን ነገር ጨርሰናል በማለትም አክሎ ሲናገር ተሰምቷል ፤ ግለሰቦቹ የመጣው ነገር ይምጣ ሁሉን በጸጋ እንቀበላለን እንጂ በማለት አቋም የወሰዱ ሲሆን ፤ ከዚህ በፊት ከፖሊስ የሸሹትን ደግሞ ከሳምንት በፊት ሊያሳስራቸው ችሏል፡፡

መስቀሎቹን በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ከቦታው ላይ በመነቃቀል ሊያስነሳቸው ችሏል
እነዚህ ሰዎች  አሳማኝ ባልሆነ ምክንያን ታስረው ቢሰነብቱም 05/09/04ዓ.ም በዝግ ፍርድ ቤት ቀርበው በዋስ መለቀቅ ችለዋል ፤፡፡በእስር ላይ እያሉ የባለሃብቱ(አቶ ታዲዎስ ጌታቸዉ) ተወካይ በሕግ ከላላ ስር ያሉትን እስረኞችን ተረኛ ፖሊስ ባለበት ‹‹እኔ ዋጋችሁን ካልሰጠኋችሁ ምን አለ በሉኝ›› እያለ ሲዝትባቸዉ እንደነበር ግለሰቦቹ ገልጠዋል፡፡ የቤተክርስትያኒቱን አስተዳዳሪ አስፈራርተዋል ተብሎ የሀሰት ክስ የቀረበባቸው ግለሰቦች በዝግ ችሎት ጉዳያቸው ታይቶ ለነገ 09/09/04 ዓ.ም ፍርድ ቤቱ ቀነ ቀጠሮ ሰጥቷቸዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እያለ ጉዳዩን ለቀናት እንኳን ወደ ኋላ ሳይሉ አሁንም ቦታው ለማስመለስ በአካባቢው የሚገኙ ወንድሞች ያላሰለሰ ጥረት እያደረጉ መሆኑን ለማወቅ ችለናል ፤ ጉዳዩ ከክልላዊ ወደ ፌደራል መንግስት የሚያመራበትን እና በአጭር ጊዜ ውስጥ ባላቸው ማስረጃዎች አማካኝነት መፍትሄ የሚያገኝበትን ሁኔታ ወንድሞችና እህቶች እየመከሩ ሲሆን ቦታውን ለማስመለስ ደፋ ቀና እያሉ መሆኑን ለማወቅ ችለናል ፡፡ እንደ ወንድሞች ብርታትና እንደ እግዚአብሔር መልካም ፍቃድ የጠላትን ወጥመድ በመበጣጠስ ቦታውን ያስመልሳሉ ብለን እንገምታልን፡፡

ቸር ወሬ ያሰማን

8 comments:

 1. eski beritu emebirihanei tiketelachihu leala mini ybalali?

  ReplyDelete
 2. cher wore Yaseman!

  ReplyDelete
 3. ይህ በእንዲህ እያለ ጉዳዩን ለቀናት እንኳን ወደ ኋላ ሳይሉ አሁንም ቦታው ለማስመለስ በአካባቢው የሚገኙ ወንድሞች ያላሰለሰ ጥረት እያደረጉ መሆኑን ለማወቅ ችለናል ፤ ጉዳዩ ከክልላዊ ወደ ፌደራል መንግስት የሚያመራበትን እና በአጭር ጊዜ ውስጥ ባላቸው ማስረጃዎች አማካኝነት መፍትሄ የሚያገኝበትን ሁኔታ ወንድሞችና እህቶች እየመከሩ ሲሆን ቦታውን ለማስመለስ ደፋ ቀና እያሉ መሆኑን ለማወቅ ችለናል ፡፡ እንደ ወንድሞች ብርታትና እንደ እግዚአብሔር መልካም ፍቃድ የጠላትን ወጥመድ በመበጣጠስ ቦታውን ያስመልሳሉ ብለን እንገምታልን፡፡

  ReplyDelete
 4. የቅድሰት ቤተክርስቲያን የመጨረሻው የላዕላይ ሥልጣን ያለው ቅዱስ ስኖደስ እንደሆነ ይታወቃል :: ይህ ቅዱስ ስኖደስ የሚወስናቸው ውሳኔዎች በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ለቤተክርስቲያን የሚበጁ እንደሆነ ተግባራዊም መደረግ እነዳሉበት እሙን ነው::ነገር ግን ቅዱስ ስኖደስ የሚወስናቸው ውሳኔዎች በፓትርያርኩ እምብተኝነት በመንግሥት ከለላ ሰጭነት ተግባራዊ መደረግ ከተተው ቆይቶአል፡፡ ቅዱስ ስኖደስም ጥርስ የሌለው አንበሳ ሆኖአል ማለት ይቻላል፡፡ይህን በማየታችንም የቅድሰት ቤተክርስቲያን ልጆች በቁጭት ከመብገን ባለፈ መፍትሔ ማምጣት አልቻልንም፡፡ይልቁንም መፍትሔ ማማጣት ያለባቸው አባቶች ጳጳሳት ብቻ እንደሆኑ በማመን በአባቶች ላይ ያለንን ተስፋ እስከ መቁረጥ የደረስንም አለን፡፡ ይህንንም በደጀ ሰላም በአንድ አድርገን የጡመራ መድረኮች ከምሰጡ አስተያያቶች መረዳት ይቻላል፡፡  ስጀምር ስለ ቤተክርስቲያን ችግር እንደየሚናችን ሁላችንንም እንደሚያገባን መረዳት አለብን ፡፡አባቶች ድቁና ቅስና ልሾሙ እኛ ምእመናን የሚንመሰክርበት አሠራር መኖር አለበት፡፡ እርግጥ ነው ሊያሥር ልፈታ ልያጠምቅ ቀድሶ ልያቆርብ አንድ ሰው የግድ ቅስናና ከዚያ በላይ የክህነት ደረጃ ልኖረው ግድ ይለዋል ፡፡ ግን አንድ ሰው ካህን ስላልሆነ በአስተዳደር በገንዘብ አያያዝ ጉዳይ ወዘተረፈ አያገባውም ማለት አይደለም ፡፡  በእርግጥ አባቶች መሔድ ያለባቸውን ደረጃ እስከመጨረሻ ሔደዋል የሚል ድምዳሜ ባይኖረኝም ከአቅማቸው በላይ የሆነ ጉዳይ ያለ ይመስለኛል:: እንደ እኔ እምነት አብዘኞቹ አባቶች ስለቤተክርስቲያን ነፍሳቸውን እንኩዋን አሳልፈው ልሰጡ የተዘጋጁ ናቸው::ነገር ግን ነፍሳቸው አልፋ ሥራ መሠረት አለበት ::የደርግ መንግሥት ብሆን ገድሎ ስለምፎክር አባቶች ለሃይማኖታቸው ስሞቱ ምእመኑ ይሰማል ወደ ቀጣይ እርምጃም የሔዳል: አሁን ባለው ሁኔታ ግን ገና ከማሰባቸው ልገደሉ ይችላሉ:: በሌላ ምክንያት እንደ ሞቱም የውሸት ወሬ ወዲያው ይቀነባበራል ፡፡ስለዚህ አባቶች ሥራ የማይሠራበት ለምእመናን ስለ ሃይማኖታቸው ጥብዐት የማይጨምር ከንቱ ሞት ከምሆን ጊዜ ከመጠበቅ ወጭ ምንም ማድረግ አይችሉም፡ ታፍነዋል፡፡  መፍትሔው ያለው በምእመናን እጅ ነው፡፡

  1)ምእመናን በአንድነት መንግሥት በሃይማኖታችን ጠልቃ መግባቱን እንዲያቆም ይልቁንም ቤተክርስቲያኒቱን ለማዳከም ከሚሠራው ግልጽና ስውር ሤራ እንዲታቀብ መጠየቅ ፡፡ይህንን በግንባር ቀደምትነት በማስተባበር የሰንበት ትምህርት ቤቶች ትልቅ ሚና መጫወት ይችላሉ ፡፡ ምቹ ሁኔታ ያላቸውም እነርሱ ናቸውና ::

  2)በቤተክርስቲያን ጉዳይ ሁሉም ምእመን እንደሚያገበው መረዳት

  3)በየትኛው የቤተክርስቲያን አገልግሎት ማን መሳተፍ እንደሚችል ግልጽ ግንዛቤ መያዝ

  4)ሕግጋተ ቤተክርስቲያንና ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን ማወቅ

  ከላይ ከ2-4 የተጠቀሱትን ለማሳወቅ መምህራነ ቤተክርስቲያን ትልቅ ኃላፊነት አለባቸው፡፡

  የሰማን በማሰማትና በማስረዳት ዛሬ ነገ ሳንል መሥራት ያለብን ይመስለኛል፡፡ ምክንያቱም የቤተክርስቲያን ጉዳይ ከእጃችን ወደ መውጣት እየተቃረበ ነው፡፡

  ፓትርያርኩ ከውስጥ የተሐዲሶ መናፍቃን አርበኞችን ሲያደራጁ መንግሥት ከውጭ የሃይማኖት ነጻነት በሚል በፍርድ ቤት ቤተክርስቲያንን ለሁለት ለመክፈል እየቁዋመጠ ነው፡፡

  መንግሥት ቤተክርስቲያንን ለማዳከም ከመጀመሪያው አጀንዳ እንደ ነበረው ከዚህ በፊት በሰፊው ማንበባችንና ማስነበባችን ይታወሳል፡፡

  ይህ ስባል “እግዚአብሔር ያውቃል መጸለይ ብቻ……” የሚትሉትን ረስቼ አይደለም:: ግን እግዚአብሔር በሰው አድሮ እንደሚሠራ መረዳት ያለብን ይመስለኛል :: በእርግጥ ሁሉም በጎ ሥራ በጸሎትና በእግዚአብሔር ኃይል ነው የሚሠራው፡፡

  የቤተክርስቲያን ጉዳይ ሳይቃጠል በቅጠል እንዲሉ ከእጃችን ሳይወጣ ዛሬ ነገ ሳንል እንታደግ ፡፡

  ማላሰብያ ፡ምን አልባት ከዚህ በፊት ለብዙዎቻችን የሚመስለን የመንግሥት የመረጃ ደኅንነት ኤጄንሲ ማን ከማን ጋር ምን እንዳወራ ለመከታተል የሚችለው ስልክ ስንደዋወል ብቻ ነበር::

  ተንቀሳቃሽ ስልካችሁን አጥፍታችሁ ባትሪዉን ካላወጣችሁ ወይም ከስልካችሁ ተለይታችሁ ካላወራችሁ ባስተቀር ሳትደዋወሉ ተሰብስባችሁ ከማን ጋር ምን እንዳወራችሁ በቀላሉ የመንግሥት ደኅንነት መረጃ ቁዋት ውስጥ ልገባ ይችላል::

  ጾዳቤ(Email) ስትጠቀሙም ከስማችሁ ጋር ግኑኙነት የሌለውን account በመክፈትና password በመጠቀም አንድ ቦታ ወይም የግል ኮምፒዩተር ሳይሆን በተለያየ ቦታ ወይም ብዙ ሰው በሚጠቀምበት በመላላክ ስለ ቤተክርስቲያን መወያየት ትችላላችሁ፡፡

  ReplyDelete
 5. የቅድሰት ቤተክርስቲያን የመጨረሻው የላዕላይ ሥልጣን ያለው ቅዱስ ስኖደስ እንደሆነ ይታወቃል :: ይህ ቅዱስ ስኖደስ የሚወስናቸው ውሳኔዎች በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ለቤተክርስቲያን የሚበጁ እንደሆነ ተግባራዊም መደረግ እነዳሉበት እሙን ነው::ነገር ግን ቅዱስ ስኖደስ የሚወስናቸው ውሳኔዎች በፓትርያርኩ እምብተኝነት በመንግሥት ከለላ ሰጭነት ተግባራዊ መደረግ ከተተው ቆይቶአል፡፡ ቅዱስ ስኖደስም ጥርስ የሌለው አንበሳ ሆኖአል ማለት ይቻላል፡፡ይህን በማየታችንም የቅድሰት ቤተክርስቲያን ልጆች በቁጭት ከመብገን ባለፈ መፍትሔ ማምጣት አልቻልንም፡፡ይልቁንም መፍትሔ ማማጣት ያለባቸው አባቶች ጳጳሳት ብቻ እንደሆኑ በማመን በአባቶች ላይ ያለንን ተስፋ እስከ መቁረጥ የደረስንም አለን፡፡ ይህንንም በደጀ ሰላም በአንድ አድርገን የጡመራ መድረኮች ከምሰጡ አስተያያቶች መረዳት ይቻላል፡፡  ስጀምር ስለ ቤተክርስቲያን ችግር እንደየሚናችን ሁላችንንም እንደሚያገባን መረዳት አለብን ፡፡አባቶች ድቁና ቅስና ልሾሙ እኛ ምእመናን የሚንመሰክርበት አሠራር መኖር አለበት፡፡ እርግጥ ነው ሊያሥር ልፈታ ልያጠምቅ ቀድሶ ልያቆርብ አንድ ሰው የግድ ቅስናና ከዚያ በላይ የክህነት ደረጃ ልኖረው ግድ ይለዋል ፡፡ ግን አንድ ሰው ካህን ስላልሆነ በአስተዳደር በገንዘብ አያያዝ ጉዳይ ወዘተረፈ አያገባውም ማለት አይደለም ፡፡  በእርግጥ አባቶች መሔድ ያለባቸውን ደረጃ እስከመጨረሻ ሔደዋል የሚል ድምዳሜ ባይኖረኝም ከአቅማቸው በላይ የሆነ ጉዳይ ያለ ይመስለኛል:: እንደ እኔ እምነት አብዘኞቹ አባቶች ስለቤተክርስቲያን ነፍሳቸውን እንኩዋን አሳልፈው ልሰጡ የተዘጋጁ ናቸው::ነገር ግን ነፍሳቸው አልፋ ሥራ መሠረት አለበት ::የደርግ መንግሥት ብሆን ገድሎ ስለምፎክር አባቶች ለሃይማኖታቸው ስሞቱ ምእመኑ ይሰማል ወደ ቀጣይ እርምጃም የሔዳል: አሁን ባለው ሁኔታ ግን ገና ከማሰባቸው ልገደሉ ይችላሉ:: በሌላ ምክንያት እንደ ሞቱም የውሸት ወሬ ወዲያው ይቀነባበራል ፡፡ስለዚህ አባቶች ሥራ የማይሠራበት ለምእመናን ስለ ሃይማኖታቸው ጥብዐት የማይጨምር ከንቱ ሞት ከምሆን ጊዜ ከመጠበቅ ወጭ ምንም ማድረግ አይችሉም፡ ታፍነዋል፡፡  መፍትሔው ያለው በምእመናን እጅ ነው፡፡

  1)ምእመናን በአንድነት መንግሥት በሃይማኖታችን ጠልቃ መግባቱን እንዲያቆም ይልቁንም ቤተክርስቲያኒቱን ለማዳከም ከሚሠራው ግልጽና ስውር ሤራ እንዲታቀብ መጠየቅ ፡፡ይህንን በግንባር ቀደምትነት በማስተባበር የሰንበት ትምህርት ቤቶች ትልቅ ሚና መጫወት ይችላሉ ፡፡ ምቹ ሁኔታ ያላቸውም እነርሱ ናቸውና ::

  2)በቤተክርስቲያን ጉዳይ ሁሉም ምእመን እንደሚያገበው መረዳት

  3)በየትኛው የቤተክርስቲያን አገልግሎት ማን መሳተፍ እንደሚችል ግልጽ ግንዛቤ መያዝ

  4)ሕግጋተ ቤተክርስቲያንና ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን ማወቅ

  ከላይ ከ2-4 የተጠቀሱትን ለማሳወቅ መምህራነ ቤተክርስቲያን ትልቅ ኃላፊነት አለባቸው፡፡

  የሰማን በማሰማትና በማስረዳት ዛሬ ነገ ሳንል መሥራት ያለብን ይመስለኛል፡፡ ምክንያቱም የቤተክርስቲያን ጉዳይ ከእጃችን ወደ መውጣት እየተቃረበ ነው፡፡

  ፓትርያርኩ ከውስጥ የተሐዲሶ መናፍቃን አርበኞችን ሲያደራጁ መንግሥት ከውጭ የሃይማኖት ነጻነት በሚል በፍርድ ቤት ቤተክርስቲያንን ለሁለት ለመክፈል እየቁዋመጠ ነው፡፡

  መንግሥት ቤተክርስቲያንን ለማዳከም ከመጀመሪያው አጀንዳ እንደ ነበረው ከዚህ በፊት በሰፊው ማንበባችንና ማስነበባችን ይታወሳል፡፡

  ይህ ስባል “እግዚአብሔር ያውቃል መጸለይ ብቻ……” የሚትሉትን ረስቼ አይደለም:: ግን እግዚአብሔር በሰው አድሮ እንደሚሠራ መረዳት ያለብን ይመስለኛል :: በእርግጥ ሁሉም በጎ ሥራ በጸሎትና በእግዚአብሔር ኃይል ነው የሚሠራው፡፡

  የቤተክርስቲያን ጉዳይ ሳይቃጠል በቅጠል እንዲሉ ከእጃችን ሳይወጣ ዛሬ ነገ ሳንል እንታደግ ፡፡

  ማላሰብያ ፡ምን አልባት ከዚህ በፊት ለብዙዎቻችን የሚመስለን የመንግሥት የመረጃ ደኅንነት ኤጄንሲ ማን ከማን ጋር ምን እንዳወራ ለመከታተል የሚችለው ስልክ ስንደዋወል ብቻ ነበር::

  ተንቀሳቃሽ ስልካችሁን አጥፍታችሁ ባትሪዉን ካላወጣችሁ ወይም ከስልካችሁ ተለይታችሁ ካላወራችሁ ባስተቀር ሳትደዋወሉ ተሰብስባችሁ ከማን ጋር ምን እንዳወራችሁ በቀላሉ የመንግሥት ደኅንነት መረጃ ቁዋት ውስጥ ልገባ ይችላል::

  ጾዳቤ(Email) ስትጠቀሙም ከስማችሁ ጋር ግኑኙነት የሌለውን account በመክፈትና password በመጠቀም አንድ ቦታ ወይም የግል ኮምፒዩተር ሳይሆን በተለያየ ቦታ ወይም ብዙ ሰው በሚጠቀምበት በመላላክ ስለ ቤተክርስቲያን መወያየት ትችላላችሁ፡፡

  ReplyDelete
 6. bakihe ataseferara menegeste menem ayametame egiziabehere yaweqale!!!!

  ReplyDelete
 7. ኢትዮጵያ ውስጥ ብሎጋችንን ለማንበበብ ይህን ሊንክ ይጠቀሙ
  http://www.andadirgen.blogspot.in

  Please post this everywhere,like facebook. And may be you should say it this way. Please distribute this for those who can not access this link easily to those in Ethiopia.

  ReplyDelete
 8. Like Kahinat Getachew Don Minale Keneger meleyet bichilu -Fetena bayihonu -Beyegizew yeelihi sira Bayiseru-Sewn & egizabherin mefirat melkam new
  And Adirgen Degimo Kahinun Ato yemalet mebt yelachhum- Kahinun Ato lamalet siltsan yesetsachihu Manew ?Kihint meyaz Kechalachihu Kihinet Mestsetim tichilalachihu malet new ?Leke Kahinat Getachew Donn Ato Malet yemichilew Papas Weyim Sinodos bicha yimeslegal ketesasatku Armug
  Egiziabher yakeberewn sinaward -Kahinun Ato sinil-Papasun Sisedib Bete Kirsityan Kebad yehone fetena metsabat enj yeteshale neger yelem Degimo Betsam Yemgermew Kahinun Ato -Papasun Hatsiatega-Yesewn Bedel Hulu Yemitimezegibut yebete kirstiyan ljoch nachihu Sedibo lesedabi mestset new
  Ebakachihu Abatochachinn Lemesdebi - Kidusann Lemasadedi- Bete kirstyann lemafires Abba Selam -Awde Mihiret-Deje Birhan yetebalut yibekalu enante Melkam zena akirbu Egizabher yirdachihu

  ReplyDelete