Saturday, October 29, 2011

Before One Month.......

   መነኩሴው በተክሊል ጋብቻ መፈፀማቸው
  • ምንኩስናው ቢፈርስ እንኳን በተክሊል ማግባት አይቻልም.. - ቤተክርስቲያን
  • ከሳምንት በፊት ቆቤን ለቸገረው ሰጥቻለሁ.. - ሙሽራው
  • ምንኩስናውን አፍርሻለሁ ስላለኝ ጋብቻውን ተቀብያለሁ.. - ሙሽሪት
  • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ኮሌጅ የተመረቁት ..መነኩሴ.. የምንኩስና ሥርዓቱን ጠብቀው ምንኩስናቸውን ሳያፈርሱ በሙሽሪቷ የትውልድ አገር በሀዲያ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን ቤተ መቅደስ በይፋ በተክሊል ሥርዓተ ጋብቻ መፈፀማቸው አነጋጋሪ ሆኗል፡፡

ቤተክርስቲያን የጋብቻ እና የምንኩስና ሥርዓት እንዳላት የሚናገሩት የጉራጌ ከንባታና ሐዲያ ሀገረ ስብከት ጳጳስ አቡነ ቀለምጢዎስ፤ አንድ መነኩሴ ሥርዓቱን ፈሞ ምንኩስናውን ሲወስድ ከዓለማዊ ነገር ተገልሎ ቆቡን እንደሚስት አግብቶ መኖር እንዳለበት ተናግረዋል፡፡ ቆቡን ሳያወልቅ ወይም ምንኩስናውን ሳያፈርስ ምንም ዓይነት ዓለማዊ ሥርዓት መፈፀም እንደማይችልም አስገንዝበዋል፡፡

ነገር ግን መንፈሳዊ ሆኖ መኖር ካቃተው ወደ መነኮሰበት ገዳም አሊያም ጠቅላይ ቤተክህነት ቀርቦ ምንኩስናውን አፍርሶና ቆቡን ጥሎ አለማዊ ሆኖ መኖር እንደሚችል ገልፀው፤ ይህም ሆኖ ግን በተክሊል ማግባት ፈሞ እንደማይችል፤ ይህንንም ሥርዓቱ እንደማይፈቅድ ጠቁማዋል፡፡

እሳቸው በሚያስተዳድሩት ሀገረ ስብከት ሥር አንድ መነኩሴ በይፋ በተክሊል ሥርዓተ ጋብቻ ፈሟል መባሉን ሰምተው፣ ጉዳዩን በጥብቅ እየተከታተሉት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ጋብቻውን ፈመዋል የተባሉትን አባ ገብረክርስቶስ ታምሩ አነጋግረናቸው፤ ከሳምንት በፊት ከመንፈሳዊ ኮሌጅ ተመርቀው ቤተክህነቱ ሥራ እንዲመድባቸው ሲጠይቁ ሊመደቡ እንዳልቻሉ እና እስኪመድባቸው እንኳን እዛው ኮሌጅ ውስጥ ማረፍያ እንዲሰጣቸው ሲጠይቁ ከጊቢው በጥበቃ ሰራተኛ ተገፍትረው መውጣታቸውን ለአዲስ አድማስ ገልፀው፤ በድርጊቱ ተናደው ቆባቸውንም እዛው ለቸገረው ሰጥተው ቤተክህነትን ጥለው ወጥተው ጋብቻውን መፈፀማቸውን አረጋግጠዋል፡፡

ሙሽራዋን ቀደም ሲል በጓደኝነት ይዘዋት እንደነበር ያልሸሸጉት አባ ገብረክርስቶስ፤ እስከ ሰርጉ እለት ድረስ ግንኙነት አለመፈፀማቸውን ሰርጉ በተክሊል እንዲሆን የወሰኑትም ..ለልጅቱ ብዬ ነው.. ብለዋል፡፡

..መነኩሴው ሁሉ በየጓዳው የሚያደርገውን እኔ በአደባባይ ስላደረኩት ነው ወሬ የሚሆነው?.. ሲሉ የሚጠይቁት አባ ገብረክርስቶስ፤ ..ተክሊልም ሆነ ምንኩስና ሥርዓት ነው በሥርዓቱ መሰረት ቆቤን ጥዬ ትዳር መስርቻለሁ.. በማለት አስረግጠው ተናግረዋል፡፡

የ26 ዓመቷ ሙሽሪትም በበኩሏ፤ ግንኙነት ከጀመረን ሁለት ዓመት አልፎናል በወቅቱ ..እግዚአብሔር ጋብቻ እንድፈም ፈቅዷል፤ ምንኩስናየን አፍርሼ መጥቻለሁ ብሎኛል እሱን አምኜ ጋብቻ ፈሜያለሁ፤ አሁንም እሱን ነው የማምነው.. ስትል መልስ ሰጥታለች፡፡

ሙሽራው መነኩሴው ስለመሆኑ እንደማያውቁ የገለፁት የሙሽሪት ቤተሰቦች፤ በጉዳዩ ማዘናቸውን የገለፁ ሲሆን ሙሽራው በበኩሉ ..እኔ ለቤተሰቦችሽ ንገሪ ብያት ነበር፤ ያልተናገረችው እሷ ናት.. ሲሉ መልሰዋል፡፡



‹‹ቤተክርስትያናችን ጠያቂም ተጠያቂም ሰው የሌለባት መሆኑን ሳስበው…………… በጣም አዝለሁኝ›››


አዲስ አድማስ

4 comments:

  1. ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባ አሉ....በቤተክርስቲያን ላይ እንዲህ ያለ ድፍረት......በእውነት ያሳዝናል፡፡

    ReplyDelete
  2. የራሴን ታሪክ ነገርኩህ፤ አንተንም ሆነ ደጋፊዎችህን አይነካም። ምነዋ! ያላወጣኸው?
    ቂቂቂቂቂ! እኔም ላገባ ነኝ ስል ቅር አለህ? አንተ አግብተህ፤ እኔን ለመከልከል ትሻለህ?
    ክርስቲያን ራስ ወዳድ አይደለም። እሱ ማድረግ የማይፈልገውን ነገር በሌላው ላይ አይጭንም። ምነው ምንኩስናህን ተውክ ብሎ የሚጠይቀኝ ካለ ለዚያ ፈራጅ መተው ሲገባህ አንተ እርሱን ተክተህ ፈረድህ!!!ለምን? እኔ ግን ድሮም ያስገደደኝ አልነበረም፤ አሁንም የሚያስገድደኝ የለም ብያለሁ። አንተና አንተን መሰሎች እዚያው ቆይ ብላችሁ በሃሳባችሁ ለማስገደድ ካልፈለጋችሁ በስተቀር። እኔን ለማስተማርና ስህተት ፈጽመሃል ብለህ የምታዝንልኝ ከሆነ ይህንን ጽሁፍ አውጣ፤ አድራሻዬን ልላክልህ፤ ከዚያም አስተምረኝ። አትፍራ እሺ!

    ReplyDelete
  3. This is right Choise for those young, hot monks. He did better.

    ReplyDelete
  4. min yibalal EGZIABIHER lehulachinim libona yisiten enji. lanifetsimew ayasigemiren

    ReplyDelete