ቀደምት የኮፕቶች ፈተና
በቤተክርስትያን መድረክ ላይ አብዩን ሚና ሲጫወቱ የነበሩት የእስክንድርያና የአንፆኪያ(ሶርያ) አብያተ ክርስትያናት ቀደም ሲል በ451ዓ.ም በልዮን ጦማር ምክንያት በተፈጠረው መለያየት ገዥዎቻቸው በነበሩት እና የሁለት ባህርይ እምነት ደጋፊ በሆኑ ነገስታት በኋላ ግብፅንና ሶርያን በተቆጣጠሩ እስላሞች ባላባራ የመከራ ዝናብ በመደብደባቸው ፤ የቀድሞ ቦታቸውን አጥተው በምዕመና ቁጥር ተመናምነው አሁን ያሉበት ደረጃ ላይ ደርሰዋል፡፡ አነዚህ አብያተ ክርስትያናት ለዚህ ሁሉ ተጠያቂ የሚያደርጉት በወቅቱ የነበሩትን የሮም ካቶሊክና የግሪክ ቤተክርስትን መሪዎችን ነው፡፡
በቅርብ ጊዜያት በግብፃውያን ክርስቲያኖች ላይ አደጋዎች እየበዙ ስለመጡ ሰዎች ወደ ውስጥ ሲገቡ በኤልክትሪክ መፈተሸ መሳሪያ እየተፈተሹ ነው፡፡ በየትኛውም የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ስትገቡ መፈተሸ ግድ ነው ፡፡ ይህ የሚያሳየን ምን ያህል ፈተና ላይ እንዳሉ፤ የተሸከሙት ቀንበር ከባድ መሆኑን ጭምር ነው፡፡
- ለተቃውሞ በወጡት ኦርቶዶክሶች ላይ በጎማ ታንክ ሄደውባቸዋል
- «እንደ አባቶቻችሁ ለእግዚአብሔር ብቻ ስትሉ አገልግሉ፡፡ የናንተ አባቶች ለእግዚአብሔር ብቻ ሲሉ የሚያገለግሉ ነበሩ» አቡነ ሺኖዳ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አማኞች ያስተላለፉት መልእክት
- በመንግስት መስሪያ ቤቶች ውስጥ ይሰሩ የነበሩት ክርስትያኖች ጥፋት ክርስትያን በመሆናቸው ብቻ ይባረሩ ነበር፡፡
- ገደብ የለሽ ግብርና የነፍስ ወከፍ ታክስ እንዲከፍሉ ይገደዱ ነበር፡፡
- አንድ ፓትርያርክ ሞቶ ሌላ ለመተካት ከገዥዎች ፍቃድ ለመጠየቅ ከፍተኛ ገንዘብ ይሰጥ ነበር፡፡
- በእስክንድርያ ቤተክርስትያን ፓትርያርኮች ላይ እስራት እና ስቃይ ገዥዎቹ ያደርሱባቸው ነበር፡፡
- በመስቀል ጦርነት ጊዜ እስላሞቹ በተዋህዶዎችና በምዕራብ መለካውያን መካከል የተፈጠረውን ስር የሰደደ ቅራኔ ግንዛቤ ውስጥ ሳያስገቡ ክርስትያን በመሆናቸው ብቻ በተዋህዶዎች ለመስቀል ጦረኞች(ካቶሊኮች) ያግዛሉ ብለው በመጠራጠር በዓይነ መዓት ይመለከቷቸው ነበር፡፡
- አብያተ ክርስትያናቱን ከነሀብታቸው ያለ የሌለ ሀብታቸው ተሟጦ የተወረሱበት ጊዜ ነበር፡፡
- የሱኒ እስልምና እምነት ተከታይ የነበረው ሳላዲን የተባለው የግብፅ ገዥ የአስተዳደር ስራውን እንደጀመረ ክርስትያኖችን ከተለያዩ የስራ ቦታዎች ከማባረሩ በተጨማሪ የውርደት ምልክት የሆነው ከጥቁር ልብስ በስተቀር ነጭና በተለያዩ ህብረ ቀለማት ያጌጡ ልብሶችን እንዳይለብሱ ፤ ፈረስ እንዳይጋልቡ ፤ ከፍ ያለ መቀጫ ገንዘብ ለመንግስት እንዲከፍሉ በማዘዙ ክርስትያኖቹ በግፍ የተጣለባቸውን ገንዘብ ለመክፈል ያለ የሌለ ሐብታቸውን ሸጠዋል፡፡ ርስታቸውንም ለእስላሞች እንዲሸጡ በመገደዳቸው ርዕስት አልባ ሆነዋል፡፡ የመከራው የግፉን ቀንበር መሸከም ያልቻሉት አንዳንድ ክርስትያኖችም በነፃነት ለመኖርና ባለመብት ለመሆን የእስልምና እምነት መቀበል የግድ በመሆኑ ሳይወዱ በግድ ሰልመዋል
ኮፕቶችና የጊዜው ፈተናቸው
በግብፅ ውስጥ የሚኖሩ የክርስትያኖች ቁጥር የህዝቡን 10 በመቶ በላይ ሲሆን በቁጥም ከ8ሚሊየን ይልቃል በሀገራቸው ፤ እትብታው በተቀበረበት ቦታ ላይ የሁለተኛ ዜግነት ተደርገው ነው የሚወሰዱት በአሁኑ ጊዜ ኮፕቶች የማይሸከሙትን ጫና በእስላማውያኑ እየደረሰባቸው ይገኛል፡፡ ቤተክርስትያን መስራት አይችሉም ፤ ተገደው ከሙስሊሞች ጋር እንዲጋቡ ያደርጓችዋል ፤ አንድ ሰው ከክርስትና ወደ እስልምና ተገዶ እንዲቀይር በማድረግ በመፅሄቶቻቸው በጋዜጦቻቸው ሲያወጡ ፤ አንድ ሰው ግን አምኖ ከእስልምና ወደ ክርስትና እምነት ቢቀይር የሚገጥመው ሞት ብቻ በመሆኑ ዝምታውን መርጠው ሀገር ቀይረው ይኖራሉ እንጂ ባደጉበት አካባቢ የመኖር ነፃነታቸው የተገፈፈ ነው፡፡
የሙባረክ መንግስት በስልጣን ላይ እያለ የተቃውሞ ድምፅ በካይሮ ምድር በጣሂር አደባባይ ሳይሰማ በ2011 አዲስ ዓመት የመጀመሪያው ቀን ላይ የኮፕት ኦርቶዶክሶች የጌታችንና የመድሐኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ልደቱን በቤተክርስትያናቸው ላይ አክብረው ወደ ቤታቸው ለመሄድ ከቤተ መቅደስ ሲወጡ መንግስት በቂ ፖሊስ ባለመመደቡ አክራሪ ሙስሊሞች ሶስት መኪና ላይ ባጠመዱት ቦምብ ምክንያት አካባቢውን ዋይታና ለቅሶ እንዲነግስበት ያደረጉ ሲሆን ‹‹በየአደባባዮቻቸው እንባ እጅግ እያፈሰሱ ሁሉም አልቅሰዋል።›› ትንቢተ ኢሳይያስ 15፤3 የክርስትያኖች ደም ያለአግባብ እንደ ውሀ የፈሰሰበት ፤ የ33 የኮፕት ክርስትያኖች ህይወት ያለፈበት ጊዜ ነበር፡፡ ‹‹ጌታ እግዚአብሔርም ከፊት ሁሉ እንባን ያብሳል›› ትንቢተ ኢሳይያስ 25፤8 ብሎ ኢሳያስ እንደተናገረው እግዚአብሔር እንባቸውን አንድ ቀን እንደሚያብስላቸው በመተማመን ከነፈተናቸው በእምነታቸው ፀንተው እየኖሩ ይገኛሉ::
በቅርብ ጊዜያት በግብፃውያን ክርስቲያኖች ላይ አደጋዎች እየበዙ ስለመጡ ሰዎች ወደ ውስጥ ሲገቡ በኤልክትሪክ መፈተሸ መሳሪያ እየተፈተሹ ነው፡፡ በየትኛውም የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ስትገቡ መፈተሸ ግድ ነው ፡፡ ይህ የሚያሳየን ምን ያህል ፈተና ላይ እንዳሉ፤ የተሸከሙት ቀንበር ከባድ መሆኑን ጭምር ነው፡፡
በአክራሪ ሙስሊሞች በተለያዩ የግብጽ አካባቢዎች በክርስቲያኖች ላይ የሚፈጸሙትን ጭፍጨፋዎችና ግድያዎች እንዲሁም ወጣት ክርስቲያን ሴቶችን በግድ እያገቡ ማስለም እና ሌሎች የሰብዓዊ መብት ረገጣዎችን በማስመልከት በ1971 ኖቬምበር 14 ቀን በመንበረማርቆስ የተቀመጡት ፖፕ ሺኖዳ እንዲህ ብለው ነበር
“ስሙ ወንድሞቼ፤ ልናገረው የምሻው ብዙ ነገር በአእምሮዬ ነበረኝ። በልቤም ውስጥ ከዚያ የሚበልጥ ብዙ ነገር አለ። ይሁን እንጂ ዝም ማለትን እመርጣለሁ። እኔ ዝም ማለትን የመረጥኹት (በምትኩ) እግዚአብሔር እንዲናገር ስለምፈልግ ነው። እመኑ፤ ዝምታችን ከመናገር በላይ ገላጭ ሊሆን ይችላል። እግዚአብሔር ደግሞ ዝምታችንን እያዳመጠ ነው። እግዚአብሔር ዝምታችንን ይሰማል። የዝምታችንን ትርጉምና እየደረሰብን ያለውን መከራም ያውቃል። መከራ እየተቀበልንበት ስላለው ጉዳይ ነገራችንና ችግራችንን ሁሉ ለእግዚአብሔር አሳልፈን እንሰጣለን። በእጆቹም ላይ እንተወዋለን። እናም ‘ያንተ ፈቃድ ይሁን/ ወይኩን ፈቃድከ’ እንላለን። (ጌታ ሆይ) ‘ይህንን ችግር መፍታት ከፈለግኽ ፈቃድህ ይሁን፣ የመከራን መስቀል እንድንሸከም ከፈቀድክም… (ካሉ በኋላ እንባቸውን እያፈሰሱ አለቀሱ) “…ችግራችንን ለእግዚአብሔር እንስጥ/ እንተው ያልኩበት ምክንያት እግዚአብሔር ሁሉን የሚገዛ/ የሚቆጣጠር ስለሆነ ነው። እርሱ ሁሉን ያያል። ሁሉንም ነገር ይሰማል። ሁሉንም ነገር ያውቃል።” በማለት ነበር
ክርስትያኖቹ ሰላማዊ እንቅልፍ በተኙበት ሰው መግደል ጀነት(ገነት) እንደሚያስገባ በተነገራቸው ሙስሊሙች በሰይፍ እየተሰየፉ ይገኛሉ ፡፡ከወራት በፊት ለ30 ዓመት ግብፅን ሲያስተዳድራት የነበረው የሁስኒ ሙባረክ መንግስት በጣሂር አደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ በወረደ ሳምንት ሳይሞላው በአክራሪ እስላሞች ለሊት የሚኖሩበት ቤት ጣራ ቀደው በመግባት የ11 ሰውን ህይወት ነበር የቀጠፉት፡፡ ይህን የመሰለ ዘግናኝ ድርጊት ለማድረግ ማሰብም ሆነ ድርጊቱን መፈፀም አስላማዊ ትምህርቱ ያመጣው ተፅህኖ መሆኑ እሙን ነው፡፡
በቅርቡ በኮፕት ኦርቶዶክሶች የሀገሪቱ የዜና ማሰራጫ ጋር ሄደው ባሰሙት ሰላማዊ ድምጽ ግጭት የተፈጠረ ሲሆን በግጭቱ ፖሊሶች ህግ ከሚፈቅደው ውጪ ለተቃውሞ በወጡት ኦርቶዶክሶች ላይ በጎማ ታንክ ሄደውባቸዋል ፤የአለም መንግስታት የተለያዩ የእምነት ተቋማት የ26 ሰዎችን ነፍስ የቀጠፈውን ፤ በመቶዎች የሚቆጠሩ ክርስትያኖች ከፍተኛ የአካል ጉዳት የደረሰበትን ሁኔታ ግጭት ሲያወግዙ በዘጠኝ ወር ጊዜ ውስጥ ከ80 በላይ ክርስትያኖች እንደተገደሉ ከቢቢሲ ዘገባ ለመረዳት ችለናል፡፡
ኮፕቶችና እኛ
ኦርየንታል ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያናት ከሚባሉት ውስጥ የአርመን ፤ የኢትዮጵያ፤ የኤርትራ ፤ ሶሪያ የህንድ እና የግብፅ አብያተ ቤተክርስትያናት ይገኙበታል፡፡ በጠቅላላው ከፍተኛ የአማኝ ቁጥር በመያዝ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን የመጀመሪያውን ረድፍ ትይዛለች:: እነዚህ አብያተክርስትያናት በዘመናት በፊት በብዙ ነገር የሚረዳዱ እንደ አንድ ቤተክርስያን የሚቆጠሩ ሲሆኑ ለምሳሌ ለኢትዮጵያ ቤተክርስትያን እስከ 1951 ዓ.ም ድረስ ከግብፅ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ነበር ፓትርያርክ የሚሾምላት፡፡ ብፁእ አቡነ ባስልዮስ የመጀመሪያው ፓትርያልክ ተብለው እሲኪሾሙ ድረስ ለ1600 ዓመታ ያህል 111 (አንድ መቶ አስራ አንድ) ያህል ፓትርያርኮች ከግብፅ ምድር ተሹመው ቤተክርስትያናችንን ሲያስተዳድሩ ቆይዋል፡፡
አፄ ኃ/ስላሴ ከግብፅ ፓትርያርክ ጋር
ከ4መቶ ዓመታ በፊት ታሪክ እንደሚያስረዳን በአፄ ዳዊት ዘመነ መንግስት ኮፕቶች እንደ አሁኑ ጊዜ ስቃዩ በዝቶባቸው የክርስትያን መንግስት ለነበራት ለኢትዮጵያ መልዕክት ልከው ነበር ፡፡ በግብጽ ያሉ ሙስሊሞች እየበዙ ኃይላቸው እየጠነከረ ሲሔድ በእስክንድርያ የሚኖሩትን ክርስቲያኖች ላይ ሥቃይ ያጸኑባቸው ጀመር ክርስቲያኖቹም አንድ ሆነው መክረው ለኢትዮጵያዊ ዓፄ ዳዊት እንዲህ የሚል መልዕክት ላኩ “ንጉሥ ሆይ! በዚህ በግብጽ ያሉ እስላሞች መከራ አጽንተውብናልና ኃይልህን አንሥተህ አስታግሥልን ብለው ጠየቁት” ዳግማዊ ዓፄ ዳዊትም ለመንፈሳዊ ኃይማኖት ቀንተው የክርስቶስ ፍቅር አስገድዶአቸው ፳ ሽህ ሠራዊት አስከትለው ወደ ግብፅ ዘመቱ በዚህ ጊዜ በግብፅ ያሉ ኃያላን ፈሩ ተሸበሩ ንጉሡ ዳግማዊ ዳዊትም እንዲህ የሚል መልዕክትና ማስጠንቀቂያ ለሙስሊሞቹ ላኩ ‹‹በተፈጥሮ ወንድሞቻችሁ ከሆኑት ክርስቲያኖች ጋር ካልታረቃችሁ ሀገራችሁን መጥቼ አጠፋዋለሁ›› ፡፡የንጉሡ መልዕክት ለሙስሊሞቹ እንደደረሳቸው ፈርተው እንደ ጥንቱ በየሃይማኖታቸው ፀንተው በሰላም እንዲኖሩ ከክርስቲያን ወንድሞቻቸው ጋር ታረቁ፡፡
መታረቃቸውን ዳግማዊ ዳዊት ሰሙ በዚህም ጉዳይ ንጉሡ በጣም ደስ አላቸው እገዚአብሔርንም አመሰገኑ በግብፅ የሚኖሩ ክርስቲያኖችም ከ፲፪ ሺህ ወቄት ወርቅ ጋር ደስታቸውን ለኢትዮጵያዊው ንጉሥ ለዳግማዊ ዳዊት በደብዳቤ አድርገው ላኩላቸው ንጉሡም የደስታውን ደብዳቤ ተመልከተው ደስ ኣላቸው ፤ ወርቁን ግን መልሰው በመላክ እንዲህ የሚል ደብዳቤ ፃፉ ‹‹በግብፅ የምትኖሩ የክርስቶስ ተከታዮች ሆይ እንኳን ደስ አላችሁ የላካችሁልኝን ፲፪ ሺህ ወቄት ወርቅ መልሼ ልኬላችኋለሁ የእኔ ዓላማ ወርቅ ፍለጋ አይደለም የክርስቶስ ፍቅር አስገድዶኝ ነው በተቻለኝ መጠን ችግራችሁን ሁሉ አስወገድኩላችሁ …..››
ይህ የሚያሳየን ቀደምት አባቶቻችን በክርስትና ላይ የሚደረግ ጥቃት ራስ ላይ እንደደረሰ አድርገው ቆጥረው በቻሉት መጠን ጦርም ሰብቀው ይሁን በሌላ መንገድ መፍትሄ እንደሚሹላቻ ነበር:: አሁን ግን ጊዜው የተገላቢጦሽ ሆነና የክርስትያኖች ደም ሲፈስ በአይናችን እያየን በጆሯችን እየሰማን እንዳላየን ማለፉን መርጠናል፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ሲኖዶስ እንኳን ኦፊሺያል የሆነ ደብዳቤ ለኮፕት ክርስትኖች የሀዘናቸው ተካፋይ መሆኑን እግዚሐብሔር ባጋጠማቸው ፈተና እንዲያፅናናቸው ደብዳቤ ለመፃፍ አለመቻላችንን ሳስበው በጣም ይገርመኛል:: እንደ አባቶቻችን ጦር ሰብቀን ያሉበትን ጫና እናስለቅቃቸው አላልኩም፡፡ ባይሆን አንድ ነጠላ ገፅ መልዕክት ፅፈን ብናፅናናቸው መልካም መስሎ ስለታየኝ ነው:: አሁን ካሉት አባቶቻችንስ ይህን ሀሳብ የሚያነሳ አባት ጠፍቶ ነው? በመሰረቱ የራሳችንም ችግር አላስተነፍስ ብሎናል ይህን አውቃለሁ ፤ ችግሮቻችን እግር አውጥተው መሄድ ከጀመሩ ሰንበትበት ብለዋል ፡፡ ቤተክርስትያችን የእሷ ባልሆኑት ሰዎች እናድስሽ ፤ መታደስ አለባት በሚሉ ሰዎች ብትከበብ እንኳን ሌላ ቦታ የሚደረግ ኢ-ክርስትያናዊ የሆነ ምግባርን ኦፊሺያል በሆነ መልኩ መቃወም መቻል አለብን የሚል እምነት ስላለኝ ነው፡፡
እርስዎ ምን ይላሉ?
‹‹እግዚአብሔር ለኮፕት ኦርቶዶክሶች መፅናናቱን ይስጣቸው››
ጥቂት ምንጭ
- ከመላኩ አዘዘው ድህረ ገፅ (ግማደ መስቀሉ)
- አናቅፅ ሲኦል (ከብርሀኑ ጎበና)
ታላቁ የክርስቲያኖች ፈለግ ሀዋርያው ማርቆስ ሀዲስ ኪዳንን በሰበከባት ምድር እንዲህያለው ሰማአትነት የሚቀናበት ነው:: በርግጥም አቡነ ሺኖዳ እንዳሉት ዘመኑ የመገፋት ነው:: ስለ ጌታ ስም መከራ መቀበል ካልቻልን እንደምን ይሆናል?
ReplyDeleteየዓለም ወግ ሁኖ ሳይሆን: ስለእምነታችን ብለን ግን : ጸሃፊው እንዳሉት ወንድሞቻችንን ማሰብ ያሻናል::
<> This is expected from all of us
ReplyDeleteGeta nefsachewn yimar!
ReplyDeleteAmklake kedusan nefsachewen yimar.enesus yekbren aklil yekebelalu.yiblagn ezih midr lay hhonew christianochen lemiasadedut.
ReplyDelete