Wednesday, October 19, 2011

ከእሳት የተረፉ ቅርሶች


የመሐል ዘጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የተተከለው በ1292ዓ.ም. ሲሆን በርካታ ጥንታውያን ስዕላት፣የብራና መጻሕፍትና ሌሎች ቅርሶች የሚገኙበት ቤተ ክርስቲያን ነው። ቤተ ክርስቲያኑ ከ1986-1989ዓ.ም. እድሳት ተደርጎለት ከ1989 ጀምሮ ሙሉ አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል።

ቤተ ክርስቲያኑን ሙሉ በሙሉ ያወደመው እሳት ባልታውቀ ምክንያት የተነሳው የካቲት 5 ቀን 2002 ዓ.ም. ነበር። 

እሳቱ ቤተ ክርስቲያኑን ሙሉ በሙሉ ያወደመ ሲሆን አብዛኞቹ የቤተ ክርስቲያኑ ጥንታዊያን የብራና መጻሕፍት እና ቅርሶች ያሉበት ዕቃ ቤት ግን ምንም አደጋ አልደረሰበትም። ታቦታቱም ምስጢራዊ በሆነ እሳት በማይደርስበት ቦታ ተቀምጠው ስለነበር ቃጠሎ አልደረሰባቸውም ።ጽላቶቹ ከቤተመቅድሱ ስር ባለ እሳት በማይደርስበት ቦታ ተቀምጠው ስለነበር የካቲት 7 ቀን 2002 ዓ.ም ተገኝተዋል። ምንም ጉዳት ሳይደርስባቸው በቁፋሮ የተገኙ መሆኑ የዛሬ ዓመት ትውስታችን ነው ፡፡  የዚህን ቤተክርስትያን ታሪክ ፤ ውስጡ ያሉትን ከእሳት የተረፉ ቅርሶች ፤ ብታውቋቸው ጥሩ ነው ብለን ስላሰብን የቤተክርስትያኑ ሰበካ ጉባኤ ያዘጋጀውን ‹‹የገዳም ዘጌ አጭር ታሪክ ለታሪክ አጥኝዎች የተዘጋጀ›› መፅሐፍ አቅርበንላችዋል፡፡


አቡነ በትረማርያም በህይወት ሳሉ ንጉስ አምደ ፅዮን የሰጣቸው ስዕለ ማርያም 
ሲመለከቷት አይኗ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አብሮ የሚዞር የምትንቀሳቀስ ምትመስል
መቅረዞች፤ የአፄ ዘርአይያቆብ የስጦታ የብር መሶብ ወርቅ ፤
የአፄ ይኩኖ አምላክ የስጦታ ዘውድ(1270-1285እ.ኤ.አ)  
ትልቅ በብራና ላይ የተፃፈ ገድለ ጊዮርጊስ በግዕዝ የተፃፈ ሆኖ 
የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጋድሎ ስዕላዊ መግለጫ በመስጠት የሚያሳይይህን መፅሀፍ ፖስት ያደረግንበት ምክንያት

  • የዘጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወበትረማርያም ጥንታዊ እና ታሪካዊ ገዳም የውድና ብርቅዬ ቅርሶች ባለቤት በመሆኑ ለሀገር ውስጥና ለውጭ ሀገር አጥኝዎች  ታሪክና ቅርሶች እውነተኛ መረጃ ለመስጠት
  • በገዳሙ ተጋድሎ ሲያደርጉ በዘጌ ስለነበሩ ቅዱሳን ተግባራ እና እሴቶቻቸውን ለመጭው ትውልድ የማተላለፍ ኃይማኖታዊ ግዴታችንን ለመወጣት
  • የገዳም ዘጌ አባት ስለሆኑት ቅዱስ አባት አቡነ በትረ ማርያም የህይወት ታሪክ ወይም ገድል ፍንጭ ለመስጠት 
  • መተጨማሪ በየደብሮቻችን ያሉትን አባቶቻችን ያቆዩልንን የቤተክርስትያኒቷን ቅርሶች ይህ አግዚሐብሔር በተአምሩ ከእሳት ያተረፈልንን ቅርሶቻችንን በመመልከት የተለየ ትኩረት እንድንሰጣቸው ለማድረግ ጭምር ነው
  • በአሁኑ ሰዓት እየተሰራ ላለው ቤተክርስትያን የበኩልዎን አስተዋፅዎ ያደርጉበታል ብለን የቤተክርስትያኑን ታሪክ ወደ pdf ቀይረን አዘጋጅተንዎለታል፡፡


ይህን መፅሀፍ በpdf ለማንበብ ከፈለጉ

                                          በPdf ያንብቡ

‹‹እግዚአብሔር ቤተክርስትያንን ይጠብቅ››

No comments:

Post a Comment