Thursday, October 13, 2011

የኮምሽኑ ገንዘብ ያለ አግባብ እየባከነ መሆኑን ፓትርያርኩ አስታወቁ


(ጥቅምት 2 2004 ዓ.ም ) አዲስ ዘመን ጋዜጣ የፊት ገፅ ያስነበበው ዜና
  • ‹‹ይህ ጉዳይ አስወቃሽ እና አሳሳቢ ነው›› አቡነ ጳውሎስ
  • ሊቀጳጳሳቱ ፈርሙ ሲባሉ መፈረም እንጂ ጉዳዩን እንደማይከታተሉት ጠቅሰዋል፡፡ በዚህ ምክንያት የሚባክነው ገንዘብ ‹‹ፓትርያርኩ ዝም ብለው እያዘረፉት ነው›› እየተባለ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
  • በልግስና የሚገኝው ገንዘብ በተግባር ላይ እየዋለ የሚገኝበት መንገድ አነጋጋሪ ሆኗል
  • ሰዎችን ከሞት ለማዳን በሕይወት እና በሞት መካከል ያሉትን ወገኖች የመኖር ተስፋን ለመስጠት በልግስና የሚመጣን ገንዘብ ያለአግባ ማባከን እንደማይገባ አቡነ ጳውሎስ አሳስበዋል፡፡ ጉዳዩ ከሳቸው ጀምሮ እስከ አጥቢያው ያሉ የቤተክርስትያኗን መሪዎች እንደሚመለከት አብራርተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ገንዘብ ያለአግባብ እየባከነ መሆኑን የቤተ ክርስቲያኗ ፓትሪያርክ አቡነ ጳውሎስ ማስታወቃቸውን አዲስ ዘመን ዘግቧል፡፡

ፓትሪያርኩ ኮሚሽኑና ፓዝፋይንደር የተባለ ድርጅት በትብብር ባዘጋጀው መድረክ ላይ በድንገት በመገኘት፣ በኮሚሽኑ በሚከናወኑ የልማት ሥራዎችና በገንዘብ አወጣጥ ዙሪያ በርካታ የሰዎች አስተያየቶች እየደረሱዋቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በቤተ ክርስቲያኗ አሠራር መሠረት በየትኛውም ሀገረ ስብከት የሚከናወነው ሥራ ሁሉ ከሊቀ ጳጳሱ ዕውቅናና ፈቃድ ውጪ መከናወን እንደሌለበት አመልክተው፤ እየተካሄደ የሚገኘው እውነታ ግን ከዚህ አሠራር የተገላቢጦሽ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ‹‹የተመደቡት የልማት አስፈጻሚዎች ማንንም አያማክሩም፤ የልማት ማስፈጸሚያ በሚል ገንዘብ ለመውሰድና ለማነጋገር ወደ ማዕከላዊ ኮሚሽን ሲመጡም ማንንም አያናግሩም፤ ችግሮችንም ሆነ መሠራት ያለባቸውን ነገሮች ለሊቀ ጳጳሱ አያስረዱም፡፡ የተመደበውንም ገንዘብ ከሚገባው በላይ ያወጣሉ፤›› በማለት መናገራቸውን ዘገባው አመልክቷል፡፡

To Read in PDF Click here
በ Image መልክ ለማንበብ Click Read More





‹‹ከኛ የሚያመልጥ እርስዎ ጋር የማይደርስ ምንም ወቅታዊ መረጃ የለም››

No comments:

Post a Comment