Tuesday, October 11, 2011

መንግስት ዋሃቢዝምን በይፋ ተቃወመ

Wahabism in Ethiopia as "CULTURAL IMPERIALISM" (http://andadirgen.blogspot.com/2011/09/wahabis-challenge-ethiopian-muslims.html) በሚል 09/13/2011 ርዕስ ዊኪሊክስ ያወጣውን ከኢትዮጵያ የአሜሪካ ኢምባሲ ወደ ዋሽንግተን በአምባሳደር ዶናልድ ያማማቶ ጊዜ የተላከውን ሙሉ መረጃውን ከዚህ በፊት ማስነበባችን ይታወቃል፡፡

መስከረም 25/2004 ዓ.ም በፌደራል ፖሊስ የመሰብሰቢያ አዳራሽ በፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር አማካኝነት የተመራው የግማሽ ቀን ስብሰባ የሚመለከታቸው የሀይማኖት አባቶችና የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት የተገኙ ሲሆን ዋሃቢዝም የእስልምና ሐይማኖት መሰረት አድርጎ የተነሳ ሐገሪቱን በእስልምና ሐማኖት መሰረት መተዳደር አለባት የሚል ቀዳሚ መፈክር ያለው ሲሆን ሌሎች የእምነት ተቋማትን የማይቀበል እና በሳውዲ አረቢያ እና መሰል ሐገራት ከፍተኛ ገንዘብ እርዳታ የሚንቀሳቀስ በኢትዮጵያ ውስጥ በሐረር ፤ በአርሲ ፤ በወለጋ ፤ በባሌ፤ በደሴ ስውር አጀንዳ ይዞ የቆመለትን አላማ ለማሳካት ተከታዮችን እየመለመለ የሚያሰለጥን አመለካከቱን በሙስሊሙ ከፍተኛ የስልጣን ደረጃ ላይ ያሉ ሰዎችን ባማከለ መልኩ የሚሰራ ተቋም ሲሆን የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር በዶ/ር ሽፈራው በስብሰባው ላይ 
እንደተገለፀው መንግስት ስለሚደረገው ነገር የፅሁፍ ፤ የምስልና የድምፅ መረጃ ያለው መሆኑን በማመልከት ይህ እምነት በኢትዮጵያ ውስጥ እንዲካሄድ እንደማይፈቅድ ፤ የኢትዮጵያን ህገ-መንግስት በሚፃረር መልኩ የሚንቀሳቀስ እና ሙስሊም ነጋዴዎች ግብር መክፈል ያለባቸው ለእስልምናው ተቋም እንጂ ለመንግስት አለመሆኑን የሚገልፅ የእስልምና ተቋም ስለሆነ በኢትዮጵያ ቦታ እንደማይኖራቸው እጃቸውን በዚህ እምነት ውስጥ የከተቱ ከፍተኛ የእስልምና መሪዎች ስላሉ እንዲጠነቀቁና እጃቸውን እንዲያወጡ ትዕዛዝም ማስጠንቀቂያም አዘል መልዕክት አስተላልፎ ስብሰባው ከቀትር በፊት ሊያልቅ ችሏል፡፡

እኛስ ከዚህ ምን እንማር ?

ብዙ ነገሮችን ገና ከመጀመሪያቸው ባልሆነ መንገድ ሲሄዱ እያየን ‹‹ይህ የቤተክርስትያን ስርዓት አይደለም›› ማለት አቅቶን አሁን ያለንበት ደረጃ ላይ መድረስ ችለናል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ለያዥና ለገናዥ ያስቸገሩት ሰዎች መጀመሪያ ስህተታቸውን ፤አካሄዳቸውን እንዲያርሙ ‹‹ተው›› ያላልናቸው ግለሰቦች ናቸው፡፡ ይህን የመሰለ ችግር ይመጣል ብለን አስበንም አለማወቃችን ቀድመን ባለመጠንቀቃችን ችግሩን ያመጡት እነሱ ብቻ ሳይሆኑ የኛም ንዝልሀልነት መሆኑን ማወቅ አለብን ፡፡ ሲጀምሩ የቤተክርስትያንን ስርዓቷን በማን አለብኝነት ከስርዓቷ ውጪ በአውደ ምህረት ላይ ያልተገባ መዝሙር ሲዘምሩ አብረን አጨብጭበናል እልልም ብለናል ፡፡ ያሬዳዊ ዜማን ከአእምሯችን ለማጥፋት ግጥሞቻችን እና ዜማዎቻችን ሲቀየሩ ፤ ከመናፍቃን ካሴት ግጥም ተገልብጦ ኦርቶዶክሳዊ በማስመሰል ተሃድሶያውያኑ ዘምረው ሲያዘምሩን ፤ ካሴቱን ሲያመጡልን በመግዛት ለአላማቸውን ተባብረናል ፤ በሚሊኒየም አዳራሽ ገቢው ለቤተክርስትያን ማሰሪያ ብለው ሲጠሩን እንደ በግ ተነድተን ሄደንላቸዋል ኋላ ከአንድ ሚሊየን ብር በላይ የት እንደገባ ባይታወቅም ፤ ብሩን የበላው ጅብ ባይጮህም ፤ በእግዚሐብሔር አውደ ምህረቱ ላይ ታቦቱ ከማደሪያው ወጥቶ የሚያርፍበት ቦታ ላይ ያልተገባ ነገር ሲደረግ አይናችን እያየ ጆሯችን እየሰማ እግዚሐብሔርን ካልፈሩ እኛ ምን አገባል ብለናል ፤ ነገሮች ሲጀመሩ ባለማስተዋል እያየን ያለፍናቸው ድንገት አድገውና በቅተው ሲመጡ አይሆንም ስንል ሰሚ ያጠነው ፤ መጀመሪያ መናገር አለመቻላችንና ‹‹ተው›› የሚል አካል ባለመኖሩ በአሁኑ ሰዓት በቤታችን ብዙ ነገሮች እንደተመሰቃቀሉ ይገኛሉ:: የእስካሁኑ ዝምታችን መቆም ያለበት አሁን ላይ ነው፡፡  ቤተክርስትያንን የዘማሪው ፤ የሰባኪው ፤ የአስተዳዳሪው ፤ የቤተክህቱ ፤ የፓትርያርኩ ብቻ ያደረጋት ማነው? ‹‹ቤተክርስትያን የሁላችን ናት ሁላችንም የቤተክርስትያን ነን›› በመጀመሪያ ከስርዓት ውጪ የሆኑትን ሰዎች የመገሰፅ፤ ትክክል አይደለህም ፤ ስርዓታችን አይደለም ፤ ተው ፤እረፍ የማለት ባህሉን ልናዳብረው ይገባል፡፡ የዛኔ ቆሞ ከመታዘብ እና ከማየት ይልቅ ለቤተክርስትያን ለችግሯ የመፍትሔ አካል መሆን እንጀምራለን ማለት ነው፡፡


መንግስት ነገሮችን ከመነሻቸው አጣርቶ መፍትሄ መስጠቱ ወደፊት የሚመጣውን አደጋ የማስቀረት አንዱ መንገድ ስለሆነ ይህን የመሰለ አካሄድ ውሎ አድሮ ለእኛም ፈተና መሆኑ ስለማይቀር እርምጃው ይበል የሚያስብል ነው፡፡ የአንድ አድርገን ብሎግ አዘጋጅ እኛም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳውያን በጊዜው እየተደረገ ያለውን ሁኔታውን ብናውቀው ጥሩ ነው ብሎ ስላመነ ለእናንተ ለአንባቢያን በዚህ መልኩ ሊያዘጋጅ ችሏል፡፡

ስለ ዋሃቢዝም ለማንበብ Wahabism in Ethiopia as "CULTURAL IMPERIALISM"(http://andadirgen.blogspot.com/2011/09/wahabis-challenge-ethiopian-muslims.html)  

2 comments:

  1. God bless you,keep on ur idea sharing!!!!!!!!!please please don't sleep!it is not the time that any one asleep for his/her religion keeping!

    ReplyDelete
  2. To protect the orthodox church, the solution would be teaching the reality about GOD and Jesus Christ. Who is the savior from our sin/or the world sin? And Know for whom worshiping is necessary, and How?
    Please, would you recommend all the orthodox Church members to read the Original Holy Bible?

    ReplyDelete