Thursday, October 27, 2011

የመናፍቃንን መዝሙር መስማት..........

ዲያቆን ህብረት የሺጥላ 
(ከሕይወተ ወራዙት መፅሀፍ ላይ የተወሰደ)

  • ዘፈን መስማት ኃጢአት ነው የመናፍቃንን «መዝሙር›› መስማት ግን ዓመፅና ክህደት ነው፡፡ ኃጢአት የምግባር ሕፀፅ ሲሆን ዓመፅ ደግሞ የሃይማኖት ሕፀፅ ነው፡፡ የቱ የሚከፋ ይመስልሃል?  
  •  «የመናፍቃንን መጽሐፍ ከመመልከት ተከልከል››ማር ይስሐቅ  :: 
  • «ዑቅ ከመኢትቅረብ ኀቤሃ - ወደ እርሷ ከመቅረብና ገልጾ ከማየት እንኳን ተጠንቀቅ›› ይላል፡፡ ምክንያቱንም ሲያስረዳ መንፈሰ ጽርፈት / የስድብ መንፈስ/ እንዳያድርብህ ነው ይላል፡፡  በእርግጥ ይህ ቃል የተነገረው የመናፍቃንን መጽሐፍ ስለማንበብ ነው፡፡ ማር ይሥሐቅ ከላይ እንዳስጠነቀቀን የመናፍቃንን መጽሐፍ ማንበብ ክፉ ነገር ነው፡፡ መጽሐፋቸውን ከማንበብ በላይ በዘፈን ዜማ የወዛ «መዝሙራቸውን መስማት›› እጅግ አይከፋምን? ስለዚህ እንደ መጽሐፋቸው ሁሉ «መዝሙራቸውንም›› መስማት ይከለክለናል፡፡
  • እነርሱ «የምስጋና መዝሙር›› ቢሏቸውም አስተውሎ ለሰማቸው ፉከራና ሽለላዎች ናቸው፡፡
  • የመዝሙሮቻቸው የጌታችንና የመድሐኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ስሙን ሲያነሡ ልክ ባልጀራቸውን እንደሚጠሩ ያህል በድፍረት መሆኑ ደግሞ እጅግ ያሳዝናል፡፡ ታዲያ አንተ መዝሙራቸውን እየሰማህ ከእነርሱ ጋር «ኢየሱስ ጓዴ›› ለማለት ልብህ ይከጅላልን? 
‹‹ይህ ነው ምስጋናቸው›› ይመልከቱት


ዘፈን መስማትና ዘፋኝነት ለመናፍቃን መዝሙር ሊያጋልጥ ይችላል፡፡ ምክንያቱም የመናፍቃን መዝሙር ከሚያስጨፍር ዘፈን አይለይምና፡፡ እንዲያውም አንዳንድ ኦርቶዶክሳዊያን ወጣቶች ለመናፍቃን መዝሙር የቀረበ አመለካከት እንዲኖራቸው ያደረገው በውስጣቸው ያለው የዘፈን እርሾ ነው፡፡ ብዙ ዘፋኞች ወደ መናፍቅነት እንዲሄዱና በዚያም «ዘማሪ›› እስከመባል መድረሳቸው በዚህ ውጤት ነው፡፡

የተዘረዘሩትን ጉዳቶች ጨምሮ ለከፍተኛ ጉዳት ያጋልጣል፡፡ ብዙ እጥፍ ይከፋል፡፡ ዘፈን ማስማት ኃጢአት ነው የመናፍቃንን «መዝሙር›› ማስማት ግን ዓመፅና ክህደት ነው፡፡ ኃጢአት የምግባር ሕፀፅ ሲሆን ዓመፅ ደግሞ የሃይማኖት ሕፀፅ ነው፡፡ የቱ የሚከፋ ይመስልሃል?

ከባሕር ማዶ ያሉ በርካታ ዘፋኞች ታሪክ ሲጠናና ቃለ መጠይቅ ሲደረግላቸው የሚናገሩት «የቤተ ክርስቲያን ዘማሪ›› እንደነበሩ ነው፡፡ አብዛኞቹ ለዘፋኝነታቸው መነሻ የሆናቸው «መዝሙር›› እንደሆነ አበክረው ይገልጻሉ፡፡

የእነዚህ ዘፋኞች ገለጻ የሚያመለክተው የ«መዝሙር›› ተብዬው ዜማና መሣሪያቸው ከዘፈን ዜማና መሣሪያ ጋር ምንም ልዩነት ስለሌለው ወደ ዘፈን እንደተሳቡ ነው፡፡ ሰይጣን ሰዎችን በለመዱት መሳብ ሥራው ነውና፡፡ የሰው ልብ ማረፊያ ይሻል፡፡ የሰው ልብ ሌላ ለመያዝ ካለሆነ በቀር የያዘውን ለቆ በባዶ መቀመጥ አይሆንለትም፡፡ ይህን የሚያውቅ ሰይጣን መዝሙርን ሲያስለቅቅ ዘፈንን ያስጨብጣል፡፡

ለፈጣሪ ክብር ምሰጋና ይግባውና እኛ ኢትዮጵያውያን እንደ ባሕር ማዶ ሰዎች የመዝሙርና የዘፈን ልዩነት ጠፍቶን ግራ እንድንገባ የሚያደረግ ችግር የለብንም፡፡ ምክንያቱም የመዝሙራችን ዜማ ከዘፈንም ሆነ ከመናፍቃን መዝሙር ዜማ የተለየ ሲሆን የመዝሙር መሣሪያችን ደግሞ ከዘፈንና ከመናፍቃን የመዝሙር መሣሪያ በእጅጉ ይለያልና፡፡

ሆኖም እንደ ባሕር ማዶ ዘፋኞች ሁሉ በኛ አገርም ያሉ በርካታ አዝማሪዎችና ዘፋኞች «ዘማሪ ነበርኩ፣ መነሻዬ የቤተክርስቲያን መዝሙር ነው፡፡›› ሲሉ ይደመጣል፡፡ በእርግጥ ከዘማሪነት እስከ ድቁናና ምርግትና/መሪጌትነት/ ማዕረግ የደረሱ በርካታ ሰዎች ወደ ዘፋኝነት ያዘነበሉና የሄዱ እንዳሉ ይታመናል፡፡ ጥቂቶች ግን ዘፈኖቻቸውን ከሚያዳምጡላቸው ሰዎች መካከል አብዛኞቹ የቤተ ክርስቱያን ሰዎች ናቸው ብለው ስለሚያምኑ ተቀባይነትን እንደሚያገኙ አስበው «ዘማሪ ነበርኩ›› እያሉ ይዋሻሉ፡፡

ቤተክርስቲያን የመናፍቃንን «መዝሙር›› እንዳይሰሙ ልጆቿን የምታስተምረው የዜማ ዕቃዎቿ ከመናፍቃን የመዝሙር መሣሪያዎች ልዩ ስለሆኑ ብቻ አይደለም፡፡ ይህ አንዱ ቢሆንም ዋናው ግን መናፍቃን የሚምሩትና የሚሠውት ለአጋንንት ስለሆነ ነው፡፡

ክስርቲያኖች ደግሞ የአጋንንትንና የጌታን ጽዋ መጠጣት አይችሉም፡፡ መዝሙር መሥዋዕት መሆኑን አታውቅምን? ወይስ በእስራኤል ዘሥጋ ዙሪያ የነበሩ አሕዛብ ክርስቲያኖችን ከብበው ለሚኖሩ መናፍቃን ምሳሌ መሆናቸውን ትጠራጠራለህ? ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እስራኤል ዘሥጋ ከአሕዛብ ጋር ሊኖራቸው የሚገባውን ጠንቃቃ ግንኙነት ለክርስቲያኖች ሁሉ ትምህርት እንደሆነ አድርጎ አስፍሮታል፡፡/1ቆሮ 10÷18-22/

ብዙ ሰዎች «ዘፈን ከመስማት አይሻልምን?›› እያሉ የመናፍቃንን መዝሙር ለማስማት ይከጅላሉ፡፡ ሐዋርያው «አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት›› ሲል በተናገረው ቃል ታምናለህ? /ኤፌ4÷5/ እንግዲያውስ የመናፍቃንን ስብከትና መዝሙር ከመስማት ተከልከል፡፡

በአንዲት ሃይማኖት ስታምን መናፍቃን ሁሉ «በስሜ ይመጣሉ›› ተብሎ በትንቢት እንደተነገረባቸው ምንም እንኳን ስመ ክርስቶስን እየጠሩና «ክርስቲያኖች ነን›› እያሉ ቢመጡም ሁሉም «ውሸተኞች ሐዋርያትና ተንኮለኞች ሠራተኞች›› መሆናቸውን ትረዳለህ፡፡ /2ቆሮ11÷13/ዋናው ግን ትክክለኛዋ ሃይማኖት አንዲት ብቻ መሆኗን እርሷም ርትዕት ተዋሕዶ መሆኗን ማመንህ ነው፡፡

እስራኤላውያን በዘመናቸው በዙሪያቸው ባሉ የአሕዛብ አምላክ ስም እንዳይምሉና እንደ አሕዛብም እንዳይዘፍኑ፣ በአጠቃላይ የጣዖት ስም እንዳይጠሩና ከአፋቸውም እንዳይሰማ ታዘው ነበር፡፡ ትእዛዙም «የሌሎችንም አማልክት ሰም አትጥሩ÷ከአፋችሁም አይሰማ፡፡›› የሚል ነበር፡፡ /ዘጸ23÷13/  በዘመነ ኦሪት እግዚአብሐርን ያመልኩ የነበሩ እስራኤል ዘሥጋ የክርስቲያኖች /የእስራኤል ዘነፍስ/ ምሳሌ ነበሩ፡፡ በዙሪያቸው የሚገኙ ጣዖት አምላኪዎች አሕዛብ ደግሞ ዛሬ በክርስቲያኖች ዙሪያ ለሚገኙ መናፍቃንና አረማዊያን በሙሉ ምሳሌ ናቸው፡፡

ልዩነቱ የዛሬዎቹ መናፍቃን ክርስቲያኖች የያዙትን መጽሐፍ አንግበውና ስመ ክርስቶስን እየጠሩ መምጣታቸው ብቻ ነው፡፡ «ይህም ድንቅ አይደለም ሰይጣን ራሱ የብርሃንን መልአክ እስኪመስለ ድረስ ራሱን ይለውጣለና፡፡ እንግዲህ አገልጋዮቹ ደግሞ የጽድቅን አገልጋዮች እንዲመስሉ ራሳቸውም ቢለውጡ ታላቅ ነገር አይደለም፡፡´/2ቆሮ11፡14-15/
ስለዚህ እስራኤል «የሌሎችን አማልክት ስም›› እንዳይጠሩ የሚያስጠነቅቀው ቃል ከክርስቲያንነት አንጻር ስንመለከተው የመናፍቃንን መዝሙር መስማትና ስመ አምላካቸውንም አስመስሎ መጥራት እንደማይገባ ያስተምረናል፡፡  ስመ ክርስቶስ አንድ ቢሆንም በዚህ ስም ውስጥ የሚወከሉና በእምነት ሊቀበሏቸው የሚገቡ በርካታ ቁም ነገሮች አሉ፡፡ በእነዚያ ላይ የሚፈጠር ልዩነት በበዛ ቁጥር የስሙ ውክልናም እንደዚሁ ይበዛል፡፡

በመሆኑም መናፍቃን በክርስቶስ ላይ ያላቸው እምነት እንደ ኦርቶዶክሳዊያን እስካልሆነ ድረስ እነርሱ ክርስቶስ ብለው በሚጠሩበት ጊዜ ይህ ስም ያለው ውክልና ኦርቶዶክሳውያን ሲጠሩት ከሚኖረው ውክልና በእጅጉ ይለያል፡፡ ታዲያ የስሞች መመሳሰል ስላለ ብቻ የመናፍቃንን መዝሙር ስለ እግዚአብሔር እንደተዘመረ አድርጎ መቀበል እንዴት ይቻላል?

ቅዱስ ጳውሎስ አንድ ሰው ወንጌል ጨብጦና ስመ ክርስቶስን እየጠራ ቢመጣም ስለክርስቶስ የሚናረው የወንጌልን ቃል አጣሞ ሐዋርያት ካስተማሩት ትምህርት የተለየ ከሆነ ያ ሰው ክርስቶስን ሳይሆን «ሌላ ክርስቶስ›› ን እየሰበከ መሆኑን አስረድቷል፡፡ ያ ሰው የያዘውንም ወንጌል ሌላ ወንጌል ነው ይለናል፡፡ እንዲህ ሲል «የሚመጣውም ያልሰበክነውን ሌላ ኢየሱስ ቢሰብክ÷ ወይም ያላገኛችሁትን ልዩ መንፈሰ ወይም ያልተቀበላችሁትን ልዩ ወንጌል ብታገኙ÷ በመልካም ትታገሡታላችሁ?›› /2ቆሮ11÷4ገላ1÷6-9/

ብዙ ነገሮች ተመሳሳይ መስለው ግራ ቢገባህም መናፍቃን የሚያመልኩት ኢየሱስ ኦርቶዶክሳዊያን ከሚያመልኩት ኢየሱስ የተለየ መሆኑን ከላይ በሰፈረው የሐዋርያው ቃል አስተውል፡፡ ይህን ስትረዳ የመናፍቃንን መዝሙር መዘመርና መስማት ምን ያህል ለሰይጣን መገዛትና ስሕተት መሆኑን ትረዳለህ፡፡

ይህን ጠንቅቀው የተረዱ አባቶቻችን ሰለስቱ ምዕትም እንደ ሐዋርያት ሁሉ «ከአርሲሳን ጋር አትጽልይ፡፡ እኒህም መናፍቃን ናቸው፡፡ ከአሕዛብም ጋር ቢሆን፡፡›› ብለዋል፡፡ /ሃይአበ ዘሠልስቱ ምዕት/ መዝሙር ጸሎት መሆኑ ይጠፋሃል? ወይስ ለአባቶችህ ትምህርትና ምክር ግድ የለህም? መዝሙር ጸሎት እስከሆነ ድረስ ከመናፍቃን ጋር አትጸልይ ማለት መዝሙራቸውን አትስማ ማለት ነው ተብሎ ሊተረጎም ይችላል፡፡

ማር ይስሐቅም «የመናፍቃንን መጽሐፍ ከመመልከት ተከልከል›› ይላል፡፡ እንዲያውም ጠንከር አድርጎ «ዑቅ ከመኢትቅረብ ኀቤሃ - ወደ እርሷ ከመቅረብና ገልጾ ከማየት እንኳን ተጠንቀቅ›› ይላል፡፡ ምክንያቱንም ሲያስረዳ መንፈሰ ጽርፈት / የስድብ መንፈስ/ እንዳያድርብህ ነው ይላል፡፡ በእርግጥ ይህ ቃል የተነገረው የመናፍቃንን መጽሐፍ ስለ ማንበብ ነው፡፡ ማር ይሥሐቅ ከላይ እንዳስጠነቀቀን የመናፍቃንን መጽሐፍ ማንበብ ክፉ ነገር ነው፡፡ መጽሐፋቸውን ከማንበብ በላይ በዘፈን ዜማ የወዛ መዝሙራቸውን መስማት እጅግ አይከፋምን? ስለዚህ እንደ መጽሐፋቸው ሁሉ መዝሙራቸውንም መስማት ይከለከላል፡፡

በቅዱስ መጽሐፍ ‹‹የማረኩን በዚያ የዝማሬን ቃል ፈለጉብን፡፡የእግዚአብሔርን ዝማሬ በባዕድ አገር እንዴት እንዘምራለን?›› የሚል አስደናቂ ቃል ተጽፎ ይገኛል፡፡ ይህን ቃል ቅዱስ ዳዊት ወደ ባቢሎን ተሰደው ስለነበሩ እስራኤላዊያን በትንቢት መልክ ተናግሮታል፡፡ በዚህ ዓረፍተ ነገር ውስጥ እስራኤላዊያን «የአግዚአብሔርን ዝማሬ›› በባዕድ አገር እንደማይዘምሩ አረጋግጠዋል፡፡ /መዝ 136÷3-4/

አንተስ ብትሆን? የእግዚአብሔርን ዝማሬ በዘባቾች መኻል ትዘምር ነበርን? አቋምህ እንደ እስራኤላዊያን «አልዘምርም ነበር›› የሚል ከሆነ የራስህን ለእነርሱ አለዘምርም ማለትህ መልካም ነው፡፡ የእነርሱን ዘፈንንና የአምልኮታቸውን መዝሙር ዝፈን ወይም ዘምር ቢሉህስ ታደርገዋለህ? አላደርገውም እንደምትል አይጠረጠርም፡፡ እንዲህ ከሆነ በዙሪያህ ያሉ መናፍቃንና አህዛብ ያንተን ባትዘምርልንም እኛ ስንዘምር ተቀብለን ወይም ስማን ሲሉህ ለምን እሺ ትላቸዋለህ? በሌላ አቅጣጫ ላየው ሰው የነቢዩ የዳዊት ቃል የመናፍቃንን መዝሙር ክርስቲያኖች መስማት እንደሌለባቸው ያስረዳል፡፡

የመናፍቃን መዝሙር ፍጹም ሥጋዊ ነው፡፡ ይህም በዜማውና በማጀቢያ መሣሪያው ብቻ አይምሰልህ፡፡መልእክቱንም ብትመረምረ አንድም ቦታ ኃጢአተኛነትህን እንድትመረምር የሚያደርግ የጸጸትና የንስሐ ቃል አታገኝበትም፡፡ የምትሰማው ሁሉ ስለ ፈውስ፣ ስለማግኘት፣ ስለ ብልጽግና፣ ስለ ክብር፣ ጠላትን ድል ስለማድረግና ስለ መሳሰሉት ሥጋዊ ነገሮች ብቻ ነው፡፡ እነዚህ ነጥቦች በይዘታቸው መንፈሳዊ ናቸውን? ሰማያዊ ነገርንስ ያሳስባሉን? እነዚህ ሁሉ ምንም እንኳን እነርሱ «የምስጋና መዝሙር›› ቢሏቸውም አስተውሎ ለሰማቸው ፉከራና ሽለላዎች ናቸው፡፡

በተጨማሪም ከላይ ሐዋርያው መናፍቃን የሚያመልኩት ኢየሱስ «ሌላ ኢየሱስ ነው›› በማለት ያስረዳን እንደተጠበቀ ሆኖ በየመዝሙሮቻቸው የጌታችንና የመድሐኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ስሙን ሲያነሡ ልክ ባልጀራቸውን እንደሚጠሩ ያህል በድፍረት መሆኑ ደግሞ እጅግ ያሳዝናል፡፡ ታዲያ አንተ መዝሙራቸውን እየሰማህ ከእነርሱ ጋር «ኢየሱስ ጓዴ›› ለማለት ልብህ ይከጅላልን? በዚሁ ላይ መናፍቃን ቅዱሳንና መላእክትን ማቃለላቸው ሳያንሳቸው የባሕርይ አምላክ ክርስቶስን ለማኝና አማላጅ በማድረግ በየመዝሙሮቻቸው በፍጡራን ቦታ ያስቀምጡታል፡፡ ለክርስቲያኖች ይህን የመሰለውን የመናፍቃን መዝሙር ሁሉ መስማት እጅግ አያሳፍርምን?

መናፍቃን እምነታቸውን በመዘሙሮቻቸው ስለሚያንጸባርቁ ያንን ለመስማት መቅረብህ እምነታቸውንም እንደመቀበል ይቆጠርብሃል፡፡ በነገረ ሃይማኖት «ለማስማት መቅረብ›› ብቻ ራሱ እንደመታዘዝና አምኖ እንደመቀበል ይቆጠራልና፡፡ ለምሳሌ፣- መልካሙን ትምህርት ለመስማት ወደ ቤተ ክርስቲያን ብትገሰግስ መሥዋዕት ከማቅረብ በላይ ሆኖ ይቆጠርልሃል፡፡ «ለማስማት መቅረብ ከሰነፎች መሥዋዕት ይሻላል›› ተብሏልና፡፡/ መክ5÷1/
    




8 comments:

  1. ቃለ ህይወት ያሰማልን

    ReplyDelete
  2. ቃለ ህይወት ያሰማልን

    ReplyDelete
  3. Egiziabehere yestelegne,kalehiwot yasemalegne

    ReplyDelete
  4. yezefen dardaru esikisita new endemibalew hulu binitenekek melikam new. Kale hiyiwet yasemalin!!!

    ReplyDelete
  5. egzihabher libona yisten!!

    ReplyDelete
  6. Be iwunet hatyat yemaymesil gin ke tilk kihdet melisachugnalna kalehiwot yasemaln.

    ReplyDelete
  7. abet gud eko new!tadiya yih eskista wode gehaneb mewureja tiru dildiy new.libonawun mastewalun ystachew.kezih menfes fetariyachn EYESUS KIRSTOS ytebiken amen!

    ReplyDelete