Monday, October 17, 2011

ገና ጊዜው ብዙ ያሰማናል


አንድ ግለሰብ ወደ ምዕራብ ሐረርጌዋ ሂርና ከተማ መጣ ሥልጣነ ክህነትም አለኝ በማለት በከተማ ውስጥ ወደሚገኘው ጥንታዊው ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን በመግባት ማገልገል ጀመረ እስካሁን ድረስ ከየት መጣህ? ሥልጣነ ክህነት የሰጠህ ሊቀ ጳጳስ ማን ነው? ከየትኛው የአብነት ትምህርት ቤት ተማርክ? ወዘተ ወዘተ የሚል ጥያቄ የጠየቀው የለም ብቻ ቃሉን ብቻ በማመን የቤተ ክርስቲያኑ የአገልግሎት በር እስከ ውስጥ ቤተመቅደስ ድረስ ተፈቀደለት እርሱም ገባ ማገልገል ጀመረ ለአንድ ወር ያህል ከመቅደስ ሳይለይ አሐዱ አብ ብሎ ቀደሰ ቅዱስ ብሎ ኪዳን አደረሰ፤ ጊዜው ሲደርስ ከደብሩ አለቃ ተሰናብቶ መሸኛ ደብዳቤም ተቀብሎ ለአንድ ወር ያህል ማለዳ በኪዳን ሰርክ በጉባኤ ያገለገለባትንም የቅድሰት ሥላሴ ደብር ተሰናብቶ ሄደ፡፡ ግለሰቡ በቀጥታ የሄደው ወደ ሌላኛዋ የምዕራብ ሐረርጌ ዋና ከተማ ወደ ጭሮ /አስበ ተፈሪ/ ነበር፡፡ በዚያም የሆቴል አልጋ ይዞ ያድራል፡፡  ያደረበት ሆቴል በማለዳ በሆቴሉ ያደሩ ደንበኞችን ስም ዝርዝር እንደተለመደው ለፖሊስ ሪፖርት አደረገ፡፡ ሪፖርቱን የተመለከተው ፖሊስ ጥርጣሬ ያድርበትና አንድ ወር ሙሉ ያገለገለባት ቤተክርስቲያን ካህናት እና ምዕመናን ያልጠየቁትን የማንነት እና የከየት መጣህ ጥያቄ ይጠይቃል፡፡ ሰውየው ለሆቴሉ ያስመዘገበው ስም ሒረጂም ሲሆን ከወሎ አካባቢ መምጣቱን እና የእስልምና ዕምነት ተከታይ መሆኑን ያረጋግጣል፡፡ ሰውየው ክርስትና የተነሳው በ 2002ዓ.ም መሆኑን ሲያምን የያዘው ማስረጃ ደግሞ ቅስና የተቀበለው በ 1995ዓ.ም. መሆኑን ያሳያል፡፡ በተጨማሪም የሂርና ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን የራስጌና የግርጌ ማሕተም የተመታባቸው በርካታ ነጭ ወረቀቶች በግለሰቡ እጅ ተይዟል፡፡ በመሆኑም ፖሊስ ግለሰቡን እና የሂርና ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን አስተዳደሪን በቁጥጥር ስር አውሎ ፍርድ ቤት አቅርቧቸዋል፣ የዞኑ ፍርድ ቤትም የደብሩን አለቃ በዋስ የለቀቃቸው ሲሆን አንደኛ ተከሳሽ በማረሚያ ቤት እንዲቆዩ በማድረግ ለጥቅምት 14 ቀን 2004ዓ.ም. ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል፡፡


ተመልካች ባጣው በዚሁ የምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ሰፊና ከ90 በላይ አብያተ ክርስቲያናት ያሉት ቢሆንም በርካታ አብያተ ክርስቲያናት የተዘጉበት እና ከፍተኛ የተሀድሶ እንቅስቃሴ የነገሰበት ነው፡፡  ካሁን በፊት በሐረር ከተማ የተሰጠውን የተሐድሶ ሠራዊትነት ሥልጠና ያስተባበረው መ/ር ገበየሁ ይስማው፣ የወረዳው ሊቀ ካህን አባ ብርሃነ መስቀል እና ዲ/ን በረከት የዚሁ ተመልካች ያጣው ሀገረ ስብከት ሰራተኞች ሲሆኑ በሥልጠናው ከተሳተፉት “አገልጋዮች” ውስጥ 12ቱ በዚሁ ሀገረ ስብከት ስር እስከ ደብር አስተዳደሪነት በሚደርስ ኃላፊነት የሚያገለግሉ  አገልጋዮች ይገኙበታል፡፡ በተለይም ከ2000ዓ.ም ወዲህ በዲ/ን በጋሻው አማካኝነት በርካታ ግለሰብ አምላኪ ማኅበራትን እንደ አሸን በመፈልፈል ሳያውቁት የተሐድሶ እንቅስቃሴው ዓላማ ተልዕኮ ፈጻሚ በማድረግ ከባድ አደጋ እያደረሰበትም ይገኛል፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን የምስራቅ ሐረርጌና የድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ስልጠናውን በተካፈሉት ሰራተኞቻቸው ላይ የማስተካከያ እርምጃ ሲወስዱ እንኳን የምዕራብ ሐረርጌው ሀገረ ስብከት ምንም እንዳልተፈጠረ ዝምታን መምረጡ ከላይ ያነበባችሁት እውነተኛ ታሪክ በካህናቱ የዋህነት አልያም በአሕዛብ ተንኮል ብቻ የተፈጸመ አድርጋችሁ እንዳታስቡ አያደርጋችኋል፡፡

በማቲዎስ አጥምዛ

6 comments:

  1. እጅግ በጣም አስገራሚ ወሬ ለቤተክህነት ደሞ እጅግ በጣም አሳፋሪ ታሪክ ለእኛ የቤተክርስቲያን ልጆች ደግሞ አንገትን የሚያስደፋ አስተዳደራዊ ድክመት! መቼ ይሆን ከእንዲህ አይነቱ አሰራር የምንራራቀው! እግዚአብሄር መፍትሄውን ያሳየን ዘንድ ሁላችንም እንጸልይ! የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሄር ጸሎታችንን ይሰማናል!!!!!
    መ.ዘ ከሽሮሜዳ

    ReplyDelete
  2. Kidanemariam Ze Negelle BoranaOctober 17, 2011 at 9:09 AM

    yebase atamta malet yishalal? woyis yesemi yaleh bilo mechoh?!

    ReplyDelete
  3. betam yigerimal ahiya kejib yiwulal endegenam berem bihon ke araju yiwulal wey kiristina endezih yihun eras asalifo mestet yihun? min enilalen lehulachinim egziabher amlak libona yisten newa lela min yibalal tadisa. bere hoy sarun ayehina gedelun satayi ................ hon yegna mecheresha.

    ReplyDelete
  4. ya sazinal tadiya min enilalen bere kearaju yiwulal malet yihe ayidelem ende ahiyam bihon kejib kerimuwal ........ lehulum amlak libona yadilew bere hoy sarun ayehina gedelun satayi elim balew gedel serig degesih wey ( motin malet new) yihe honual yegna mecheresha ebakachihu le enatachin enirara bizu malet sichal kirstian bilih silehon lebilihi ayimekirum le anbessa ayimetirum new ayidel ? abatochi yalun

    ReplyDelete
  5. በጋሻው አንተ አታላይ ክህደትህ ያዋጣህ ይሆን? በአንተ ምክንያት ቤተክርስቲያናችን ላይ ያደረስከውን በደል መድሀኒያለም ይይልህ. በአደባባይ የአዞ እንባ አልቅሰህ ሰውን ለመሳብ ያደረከው ማጭበርበር ተረድተናል ለዚህም የእጅህን የክርስቲያን አምላክ ይስጥህ ከዲያቢሎስ ቀጥሎ ሁለተኛው ዲያቢሎስ ምሳሌ ነህ። ስንቱን ዘማሪ ይዘህ ገደል ገባህ? ማስተዋልን ይስጣችሁ

    ReplyDelete
  6. ameen lehulachinim mastewalin yisten gin e/r begashawin behiywotu melikam ayadirigilet yetewahido amlak yifiredibet

    ReplyDelete