Tuesday, October 25, 2011

ማኅበረ ቅዱሳንን ከምሁራንና ከካህናት ጋር ለማጋጨት እየተሞከረ ነው


  •  ማኅበሩ ምላሽ አለመስጠቱ ብዙዎችን አበሳጭቷል፤ 
(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 14/2004 ዓ.ም፤ ኦክቶበር 25/2011)፦ ተፋፍሞ በቀጠለው የፀረ ፕቴስታንታዊ ተሐድሶ እንቅስቃሴ መሪ ነው የሚሉትን ማ/ቅዱሳንን በመቃወም ላይ የሚገኙት የተሐድሶ-መናፍቃን አሁን በያዙት አዲስ ስልት ማኅበሩ ከታዋቂ ምሁራን እና ካህናተ ቤተ ክርስቲያን ጋር ለማጋጨት እየሞከሩ ነው።  


በዚህ አዲስ የማጋጨት ተግባር “ማኅበረ ቅዱሳን ተሐድሶ-መናፍቃን ናቸው ብሏችኋል” ከተባሉት መካከል ታዋቂዎች ምሁራን ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ እና ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም ሲገኙበት ከእነርሱም በተጨማሪ ካህሣይ ገብረ እግዚአብሔር፣ ግርማ ኤልያስ (ከዚህዓለም በሞት የተለዩ)፣ ሊቀ ሊቃውንት ወርቅነህ ኀይሌ፣   ሊቀ ማእምራን / አማረ ካሣዬ፣ ሊቀ ኅሩያን ከፈለኝ ወልደ ጊዮርጊስ እና ዲ/ን በእደ ማርያም እጅጉ ይገኙበታል።

ማኅበሩ ግን በፈንታው እየተካሄደበት ላለው ዘመቻ ምንም ዓይነት መልስ ባለመስጠቱ ቆይቶ ተጎጂ ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል።

“እኛስ ማህበረ ቅዱሳንን እናውቀዋለን ፡ የተጎዱ ቤተክርስቲያናትን ሲያስጠግን ፣ ገዳማትን ሲረዳ ፣ የተዘጉ ቤተክርስቲያናትን ሲያስከፍት ፣ የአብነት ትምህርት ቤቶችንና ተማሪወችን በብዙ ነገር ሲያግዝ ፣ በገጠር ላሉ ምእመናን ወንጌልን በነፃ ሲያስተምር ፣ ለቤተክርስቲያን ጠቃሚ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የውይይት መድረኮችን ሲያዘጋጅ ፣ የዩንቨርሲቲና የኮሌጅ ተማሪወችን ከመናፍቃን ይጠብቅ ዘንድ ሰብስቦ ሲያስተምር ፣ በግእዝ ብቻ ተፅፈው የነበሩ ቅዱሳን መፃህፍትን ወደ ተለያዩ ቋንቋወች በመተርጎም ለህብረተሰቡ ሲያቀርብ ፣ መንፈሳዊ መፅሄቶችንና ጋዜጦችን በየጊዜው ለአንባቢያን ሲያደርስ ፣ ስርአተ ቤተክርስቲያን ይከበር ሲል ፣ ስርአቱን የጠ...በቀ መዝሙራትን ሲያወጣ ፣ ቤተክርስቲያንን ለመውረር የሚተጉ መናፍቃንን የከፋ ግብራቸውን በማስረጃ እያጋለጠ ቤተክርስቲያንን ከተኩላወች ሲጠብቅ ፣ እኛስ ማህበረ ቅዱሳንን እናውቀዋለን - - -
 ይህን ሁሉ ስለመስራቱ በተለይም መናፍቃን እንዳሻቸው በቤተክርስቲያን ላይ እንዳይቦርቁ ዘብ ሆኖ በንቃት ተዋህዶን በመጠበቁ መናፍቃንና መሰሎቻቸው ይህን ማህበር ለማጥቃት ቢነሱ የሚደንቅ አይደለም፡፡ እኛስ ማህበረ ቅዱሳንን እናውቀዋለን መናፍቃንንም አናጣቸውም፡፡”
የስም ማጥፋት ዘመቻ በጋዜጣ ….. 
ማህበረ ቅዱሳን ይህን አይቶ ለምን ዝምታን መረጠ?
እኛም እርስዎ እንዲያነቡት ጋዜጣውን ስካን አድርገን አቅርበንልዎታል
READ IN PDF click here
Click see more to read by image 

‹‹የመረጃ ምንጭ ሆነን እንሰራለን››

2 comments:

  1. ጎበዝ ''ለአባ ሰላማ'' ድረ ገጽ እማ ማኅበረ ቅዱሳን መልስ ከሰጠ ሌላው አገልግሎቱ ሁሉ ተረሳ ማለት ነው ''አባ ሰላማ'' ድረ ገጽ እኮ ቀንደኛ የተሃድሶ ድርጅት ነው ስለዚህ የማዳከም ስራው አንድ አካል ነው

    ReplyDelete
  2. እናንተ አላችሁለት አይደል እንዴ እሱ ሲያቀዝ እናንተ የገደል ማሚቶ መይክራፎን ምንትሰራላችሁ ሳሎን ተቀምታችሁ ከማጀት ስትዛዙ አቤት ማለት ነው አለባችሁ መልስ ለመስጠት በርቱ ለእኛ ማንከማን ጋር እንዳለና ምን ማድረግ እንዳለብን እናውቃለን

    ReplyDelete