Tuesday, October 11, 2011

ሲኖዶስ ሲቀርብ......የተሃድሶ ትንቅንቅ በሰሜንና በምስራቅ


  • ‹እኔ የማስተምረው ስለ ኢየሱስ ነው ይህንንም የማረገው ጸጋየ ኢየሱስ ስለሆነ ነው›› አቶ በጋሻው
  • የጎንደር ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን የተሐድሶ መናፍቃንን ሴራ የሚያጋልጥና ወቅታዊ ሥልጠና   ተሰጣቸው
  • የሐረርን ተሃድሶ ቡድን  አቡነ ጳውሎስ አነጋገሩ
  • በጋሻው ‹‹ከአባጳውሎስ ጋር የታረቅኹት በሁለታችንም መሀል ያለው ሰው እንዳይጎዳ ነው አለ››
  • የድሬዳዋ ሀገረ ስብከት የተሃድሶ አጣሪ ኮሚቴ ሁሉም የተሃድሶ ሰራዊት ስልጠናውን መሰልጣናቸውን አረጋገጠ
  •  “አባ” ናትናኤል ጎንደር ውስጥ የተሃድሶ ሰራዊት ስልጣና  እየሰጡ ነው                       
  • “ዛሬ ትኩስ ዳቦ ፈላጊው በዝቷል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ትኩስ ዳቦ የላትም፡፡እሷ ወገቧን በደረቅ ጠፈር ዐሥራ ሌላውን መግባለች እንጂ….”(ብፁዕ አቡነ እንድርያስ)
  • “ከዚህ በኋላ አካባቢያችንን ነቅተን እንጠብቃለን…….”ሊቃውንቱ
  • “ተሐድሶ የለም ለሚሉት በቂ መስረጃ ይዘናል………” ልዑካኑ
ተሳታፊዎች
ተሳታፊዎች

ከመስከረም ፳፪-፳፮ ፳፻፬ ዓ.ም ማለትም ለ አምስት ተከታታይ ቀናት በደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት በደብረ ታቦር ከተማ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሁለገብ አዳራሽ በተሰጠውና በወቅታዊ የተሀድሶ መናፍቃን ስውር እንቅስቃሴ ላይ ባነጣጠረው በዚህ ሥልጠና ላይ ከ ፻፶ (አንድ መቶ ሃምሳ) በላይ የአቋቋም፣የዜማ ፣የትርጓሜ መጻሕፍትና የቅኔ መምህራኑን ጨምሮ ከ ዐሥራ ሁለት ወረዳዎች ማለትም፤ ፋርጣ ደራ ላይ ጋይንት ፎግራ ምዕራብ እስቴ ታች ጋይንት ሊቦ ከምከም ምሥራቅ እስቴ ደብረ ታቦር ወረዳ እብናት ስማዳ የተውጣጡ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣የየወረዳው ቤተ ክህነትና የሀገረ ስብከት ኃላፊዎች፣በማኅበረ ቅዱሳን የደብረ ታቦር ማዕከል አባላት ተሳታፊ ነበሩ፡፡የዚህ ስልጠና አዘጋጅና አስተባባሪ ማኅበረ ቅዱሳን ሲሆን ስልጠናው የተሰጠውም ከአዲስ አበባ ዋናው ማዕከል በመጡ ልዑካን ነበር፡
በዚህ ስልጠና የተካተቱት ርዕሶች ወቅታዊ የተሀድሶ እንቅስቃሴ፣ነግረ ድኅነት፣የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ነገረ ክርስቶስና ሕገ እግዚአብሔር የሚሉ ሲሆኑ ከነዚህም ውስጥ ሁለቱ በክፍሉ ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ እንድርያስ መሸፈናቸውን በደብረ ታቦር  ከተማ ካሉት ገብርኄራውያን ለማወቅ ተችሏል፡፡ልዑካኑ ከስልጠናው በተጓዳኝ በከተማው በተመረጡ ሁለት አብያተ ክርስቲያናት የሦስት ቀን የዓውደ ምሕረት ጉባዔ ላይ መሰረታዊ የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ሰጥተዋል፡፡ የባሕር ዳሩ ዘጋቢያችን በሥልጠናው ሊቃውንቱ የተደሰቱ ሲሆን “ማኅበረ ቅዱሳን ገዳማትንና የአብነት ትምህርት ቤቶችን በገንዘብና በቁሳቁስ ከመርዳቱ በተጨማሪ የቤተ ክርስቲያን ጠላቶች እየማሱት ያለውን የጥፋት ጉድጓድ እቦታችን ድረስ መጥቶ ስላሳወቀን ከፊት ይልቅ ኮርተንበታል” ማለታቸውንም ጨምሮ ገልጾልናል፡፡ሥልጠናው በአምስቱም ዕለታት ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት ተኩል እስከ ስድስት ሰዓትና ከምሳ በኋላ ከቀኑ ስምንት ሰዓት እስከ ዐሥራ አንድ ሰዓት ድረስ ይሰጥ አንደነበረም ከደረሰን ዘገባ ለማወቅ ተችሏል፡፡  ይህ በእንዲህ እንዳለ በአነጻሩ ደግሞ የተሃድሶ ሰራዊት አባላትም የአልሞት ባይ ተጋዳይነት ትግል በየቦታው ቀጥሏል፡፡
የሐዋሳ ደብረ ሰላም ቅድስት ሥላሴ ቤተ-ክረስቲያን አስተዳዳሪ የነበሩት አባ ናትናኤልና የሐዋሳን የተሃድሶ ቡድን በበላይነት ሲምሩ የነበሩት መነኩሴ  የግንቦት ርክበ ካህናት ባስተላለፈው ውሳኔ ተደናግጠው የቤተ-ክረስቲያኑን ገንዘብ ዘርፈው እና ፀሎት በእንተ ማህበረ-ቅዱሳን ጽፈው መፈርጠጣቸው ይታወቃል፡፡የስደቱ ጉዞ አልሳካ በማለቱ ተመልሰው በመምጣት ከመስከረም 15/2004ዓ.ም ጀምሮ ጎንደር ከተማ ላይ እማሆይ ነጠረች መታሰቢያ ሆቴል አልጋ ቁጥር 20 ላይ ከትመዋል፡፡    
ከአቡነ ኤልሳዕ ቡራኬ ልቀበል እና ሰላም ልላቸው ነው የመጣሁት እኔ በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ብስራተ ገብርኤል አለቅነት ተሹሜ አለሁኝ በማለት አገላጋይ ካህናትን በተለይም ዲያቆናትን በመቅረብ ፀሎት በእንተ ማህበረ-ቅዱሳን መፅሐፋቸውን በነጻ ከሰጡ በኋላ ስለመፅሐፉም ማብራሪያ እየሰጡ ይገኛሉ፡፡
ከመጡ ጀምሮ የተለያዩ ደብር አገላጋይ ካህናትን በተለይም ዲያቆናትን አንድም፣ ሁለትም እየሰበሰቡ  ሻይ ቡና አልፎ አልፎ ምሳ እየጋበዙ በየተራ ሆቴል ላይ የተሃድሶ ሰራዊትነት ስልጠና እያሰለጠኑ ነው፡፡ ሥልጠናውንም በውይይት መልክ መስጠትን እንደአማራጭች ወስደውታል፡፡     “ገድላትና መልካ መልክ አያስፈልጉም“፡፡ በማለታቸው“ተሃድሶ ማለት እናንተናችሁ አሁን ገባን” የሚል ተቃውሞ ከሰልጣኞች የገጠማቸው ሲሆነ  የእነዛ የሰይጣን ማኅበር ወሬ ነው ብለው ለማስተባበል ቢሞክሩም  “አይ ሰይጣን ሆነው የፈተኑን እርስዎ ነዎት “…. በማለት ብዙዎቹ ጥለዋቸው ሔደዋል፡፡
በተጨማሪም  ጂሩ ውስጥ በደብረ ልእልና ቅድስት አርሴማ  ቤተክርስቲያ ንግስ ላይ እንዳያስተምር ምእመናን ስለከለከሉት ከለከሉት ምእመናን ለምን ብሎ ለመወያየት የሞከረው የግብር አባታቸው በጋሻው ደሳለኝ የመጣሁት  ላስተምር ሳይሆን ለሱባኤ ነው በማለት ለማጭበርበር የሞከረ ሲሆን ከምእመናን የቀረቡለትንም የተለያዩ ጥያቄዎች ሽምጥጥ ባለ ውሸት መልሷል፡፡ ለምሳሌ መናፍቁ አባ ናትናኤል ይመሩት በነበረው የሐዋሳ ደብረ ሰላም ቅድስት ሥላሴ ቤተ-ክረስቲያን የተዘጋጀውና ባለ 60 ገፅ የኦዲት ሪፖርት ለምእመኑ የተገለጸ ሲሆን 900‚000 (ዘጠኝ መቶ ሽ) ብር በላይ ጎደሎ ተገኝቷል፡፡ በጉዳዩም ሀገረ ስብከቱ እና ጠቅላይ ቤተ-ክህነት እየመከሩበት ይገኛሉ፡፡
.“የአዲስ አበባ ህዝብ አሁን ይቅርታ እየጠየቀኝ ነው ወጣቱ ግን ስተቱን አላምን ብሏል አሁንም አልተመለሰም ከሲኖዶስ በኋላ እኔ ሳስተምር ታያላችሁ፡፡  የአዲስ አበባ ጉባኤዎች እየተዘጉ ነው ወይም ቀንሰዋል ይህንን የተመለከቱ አባቶች አንደገና እየለመኑኝ ነው፡፡ በዚህም ከጥቅምት በኋላ የትኛውም ደብር አልከለከልም፡፡ ስለ ቅዱሳን አታስተምርም ተብሎ ለተጠየቀው ሲመልስም እኔ የማስተምረው ስለ ኢየሱስ ነው ይህንንም የማረገው ጸጋየ ኢየሱስ ስለሆነ ነው አሁንም ተሀድሶ የለም የማህበረ ቅዱሳን ፈጠራ ነው ማኅበረ ቅዱሳን እኔን የሚያሳድደኝ መድረኩን ሰለቀማኋቸው ነው፡፡ ከፓትርያሪኩ ጋር የታረኩት በኔና በሳቸው መካከል ያለው ህዝብ እንዳይጎ ነው እንጂ አሁንም የማልስማማባቸው ችግሮች አሉኝ፡፡የፓትርያርኩ ችግር የዘር ጉዳይና ሥነ ምግባር ነው”፡፡ ብሏል፡፡
የእሱ የግብር ጓዶች የሆኑት የሀረር ተሃድሶዎችም አቡነ ያሬድ ይነሱልን፣ ሥራ አስኪያጁ ጥቅመኛ ስለሆኑ ይነሱልን፣ የማኅበረ ቅዱሳን ጽ/ቤት ይዘጋልን ፣በማለት በተደጋጋሚ የተሐድሶ መናኸሪያ የሆነችው የሐረር ከተማ አሁንም መሪነቱን ይዛ መቀጠሏ አልቀረም፡፡ ባለፈው የደብር አስተዳዳሪዎችን፣ካህናትንና ዲያቆናትን በተሐድሶ ሰራዊትነት አሰለጠነት ዛሬ ደግሞ በእነ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስና በእነ ብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ ላይና እንዲሁም በታለቁ አባት በብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ላይ ምራቃቸውን የተፉት ተሐድሶዎች እንደሁም መሰረት ድንጋይ ይጣላል ብለው 40,000 የሀረር መድሀኒአለም ቤተክርስቲያንን ገንዘብ የበሉት የሰበካ ጉባኤ ብር ሲቆጠር በኪሳቸው  የተገኘባቸው ተሰባስበው ገንዘብ ማኅበረ እስጢፋኖስ ብለው ከመሰረቱት የተሀድሶ ማኅበር ወጭ አድርገው ሙሉ አባላቱ ሳይስማሙበት በአንዳንድ የቤተክርስቲያን ጠላቶች /ግብረ በሎች/ ለሆኑት የእጅ መንሻ አስራ አምሰት ሺህ ብር /15,000/ በመያዝና የሐረር መድኃኒአልም ቤተክርስቲያን የኔ ቢጤዎችን ጭምር በማስፈረም አዲስ አበባ መስከረም 20 ቀን 2004 ዓ.ም ይገባሉ፡፡
መስከረም 21 ቀን 2004 ዓ.ም ደግሞ በሐዋሳ ከተማ ያልተሳካለት በጋሻው ደሳለኝ የደብዳቤው ፎርማት ተሰጥቷቸው እንዴት መናገር እንዳለባቸው እንዳለው ጋጠወጥ ንግግር እንዳይናገሩ ካደረጋቸው በኋላ ሰኞ መስከረም 22 ቀን 2004 ዓ.ም አባ ጳውሎስን አግኝተዋል፡፡ በዚህ ውይይት ውስጥ እንደተለመደው አራት ጉዳዮች ላይ አትኩረው ተናግረዋል፡፡ የመጀመሪያው አቡነ ያሬድ ይነሱልን የወንጌል ጠላቶች ከሆኑት ጋር እየተባበሩ ወንጌል እንዳይሰበክ፣ ከአዲስ አበባ ፀጋው የበዛላቸው ሰባክያን እንዳይመጡ አግደውብናልና በአስቸኳይ ይነሱልን፡፡ እነ አቡነ ቀውስጦስና አቡነ ዜና ማርቆስ ተሐድሶ እያሉ ብዙዎቻችንን አስወጡን አሁንም ማኅበረ ቅዱሳን ተሐድሶ እያለ ሊያስወጣን ስለሆነ ቢሮው እንዲዘጋ፡፡ የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ መጋቤ ሰናያት ሐይለማርያም  በጥቅም ተያያዘ ስለሆነ ከሀገረ ስብከታችን ደም ሳይፋሰስ ይነሳልን፡፡ እያሉ ሲገልጹ ነበር በተለይ ደግሞ የሐረሯ ሔሮድያዳ /ስመኝ/ ኦርቶዶክሳዊ ባልሆነ ንግግር እየደነፋች ትሳደብ ነበር፡፡  ፓትርያርኩ ግን በሰጡት ምላሽ እኔ የማንሳት ሥልጣን የለኝም ሲኖዶስ ደርሷል እናየዋለን ብለዋል፡፡ አባ ጳውሎስም ማናችሁ ምንድናችሁ ሳይሉ እንደተለመደው ማኅበረ ቅዱሳን አሳደደን በሚለው አዝማች  ስለመጡ ብቻ እውቅ ተሀድሶ የሆኑትን ‹‹እየሱስ ጌታ ነው›› እያሉ ሲያወሩም  ቁጭ ብለው ሰምተዋቸዋል እንደውም እንዳንድ የቤተክህነቱ ሰዎች ማኅበረ ቅዱሳን አሳደደን የሚለውን ይህ ስልት እኮ የተበላ እቁብ ነው ሲሉ ተሰምተዋል፡፡  እዚህ ላይ ሁለት አካላትን ገብርኄር ታደነቃለች፡-
1ኛ. አቡነ ያሬድን የድሮ ተሐድሶዎች አሁን ተሰባስበው ወደ አዲስ አበባ ሲሄዱ አይወክሉንም የሚሉ ሲነሱ፡፡ እረፉ የእኛ አይደሉም እነሱ ከሰሱን ብለን መልስ አንሰጥም፡፡ ለእነሱ እውቅና መስጠት ነውና፡፡ የማይመለከታቸው ናቸው በሄዱበት ቢሄዱ እኔ ላይ ምንም የሚያመጡት ነገር የለም ነበር ያሉት
2ኛ. የሐረር ማኅበረ ማርያም አባላትም በተለያየ መንገድ ባመጡላቸውም በዚህ መጥፎ ሥራ አንተባበርም በማለታቸው ሳናመሰግናቸው አናልፍም፡፡
ከዚህ ጋር ማለት ምንፈልገው የሀረር ህዝብ በደንብ ሊያስብበት የሚገባው ዛሬ ቤተክህነቱ የሌሎች ሆኗል አይደረግም የምትሉት ሊደረግ ይችላል፡፡  ጴንጤዎቹ ሄደው ጳጳስ ሊያስነሱ ይችላሉ፡፡ ለምን እዚህም ያሉትም የእነሱ ስለሆኑ፡፡
ለማንኛውም የሐረር ከተማ ህዝብ እየከፈለ ያለውን መሰዋዕትነት ሳናደንቅ አናልፍም፡፡ የድሬዳዋ ሀገረ ስብከትም በሀረር ከተማ የተሃድሶ ሰራዊት ስልጣና ከሰለጠኑት 17 ሰዎች ውስጥ የድሬዳዋ ሀገረስብከት ሰራተኞች 4 ያሉበት ሲሆን እነዚህን የሚያጣራ 6 አባላት ያሉት ኮሚቴ አቋቁሟል፡፡  ሊቀ ብርሃናት ቀለመወርቅ ቢምረው ሰብሳቢ፣ ሊ/ት ማቲያስ በቀለን ጸሐፊ አድርጎ በመምረጥ ከየአጥቢያው የቀረበላቸውን በመመርመር የካዱትም ጭምር በማሳመን አራቱም በተለይ ዲ/ን ቤዛ እና ዲ/ን ይትባረክ የተባሉት የክህደት ደብዳቤ ለሀገረ ስብከት አስገብተው የነበረ ቢሆንም አጣሪ ኮሚቴው እነመጋቢ ብሉይ ዮሴፍ ደሳለኝ ባቀረቡት መስቀለኛ ጥያቄ መሄዳቸውን አምነዋል፡፡ ከዛም  ለሀገረ ስብከቱ አስተዳደር ጉባኤ ቀርቦ ወደ ጠቅላይ ቤተ ከህነት ተልኳል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የድሬዳዋ ምእመናን ከማጣራቱ ጀምሮ ሂደቱ ችግር እንድገጥመው መሰናክል ሲፈጥሩ የነበሩ አካላት አሁንም ሳያቀርቡት እንዳይቀሩ በመስጋት አንዳንድ ምእመናን እንቅስቃሴ ጀምረዋል፡፡ ይህ ውጤት እንዲመጣ ከፍጣኛ አስተዋጾ ያበረከቱት በውሳኔም የተሻለና ተመጣጣኝ ውሳኔ የወሰኑት የድሬዳዋ ቅዱስ ገብርኤል ሰበካ ጉባኤ አባላት ናቸው ተብሏል፡፡ የቅዱስ ሚካኤል ሰ.ጉባኤ ጽ.ቤት ከገብርኤል ቀጥሎ ሁለተኛውን ደረጃ ይይዛል፡፡ አንዳንድ አስተያየት ሰጭዎች እንደተናገሩት “የቤተ ክርስቲያናችን ጠባቂ የተባሉት የመንጋው እረኛ” አቡነ ጳውሎስ ተሃድሶ የለም ብለው በተናገሩ ሳምንት እንዲህ መሆኑ ያሳዝነናልም ብለዋል፡፡
ወረታው ቢልልኝ ከባሕር ዳር ከልብ እናመሰግናለን ባሕርዳር አካባቢ ያለውን በዘጋባ ስለተባበሩን
Posted by ገብር ኄር
በፍቅር ሃለፎምfkrhalefom95@gmail.com

2 comments: