Monday, October 3, 2011

‹‹ፓትርያርክነቱንስ ትደርስበታለህ................

አቡነ ቴዎፍሎስ ሹመታቸው ሲፀድቅ ጃንሆይ ዘንድ በቀረቡበት ጊዜ 

‹ፓትርያልኩነቱን ትደርስበታለህ ሸክሙን አትችለውም እንጂ›› በሚል ርዕስ አጠር ያለ ፅሁፍ ማቅረባችን እና ይህን ፅሁፍ ያገኝንበትን መፅሃፍ ለማቅረብ ቃል መግባታችን ይታወቃል፡፡ የዚህ መፅሀፍ ፀሀፊ ደራሲ አቶ ጥላሁን ብርሀነ ስላሴ ይባላሉ የተሸፋፈኑ የታሪክ ሃቆችን ፈልቅቀው በማውጣት እና የአንባቢን አእምሮ የሚኮረኩሩ ታሪኮችን በመፅሀፍ መልክ አዘጋጅተው በማቅረብ ይታወቃሉ እኝህ ሰው ከፃፉት መፅሀፍ ውስጥ እኛን ይመለከተናል ብናቀው አይከፋም ብለን ያሰብነውን ክፍል ከመፅሀፉ ላይ ስካን በማድረግ አንባቢ በቀላሉ ሊያነበው በሚችለው መልኩ ‹‹ሃይማኖት እና ንጉሰ ነገስቱ›› የሚለውን አንዱን ክፍል  ወደ Pdf መልክ ቀይረን አዘጋጅተነዋል:: 




ሃይማኖት እና ንጉሰ ነገስቱ..........................
  • ‹‹እኔ አባ ባስልዮስ ዛሬ ለኢትዮጵያ ሊቀ ጵጵስና ተመርጬ ጃንሆይ ሹመቴን ፈቅደውልኝ አሁን በግርማዊነትዎ ፊት ቀርቤ ለኢትዮጵያ ቤተክርስትያን እና ለግርማዊነትዎ አገልጋይ መሆኔን ስገልጥ በፊትዎ የታመንኩ አገልጋይ ነኝ ፡፡ ሃይማኖት እና እውነት ይመሰክሩልኛል›› የመጀመሪያ ፓትርያልክ አቡነ ባስልዮስ ጃንሆይ ሹመታቸውን ሲያፀድቁላቻው የተናገሩት ይህ ነገር እንደሚያመላክተን በንጉሱ ጊዜም ቢሆን ፓትርያልክነት እና ቅዱስ ሲኖዶስ ከመንግስት እጅ ያልፀዳ አካሄድ እንደነበረው ነው፡፡

  • አቡነ ቴዎፍሎስ ሹመታቸው ሲፀድቅ ጃንሆይ ዘንድ ቀረብ ብለው ‹‹ መርጠው ስለሾሙኝ በጣም አመሰግናለሁ›› ሲሉ የሰሙ ካህናት ለካስ በምርጫ አይደለም ያሸነፉት በማለት ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ጥምድ አድርገው ያዟቸው፡፡ 

  • አቡነ ቴዎፍሎስ የአቡነ ጳውሎስን ሁኔታ ተመልክተው ‹‹ፓትርያርክነቱንስ ትደርስበታለህ ሸክሙን አትችለውም እንጂ›› ብለዋቸዋል፡፡ አቡነ ጳውሎስ ይህው 19ኛ ዓመታቸውን ደፍነዋል ቤተክርስትያን ግን እሳቸው ወንበሩ ላይ ከተቀመጡ ጀምሮ በዘመኗ አይታ የማታውቀውን ፈተና ላይ ትገኛለች እውነትም ብፁዕ አቡነ ቴዎፍሎስ የተናገሩት ነገር ፍፃሜው አሁን እንደሆነ ማን ያውቃል?
  • የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ሊቀ ጳጳስ ብፁእ አቡነ ባልዮስ ‹‹ተፈሪ ሊነግስ እኔ ሊቀ ጳጳስ ልሆን ታዟል ›› እያሉ መተንበያቸውን ተፈሪ ሰምተው አስጠጓቸው




አቡነ ቴዎፍሎስ ለአቡነ ጳውሎስ ሲመተ ጵጵስና ሲሰጧቸው(1968)





በpdf ለማንበብ.....
http://www.4shared.com/document/28Mc2JqX/patrialech_and_Gov.html



የመፅሀፉ ስም ፡የ20ኛው ክፍለዘመን ኢትዮጵያ

ደራሲ፡- ጥላሁን ብርሃነ ስላሴ ቤተ

የገፅ ብዛት 430

2 comments:

  1. ማቆች ሆይ ቀዝቀዝ በሉ!!

    እንዳትቀሰፉም ቀደም፣ ቀደም አትበሉ፡፡ መጥፊያችሁ እንዳይሆን ከአንደበታችሁ የሚወጣውን መርዝ ቆጥቡ፡፡ ቤተክርስቲያናችን እንደ ጥንት ሥርዓቷ ትኖር ዘንድ እንሻለን፡፡ በእግራችሁ ራሳችሁን ለማከክ አትሞክሩ፡፡ ተንኮላችሁን ቀንሱ!! ቀንሱ!! ቀንሱ!! ቀንሱ!! ቀንሱ!! ቀንሱ!! ………………

    ReplyDelete
  2. it's good please keep on!

    ReplyDelete