Tuesday, October 25, 2011

ከቅዳሜው ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶን የሚቃወም ትዕይንት ጋራ በተያያዘ ፖሊስ ተጨማሪ ወጣቶችን እየያዘ ነው



  • ፓትርያርኩ፣ ተሐድሶዎቹን ደግፈው ለቆሙትና በፖሊስ ለታሰሩት ወጣቶችለቀለብ እንዲሆናቸው በሚል፣ ዛሬ 10 ሺህ ብር ልከዋል እየተባለ ነው 
  • ለሌሎቹ ወጣቶች ግን ስላደረጉት ነገር ምንም አልተሰማም፤
(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 14/2004 ዓ.ም)፦  “ተቻችሎ እና ተከባብሮየኖረውን ሕዝብ ወደ ብጥብጥ በመምራት እና ሰው በመደብደብ የሚሉ ሁለት የወንጀልክሦች የቀረቡባቸው “የአዲስ አበባ የጥምቀት ተመላሽ ወጣቶች ማኅበር” ስምንት አባላትትላንት ጥቅምት 12 ቀን 2004 .ም ጠዋት  በአዲስ አበባ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ /ቤትአራዳ ምድብ ችሎት ቀርበው ከስምንቱ መካከል ስድስቱ እያንዳንዳቸው በብር 600 ዋስ እንዲወጡ ሲወሰንላቸው፣ የተቀሩት ሁለቱ ደግሞ ለጥቅምት 16 ቀን 2004 ዓ.ም እንዲቀርቡ ፍርድ ቤቱ ትእዛዝ ሰጥቶ ነበር - ዋነኛ አስተባባሪዎች ናቸው በሚል፡፡
ይሁንና ቤተሰቻቸው የዋስ ሂደቱ ጨርሰው የፍርድ ቤቱን ትእዛዝ ወረዳ ዘጠኝ (ቀጨኔ)ለሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ ቢሰጡም ፖሊስ “ይፈለጋሉ” በሚል ወደ ማእከላዊ ወንጀል ምርመራ ወስዷቸዋል፡፡ ስድስቱ ወጣቶች ትንት ወደ ማእከላዊ ወንጀል ምርመራ ከተወሰዱ በኋላ ጥቅምት 11 ቀን 2004 ዓ.ም ምሽት የፀረ - ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ትዕይንት ከተካሄደበት ከቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ተይዘው በዚያው ከቆዩና ዋነኛ አስተባባሪ ናቸው ከተባሉሌሎች ሁለት ወጣቶች ጋራ ተቀላቅለዋል፡፡ ቀደም ሲል በማእከላዊ ወንጀል ምርመራ የነበሩት ሁለቱ ወጣቶች ሜክሲኮ አካባቢ በሚገኘው የፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ቀርበው እንደነበረ ተመልክቷል፡፡

ንት የተቀላቀሏቸው ስድስቱ ወጣቶች ደግሞ በዛሬው ዕለት እዚያው ሜክሲኮ አካባቢ በሚገኝ የፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት መቅረባቸው ታውቋል፡፡ ፖሊስ “ያልተያዙና መያዝ የሚገባቸው የቀሩ አስተባባሪ ወጣቶችን ለመያዝ” በሚል ተጨማሪ 15 ቀን እንዲሰጠው ጠይቆባቸዋል፡፡ ይሁንና ዳኛዋ ተጨማሪ ሰባት ቀናትን ብቻ በመፍቀድ ወጣቶቹ ለጥቅምት 20 ቀን 2004 ዓ.ም እንዲቀርቡ ትእዛዝ ሰጥተዋል፡፡

የወጣቶቹ በእስር መቆየት እንደሚያሳስበው የገለጸው “የአዲስ አበባ ጥምቀት ተመላሾች ወጣቶች ማኅበር” በበኩሉ የወጣቶቹ ጥያቄ ፖሊቲካዊ ወይም ብጥብጥ መፍጠር ሳይሆን እንደ አዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች ሁሉ የተሐድሶ ኑፋቄን መግታት እና የኦርቶዶከሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን መንነት ማስከበር ብቻ መሆኑን በማስረዳት ወጣቶቹ በተገቢው (በተፋጠነ) ፍትሕ ነጻ እንዲወጡ ጠይቋል፡፡ ይህንንም በሰላማዊ ሰልፍ ለመጠየቅ እያሰበበት መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

በደረሰን መረጃ መሠረት አሁን በእስር ላይ ከሚገኙት ወጣቶች ስም ዝርዝር ውስጥ ዘጠኙ የሚከተሉት ናቸው፡-
1.    ግዛቸው ዮሐንስ፣
2.   ቡሩክ ታደሰ፣
3.   ማዕርጉ በዛብህ፣
4.   ክንፈ ገብርኤል ከበደ፣
5.   ኀይሉ ይመር፣
6.   ደሳለኝ ሀብተ ወልድ፣
7.   መኮንን (?)፣
8.   መኮንን ገዛኸኝ
9.   ዳኛቸው ገዛኸኝ

በተያያዘ ዜና ቅዱስ ፓትርያኩ ተሐድሶዎቹን በመደገፍ ከሐዋሳ ለመጡት ወጣቶች ብቻ ብር 10,000 መላካቸው እየተነገረ ነው። ገንዘቡ በአቡነ ጳውሎስ ስም ከሌላ አካል የተሰጠ ይሁን በርግጥም ራሳቸው ፓትርያኩ ላኩት እየተጣራ ቢሆንም ለደጀ ሰላም የደረሰው የሞባይል ፉቴጅ ፊልም በቅድስት ማርያም በነበረው የሕገ ወጥ ቡድኑ ተቃውሞ አስተባባሪዎቹ ‹‹በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ጥቅምት 11 ቀን 2004 ዓ.ም የደረገውን ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴ የአገልጋዩን ዓላማ በመደገፍ የሰበሰቡ ምእመናን ዝርዝር›› በሚል ቅጽ ምዝገባ ሲካሄዱ እንደነበር ተረድተናል፡፡ ይህም የሕገ ወጥ ቡድኑ አባላት ለውጭ ተባባሪዎቻቸው የሚያቀርቡትና በየዋሁ ምእመን ስም እንዲህ ያሉ ድጋፎችን የሚያገኙበት የጥቅም ማካበቻ ስልት እንደሆነ እናስባለን፡፡

ወጣቶቹ ጥቅምት 11 ቀን 2004 ዓ.ም ከተያዙ በኋላ ሌሊቱን ያሳለፉት በወረዳ ሁለት ፖሊስ ጣቢያ ሲሆን ወደ ፖሊስ ጣቢያው ሲገቡ ‹‹ለደኅንነት›› በሚል የአገታቸውን ማዕተብ እንዲበጥሱ መገደዳቸው ተነግሯል፡፡ ከእነርሱም መካከል አንዱ ወንድም በአንገት ማተብ ሊፈጸም የሚችል አደጋ የለም፤ ማተቤንም አልበጥስም በሚል ትእዛዙን መቃወሙ ተመልክቷል - እውን ይህ ትእዛዝ ለ‹ደኅንነት› ወይስ ሌላ ሰንሰለታዊ የፕሮቴስታንታዊ-ተሐድሶ ፈቃድ ፈጻሚዎች (እጅ ጠምዛዦች) መኖራቸውን ማሳያ?

ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን

3 comments:

  1. “ተቻችሎ እና ተከባብሮየኖረውን ሕዝብ ወደ ብጥብጥ በመምራት” የሚለው አባባል በሥልጣን ላይ ሆነው ስልጣናቸውን አላግባብ የሚጠቀሙበትን አይመለከትም እንዴ? እረ የመንግሥት ያለ!!!

    ReplyDelete
  2. ምንያደርጋል መንግስት ሽብርተኛ ይላል በሜዳ እናንተ እዚህ እያላችሁ ለብጥብጥ የምታነሳሱ

    ReplyDelete
  3. abetu fetarye endet tadergen yehon !!!!!!!!
    seyetan seyetenual sewochem yegede mutegn belew yezewutale
    gooooooooode new!!!!!!!!!

    ReplyDelete