- በሐውልቱ ላይ የቅዱስ ሲኖዶሱ ውሳኔ ምን ውሀ በላው ? ለምንስ አልተፈፀመም? ሲኖዶሱ ጥርስ የሌለው አንበሳ ሆኖ ይሆን? ወይስ ‹‹የውሾን ነገር ያነሳ ውሾ ይሁን›› ተብሎ ይሆን ?
- ከመንግስት ጀርባ ለመንጠልጠል የተጠቀሙበት ስልት ‹‹የዘመናት የፖለቲካ አጀንዳ ያላቸው ናቸው እንጂ የሐውልቱን መቆም የተቃወሙት ሌላ በፀጋ ነው የተቀበለው›› ይህ ምን ማለት ነው?
- አባ እንጦስ በላይኛው ግብፅ በሚገኝው ጭልጥ ባለው በርሃ ከዲያቢሎስ ጋር የተዋደቀው የዲያቢሎስ መንጋ በህይወትና በሞት መካከል ጥለውት የሄዱት ስላጠለቀው አስኬማ ፤ ስለተቀበለው ክህነት ፤ ስለሚጠብቀው ድንግልና እና ይልቁንም ለአለም ሁሉ ቤዛ ይሆን ዘንድ በቀራንዮ አደባባይ ደሙን ስላፈሰሰው እየሱስ ክርስቶስ ነበረ፡፡ ተጋድሎውን ሁሉ የፈፀመው የደከሙ ወንድሞች ባህታውያንን ለማፍራ ነበር፡፡ እናንተስ በሲኖዶስ ዙሪያ ተቀምጣችሁ ውሳኔ የምትወስኑ አባቶቻችን ከዮሐንስ አፈወርቅ ምን ተማራችሁ? ከእንጦስ ከመቃርስ ምን አተረፋችሁ ? ገድላቸውን ታቅፋችሁ ተኛችሁ ወይስ…..?
- ‹‹ከጥሩ ሽቶ መልካም ስም ይሻላል ›› እንዲሉ ለሐይማኖታችሁ እና ለስማችሁ ታሪክ እንዲዘክራችሁ ምን ሰራችሁ? እንዲህ ለምታደርጉ የሚያስጨንቃችሁ ዘመን እንዲመጣ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለውድ ልጁ ለጢሞትዎስ የፃፈለትን መልዕክት አስታውሱ
- ፓትርያርኩ አካሔዳቸው ከእግዚአብሔር ጋር ካደረጉ የምን ሽልማት ነው? የምስ መወደስ ? የምንስ የመኪና ስጦታ? ነው፡፡ ላበረከቱት በጎ ምግባር ክርስቶስ ሊሰጣቸው ያሰበው በረከት ከመኪና አይበልጥምን ?
Thursday, October 20, 2011
‹‹የውሾን ነገር ያነሳ ውሾ ይሁን›› ተብሎ ይሆን ?
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
GIRUM NOW ENDHI FERSO YASAYEM.
ReplyDelete