Friday, October 28, 2011

አፅም የማይበሰብስበት


(አንድ አድርገን ጥቅምት 17/2004ዓ.ም) የሰው ልጅ ቅሪተ አካል  ዓመታት ሳይፈርስና አፈር ሆኖ ሳይደቅ ሞቶም  የአጥንቱ ቅሪት ሙሉ አፅሙም የማይፈርስበት ስፍራ አለ ቢባሉ ምን ይላሉ? በምናብ ተከተሉን.....
ወደ አማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰሜን ሸዋ ዞን የቦታው መጠሪያ መልከ ፀዴቅ ገዳም ይባላል፡፡ በሚዳ ወረሞ ወረዳ ከመራኛ ከተማ አቅራቢያተዳፋት ከተከበበ ልዩ ስፍራ የመሸገ ነው አዲ አበባ 230 ኪሎ ሜትር ገደማ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ገዳሙ ያረፈበት መልክአ ምድራዊ አቀማመጥ እጅግ የሚማርክ ነው ፀጥታው ዙሪያው የተወረወሩት ቁልቁለቶች የየራሳቸው መልክ ያስደንቃል፡፡ ጉልበት የሚያንደረድረው የገዳሙ መውረጃ ደረጃ ከግማሽ በላይ በጥሩ ሁኔታ የተገነባ ነው፡፡


አቡነ መልከ ፀዴቅ ማናቸው?
ይህ ገዳም አቡነ መልከ ጸዴቅ ገዳም ነው የሚባለው ፡፡ አቡነ መልከ ፀዴቅ በቀድሞ በጎጃ ክፍለሀገር በዳሞት በሀገረ ኤናይ የተወለዱ እና ዘመናቸውን በብህትውና ኖረው በዚህ ስፍራ በመዝጋት በፆምና በፀሎት ፈጣሪያቸውን እያገለገሉ ያለፉ የተቀበሩትም ከገዳሙ ዋሻ አናት በሚገኝው ስፍራ እንደሆነ ገድላቸው ያስረዳል፡፡

ከተራራው አናት በተፈለፈለው ዋሻ ውስጥ ፅላታቸው ያረፈበት ቤተክርስትያን ይገኛል ፡፡ በሌላው ጥግ ከዋሻው ሰርጎ የሚንጠባጠበውን ጠል ተቋቁመው የሚኖሩ መናኝ መነኮሳት ይገኛሉ ፡፡ የዚህ ስፍራ ድንቅነት ከሚያጎሉት አንዱና ዋንኛው ያልበሰበሱና ያልፈራረሱ አፅሞች ናቸው፡፡ የገዳሙ አስጎብኚ ቀጥታ ወደ መቃብር ቤቱ ዋሻ ወሰዱን በሩ ላይ የተሸፈነው መጋረጃ ተገለጠ የተመለከትነው ነገር የማይታመን ነበር….. ‹‹እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ላይ ድንቅ ነው ››መዝሙረ ዳዊት 68፤35 ብዙ አፅሞች የዋሻው ግድግዳ ተደግፈው ቆመዋል፡፡ ታስረው የተደረደሩ እንጂ ከሞቱ ረዥም አመታት የሆናቸው አይመስሉም ከአፅማቻ  ይልቅ የተሸፈኑበት ጨርቅ ከዚህ በላይ መኖር አልቻልኩም የሚሉ ይመስላሉ፡፡ ህይወት የሌላቸው ግን ህይወት ያለውን የሚያስደምሙ ..በእግሮቻቸው የቆሙ አፈር ያላበሰበሳቸው አፅሞች ‹‹ሁሉን የምትገዛ ጌታ አምላክ ሆይ፥ ሥራህ ታላቅና ድንቅ ነው፤›› የዮሐንስ ራእይ15 ፤3-4 ያስብላል::

መሪጌታ አባ ወልደ ማርያም ገዳሙ መነኩሴ እና እንግዳን በመቀበል የሚያስጎቡ ናቸው፡፡ ይህን ሚስጥር ፈጣሪ ለአቡነ መልከ ፀዴቅ ከገባላቸው ቃል ኪዳን  መሆኑን ነው የነገሩን መልከ  ፀዴቅ አምላካቸውን በሚገባ የታዘዙ ነበሩ ፡፡ እናም ያንተ አፅም ባረፈበት  በዚህ ስፍራ የሚቀበር ሁሉ አፅሙ አይበሰብስም ፤ አይፈርስም ሲል ቃል ገብቶላቸዋል እየተመለከታችሁ ያለው ይህንኑ ነው አሉን፡፡

እየተመለከትነው ያለነው ይህንኑ ነው፡፡  ያልፈራረሱ ፤ ያልበሰበሱ ፤ ከመግነዛቸው ያልተፈቱ አፅሞች  ፡፡ ይህንን አይነት ተዓምር በዚያው በሰሜን ሸዋ ዚን ላሎ ማማ አርበሀራ መድኃኒያለም በታች ይባም እና በመርሀቢቴ አጼ ዋሻ የሚስተዋል ቢሆንም ይህኛው ለየት ያለ ነው በቁጥራቸው በርከት ያሉ ያልፈራረሱ አፅሞች ይገኙበታል፡፡
‹‹እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ላይ ድንቅ ነው›› መዝሙረ ዳዊት 68፤35

2 comments:

 1. Thanks, Egziabher yistilin! But please do check your spelling errors before you post.

  ReplyDelete
 2. ስላም ለእናተ ይሑን እግዚአብሔ በቅዱሳኑ ላይ አድሮ ለእኛ ደካማ ለሆን የሰው ልጆች የልብን
  ዝገት የሚያጸዱበት ምስክር የሚሆን በጻድቁ አቡነ መልከ ፀዲቅ ገዳም ተገኝታችሁ እኛንም ባህ
  ር ማዶ ላለነው የተዋህዶ ልጆች ከበረከታችሁ ስለ አደረሳችሁን እግዚአብሔር ደግሞ ደጋግሞ ጸጋውን ያድልልን
  ሌላው ደግሞ ከጻድቁ ገድል ከገዶሙ ወይራ ወይንም አጸድ ቆርጦ ይዞመውጣት የማይሞከር
  ነው የጻድቁን ቃልኪዱን ይደረግልኛል ብሎ አምኖ ለ ሰባት ቀን ደጅየጠና ባዶውን አውመለስም

  ReplyDelete