Friday, May 18, 2012

የቅዱስ ሲኖዶስ ስድስተኛ ቀን ውሎ (ዘግይቶ የደረሰን)

  • በጋሻው ደሳለኝ  የቀረበበት መረጃ  የሚያስወግዙት መሆኑን ተገልጧል፡፡ 
  • ፓትሪያሪኩ የማኅበረ ቅዱሳን ህልውና አደጋ ለመጋረጥ እየሞከሩ ነው፡፡ ብጹዓን ሊቃነጳጳሳት እያንዳንዱ አጀንዳ በጥንቃቄ ማየቱን ቀጥለውበታል፡፡
  •  ፓትሪያሪኩ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ሃይማኖታቸውን እንዲመሰክሩ ተጠይቀዋል፡፡
  •  ብጹዕ አቡነ ገብርኤል የሲዳማ ሃገረስብከት ሊቀጳጳስ ሆነው እንዲቀጥሉ ተወስኗል፡፡
  •  መ/ር እንቁ ባህርይ ተከስተ ከሓላፊነቱ እንዲነሳ የውሳኔ ሃሳብ ቀረበ
(ግንቦት 11 ፤ 2004 ዓ.ም)፡- በአምሰተኛው ቀን ከሰዓት በኋላ ቅዱስ ሲኖዶስ ማኅበራትን በተመለከተ የቀረበለትን አስራ ስድስት ገጽ ጽሁፍ በንባብ አድምጧል፡፡ ሰባት አባላት ባሉት ኮሚቴዎች ተዘጋጅቶ እንደ ቀረበ የተነገረለት ጽሁፉ በዋነኛነት የማኅበረቅዱሳን ህልውና አደጋ ለመጋረጥ ታልሞ የቀረበ ነው፡፡ ጽሁፉን ለማዘጋጀት ንቡረእድ ኤልያስ፣ ከተሃድሶ መናፍቃን ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት እንዳለው የሚነገርለት አእመረ አሸብር፣ / ዳንኤል ሰይፈ ሚካኤል ተጠበውበታል፡፡ በተለይም / ዳንኤል ሰይፈሚካኤል የአንበሳ ድርሻ እንዳላው እየተነገረ ነው፡፡
ንቡረእድ ኤልያስ ጽሁፉን በንባብ ያቀረቡ ሲሆን ማኅበራት ለቤተክርስቲያን አንድነትና ሰላም አደጋ እየሆኑ መጥተዋል፡፡ የቤክርስቲያንን ማዕከላዊ አስተዳደር ጥያቄ ውስጥ ያስገባል በሚልአሳማኝበሆነ መንገድ ያስረዳል፡፡ በጽሑፉም በጠቅላይ ቤተክህነት ያሉት መምሪያዎች ስብከተ ወንጌል፣ገዳማት መርጃ፣ ህትመት፣ የህግ አገልግሎት፣ .. የሚሉ ክፍሎች በማደራጀት የጠቅላይ ቤተክህነቱን ስልጣንና ተግባር ተገዳድረዋል፡፡ ስለሆነም ማህበራቱ እንዲዘጉና ንብረታቸው ለአጥቢያ ቤክረስቲያናት ገቢ እንዲደረግ ይጠይቃል፡፡ ጽሁፉ ቀርቦ ካለቀ በኋላ ፓትሪያሪኩ ከወትሮው በተለየ ሁኔታይሄ ለቤክርስቲያንንም ለአገር አደጋ ስለሆነ መወሰን አለብንያሉ ሲሆን ከርሳቸው በኋላ የተናገሩት ሁለት አባቶችም የቀረበውን ነገር በቅንነት ተመልክተው በሃሳባቸው ይስማማሉ፡፡ ፓትሪያሪኩ የሁለቱን አባቶች ንግግር ከሰሙ በኋላቃለ ጉባኤይመዝገብልኝ ብለው በፍጥነት ለማለፍ ሲሞክሩ አባቶች ጥርጣሬ ስለገባቸው ጽኁፉ ኮፒ ተደርጎ እንዲሰጣቸውና ጥልቅ ውይይት እንዲደረግበት በመጠየቃቸው አጀንዳው አድሯል፡፡የጽሁፉ አቀራረብ በአጠቃላይ ማኅበራት የሚመለከት በሚመስል መልኩ የቀረበ ቢሆንም ጥናቱ ሙሉ በሙሉ የሚያተኩረው ማሕበረ ቅዱሳን ላይ ብቻ ነው፡፡ ቤተክርሰቲያን 40 ሺህ በላይ ማኅበራት ቢኖሯትም አብዛኞቹ ተቋማዊ አደረጃጀት የላቸውም፡፡ ጥቂት የአገልግሎት ማህበራትም አደረጃጀት ያለቸው ቢሆንም በተወሰነ(specific) የአገልግሎት ዘርፍ ላይ ብቻ የሚያተኩሩ ናቸው፡፡

ማኅበረቅዱሳን ግን ሁሉን አቀፍ አገልግሎት የሚሰጥ፣ ተቋማዊ አደረጃጀት ያለው፣ቤተክርሰቲያኗ በምትደርስባቸውና ባልደረስባቸው ቦታዎች ሁሉ አለም አቀፍ የሆነ አገልግሎት የሚስጥ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይህ ነው ጥናታዊ ጽኁፍ ስም የቀረበው፡፡ በተሸፋፈነ መንገድ ማኅበሩን ለመዝጋት የተሴረ ሴራ መሆኑን እየተነገረ ነው፡፡ከዚህ በመቀጠል ተሃድሶ መናፍቃንን የተመለከተውን ሪፖረት መስማት የጀመረ ሲሆን ለጠዋት እንዲያድር ተደርጎል፡፡

በትናንቱ ጠዋት ስብሰባ የተሃድሶ መናፍቃን በተመለከተ በማሕበረ ቅዱሳንና በሰንበት /ቤቶች በኩል የቀረቡትን መረጃዎች የሊቃውንት ጉባኤ አጣርቶ ለሊቃነ ጳጳሳት ኮሜቴ ያቀረበውን ሪፖረት ላይ ተወያይተዋል፡፡ በሪፖረቱ ላይም ሰባት ግለሰቦችና ስድስት ማኅበራት እንዲወገዙ የውሳኔ ሃሳብ ቀርቧል፡፡ዝርዝራቸውም የሚከተለው ነው፡፡


የማኀበራቱ ስም
1.
የእውነት ቃል አገልግሎት
2.
የቅድስት ልደታ ለማርያም መንፈሳዊ ማኅበር
3.
አንቀጸ ብርሃን
4.
የምሥራች አገልግሎት
5.
ማኅበረ በኵር
6.
ማኅበረ ሰላማ

ግለሰቦቹ ስም
1. “መርጌታጽጌ ስጦታው
2. “
ዲያቆንአሸናፊ መኰንን
3.
ደረጀ ገዙ
4.
በዛ ስፍርህ
5.
ግርማ በቀለ
6.
አግዛቸው ተፈራ
7. ‹
መጋቤ ጥበብሰሎሞን ጥበቡ ናቸው፡፡

·        ማኅበረቅዱሳን መረጃ ካቀረበባቸው ሰምንት ሰዎች ውስጥ ሰባቱ እንዲወገዙ የውሳኔ ሃሳብ የቀረበ ሲሆን ስምንተኛው በጋሻው ደሳለኝ በተደጋጋሚ ጥሪ ቢደረግለትም ሊቀርብ አለመቻሉን፤ የቀረበበት መረጃ ግን የሚያስወግዙት መሆኑን ተገልጧል፡፡
በአዲስ አበባ ሰንበት /ቤቶች አንድነት በአባ ሰረቀ እና ጌታቸው ዶኒ ላይ ባቀረቧቸው ማስረጃዎች የግለሰቦቹ የሃይማኖት ሕጸጽ መመርመሩን ሪፖርቱ ያስረዳል፡፡ በዚህም አባ ሰረቀየፓትሪያሪኩ፣ የአባቶች እምነት የእኔም ነው፡፡በማለት ራሳቸውን ገለልተኛ ማድረጋቸውን፣ እንዲሁም ጌታቸው ዶኒ ስላቋቀመው የቅን ልቡና የመንፈሳዊና የፈውስ አገልግሎት የእምነት ተቋም ሲጠየቅ ‹‹ልጆቼን የማበላው ተቸግሬ ነው፡፡በማለት መመለሳቸውን የሌላ እምነት ተከታይ ስለመሆናቸው የቀረበባቸውን ማስረጃ(ደብዳቤ) የእኔ አይደለም አሻራ ይመርመር ማለታቸውን ተብራርቷል፡፡ መቂ ከተማ ላይ 1.5 ሚለዮን ብር ቤት መሰራት የቻሉት ጌታቸው ዶኒ ልጆቼ ማበላቸው ስላጣሁ ነው ሌላ የእምነት ተቋም የመሰረትኩት ማለታቸው አስገራሚ ሆኗል፡፡

በኮሚቴው ሪፖርት ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን ምልዓተ ጉባኤውየፓትሪያሪኩን ሃይማኖት ሳናውቅ በዚህ አጀንዳ ላይ መወሰን አንችልም፡፡ ቅድሰት ድንግል ማርያም ንጽሐ ጠባይ አልነበራትም ብለው መመረቂያ ጽሑፎ ላይ ጽፈዋል፡፡ ይሄ የሃይማኖት ጉዳይ ስለሆነ መልስ ይስጡን?” በማለት የጠየቀ ሲሆን ፓትሪያሪኩምየመመረቂያ ጽሑፌ ኮፒ ተደርጎ ይሰጠኝና ተዘጋጅቼበት ነው መልስ የምሰጠውበማለታቸው የርሳቸውን መልስ ከሰማ በኋላ በተሃድሶ መናፍቃን ላይ ውሳኔ ለማሳለፍ ለዛሬ ጠዋት አጀንዳው አድሯል፡፡

በቀጣይነት የታየው አጀንዳ የሲዳማ ሃገረስብከት በሚመለከት ከቀትር በኋላ ውይይት ያደረገ መሆኑን ምንጮቻችን ዘግበዋል፡፡የሃገረስብከቱ ሊቀጳጳስ ብጹዕ አቡነ ገብርኤል እንዲቀጥሉ ወስነዋል፡፡ ዛሬ ጠዋት ላይ የፓትሪያሪኩን ሃይማኖት መልስና ተሃድሶ መናፍቃን በተመለከተ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሏል፡፡ በመቀጠልም ማኅበረቅዱሳንና የሠንበት /ቤች ማደራጃ መምሪያ በተመከተ ይነጋገራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ዘግይቶ በደረሰን ዜና፡- ማኅበረቅዱሳንና የሠንበት /ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሚመለከተውን አጀንዳ ማየት የጀመሩ ሲሆን ምልዓተ ጉባኤው / እንቁ ባህርይ ተከስተ ከሓላፊነቱ እንዲነሳ የውሳኔ ሃሳብ በማቅረብ የጠዋት ውሎ የፈጸመ ሲሆን ከቀትር በኋለ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡መ/ እንቁ ባህርይ ተከስተ ለጊዜው ይዘቱ በውል ያልታወቀ ደብዳቤ ለጳጳሳት ሲበትን ታይቷል፡፡ ዝርዝሩን እንደደረሰልን እናቀርባለን፡፡

ቸር ወሬ ያሰማን!

8 comments:

  1. Andadirigen, thanks for the info. I understand the difficulty of getting information on the same date of the event. But can you please make sure that you write the day like monday.. on bracket whenever you say this morning.. bla bla

    It is good news if aba enkubahiry can be dismissed.

    ReplyDelete
  2. ፓትሪያሪኩም “የመመረቂያ ጽሑፌ ኮፒ ተደርጎ ይሰጠኝና ተዘጋጅቼበት ነው መልስ የምሰጠው” በማለታቸው

    Does he expect his disertation from other person? I think he wants to say that the disertation is not available or I couldn't find something like that...

    Dear andadirgen, if in case he says 'I have no my disertation', please let me know. I can send you the full version of his PhD thesis by email so that you can give it to our holy fathers.

    Just write a message here, then I will send you via ur email.

    ReplyDelete
    Replies
    1. please post it here! It would be our great pleasure.

      Delete
    2. Please you can find via google search. Here is the title of his thesis.


      Filsata: The Feast of the Assumption of the Virgin Mary and the Mariological Tradition of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church. Yohannes, Paulos, PhD.

      If you find it, read page 306. You will find the following on the first line of page 306:
      'For the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church the Virgin Mary is the example par excellence of obedience and faithfulness to God. She is two-fold virgin; i.e, virgin both in body and soul, who, though not “immaculate” or free from original sin, yet was all-holy, pure, chose to actively participate in the saving work of God, His Incarnation.'

      If you can't find the thesis, let me know so that I can send you by email. If you are living in Ethiopia, please don't send me your actual email. You can create a new e-mail and send me a message. My Email is: me.gebre@yahoo.com

      Please don't send your actual e-mail to anyone though he/she asks youn to trust him/her.

      Delete
    3. Thanks, I found it here is the link or you can search it on Google.

      http://medhanialemeotcks.org/wordpress/wp-content/uploads/2012/01/Filsata.pdf

      Delete
  3. እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሳትወለድ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ንጽህት ቅድስት ናት፤ የአዳም የውርስ ሀጢአት የለባትም፤ ከፈጣሪ በታች ከፍጡራን በላይ ናት፤ ብሎ መመስከር ምን ማሰብ፤ መዘጋጀት ያስፈልገዋል፡፡
    ችግር የሚፈጠረው ይሄ የኔ ጽሁፍ አይደለም ያሉ ዕለት ነው፡ እኔ ነኝ ካሉ ግን ለውሳኔም ቀላል ነው፡፡ አያሳስብም፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር ትክክለኛ እምነታቸውን እንዲገልጹ ይርዳን፤ ይርዳቸው ፡

    ReplyDelete
  4. ብዕሩ ዘ-አትላንታMay 20, 2012 at 6:18 AM

    አባ ጳዉሎስ ለመመለስ የተሳናቸዉን ጥያቄ መልስ ለማግኘት እናቶቻችን በቂ ናቸዉ። መዛግብት ከማገላበጥ ወደ እናቶቻችን ቢደዉሉ ያሰረዷቸዋል። አኒህን ሰዉ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ አዉግዞ መለየት ነዉ። አይደለም ሊቃዉንቱ እኔ መሐይሙ ባለኝ ትንሽ ዕዉቀት የእኔን ያክል ስለ እመቤታችን መመስከር ባለመቻላቸዉ አዉግዤአቸዋለሁ። በእርሳቸዉ ጉዳይ ምንም ቀኝ ግራዉን ማየት አያስፈልግም። ከአሁን በኋላ ለጥፋት እንጂ ለልማት የሚጠቅሙ ሰዉ አይደሉም። እስካሁን ድረስ ለተሰገሰጉት የተሀድሶ መናፍቃን ቡድን መሪ ተዋንያን ሆነዉ ቤተ ክርስቲያናችንን ሲያስጠቁ የነበሩት እርሳቸዉ እንደሆኑ በአንደበታቸዉ እየመሰከሩ ስለሆነ በእርሳቸዉ ጉዳይ መረጃ እያፈላለጉ ጊዜ መፍጀት ሥራ መፍታት ነዉ። በምድራዊ መንግሥት እንኳ ሕገ መንግሥቱን ያላከበረ እስከሞት የሚያደርስ ቅጣት ይሰጥ የለም? ፍጻሜ ሀገራቸዉ ሲዖል ቢሆንም እርሳቸዉ ሰማያዊዉን ሕገ መንግሥታችንን ክደዋልና ንደዋልምና ምን ይገባቸዋል?... መግደል የክርስትና ግብር ባለመሆኑ አዉግዞ መለየት... ብዕሩ ዘ-አትላንታ

    ReplyDelete
    Replies
    1. TO ብዕሩ ዘ-አትላንታ
      DO YOU THINK THAT IF THE SYNOD HAS DECIDED TO BE DONE AS YOU SAID WILL BE DONE IN PRACTICE? AS LONG AS I KNOW MOST OF THE DECISIONS OF THE SYNOD ARE NOT APPLICABLE IN PRACTICE. IS IT NOT BETTER TO CRY BITTERLY TO THE ALMIGHTY GOD SO THAT HE WILL GIVE US A TRUE FATHER WHO WILL SAVE US AND HIM SELF FROM LUCIFER'S HIDDEN WAR. HASN'T ABUNE PAULOS SAID THAT "I AM THE RESULT OF YOU YOUR SELF. IF I AM CRUEL TO YOU DO NOT BE ANGRY WITH ME BECAUSE I WAS GIVEN TO YOU SINCE YOU ARE CRUEL TOO" SO WHAT CAN WE EXPECT FROM SUCH FATHER?
      PLEASE PRAY TO GOD NOTHING CAN BE DONE IN THIS WORLD WITH OUT HIS KNOWLEDGE. HE CAN DO THE BEST FOR US IN THE FUTURE IF WE PRAY IN TEARS. LET HE DO THE BEST FOR ALL OF US AMEN!!!

      Delete