Thursday, May 31, 2012

“መቻቻልን የማያውቅና ለዲሞክራሲ ፀር የሆነ ሃይማኖትን መቻል አይጠበቅብንም” መጋቢ ዘሪሁን

  • ይህ በልዩነታችሁ ያጌጠ የመቻቻል ባህል ሁሌም ከእናንተ ጋር የሚቀጥል እንደይመስላችሁ ፤ ኢትዮጵያ ገና አልተፈተነችም፡፡” / አብዱላህ

(አንድ አድርገን ግንቦት ጊዮርጊስ 2004 ዓ.ም)፡- ባለፈው ሰኞ ከሰዓት ለሀገሪቱ ከጥቂት ዓመታ በፊት የእግር እሳት የሆነባት መንግስም ለመቆጣጠርና ለማስቆም ያልቻላቸው ጉዳዮች አንዱ በሀይማኖት አካባቢ ያለን ችግር ነው ፤ በመሰረቱ ቤተክርስያናች የዚህን ችግር ገፈት ቀማሽ እንጂ ችግሩን ካመጡት ጎራ የምትመደብ አይደለችም ፤ በፊት በፊት ከአክራሪ ሙስሊሞች የሚደርሰው ጉዳት ነበር አሳሳቢ ደረጃ ላይ የደረሰው ፤ አሁን ባለንበት ጊዜ ግን መንግስት የሚያካሂደው የልማት ስራ የቤተክርስያኒቱ የነገ ህልውና ላይ የሚታይ ችግር እየፈጠረ መሆኑን እያስተዋልን እንገኛለን ፤ በጊዜው ከኢህአዴግ ከፍተኛ ባለሥልጣናት መካከል የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትር / ሽፈራው ተክለ ማርያምና ሌሎች ጥቂት ባለሥልጣናት  በአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን አዲሱ ትልቁ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ሃይማኖት መቻቻል ዙሪያ  ዙርያ ለመምከር  ኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ጋር እና ከተለያዩ ሀገራት ጉዳዩ ከሚመለከታቸው መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ጋር ተሰብስበው ነበር፡፡


የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ አባላት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን፣ የኢትዮጵያ የሙስሊሞች ጉዳይ ጠቅላይ ምክር ቤት፣ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን፣ የኢትዮጵያ ኢቫንጀሊካል ቤተ ክርስቲያን ፌሎው ሺፕ፣ የኢትዮጵያ ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተ ክርስቲያንና የኢትዮጵያ ኢቫንጀሊካል መካነ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን ሲሆኑ፣ ዓላማው በኢትዮጵያ አማኞች መካከል የማኅበራዊ፣ የሞራልና የመንፈሳዊ አንድነት ለመፍጠር፣ ግጭትና ብጥብጥን ለመከላከል፣ ሰላምና ልማት ለመገንባት፣ እንዲሁም የውይይት ባህል ለማስፋፋት ነው፡፡

     ባሳለፍነው ሳምንት ቅዱስ ሲኖዶስ ተነጋግሮ አቋም የያዘባቸው ጉዳዮች አንዱ ይህን በሚመለከት እንዲህ ይል ነበር  
    ከቅርብ አመታት ወዲህ በሀገሪቱ መዲና በአዲስ አበባ የተጀመረው የኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋት ጉባኤ ፤ በሁሉም አህጉረ ስብከት ተቋቁሞ ይሰራ ዘንድ ቀደም ሲል በተሰጠው መመሪያ መሰረት በአብዘኞቹ አኅጉረ ስብከት ተመሳሳይ ተቋማት ተከፍተው ስራቸውን በማካሄድ ላይ ይገኛሉ ፤ ከዚህ አንጻር አገልግሎቱ እጅግ በጣም የጎላ ሲሆን መንግስታችንም የሀይማኖት ተቋማት ግንባር ፈጥረው የራሳቸውን ችግር በራሳቸው እንዲፈቱ ለማስቻል የሰላም ተቋሙ እንዲቋቋም መፍቀዱ የሚያስመሰግን መሆኑን እያደነቅን ፤ ተቋሙ ያልተቋቋመባቸው አህጉረ ስብከት ካሉ አቋቁመው ለሀገር ሰላምና ለህዝብ አንድነት ጠንክረው እንዲሰሩ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡” በማለት የተጀመረው ነገር ከማጠናከርና ወደ ታች ከማውረድ አኳያ አቋም መያዙ የሚታወስ ነው፡፡


በስብሰባው ላይ ፕሮፌሰር ቶማስ ሚኬል ‘Identifying Our Partners in Dialogue’ በሚል ርዕስ፣ መጋቢ ዘሪሁን ደጉ ‘Muslim Christian Co-existence in Ethiopia’ በሚል ርዕስ፣ / አብዱላህ አንቴፕሊ ‘Co-existence and Harmony in a pluralistic World: Gulen Movement as a Wording Model’ በሚል ርዕስ፣ / ሽፈራው ተክለ ማርያም ‘The New Religious Chapter in Ethiopia: The New FDRE Constitution and Practice’ በሚል ርዕስ ጥናት አቅርበዋል፡፡

መጋቢ ዘሪሁን ደጉ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ዋና ጸሐፊ ሲሆኑ፣ በጥናታቸው ሃይማኖትና የሃይማኖት መሪዎች ሰላምን፣ መቻቻልንና መግባባትን በመፍጠር በኩል ትልቅ ሚና እንደሚጫወቱ ገልጸዋል፡፡ ሃይማኖት ማኅበረሰቡ ለተለያዩ አደጋዎች የሚሰጠውን ምላሽ በመቅረፅ፣ ማኅበራዊ ኢፍትሐዊነትን በማጋለጥና የችግሮችን ማገገሚያ ቦታ በመፍጠር ትልቅ ሚናም እንዳለው አስረድተዋል፡፡ በጉባዔው አማካይነት የተለያዩ የሃይማኖት ተቋማት እጅና ልባቸውን አያይዘው በብሔራዊ ሰላምና ልማት ዙሪያ ለመሥራት መስማማታቸው ትልቅ ዕርምጃ መሆኑንም አመልክተዋል፡፡

"
እርስ በርስ በመከባበር አንዳችን ለአንዳችን ዕውቅና ሰጥተን፣ የጋራ ችግራችን ላይ በጋራ ለመሥራት እንዲሁም አንዳችን ሌላችን ላይ የምንፈጽመውን ግጭት የማቆም ባህል በቀላሉ መፍጠር አይቻልም፤" ያሉት መጋቢ ዘሪሁን ሒደቱ ግን ሁሉን አቀፍ፣ ሰፊና ጥልቅ መሆን እንዳለበት አመልክተዋል፡፡ ይህን ለማድረግም ‹‹አመለካከታችን፣ ስሜታችን፣ ፍላጎታችንና እምነታችን ጭምር ሊቀየር ይገባል፤›› ሲሉም ገልጸዋል፡፡

"
የሃይማኖት መቻቻል ማለት ሁሉንም ሃይማኖቶች በእኩልነት መቀበል፣ ሌሎችን የሚጎዱ ሃይማኖቶች የቀሰቀሷቸው ድርጊቶችን ከመተቸት መቆጠብ አይደለም፤" ያሉት መጋቢ ዘሪሁን፣ ‹‹መቻቻልን የማያውቅና ለዲሞክራሲ ፀር የሆነ ሃይማኖትን መቻል አይጠበቅብንም፤›› ሲሉ በሚወዱት የአንድ ጸሐፊ ጥቅስ አማካይነት ተናግረዋል፡፡


/ አብዱላህ ባለው ሁኔታ ኢትዮጵያ እንዳትዘናጋ ግን አስጠንቅቀዋል፡፡ ‹‹ይህ በልዩነታችሁ ያጌጠ የመቻቻል ባህል ሁሌም ከእናንተ ጋር የሚቀጥል እንደይመስላችሁ፡፡ ኢትዮጵያ ገና አልተፈተነችም፡፡ ኢትዮጵያ ይበልጥ ስትበለጽግ፣ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እጆቿን ይበልጥ ስትዘረጋ፣ በዓለም ላለው ተጨባጭ ሁኔታ ኢትዮጵያ ይበልጥ ስትጋለጥ ያኔ ትፈተናለች፡፡ አሁን በሚገባ እያጣጣማችሁት ያለው የወንድማማችነትና የእህትማማችነት ሁኔታ ያኔ ይፈተናል፡፡ ያኔ ነው ምን ያህል ጠንካራ ግንኙነት እንዳላችሁም የምትፈተኑት፤›› ብለዋል፡፡ በተጨማሪም / አብዱላህ በማሊ፣ ናይጄሪያና ኢንዶኔዥያ ተመሳሳይ ሁኔታዎች ውስጥ ጥንቃቄ ባለመደረጉ የመቻቻል ሁኔታ ችግር እንደደረሰበት ጠቅሰዋል፡፡ኢትዮጵያ ከሌሎች አገሮች ስህተት ተምራ ጠንካራ ዝግጅት በማድረግ በዓለም አቀፍ ክስተቶችም ሆነ በሌሎች ተግዳሮቶች የማይፍረከረክ ጠንካራ መሠረት እንድትጥል መክረዋል፡፡

ምንጭ ፡-  የ2004 ቅዱስ ሲኖዶስ የአቋም መግለጫ እና ሪፖርተር ጋዜጣ

2 comments:

  1. This is a very nice initiative. The bad thing is the spritual leaders have lost credibility among their fellowers. The typical example is Aba paulos of Ethiopian orthodox church. And it seems that the government is incubating this situation and treating the effect. Dr Shiferaw may not like this but the truth is this ! Look, you communicate with the religious leaders to reach the people. But the fellowers are not listening to their leaders. Because the leaders have no element of sprituality except their clothes, their place of work and their title. This has been demonstrated by the muslim community as related to Aweliya. And the government knows how the christians hate Aba paulos and it is not different for the evangelicals. The good thing would be the government has to help reniasiance of the religious institutions and make them Ethical and loyal to their teachings. To tell the truth the governments alliance with corrupt leaders of religious institutions does not take it any where beyond the meeting hall. We all love our country. We are all eager to see its peace, development and progress.This comes when we all agree and work towards this goal. When I say we all, I mean every citezin of the country. But this understanding could not be established even with in religious institutions. Dr Shiferaw I support the notion, but I see that you are dealing with irrelevant guys. Let me tell you what ordinary people on the street say : Why is the government allied with our corrupt leaders ? Does it support corruption while it has established a commision to fight this ? So your alliance with this guys have spoiled the public image of the government.

    ReplyDelete
  2. this is a very nice initiative, i support my friend above. however, those who participated and agreed with this initiative should commit themselves to trickle it down to the over all community (thier followers), the muslim and the christians, and work deeply to convince them with the same notion. it is then that, as Dr Abdulahi said, "ኢትዮጵያ ገና አልተፈተነችም፡፡ ኢትዮጵያ ይበልጥ ስትበለጽግ፣ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እጆቿን ይበልጥ ስትዘረጋ፣ በዓለም ላለው ተጨባጭ ሁኔታ ይበልጥ ስትጋለጥ ያኔ ትፈተናለች፡፡ አሁን በሚገባ እያጣጣማችሁት ያለው የወንድማማችነትና የእህትማማችነት ሁኔታ ያኔ ይፈተናል፡፡ ያኔ ነው ምን ያህል ጠንካራ ግንኙነት እንዳላችሁም የምትፈተኑት፤››
    so we need to start strengethening the common sense as Ethiopian citizens avoiding religious difference from the mind ...... of course we all need to work on this, which have connotation of our spritual relation with respect to our belief. let's keep that for our selves and for the almighty and then be one.

    ReplyDelete