Tuesday, May 15, 2012

የቅ/ሲኖዶስ መደበኛ ስብሰባ አራተኛ ቀን የቀትር በኋላ ውሎ


•  የዜና ቤተክርስቲያን አዘጋጆች ተወግዘው ከሥራ እንዲሰናበቱ የውሳኔ ሃሳብ ቀረበ፡፡
  •   ቀሲስ ዶክተር መስፍን ተገኝ "ከቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ፍርድ እና ውሳኔ አንዲሰጠኝ" የሚል ጥያቄ አቀረቡ፡፡
(አንድ አድርገን ግንቦት ሥላሴ ፤ 2004ዓ.ም)፡- በዜና ቤተክርስቲያን ርዕስ አንቀጽ ላይ ቅዱስ ሲኖዶስ ሰፊ ውይይትና ክርክር ካደረገ በኋላ ለቀትር በኋላ ስብሰባ የውሳኔ ሐሳብ የሚያቀርብ ኮሜቴ በመሰየም የጠዋቱን ስብሰባ መጠናቀቁን መዘገባችን ይታወቃል፡፡ በዚህም መሰረት የጨለማው ቡድን አባላት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የአቡነ ጳውሎስን የፕትርክና ቃለ መሃላ ጥሰት ዋነኛ የቤተክርስቲያን ችግሮች ማጠንጠኛነት እልባት ለመስጠት እያደረገ ያለውን ጥረት ለማደናቀፍ እንደ አጀንዳ ማስቀየሪያነት ታስቦ በህገወጥ መንገድ የተዘጋጀው ዜና ቤተክርስቲያን ጋዜጣ የብጹዓን ሊቃነጳጳሳት አንድነት የበለጠ አጠናክሯል፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ጉዳዩ ላይ ጠንከር ያለ ውይይትና ክርክር እንዳደረገ ምንጮቻችን ዘግበዋል፡፡
የዜና ቤተክርስቲያን አዘጋጆች ዋና አዘጋጁ መጋቤ ምስጢር ወልደ ሩፋኤል ፈታሒ፣ /ዋና አዘጋጅ ካህሳይ /እግዚአብሔር፣ የህዝብ ግኙነት ሓላፊው እስክንድር ገብረ ክርስቶስና ከድቡብ ወሎ ሃገረስብከት ተባሮ የመጣው ሣህሉ ለዛሬ ጠዋት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ቀርበው ማን እንደጻፈው? እንዲያስረዱ ተወስኗል፡፡ አብዛኞቹ የምልዓተ ጉባኤ አባላት አዘጋጆቹ ተወግዘው ከስራ ይሰናበቱ በሚለው አጽኖት ሰጥተው የተናገሩ ሲሆን ምንም እንኳ በዜና ቤተክርስቲያን ለሚወጡ ማንኛውም ጽሁፎች የጋዜጣው አዘጋጆች ተጠያቂ ቢሆኑም የጽሁፉን ትክክለኛ አዘጋጆች ለማውቅ ስለሚረዳ ዛሬ ጠዋት ቀርበው እንዲያስረዱ በመውሰን የቀትር በኋላ ውሎ ተጠናቋል፡፡
አዘጋጆች ለቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ትክክለኛ የጽሑፉን አዘጋጆች ካጋለጡ አጀንዳው ዛሬ ጠዋት ሊጠቃል እደማይችል ይገመታል፡፡ከፕሮቴንታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አራማጆችና አቀንቃኞች ጋራ ያለውን ግንኙነት እያጠናከረ የሚገኘው አእመረ አሸብር፣ እንደ ቀበሮዋ ዘለው ዘለው የሻቱትን ማዕርገ ጵጵስና ቢያጡት የተሾሙትን አባቶች በማሸማቀቅና አንገት በማስደፋት ለመሾም የቋመጡት አባ ሰረቀ፤ ለዚህም የገንዘብ ድጋፍ የሰጡት አባ ፋኑኤልና ዦቢራው ኀይለ ጊዮርጊስ ጥላሁን መኾናቸው እየተነገረ ነው፤ የአባ ጳውሎስ አይዟችኹ ባይነት (ቡራኬ) ሳይዘነጋ ማለት ነው፡፡ ይኹንና የዝግጅት ክፍሉም በጽሑፉ ላይ ማሻሻያ በማድረግና እንዲታተም በመፍቀድ፣ ምናልባትም የጥቅሙም ተካፋይ በመኾን መጠየቁ እንደማይቀር ግልጽ ነው፡፡ በማለት ደጀ ሰላም እንደዘገበችው የሴራው አቀነባባሪዎችና ተባባሪዎችም ላይ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎም ይጠበቃል፡፡
ከዜና ቤተክርስቲያን ጋር በተያያዘ ቀሲስ ዶክተር መስፍን ተገኝ የዲስና አካባበው አገረስብከት ጸሃፊ ቤተክርስቲያን የሰጠቻቸውን ሃላፊነት ለመወጣትና የቤተክርስቲያን እንድነት ለመጠበቅ እየፈጸሙት ያለውን ተግባር ለማደናቀፍ ህገወጦች ያለአግባብ ስማቸውን በቤተክርስቲያኗ ልሳን(ዜና ቤተክርስቲያን) ስላጠፉባቸው ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ እንዲሰጥበትም ጠይቀዋል፡፡
የቅዱስ ሲኖዶስ አምስተኛ ቀን የጠዋት ውሎ ተከታትለን ለማቅረብ እንሞክራለን፡፡

5 comments:

  1. please watch this:

    http://www.youtube.com/watch?v=zu8BLzlQ82M

    ReplyDelete
  2. በሰሞኑ ግርግር የታዘብኩት
    አባቶች የያዙትን አጀንዳ እንዳይነጋገሩበት ለማድረግ ፣ ብልሆቹ የከተማ ሰዎች ትኩስ ርዕስ ፈጥረውላቸው ሲያምሷቸው ፣ አንዳቸውም ዘወር አድርገው ዓላማውን ስላላጤኑት ፣ ሊወያዩበት ተቀረጸ የተባለው አጀንዳ ያለ አንድ መደምደሚያ ሊቀር ይመስለኛል ፡፡ በጋዜጣው ላይ ለማቀጣጠያነት የተዘረዘሩት ጉዳዮች ፣ አጀንዳ ማስቀየሪያ እንደሆኑ የታሰበባቸው መሆኑ የሚታየው ውጤታቸውን በመመልከት ነው ፡፡ መሥራት የሚገባቸውንና ግዴታቸው የሆነውን ፣ የሃይማኖት ግድፈትን ከማረም ይልቅ ፣ ወደ ዓለማዊውና ሥጋዊው ጉዳይ ያተኮሩ አስመሰለ /በቤትና በመኪና ጉዳይ መከራከር/ ፡፡ ይኸ ደግሞ ከገፉበት እርስ በርሳቸውም እንዳይከፋፈሉ ያስፈራኛል ፡፡

    እግዚአብሔር ለቤተ ክርስቲያናችንና ለምእመን የሚሆነውን ምላሽ በራሱ ይስጥ!!!
    አሜን

    ReplyDelete
  3. Please watch: False attack on Ethiopian Orthodox Church By Protestants & tehadso


    http://www.youtube.com/watch?v=zu8BLzlQ82M

    ReplyDelete
  4. አባቶቻችን ሴራውን የተገነዘቡት አይመስለኝም ቢገነዘቡት ኖሮ አይደለም 3 ቀን 3 ሰዓትም አይወያዩበት፣ ለማንኛውም የጨለማው ቡድን ያሰበውን ለጊዜው ያሳካ ይመስላል፤ ግን እግዚአብሄር ከእውነት ጎን ስለሆነ ተስፋ አለኝ፡፡ በአባቶች ግን አዝኛለሁ የእነሱ ክብር ስለተነካ ሶስት ቀን አባከኑ ፣ የቤተክርስቲያን ዶግማ እና ቀኖና ሲጣስ መወያየት እየሰለቻቸው ግንቦት ላይ ወደ ጥቅምት ጥቅምት ላይ ወደ ግንቦት ያሸጋግሩታል፡፡ ዘንድሮም እግዚአብሄር እንደ ሀጢያታችን ሳይሆን ስለወዳጆቹ ቅዱሳን ብሎ በርኤዴቱ ካልጎበኛቸው አጀንዳወቹን ወደ ጥቅምት አያሸጋግሩትም ማለት ይከብዳል፡፡
    አንድአድርገኖች እኛ እኮ መረጃወችን ከእናንተ እየጠበቅን ነበር፣ ግን
    አንደኛ አርዕስቶቻችሁ ብዙ ጊዜ ይጮኻሉ (ከፅሁፉ ይዘት በላይ ታጋንናላችሁ ፣ ለምሳሌ ቅ/ሲኖዶስ ሌላ ሰብሳቢ መርጦ ጉባኤውን ለመቀጠል ወሰነ የሚለው ከፅሁፋችሁ ውስጥ ስንገባ ሀሳብ ቀረበ እንጂ አልተወሰነም)
    ሁለተኛ፤ መረጃዎቹን ተሎተሎ እያወጣችሁ አይደለም በዚህ የተሀድሶ ብሎጎች እየበለጡአችሁ ነው፡፡ ቢያንስ ዋና ዋና ሃሳቦች ብታቀርቡልን ጥሩ ነው ፣ዝርዝሩን ጊዜ ወስዳችሁ በደንብ አቀናብራችሁ ብታቀርቡልን )

    ReplyDelete