Monday, May 14, 2012

የቅ/ሲኖዶስ መደበኛ ስብሰባ አራተኛ ቀን የጠዋት ውሎ


(አንድ አድርገን ግንቦት 6 ፤ 2004ዓ.ም )፡- የቅ/ሲኖዶስ መደበኛ ስብሰባ አራተኛ ቀን(ሰኞ) የጠዋት ውሎ ባለፈው ቅዳሜ ከቀትር በኋላ በነበረው ቅዱስ ሲኖዶስ ውሎ በዜና ቤተክርስቲያን ርእሰ አንቀጽ ላይ ለመነጋገር ለዛሬ ጠዋት ቀጠሮ እንደተያዘ መዘገባችን ይታወሳል፡፡ በዚሁም መሰረት ብጹዓን ሊቃነጳጳሳት የቅዳስነታቸውን እመቢተኝነትና አምባገነንት ምክንያት ስብሰባው አድካሚ ስለሆነባቸው ስብሰባውን በሌላ ሰው ይመራ የሚለው ሃሳብ ሚዛን ስለደፋ የጨለማው ቡድን አጀንዳ ማሰቀየሪያነት እንደተጠቀመበት በሚነገረው ዜና ቤተክርስቲያን ርዕስ አንቀጽ ላይ ቅዱስ ሲኖዶስ ሰፊ ውይይትና ክርክር ያደረገ ሲሆን ለቀትር በኋላ ስብሰባ የውሳኔ ሐሳብ የሚያቀርብ ኮሜቴ በመሰየም የጠዋቱን  ስብሰባ ተጠናቋል፡፡ ያለ ትምህርትና ሐዋሪያዊ ተልዕኮ መምሪያ እውቅና እንዲሁም ያለ ጋዜጣው ዋና አዘጋጅ ይሁንታ በጨለማው ሲኖዶስ አባላት የተዘጋጀው ርዕሰ አንቀጽ ላይ ብጹዓን ሊቃነ ጳጳሳት ለአቡነ ጳውሎስ አፍራሽ አካሄድ እንዳይቃወሙ በማሸማቀቅ የፓትሪያሪኩን አምባገነንት አሜን ብለው እንዲቀበሉ ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀ ነበር፡፡

 የጨለማ ቡድኑ ብጹዓን ሊቃነጳጳሳትን ለማሸማቀቅ የነበረውን ፍላጎት ባይሳካም ቅዱስ ሲኖዶስ በደራሽ አጀንዳዋች የስብሰባ ጊዜውን እንዲያባክንና የተቀረጹትን 20 አጀንዳዋች ለቀጣይ የጥቅምቱ ሲኖዶስ እንዳያሳድራቸው ተፈርቷል፡፡ ብጹዓን ሊቃነጳጳሳት የአቡነ ጳውሎስን ለህገ ቤተክርስቲያን አልገዛም ባይነት እስከ መጨረሻው ታግለው ለማስተካከልና ውሳኔ ለማሳለፍ ጥብዓትና የመንፈስ አንድነት(ልዕልና) እንደጎደላቸው ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ወገኞች እየተናገሩ ነው፡፡የውሳኔ ሐሳቡንን የቀትር በኋላውን /ሲኖዶስ ውሎ ተከታትለን ለማሳውቅ እንሞክራለን፡፡

ቸር ወሬ ያሰማን!

7 comments:

  1. ብጹዓን ሊቃነጳጳሳት የአቡነ ጳውሎስን ለህገ ቤተክርስቲያን አልገዛም ባይነት እስከ መጨረሻው ታግለው ለማስተካከልና ውሳኔ ለማሳለፍ ጥብዓትና የመንፈስ አንድነት(ልዕልና) የጎደላቸዉ አይመስለኝም፡፡ ጉዳዩን በሰከነ ሁኔታ ለመከታተል ይመስለኛል፡፡

    ReplyDelete
  2. Amen! God Eyes be up on our church!

    ReplyDelete
  3. አሸናፊው እግዚአብሔር ነውና እርሱ ነገሮችን እንዲያስተካክል ከመካከል ገብቶ ድል ሚነሳውን ድል ስነሳው ዘንድ የርሱ ፈቃድ ይሁን ተግተን እንጸልይ።

    ReplyDelete
  4. lehulume gize alewe 318 likawent benante eneyewe mekerawen tagesu

    ReplyDelete
  5. lehulume gize alewe 318 likawent benante eneyewe mekerawen tagesu

    ReplyDelete
  6. Now they are concerned when their right seems to be touched.
    really shame for us. because every thing written on the news paper is true.
    May be I don't know what is written about Abune Fanuel and America Doses.
    but the other issue as reported on abaselam unless it is rewritten all what we
    have been desperate for long time. Please if you stand for well being of our church report without histateing, no matter the issue ,whether mk is opposed or not. other wise you are also immoral just like other blog like abselama awdemihret and dejeselam etc.
    May God Protect our hope on His Church for the sake of His Lovely Mother.

    ReplyDelete
  7. This comment has been removed by a blog administrator.

    ReplyDelete