Sunday, October 2, 2011

ሐረር ሐዋሳን እየመሰለች ነው፡፡


ዲ/ን በጋሻው እና ግብር አበሮቹ በሐዋሳ ከተማ ያደረጉት እና በቁርጠኛ ምዕመናን እና የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች የከሸፈው የማበጣበጥ ስራ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ወደ ሐረር ከተማ ማዛወራቸው የሚታወቅ ሲሆን ዲ/ን በጋሻውም ግለሰቦቹን በማደራጀት እና መመሪያ በመስጠት ቀጥተኛ ተሳትፎ እያደረገ ነው፡፡ በመሆኑም ከሐረር መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን የተውጣጡ ምዕመናን የምስራቅ ሐረርጌ እና የሱማሌ ሐገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ያሬድ “ሕገ ወጥ” ያሏቸውን ሰባክያን በሐገረ ስብከታቸው ውስጥ እንዳያስተምሩ ማገዳቸውን እና ማስተማር የሚችሉትም ከጠቅላይ ቤተክህነት የሚመጡ መምህራን አልያም በሀገረ ስብከቱ የሚገኙ ሰባክያን እና ሊቃውንት ብቻ እንዲሆኑ የሚል መመሪያ ማውጣታቸው ተቃውመዋል፡፡ የሊቀ ጳጳሱን ውሳኔ በመቃወም ሊቀ ጳጳሱ ብጹዕ አቡነ ያሬድ እና የሐገረ ስብከቱ ስራ አስኪያጅ መጋቤ ሰናያት ኃይለማርያም ይነሱልን ያሉት ቁጥራቸው 20 የሚደርሱ ምዕመናን ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ላይ ናቸው፡፡


ግለሰቦቹ የፓትርያርኩ ፕሮቶኮል ለሆኑት ለአቶ ሙሉጌታ እና ለሌሎች ሰዎች ጉዳይ ማስፈጸሚያ የሚሰጥ 15000 እጅ መንሻ መያዛቸው የታወቀ ሲሆን ጥቂት ግለሰቦች በተለያየ ስም ደጋግመው የፈረሙበትና የ5000 ምዕመናን ፊርማ ያረፈበት ፒቲሽን መያዛቸውም ተረጋግጧል፡፡


የምስራቅ ሐረርጌ እና በሱማሌ ሐገረ ስብከት ስብከተ ወንጌልን አስመልክቶ ያወጣው ጠንከር ያለ መመሪያ ስነ ስርዐት የማስያዝ ግብ ያለው በመሆኑ ለቤተክርስቲያኒቱ ስርዐት ግድ የሌላቸውን ዲ/ን በጋሻውና ግብር አበሮቹን በከፍተኛ ሁኔታ ያስቆጣ ሲሆን “ከመመሪያው ጀርባ ጸረ ወንጌል የሆነው ማህበረ ቅዱሳን አለበት” ሲሉ አማረዋል፡፡በጉዳዩ ላይ የማኅበረ ቅዱሳን ሐረር ማዕከል ግን ምንም አስተያየት አልሰጠም፡፡ ተቃዉሞአቸው ለቅዱስ ፓትርያርኩ ለማቅረብ በጉዞ ላይ የሚገኙት ግለሰቦች “ከ 1987ዓ.ም ጀምሮ ብጹዕ አቡነ ዜና ማርቆስ እና ብጹዕ አቡነ ቀዎስጦስ “ተሐድሶ” እያሉ በርካታ ምዕመናንን ከቤተ ክርስቲያን አስወጥተዋል ይህ ታሪክ እንዲደገም አንፈልግም” ብለዋል፡፡


ሊቀ ጳጳሱ ብጹዕ አቡነ ያሬድ ካወጡት መመሪያ አንደኛው ማንኛውም ጉባኤ ከምሽቱ 1፡30 በፊት መጠናቀቅ ይኖርበታል የሚል ሲሆን ዲ/ን በጋሻው በሚያስተምርበት ጉባኤ ግን እስከ ሌሊቱ 7፡00 ድረስ በማስረዘም ጉባኤውን ተካፍለው በሚመለሱ ምዕመናን በተለይም ሴቶች እና ህጻናት ላይ የተለያ ጥቃቶች የሚደርስ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን “እኛ አባቶች አላግባብ በሚለጠጡ መርሐግብሮች ምዕመናን ጉዳት ሲያገኛቸው ዝም ብለን አንመለከትም ኃላፊነትም አለብን መመሪያውም ስናወጣ ከዚህ አንጻር እንጂ የማንም ግፊት አልተደረገብንም” ሲሉ ብጹዕ አቡነ ያሬድ ገልጸዋል፡፡ 
‹‹እግዚአብሔር ቤተክርስቲያናችንን ይጠብቅልን››
Posted  by ገብር ኄር
ማቴዎስ አጥምዛ (gebrher33@gmail.com)

4 comments:

  1. ሽብር መንዛት ትታችሁ እውነተኛ ክርስቲያን ከሆናችሁ ለቤተክርስቲያን አንድነትና ሰላም መጸለይ አለባችሁ፡፡ ምእመኑን አትከፋፍሉ፡፡

    ReplyDelete
  2. ለሁሉነገር ተጠያቂዎች እነሱ ናቸው ሲያስተምሩ አይታዩ ለብጥብጥ ለአድማ የተነሱ የትልቅ ትንሽ የሞላበቸው፡፡

    ReplyDelete
  3. ውይ ውይ ውይ ምን አይነት ወሬኞች ናችሁ እናንተ እግዚያብሄር የስራችሁን ይስጣችሁ

    ReplyDelete
  4. I am surprised what agenda you guys have on our church, you yourself look like the enemy of GOD and Tewahido. be sure GOD will judge you.

    ReplyDelete