Sunday, October 30, 2011

ትልቁ መርዛማ እሾህ ተነቀለ

Adios Abba Sereke!!!!!!!!!!!!!!
ቅ/ሲኖዶስ አባ ሰረቀን ከሥልጣናቸው አወረደ
(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 18/2004 ዓ.ም፤ )፦ አወዛጋቢው የሰንበት ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ሓላፊ ቆሞስ አባ ሰረቀ ብርሃን ወደል ሳሙኤል ዛሬ ቅዳሜ ከሥልጣናቸው እንዲወርዱ ቅ/ሲኖዶስ ወሰነባቸው። ከሥልጣናቸው መነሣትችም ብቻ ሳይሆን ለረዥም ጊዜ በሚከሰሱበት ከኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ እምነት ውጪ ነው  የሚባለውን እምነታቸውን የሚመረምር አምስት ሊቃነ ጳጳሳት የሚገኙበት ኮሚቴም ተሰይሟል። የኮሚቴው አባላትም ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ፣ ብፁዕ አቡነ  ናትናኤል፣
ብፁዕ አቡነሕዝቅኤል፣ ብፁዕ አቡነ እንድርያስ እና ብፁዕ አቡነ ያሬድ ናቸው።
አባ ሰረቀ ከሓላፊነታቸው እንዳይነሡ በጥብዓት ሲከራከሩላቸው የቆዩት ቅዱስ ፓትርያርኩ ይዘውት የነበረውን አቋም እንዲቀይሩ ወጣቱ በቅርቡ ያሳየውን ተቃውሞ የተረዳው መንግሥት ተጽዕኖ ሳያደርግ አልቀረም ተብሏል። መላው ኦርቶዶክሳዊ እና የፀረ ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶው ቤተሰብ እግዚአብሔርን እያመሰገነ እና ለቅ/ሲኖዶስ ያለውን አክብሮት በመግለጽ ላይ ይገኛል።
ዝርዝር ዜናውን ጠብቁ
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++

ከዚህ በፊት ከዘገብናቸው ዜናዎች መካከል የሚከተሉትን ይመልከቱ
የሰሞኑ የዜና ርዕስ የሆኑት አባ ሰረቀ ማን ናቸው? 

በአሜሪካ ምን ምን ሲሰሩ ኖሩ?

የሰሞኑ የዜና ርዕስ የሆኑት አባ ሰረቀ ማን ናቸው? በአሜሪካ ምን ምን ሲሰሩ ኖሩ?

(ደጀ ሰላም፤ ሰፕቴምበር 27/2009)፦ ሰሞኑን በማኀበረ ቅዱሳንና በጠቅላይ ቤተ ክህነት አንድ መምሪያ መካከል የተፈጠረው ውጥረት ፈንድቶ መውጣቱንና መንግሥትን ማሳተፉን ከሰማን ወዲህ ስማቸውን በጉልህ መስማት ከጀመርናቸው ሰዎች መካከል አንደኛውና ግንባር ቀደሙ ሰሜን አሜሪካ የነበሩትና በደንብ የምናውቃቸው “አባ ሰረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል” ናቸው። ስለዚህ ይህ ጽሑፍ ስለኚሁ ሰው የአሜሪካ ቆይታ እውነተኛ እማኝነት ይሰጣል። ቤተ ክርስቲያናችንን የሚመሯትና ነገ ጳጳስ ይሆናሉ ተብለው የሚጠበቁት እኚህ ሰው ምን ዓይነት ሰው እንደሆኑ ያብራራል።

አባ ሰረቀ የዛሬ 15 ዓመት አካባቢ ወደ አሜሪካ ሲገቡ ለመጀመሪያ ጊዜ የሄዱት ወደ ሎስ አንጀለስ ካሊፎርኒያ ነበር። በዚያም አባ ኃ/ሥላሴ ከተባሉ አባት ጋር የጻድቁን የአቡነ አረጋዊን ቤተ ክርስቲያን ማገልገል ጀምረው ነበር። ይሁን እንጂ አባ ሰረቀ ከመጡበት ጊዜ ጀምሮ የሄዱበት አካባቢ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናትን ሰላም በማወክና በመበጥበጥ የታወቁ እንደመሆናቸው አቡነ አረጋዊንም ወዲያውኑ መበጥበጥ ጀመሩ። የአቡነ አረጋዊ ቤተ ክርስቲያንን ቦርድ በመቅረብ “መቀደስና ማገልገል የምፈልገው በትግርኛ ቋንቋ ብቻ ነው” ማለት ጀመሩ። በዚህም የዘወትር አገልግሎት የሚሰጥባቸውን ግዕዝንና አማርኛን ዜሮ አደረጓቸው። ቦርዱን በመጠምዘዝና በማሳመን በትግርኛ ብቻ እንዲቀደስ ለማድረግም ችለው ነበር።

በዚህ መልክ ከ6-8 ወራት ከቆዩ በኋላ በቦርዱ አባላት መካከል እንደገና ጥርጥር፣ አለመግባባትና ልዩነት በመፍጠር ለመክፈል ሞከሩ። ወደ ትግርኛ የቀየሩት ቅዳሴ አላዋጣ ሲላቸው ወይም “ስልታዊ ለውጥ” ማድረግ ሲፈልጉ እንደገና “ወደ አማርኛና ግዕዝ” መመለስ ፈለጉ። በዚህ ጊዜ ቦርዱ እምቢ አለ። “ለምን መጀመሪያ ወደ ትግርኛ ወሰዱን ለምን ይመልሱናል? እኛ የእርስዎ መጫወቻ አይደለንም። ደግሞ የቤተ ክርስቲያናችን አባላት ለምደውታል” ብለው እምቢ አሉ።

አባ ሰረቀ ይህ አልሳካላቸው ሲል ዲሲ አካባቢ ከሚገኘው የመድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ተጋጭተው የወጡ የትግርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎችን በማስተባበር “ቤተ ክርስቲያን ለመክፈት” ተስማሙ። ይህ ከመድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን የወጣው ቡድን ያን ጊዜ የአሜሪካ ሀ/ስብከት አሁን የኢየሩሳሌም ሊቀ ጳጳስ የሆኑትን ብፁዕ አቡነ ማትያስን በማነጋገር “በትግርኛ ብቻ አገልግሎት የሚሰጥበት ቤተ ክርስቲያን ለመክፈት” ሞክረው ሳይሳካላቸው የቀሩ እንደነበሩ ጉዳዩን የሚያውቁ ሰዎች ይናገራሉ። እናም በሎስ አንጀለስ አቡረ አረጋዊ ያልተሳካላቸው አባ ሰረቀ ቨርጂኒያ ሌላ የአቡነ አረጋዊ ቤተ ክርስቲያን “ከፈቱ”። የሎስ አንጀለስ ምዕመናንን ያሳሳቱት ሳይበቃ የቨርጂኒያዎችንም አጭበርብረው በዘረኛ መንፈሳቸው የዋኃኑን አጠመዷቸው። ትናንትና አባ ሰረቀ “የከፈቱት አቡነ አረጋዊ ቤተ ክርስቲያን” ዛሬ ደግሞ አባ ኃ/ሚካኤልን የመሰሉ መናፍቅ መነኩሴ አቅፎ ይዟል። (አስተዳዳሪው ቀሲስ ተከስተ የተባሉ ወጣት ቄስ ናቸው)። አባ ኃ/ሚካኤል ከአባ ሰረቀ ሚሽን ተቀብለው ወደ አሜሪካ የመጡ መሆናቸው በስፋት ይነገራል፤ ይታወቃልም።

አባ ሰረቀ ወደ ቨርጂኒያ እንደመጡ የሀገረ ስብከቱን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማትያስን በመቃወም ማስተማር ጀመሩ። ብፁዕ አቡነ ማትያስን ብቻ ሳይሆን በጠቅላላው ጵጵስናንና ፕትርክናን በመቃወም “ጳጳስም፣ ፓትርያርክም አያስፈልግም” እያሉ ዐውደ ምሕረቱን ከያዙ ጀምሮ በትግርኛ ብቻ በመቀደስና ማስተማር ክፍፍልን መዝራት ጀመሩ። “ጳጳስ አያስፈልግም አዲስ ቤተ ክርስቲያን ለመክፈት ከሆነ እኔ ራሴ ‘መባረክ’ና መክፈት እችላለሁ” ማለት ጀመሩ። በዚህ የተጀመረው ልዩነት ሰፍቶ አቡነ አረጋዊን ራሱን ለሁለት ለመከፈል አበቁት።

ከዚያም የቤተ ክርስቲያኑን ስምና ንብረት በመውሰድ ጥለው ወደ አሌክሳንደሪያ (ቨርጂኒያ) ሄዱ። በዚያው ስም አቡነ አረጋዊ ብለው በመሰየም “አዲስ ቤተ ክርስቲያን ከፈቱ”። በአባ ሰረቀ ጎትጓችነት ተታለው ከመድኃኔዓለም ወጥተው የነበሩትም ምእመናን ልዩነታቸው በማቻቻል ከቀደመው ቤተ ክርስቲያናቸው ጋር ታረቁ። ይሁን እንጂ አባ ሰረቀ ንብረታቸውን በሙሉ ዘርፈው እንደወጡ እንዲቀሩ አልፈቀዱላቸውም። የሕግ ዕውቀት ያላቸው ሰው በማነጋገርና ርዳታ በማግኘት አባ ሰረቀን ሕግ ፊት አቆሟቸው። አባ ሰረቀም የወሰዱትን ሀብትና ስም በሙሉ በግድ ለመመለስ ተገደዱ። በሕግ ፊት የተዋረዱት አባ ሰረቀም አቡነ አረጋዊን አስረክበው ሲያበቁ በቅ/ጊዮርጊስ ስም “አዲስ ቤተ ክርስቲያን በቨርጂኒያ ከፈቱ”። ይህ ቤተ ክርስቲያን ዛሬም በቨርጂኒያ እንደሚገኝ ይታወቃል።

አባ ሰረቀ በዚህ መልክ ቤተ ክርስቲያንን ሲከፋፍሉና ሲያዋርዱ ቆይተው ጊዜ እየተቀየረ ሲሄድ “ጳጳስ የመሆን ሌላ ጾር ሲነሣባቸው” በፊት “አያስፈልግም” ሲሉት የነበረውን “ጵጵስና፣ ፕትርክና እና ቅዱስ ሲኖዶስ” ሸውደው “እጅ ሰጥተው” የአቡነ ጳውሎስ ጋሻ ጃግሬ ሆነው ወደ ኢትዮጵያ ገቡ። አባ ሰረቀ የዲሲና አካባቢው ማህበረ ካህናት ጉባዔ አባል በነበሩባቸው ዘመናት ሁሉ እያጥላሉ ሲሳደቡ የነበሩትን ፓትርያርክ “ካለ እርስዎ ሰው የለም፣ ቅዱስ የለም” ብለው ጫማ ስመው የመምሪያ ኃላፊነት ሽልማት ተሰጣቸው። ይሁን እንጂ ሲጓጉለት የነበረው ጵጰስና ሳይሳካላቸው ቀረ። የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት የሆኑ ብፁዓን አባቶች “እንዲህ ዓይነቱን ወንበዴ፣ ቤተ ክርስቲያንን ሲያሰቃይ የኖረ ሰው እንዴት ጵጵስና እንሾመዋለን” በማለታቸው ሳይሳካ ቆይቶ ነበር። ውስጥ አዋቂዎች እንደሚናገሩት ከሆነ በመጪው ጥቅምት በሚደረገው የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ ጵጵስና እንዲሾሙ ይቀርባሉ ከሚባሉት አባቶች መካከል አንደኛው እኚሁ ዘረኛ መነኩሴ አባ ሰረቀ ብርሃን እንደሚሆኑ ታውቋል።

አይ ዘመን፤ የሚገርመው እኚህኑ አባ ሰረቀን ዛሬ እሑድ በተላለፈው የሀገር ፍቅር ሬዲዮ ላይ ድምጻቸውን ሰማነው። ያውም የቤተ ክርስቲያን “ጠበቃና ተቆርቋሪ” ሆነው። አይ ቤተ ክርስቲያን!!! መከራሽ አያልቅ!!!
ቸር ወሬ ያሰማን

ይህ ሰው (አባ ሰረቀ) ማን ነው?
Dejeselamoch,
Who is Aba Sereke? Please post an article about him and what he did to our church, if you get information.
September 22, 2009
++++++++++++++++++++++++++++
(ከዘመቻ)
(September 25, 2009) አንድ ደጀ ሰላማዊ “አባ ሰረቀ የሚባለው ስው ማነው? ይህን ያህልስ ማቅን ለማጥፋት ታጥቆ የተነሳበትስ ዓላማው ምንድር ነው?” ሲል መጠየቁን መነሻ አድርጌ የህሊና የውልደት ስብራት ስለገጠመው አባ ሰረቀ (ስም ግብርን ይመራዋል እንዲሉ በ“ሠ” ስሙን አለመጣፌን ልብ ይሉዋል) ማንነት ጥቂት ለማለት ፈለግሁ።

ለነገሩ ይህን ያህል አጀንዳ ሊሆን የሚገባው ሰው እንኳን አልነበረም። አባ ጳውሎስ እንደ ጫማ ውስጥ ጠጠር እየቆረቆረ ዘወትር እረፍት የሚነሳቸውን ማኅበረ ቅዱሳንን ለማፍረስ “ሳልጠራው አቤት ሳልከው ወዴት የሚል፣ ህሊናውን የተነሳ ሰው ፈልጉልኝ” ብለው ወዳጆቻቸውን፣ (መቼም የልብ ወዳጅ እንደሌላቸው የታወቀ ነው፣ እንደ ንጉሴ ያሉ ጥቅመኞች ያሉትን ለማለት ነው) አደራ ባሉት መሰረት ግዕዛን ከሌላቸው እንስሳት የሚመደብ፣ እውነትን እንኳን በተግባር በስም እንኳን የማያውቃት፣ የሥልጣን ጥም ያናወዘው፣ በፍቅረ ነዋይ ልቡ የታወረ፣ አባ ሰረቀ በመብራት ተፈልጎ ተገኘ። አባ ጳውሎስም “ልቤ በሰረቀ ጸና” አሉ።

በእርሱም ልባቸውን አኖሩ። ማኅበረ ቅዱሳንን ባልዋለበት እንደዋለ አድርጎ እንዲከስ ግዳጅ ተጣለበት። ከላባው አባ ላይ ታች ማለቱን ተያያዘው። የማኅበሩን በጎ ስም የሚያጠፋ የሥድብ መጥሀፍ አጻፈና በውድቅት ሌሊት በገንዘብ የገዛቸው ግብር አበሮቹ ፖስተሩን ሲለጥፉ ሁሉ በፖሊስ አስከመያዝ ደርሰዋል። ዳሩ ግን ውሎው ከኢሕአድግ ባለስልጣኖች ጋር የሆነው አባ ሰረቀ ማህበሩን የቅንጅት ቀኝ እጅ እንደሆነና በሚድያዎቹም የሚያስተላልፋቸው መልእክቶች ምእመኑ በመንግስት ላይ እንዲነሳ የሚያደርጉ እንደሁኑ አቀረበ (ለምሳሌ በጅማውና በኢሊባቡር በክርስቲያኖች ላይ የደረሰውን ዘግናኝ ጭፍጨፋ በቤተ ክርስቲያን ላይ የደረሰውን ውድመት መግለጹን) ።

በተለያዩ ግዜያት በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ በአክራሪ ሙስሊሞች አማካይነት የደረሱትን ጭፍጨፋዎች፣ አባ ጳውሎስና መሰሎቻቸው እፍን አድርገው ልክ እንደ ተረቱ “አትናገሩ ጅቡ እኔን እየበላኝ ነው” እንደሚለው ገዳማውያኑ አባቶች እየተገደሉ፣ ክርስቲያኖች ከነ ማተባቸው እየታረዱ፣ አብያተ ክርስቲያናት እየተቃጠሉ፣ እነ አባ ጳውሎስ ግን ምንም እንዳልተፈጠረ አድርገው የቤተ ክርስቲያኒቱን ልጆች ደም ለስልጣናቸው ማቆያ ገፈራ አድርገው ሲያቀርቡ ኖረዋል።

ዛሬም አይናቸውን በጨው አጥበው የቤተ ክርስቲያኒቱን ክብር እንደለመዱት መሬት ላይ ጥለው ሄሮድሳውያን ጌቶቻቸው ሲረጋግጡት ዓለም ሁሉ እንዲያይና ቤተ ክርስቲያኒቱን መሳቅያ መሳለቂያ እንዲያደርጋት ሲያደርጉ በቴሌቪዥን መስኮት ለማየት በቃን። በሲኖዶስ መንበር ላይ ቄሳሮች ተሰይመው ሲዳኙ ለማየት በቃን በአባ ጳውሎስ ዘመነ ፕትርክና ምን ያልታየ ጉድ አለ የቤተ ክርስቲያኒቱን እድገት የማይሻውና ሰበባሰበብ እየፈለገ ቤተ ክርስቲያኒቱን የሚያጣጥላት የኢሃድግ መንግስት ቤተ ክርስቲያኒቱ ከመናፍቃንና ከአክራሪዎች ወከባ ይታደጋት ዘንድ እግዚአብሄር ያቆመውን ማኅበር በማፍረስ ቤተ ክርስቲያኒቱን ለማዳከም በያዘው ስትራቴጂ መሰረት አስቀድሞ በአባ ጳውሎስ አቀነባባሪነት በአባ ሰረቀ ተላላኪነት የተዘጋጀው ትርኢት መድረኩ ላይ እሰከሚገኙ ድረስ ተሳታፊዎቹ እንኩዋን አያውቁም ነበር። አስቀድሞ የተቀነባበረው ቅንብር በህሊና አልባው በመነኩሴ አምሳል በተሰረው ሮቦት በአባ ሰረቀ ቀርቦ በፖለቲካው አጋፋሪ መመሪያ ሰጪነት በአባ ጳውሎስ አሳራጊነት የትርኢቱ ፍጣሜ ሆነ።

በጠቅላላው አባ ሰረቀ ማለት አባ ጳውሎስ ሰራሽ ሮቦት ነው፤ አልቦ ኅሊና።

+++++++

የሊ/ካህናት ጌታቸው ዶኒ እና የአባ ሰረቀ ምስጢራዊ ደብዳቤ

    . ‹‹ወጣቱን በተሐድሶአውያን ኅብረት አዲስ ጥምቀት በማድረግ በ‹ቅን ልቦና የመንፈሳዊ የፈውስ አገልግሎት› ሥር መሰብሰብ፤››
    . ‹‹ሐሳባችንን የሚያደናቅፉ የአቡነ ሳሙኤል ደጋፊዎችን ተቋቁመን ልንጥላቸው ይገባል፤››
    . ‹‹ወላጅ በሌላቸው ሕፃናት ስም የገንዘብ እና አልባሳት ርዳታን ከሙሉ ወንጌል አማኞች ማኅበር በመቀበል እና የቤት ለቤት ማጥመቅ ተግባራትን በመፈጸም እንቅስቃሴውን ማጠናከር፤››

(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 30/2010)፦ ራሳቸውን ‹‹የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ሕጋዊ ወኪል›› በማለት በይፋ የሚጠሩት እና የሰፋሪ ገነት አቃቂ ደብረ ቁስቋም ቅድስት ማርያም እና ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ሊቀ ካህናት ጌታቸው ዶኒ፣ ቤተ ክርስቲያንን ‹‹በተሐድሶአውያን ኅብረት›› ለማጥመቅ በሚል ያቀዱበት፣ ለዚህም እንቅስቃሴያቸው ማጠናከርያ የአቡነ ጳውሎስን ሐውልት በአጥቢያቸው ከማሠራት ጀምሮ ሌሎች የገንዘብ
ማሰባሰቢያ ስልቶችን የነደፉበት እና ይህንኑ ውጥናቸውንም በመንበረ ፓትርያሪክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሰንበት ት/ቤቶች ማ/መ ሐላፊ ከሆኑት ከአባ ሠረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል ጋራ በሐሳብ የተስማሙበት እና የመከሩበት መሆኑን የሚገልጽ በእጃቸው የተጻፈ ደብዳቤ ለደጀ ሰላም ደርሶ ተመልክተነዋል፡፡
በቀን 05/02/2002 ዓ.ም እንደ ተጻፈ የተመለከተበት ይኸው ደብዳቤ የሊቀ ካህናት ጌታቸው ዶኒ የግል ማኅተም እና ፊርማ ያረፈበት ነው፡፡ የደብዳቤውን ሙሉ ቃል ዳግመኛ ታይፕ በማድረግ ከእጅ ጽሑፉ ጋራ አባሪ በማድረግ ያቀረብንላችኹ ሲኾን በይዘቱ ላይ የተመሠረተ ዝርዝር ሐተታ በቀጣዮቹ ቀናት የምናስነብብ መኾኑን እንገልጻለን፡፡
                                                     ቀን፡- 05/03/2002

ለአባ ሠረቀ ብርሃን
ለሰንበት ት/ቤቶች መምሪያ ሐላፊ፤

       የማክበር ሰላምታዬን እያቀረብኹ፣ እንደሚታወቀው ባለፈው በተነጋገርነው መሠረት ጉዳዩን እየሄድኩበት እገኛለሁ፡፡
እንደሚታወቀው አንዳንድ የአቡነ ሳሙኤል ደጋፊዎች የግል ማኅደሬን ለማበላሸት የፓትርያሪኩን ሕጋዊ ወኪልነቴን ለመሻር ደብዳቤ ጽፈውብኝ ነበር፡፡ ነገር ግን ይህን ሐሳባቸውን አክሽፌባቸዋለሁ፡፡ በመሆኑም አቡነ ይስሐቅ እንድነሣ ሊያደርጉኝ ቢያስቡም በአቡነ ገሪማ ጸሐፊነት ደብዳቤው እንዲመለስልኝ ተደርጓል፡፡ ምክንያቱም ጋዜጣ ላይ የጻፍኹት ራሴን ለማስተዋወቅ አይደለም፡፡ የፀረ ሰላም ኀይሎችን ምስጢር ነው ያወጣሁት፡፡ አባ ሠረቀ ብርሃን በእርስዎ በኩል ይጠበቅብዎታል፣ ምክንያቱም በርካታ ሰንበት ት/ቤቶችን በመምሪያው ሥር ማግኘት ስለምትችሉ፣ ቤተ ክርስቲያንን በወጣት ኀይል ነውና ማደስ የሚቻለው ጠንክረን መሥራት እንችላለን፡፡
እኛ ሣራ የወለደችን በመሆኑ እናታችንን ከኋላ ቀር አሠራር እና ባህል አላቀን፣ ወጣቱን በተሐድሶአውያን ኅብረት አዲስ ጥምቀት በማድረግ ‹‹ቅን ልቦና የመንፈሳዊ የፈውስ አገልግሎት›› ሥር ልንሰበስባቸው እንችላለን፡፡
የካናቴራ አልባሳት ማሠርያ ለማሠራት በጎ ፈቃደኞችን እየጠቆሙኝ ነው፡፡ ስለዚህ እኔም የማጥመቅ ሥራ በየቤቱ እየዞርኹኝ እያጠናከርኩኝ ነው፡፡ እርስዎም ይህን መንገድ በተሻለ መንገድ አጠናክረው ሊቀጥሉበት ይገባል፤ ስለ ገንዘቡ ሊጨነቁ አይገባም፡፡ 170 ሺሕ የሚያወጣ ሐውልት በእኛ ደብር ስለምናሠራ ከዚያ ላይ በሚገኘው ገንዘብ ልናጠናክረው እንችላለን፡፡ በዙሪያው ያሉ የአቡነ ሳሙኤል ደጋፊዎች ይህን ሐሳባችንን ሊያደናቅፉ ቢችሉ እንኳን ተቋቁመን ልንጥላቸው ይገባል፡፡
በመጨረሻም የሙሉ ወንጌል አማኞች ወላጅ ለሌላቸው ሕፃናት የገንዘብ እና የልብስ ድጋፍ ስለሚያደርጉልን ሕፃናትን መመዝገብ አለብን፡፡ በዚህ እኔ ባለሁበት ደብር አባ ገብረ ሥላሴ የተባሉት በስማቸው የመሠረቱት የሕፃናት ማሳደጊያ በርካታ ልጆች ስላሉ፣ በዚህ ማሳደጊያ ስም ልናገኝ እንችላለን፡፡ ስለዚህ በገንዘቡ በኩል በእንዲህ ዐይነት ኹኔታ ላይ ስለሆንን እርስዎ ወጣቱን በማነሣሣት ትልቅ ሥራ ሊሠሩ ይገባል፡፡ በተረፈ አዳዲስ ነገር ሲኖር በስልክ በመደዋወል እንጨርሰዋለን፡፡
                                      
 ‹‹ከመንፈሳዊ ሰላምታ ጋር››
                                         ሊቀ ካህናት ጌታቸው ዶኒ
                                   የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ሕጋዊ   ወኪል          

6 comments:

  1. Egziabher Yimesgen des Yilal.
    Abatocachinn Egziabher Yitebikilin.

    ReplyDelete
  2. yekedemewin bedelachinin yalasebebin amilak yetemesegene yihun.betechirisitiyanachinin esikemechereshaw yitebikilin. amen!!!

    ReplyDelete
  3. le ewinetegnayituna lekedemechiw haimanot yemimotu abatoch endihonu yalutin abatoch yitebikilin fetari ke enesu gar yihun. be begochu mengawist yetekelakelutin tekulawoch le betu yemikenaw amlak becherinetu bejirafu gerfo yawitalin. amen.

    ReplyDelete
  4. ለtg፡- ጉድ ነው አለ በአማርኛ በእንግሊዝኛ ሳይሆን ክርስቶስ በወንጌል ስታመነዝር አገኘናት ብለው እንውገራት የሏትን ሴት ታስታውሻለሽ ከናንተ ኃጢያት ያልሰራ ቢኖር ይውገራት ነበር ያለው የአንድ ሰው ከቤ/ክ መውጣት ክርስቶስን ይገደዋልና ይህ ሊያስደስተን አይገባም ደግሞ ሁሉን የሚያውቅ እርሱ ነው ሰው እንዲህ ነው እንዲህ ነው ስላለ መቀበል አይደለም

    ReplyDelete
  5. re:-tg; you made a mistake this an evidence not myth. If you have a mind,think critically.
    BT

    ReplyDelete
  6. ebakachuh endih aynet tera zegeba atakribu. endih aynetu ke sidib yaltenanese zegeba keyetignawum gazeta yigegnal. what we want is show love to all human beings and pray for those sinned ones. God blase Ethiopia,

    ReplyDelete