Monday, November 28, 2011

ቤተክርስትያናችንን አፈረሱብን


  • በስልጤ ዞን ቅበት ከተማ በአካባቢው ሙስሊሞችና ፖሊሶች የቅድስት አርሴማ ቤተክርስትያን አፈረሱ 
 (አንድ አድርገን ህዳር 19 ፤2004 ዓ.ም  November 29 2011 ) በስልጤ ዞን ከቅበት ከተማ 2 ኪሜ ርቀት ላይ የምትገኝው የቅድስት አርሴማ ቤተክርስትያን አርብ በ15 /03/04 በሙስሊም ፖሊስ አባላትና እነርሱን ከሚመስሏቸው ማህበረሰብ አካላት ጋር ሆነው ቤተክርስትያኗን ያፈረሷት ሲሆን ፤ በአካባቢው የሚገኝ ታማኝ ምንጭ ለማወቅ እንደቻልነው የቤተክርስትያኒቷ ጉልላት በፖሊስ አዛዡ ግቢ ውስጥ መገኘቱን በዓየይናቸው ተመልክተዋለል ፤ በዞኑ ያሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያ አማኞች የሚደርስባቸው ግፍ አስመክቶ ከስልጤ ዞን ቅበት ከተማ ትናንት በ18/03/2004 ዓ.ም ማለዳ በደቡብ ክልል ርዕሠ መስተዳድር ፅ/ቤት ክርስቲያኖች ለአቤቱታ በአምስት መኪና የሄዱ ሲሆን :: አቤቱታ አቅራቢዎች የደቡብ ክልል ርዕሠ መስተዳድር ቃል አቀባይ የሆኑት እስከ 10 ሠዓት ድረስ ሲሳለቁባቸው ውለው ያለ ምንም መፍትሄ ሸኝተዋችዋል:: አቤቱታ አቅራቢዎቹ ተመልሠው ወደመጡበት አካባቢ ቢመለሱ የመኖር ህልውናቸውናቸው አስጊ በመሆኑ በመጀመሪያ የደቡብ ክልል ፍትህ እና ፀጥታ ቢሮ ከዞኑ ፖሊስ ለሚደርስባቸው ጫና ገለልተኛ በሆኑ ፖሊስ እንዲጠበቁ ለማድረግ ቀጥሎም ለፌደራል መንግስት ለማሳወቅ አዲስ አበባ እንደሚያመሩ በባዶ ሆዳቸው መሪር እንባ እያነቡ ሲናገሩ ላያቸው ያስለቅሱ ነበር፡፡›› በማለት ዘግቦልናል ፡፡ጉዳዩን አስመልክቶ የሀገረሥብከቱ ሊቀጳጳስ አቡነ ቀሌምጦሰም ለሚመለከታቸው ደብዳቤ እንደፃፉ ለማወቅ ተችሏል፡፡



ፖሊስ ህገወጦችን በመያዝ ትክክለኛ ምርመራ በማድረግ ለዘር ፤ ለሐይማኖት ፤ ለመንግስት ሳይወግን ፍትህን ፍለጋ  ፍርድ ቤት ማቅረብ ሲገባው በስልጤ ዞን ያሉ ፖሊሶች ግን በእምነት ከሚመስሏቸው ጋር በመሆን ይህን ድርጊት መፈፀማቸው በጣም የሚያሳዝን ነገር ነው፡፡ የማህበረሰቡን ፀጥታ ጠባቂ ተብሎ የተቀመጠ አካል ወንጀል የሚፈፅም ከሆነ ማህበረሰቡ ማን ጋር ሄዶ አቤት ይበል? መንግስትና ህዝብ የጣለባቸውን ሐላፊነት የሚወጡ የፖሊስ አባላት እንዳሉ ሁሉ እንደዚህም አይነት የዘቀጠ ምግባር ያላቸውም አይጠፉም፡፡


ከሁለት ወር በፊት በአዋሽ 7 አካባቢ ልዩ ስሙ ቦርደዴ የሚባለው ቦታ ላይ የአባታችን የአቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ቤተክርስትያን በአካባቢው የሚገኙ ከአክራሪ ወገን የሚመደቡት የእስልምና ተከታዮች በአካባቢው ላይ ለ24 ሰዓት ያህል ከ4 በሚበልጡ መስኪዶቻቸውን ድምፅ ማውጫ Speaker ወደ ቤተክርስትያን አዙረው ‹‹አላህ ዋክበር›› በሚሉበት ሁኔታ ላይ ምንም ጥያቄ ያላቀረቡት በአካባቢው የሚገኙ ክርስትያኖች በዓመት አንድ ጊዜ ለ16 ቀናት ብቻ ያለውን የሱባኤ ጊዜ ለሊት ሰዓታት እና ኪዳኑ ፤ ጠዋት ትርጓሜው እና ስብከቱ ፤ ከሰዓት ቅዳሴው ረበሸን ብለው ቤተክርስትያኒቷ እንድትዘጋላቸው ለአካባቢያቸው ወረዳ አስተዳደር ሰላማዊ ሰልፍ አድርገው መጠየቃቸው የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው፡፡  ይህን ዜና ለማበብ ይህን ይጫኑ ፡፡

እየሆነ ያለውን ነገር ስናየው እና ስንመለከተው ህገመንግስቱ መንግስት ዜጎችን እኩል ማስተዳደር ያስችለው ዘንድ የሀይማኖች እኩልነትን እንደ አንድ አንቀፅ ያሰፈረ ሲሆን ፤ በተግባር እንዳየነው ግን መንግስትም ሆነ ከእሱ በታች የሚገኙት ህጉን የሚያስፈፅሙት አካላት ራሳቸው እየጣሱትና ህዝብን በህዝብ ላይ እነዲነሳሳ መንገድ ጠራጊዎች ሆነው ነው ያገኝናቸው፡፡ እስካሁን ድረስ በጅማ ፤ በስልጤ ዞኖች ፤ በምስራቅ ሐረርጌ እና አንዳንድ አካባቢዎች ብዙ አብያተክርስትያናትን አፍርሰዋል ፤ ንፁሀን ዲያቆናትን ፤ቀሳውስትን ፤ ምዕመናንን በሰይፍ ቀልተዋችዋል ፤ ደማቸውም በቅዳሴ ሰዓት ከመንበሩ ፊት አፍስሰዋል ፤ ለዚህ ሁሉ ህገወጥ አካሄድ መንግስት የወሰደው እርምጃ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፡፡ 



‹‹ በድካምና በጥረት ብዙ ጊዜም እንቅልፍ በማጣት፥ በራብና በጥም ብዙ ጊዜም በመጦም፥ በብርድና በራቁትነት ነበርሁ።
የቀረውንም ነገር ሳልቆጥር፥ ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው።››
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11፤27-28 

በዚህች አገር የሀይማኖት እኩልነት አለ እንዴ? የሀይማኖት መቻቻል እያሉ ጆሯችንን ያደነቁሩናል እነርሱን እኛ ቻልናቸው እንጂ ፤ መቼ እኛን ቻሉን ?

‹‹እግዚአብሔር ቤተክርስትያናችንን ይጠብቅ››






7 comments:

  1. በእውነት በዚህች አገር የሀይማኖት እኩልነት አለ እንዴ?

    እነሱ ቤተክርስቲያንን ሲያፈርሱ የኛስ ዝምታ ለምን ይሆን?

    ReplyDelete
  2. እስካሁን ድረስ በጅማ ፤ በስልጤ ዞኖች ፤ በምስራቅ ሐረርጌ እና አንዳንድ አካባቢዎች ብዙ አብያተክርስትያናትን አፍርሰዋል ፤ ንፁሀን ዲያቆናትን ፤ቀሳውስትን ፤ ምዕመናንን በሰይፍ ቀልተዋችዋል ፤ ደማቸውም በቅዳሴ ሰዓት ከመንበሩ ፊት አፍስሰዋል ፤ ለዚህ ሁሉ ህገወጥ አካሄድ መንግስት የወሰደው እርምጃ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፡፡

    ReplyDelete
  3. be'ewinet yehayimanot mechachal yelem ale lemilun degimo melisachin binorima noro yih neger balitedegeme neber
    menigisitis lemin zim yilal? egnas silemin zim alin? yih yene tiyake new
    abune shinoda endetenagerut'egiziabiher and ken yisemanal esun enitebikalen' endalut kesew minim endemanagegn eyawekin silehone egnam yihininu wede amilak enasasibalen

    ReplyDelete
  4. Patriarch, Papasat, Diyqonat, geleltegna, sedetegn ye bete keristian sewoch b/keristanachewen sizebetubat man yewichi telat liyakebrilachew / liferalachew new yemifelegut. Any way the real Christians suffering and sacrificing their lives now by internal and external tekulawoch are considered to be semaetat. There is no deference between these kinds of muslims, our own church menafikan, careless patriarch, scared or fearful papasat and memenan. Government? What government we talking about? All Ethiopians are surviving per the Grace and protection of GOD. We don't expect any thing from the so called Government. We already saw everybody. Nobody cares for the real Ethiopians. It is time for more fasting, prayer and receiving more suffering, which the final result being chosen to be on the right side of GOD (JESUS CHRIST) in heaven. Children of the real Orthodox don’t worry; keep up your Spirit even higher than before. It is known fact that the government and your church higher position people will take your money and property until the end of their short life time.

    ReplyDelete
  5. This kind of action is never expected to end unless we all the christian community strongly request the insane government to give equal rights for our church. Otherwise there is nothing that should pull us backwards than going to suffer whatever kind of sacrifice. lets go to change the situation or die for our church.

    ReplyDelete
  6. Mengist alebat bemitibal hager endih yale giff? Betekihnetum betemengstm betsere krstian sewoch teyzo mekerachinen ayen gobez eninesa!

    ReplyDelete
  7. እባካችሁ እውነተኛ አማኞች እንሁን፡፡ አብዛኛውን ጊዜ የምትጽፏቸው ጽሑፎች ከሰላም ይልቅ ጦርነትን የሚጋብዙ/የሚቀሰቅሱ ናቸው፡፡ ለምን በንጹህ ልባችን ፈጣሪያችንን አናመልክም፡፡ እኔ የእስልምና ሐይማኖት ተከታይ ነኝ፡ ሐይማኖታዊ ግዴታዎቼን በአግባቡ እወጣለሁ፡፡ በጣም የምወዳቸው ኦርቶዶክስ ክርስቲያን ጓደኞችና የሥራ ባልደረቦች አሉኝ፡፡ የእናንተ ዘገባ እኛን ያራርቃል እንጂ ለማንም እይጠቅምም፡፡ ሐይማኖተኛ ሰው በጣም ሐቀኛ መሆን አለበት፡፡ ሁሉንም የሰው ልጅ አንድ አምላክ ለአንድ አላማ እስከፈጠረ ድረስ ሁሉንም እኩል እንይ፡፡ በተለይ ፍትሕዊ እንሁን ከጦርነት ይልቅ የሰላም አመባሳደሮች እንሁን፡፡
    ወደ ዋናው አርዕስት ልመለስና ከላይ የተጠቀሰው ቦታ ላይ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ቤተክርስትያን አልነበረም፡፡ ለዚህ እኔው ራሴ ምስክር ነኝ፡፡ ቦታው የአንድ ድርጅት የጠጠርና ብሎኬት ማምረቻ ነበር ስላላዋጣው ተወው፡፡ (ድርጅቱ ከተዘጋ ሁለት ዓመት አይሞላውም)፡፡

    ሁለተኛው ነጥብ እዚያ አካባቢ ክርስቲያን የለም እኮ ቤተክርስቲያን ለምን አስፈለገ፡፡ ለምን ቤተክርስቲያን አጥተው ለተቸገሩ ወረዳዎች እይሰራላቸውም፡፡ እንደኔ እምነት ይህ ንቀትና ጸብ አጫሪነት ነው፡፡

    ሦስተኛው ነጥብ ቤቱ የፈረሰው በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ነው፡፡ በአካባቢው ክርስቲያን ስለሌለ ከሌላ አካባቢ የተውጣጡ ክርስቲያኖች አፍራሽ ግብረ ኃይሉን በማባረራቸው የቅበትና የአካባቢዋ ሕዝብ በንዴት ሄዶ ነው ያፈረሰው፡፡

    በመጨረሻም ሁላችንም ሟቾች ነን ለምን ለግል ጥቅማችን ብለን ተራውን ሕዝብ እንዋሻለን፡፡ ውሸት ሐራም ነው፡፡
    እውነተኛ አማኝ እምነቱን ለሰው ያስተምራል እንጂ ሌላውን እያጥላላና ግርግር እየፈጠረ እድሜውን አያራዝምም፡፡

    ReplyDelete