Thursday, August 25, 2011

ከእግዚአብሔር በታች ብንፈርድስ?


by Wendemsesha Ayele Kesis 


ነሐሴ ስምንት ተአምረኛ ሆናብኛለች። ወልቂጤ ከተማ ውሎዬን አጠናቅቄ ለጠዋት ሥራ ሰነዶችን በሶፍት ኮፒ ሳዘጋጅ ባደርኩበት ሠፈር ጩኸት ሰማሁ፤ የምሽት ጩኸቶች ምክንያታቸው ስለሚያደናግር ብዙ ጊዜም ስለማያስደስቱ ወጥቶ ማጣራቱን አልፈለግሁም፤ ባለሁበት ሳዳምጥ ቆይቼ ድምጹ ከሠፈሬ ሲርቅ ወደሥራዬ ተመለስኩ። 
ጥዋት ግን ከተማው ሲደናበር፣ ሲደናገጥ፣ ለመስማትም ለመናገርም ሲሳቀቅ አየሁ፤ በምሽት የመኪና አደጋ የሁለት ሰዎችን አሰቃቂ አሟሟት ጨምሮ ፮ ሰዎች አርፈው፣ ቀሪዎቹ ወደ ሆስፒታል መሄድ ስላለባቸው ሂደው ሌሎቹ ሲቀበሩ ምሽት ላይ ደግሞ ሁለቱ መሞታቸው ተሰማ። 

በቀብር ስነ-ሥርዓቱም ላይ «በረከቱን አፍሰው ሲመለሱ ሌላ ነገር ሳያረክሳቸው አላህ ወሰዳቸው፤ እናም ...» የሚል ማጽናኛ ተነገረ። ከወልቂጤና አካባቢው ተጠራርተው የሄዱ ባለጸጎች የበዙበት ምሁራንንና ነጋዴዎችን ያካተተ የአንድ መለስተኛ አውቶቡስና አንድ ዘመናዊ ሚኒባስ ተጓዥ ቡድን የአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከሉን የሙስሊሙን ማኅበረሰብ ቅርሶችና ታሪክ የሚያስተዋውቅ መርሐ ግብር በጋራ ታድሞ ለመመለስ ወስነው ቆይተዋል፤ እናም ነሐሴ ፰ ጠዋት ሲነሡ የተዋዋሉት ሚኒባስ ሾፌሩም ባለቤቱም ክርስቲያን ኖሮ «ሀዲስ ክፈትልን፣ ስዕሎችን አንሣልን»ሲባል ወደ ባለቤቱ «ምን ላድርግ? እኔ አላነሣም ስላቸው ሂሳባችንን መልስልን አሉኝ» አለ፤ የባለቤቱን ትእዛዝ ለመስማት፤ ባለቤትም ገንዘቡ ይቅርብኝ፤ የእመቤቴን ስዕል ከመኪናዬ ላይ አላነሣም ብሎ እርፍ። ገንዘባቸው ተመለሰ፣ ትርፍ በተናገሩት ሃይማኖትን ያንቋሸሸ ንግግር ተቀያይመው ሌላ የሙስሊም መኪና ፍለጋ ቀጠለ፣ ተሳካ፤ ሹፌሩ ግን ክርስቲያን። 

በጠዋት አዲስ አበባ ተኬደ፣ እዚያው ተውሎ ሲመሽም የመልስ ጉዞም ተጀመረ። የታደሙት ክርስቲያኖች «ኤግዚቢሽኑ የሃይማኖት ትንኮሳ ይታይበት ነበረ» ሲሉኝ «ኤግዚቢሽኑን የከፈቱት ሚኒስትሩ፣ ቦታው መንግሥት ያለበት አዲስ አበባ፣ ለምን በማስረጃ አትቃወምም ነበረ?» አልኩት አንዱን። 

ሚኒባሶች ለጉዞ ችኮላ እንደሚያመቹ ሁሉ የስጋቶቻችንም ጥግ ናቸው። መብራት አላግባብ የሚያበራበትን ከፊት የሚመጣ መኪና ሲማጸን አልሰማ ያለው ሾፌር ዳሬን ይዤ እሄዳለሁ ሲል ዕይታው በቂ አልነበረምና ዳሩን ሳይዝ ከቆመ መኪና ጋር ተላትሞ ምሽት ላይ የሰማሁትን ሰቆቃ ከሠተው፤ ሾፌሩን ደግሞ የደህንነት ቀበቶው ጎትቶት፣ ኤየር ባጉ ገፍቶት፣ ፈጣሪም ረድቶት ጭረትም ሳይደርስበት ተረፈ። 

ትኩረት ያልሰጠሁትን ዜና ውጬ ከሳምንት በኋላ ጅማ ስገባ በዴዶ ወረዳ ሰው ገድለሀል ተብለው ያለ ሕግ ቁልቁል ተሰቅለው የተገረፉትና ለወራት በወንጀል ተጠርጥረው በሕጋዊ ሂደት የታሠሩት ቄስ በፍርድ ቤት በነጻ ተሰናብተው መፈታታቸው ያስደሰታቸውና ይህን ጥረት ሲያደርጉ የነበሩት ምእመናን ከሊቀጳጳሱ ጋር እየተመራረቁ ትዝታዎቻቸውን አካፈሉን። 

በጎማ ወረዳ /አጋሮና አካባቢው/ ዳኝነት ሲጓደል ፈጣሪ ሲፈርድ፣ የ፺፱ኙ መከራ ጊዜ ተጠርጣሪዎችን ለማስለቀቅ በሐሰት መስክረዋል ተብለው የሚታሙና በምስክርነታቸውም በወንጀል የተጠረጠሩትን ነጻ ያስወጡት የአጋሮ ተጓዦች ፱ኙ በሚኒባስ ማለቃቸው፣ በዚሁ ዓመት የመስቀል ደመራ ላይ ጠብ የጫሩትና ከክሳቸው በነጻ የተሰናበቱት አባትና ልጅ ዛፍ ሥር ጫት ሲቅሙ በመብረቅ እዚያው ደርቀው ሲቀሩ፣ ከሞቱት ፮ቱ ሰማዕታት ሌላ አይተርፉም የተባሉ ፲፱ ቦታና ከዚያም በላይ በስለት የተጨቀጨቁት ሕያው ምስክሮች በሚገርም ሁኔታ ወደሙሉ ጤንነት ሲመለሱ ወዘተ... 

ሌላም ሌላም የፈጣሪን ፍርድ አስታወሱን፤ እኔም ብከትበውስ አልኩኝ። 

«ፈጣሪ ፈረደባቸው» የሚሉ ክርስቲያኖች እንዳሉ ሁሉ ሙስሊሙ ወገኖቻችን «አላህ ጠራቸው» ብለዋል። ታዲያ በዕውቀትና በሹመት ለዳኝነት ብንንጠራራና የማያዋጣውን መንገድ ቀድመን «እንደሚያስቀስፍ»፣ ሲሆንም ደግሞ እንዲማሩበት «ምክር እዝናት» እንዲሆን ብንዘግበውና ወደ አእምሯቸው የሚመለሱትን ብንረዳስ ጥቂት የፍርዱን ሥርዓት የምናግዝ አይመስላችሁም? ልማቱንም ጥፋቱንም «በረከት» ተብሎ እንዳይተረጎም፣ የሕይወትንም ጥሪ ላለማድመጥ የመውጊያውን ብረት እንዳይቃወሙ ብንነግራቸውስ? እስኪ ለማንኛውም ተጨማሪ የፈጣሪን ፍርድ ዘርዝሩ፤ እንማርበት፣ «እናመስግንበት»?!

4 comments:

  1. yegermal cftari gar mtagele

    ReplyDelete
  2. betam yemigerm tarik new! oh amlake ante lezewetr yetemesegenk neh!!! manim sirahn liankuashish weym lidebk aychalewm

    ReplyDelete
  3. God always with us and he is not late. Dear Brothers and sisters I would like to tell u ... be careful ... we need to keep talking the truth and everyone has to learn from others but I don't think they do. Miheretu yebeza meatu yerak adel yegna amelak but he is always patient of doing what they expect. He has time to do. Semaet yehonu wogenochachi bereketachew kegna gar yihun.

    ReplyDelete
  4. Betam yigermal, this is amazing...God has given his decision but what amazes me is, what happen to some of our muslim brothers and sisters? what is their kuran say? we need to investigate that and exclude some jihadists, who are covered under the name of Muslim. Christians believe that that loving one another is a part of our spiritual journey. Government has to work for Muslim and christian brotherhood...now a days things are in a bad shape. We have to change this, thanks for posting

    ReplyDelete