Monday, November 14, 2011

የአቡነ ፋኑኤል ደጋፊዎች Branch ቤተክርስትያን በመክፈት ስራቸውን ጀምረዋል

  • አቡነ ፋኑኤል እንደ ልማዳቸው በቅርብ ቀናት ቦታው ድረስ በመሄድ ይባርኩላቸዋል ተብሎ ይጠበቃል 
  • ‹‹እንደፈለግን ቤተክርስትያናትን መክፈት እንችላለን በአሜሪካን ሀገር ነው ያለነው ማንም ሊከለክለን አይችልም ›› 
  • ‹‹ነገር ግን ሁሉ በአግባብና በሥርዓት ይሁን። ›› 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1440
    ቀሲስ ኢስሃቅ እና ቀሲስ አቡኑ Branch Manager
    ". . .እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ። የሰው ልጅ ሆይ፥ ልብ አድርግ ስለ እግዚአብሔርም ቤት ሥርዓትና ሕግ ሁሉ የምናገርህን ሁሉ በዓይንህ ተመልከት በጆሮህም ስማ የቤቱንም መግቢያ የመቅደሱንም መውጫ ሁሉ ልብ አድርግ። . . ."
    ትንቢተ ሕዝቅኤል ፵፬ ፥ ፭


    በቅርቡ በተጠናቀቀው የሲኖዶስ ስብሰባ ላይ ብፁእ አቡነ ማርቆስ ‹‹እርስዎ ስልጣነ ክህነት የሚሰጡት ማን ፈቅዶሎት ነው›› በማለት አቡነ ፋኑኤልን ሲጠይቁ ‹‹እኔን ለምን ትወቅሱኛላችሁ ያዘዙኝ ፓትርያርኩ ናቸው››  ብለው ትዕዛዝ ከየት እንደተቀበሉ ለሲኖዶሱ ተናግረው ነበር ፡፡ ያገሬ ሰው ‹‹አሳ የሚገማው ከወደ ጭንቅላቱ ነው›› ይላል፡፡ አሁንም የቤተክርስትያናችን ስርአቷ እየተጣሰ ያለው በአባ ጳውሎስ አማካኝነት ነው ፡፡ እኛ እስከመቼ እኝህን አባት እንታገሳችዋለን ? ለልጆቻችንስ እኛ ጠብቀን ያላስጠበቅነውን እምነታችንን ምን እንዲያደርጉት ነው የምናስረክባቸው ?  እኛ ያልኖርንበትን እንዴት ልጆቻችን ይኖሩበታል? እስከ አሁን ድረስ የተፈጠረው ችግር ቀላል ባይሆንም አሁን ግን ብሷል ፤ መልኩንም ቀይሯል ፤ ምንድነው የምንጠብቀው ? ቤታችንን እኮ የመናፍቅ አዳራሽ አደረጉብን፤ ጌታችንና መድሀኒታችን እየሱስ ክርስቶስ በደሙ የዋጃት መሆኗን እያስረሱን እኮ ነው ፤ የአቡነ ፋኑኤል ቡድን ስራውን Branch በመክፈት በአሜሪካ ላይ ጀምሯል ፡፡ በጣም ትልቅ ስራ እየሰሩ የነበሩትን ብፁእ አቡነ አብርሀምን አንስተው ጥቅመኛውን ትዕዛዛቸውን ያለመሸራረፍ የሚያከናውኑላቸውን አቡነ ፋኑኤልን ለቦታው ይመጥናሉ ብለው ሊልኩ ነው፡፡ ከአሁን በኋላ የሚፈጠረውን ነገር ለማሰብ ቀላል ይመስለኛል ፡፡ ነጋሪም ሊያሻን አይገባም ፤ በቅርብ ቀናት ከሀዋሳው የሚብስ ነገር እንደሚፈጠር አትጠራጠሩ፡፡ ለዚህ ሁሉ ተጠያቂው አቡነ ጳውሎስ ናቸው ፡፡ 


    ‹‹ወንድሞች ሆይ፥ እንመክራችኋለን፤ ያለ ሥርዓት የሚሄዱትን ገሥጹአቸው፤ ›› 
    1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 514
    አቡነ ፋኑኤል በአቡነ ጳውሎስ ትዕዛዝ በሰሜን አሜሪካ ከወራት በፊት ያለ አህጉረ ስብከታቸው ለአራት አጥቢያዎች ሥልጣነ ክህነት በመስጠትና አዲስ ቤተ ክርስቲያንን በመባረክ ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን ከመጣሳቸውም በላይ ከቤተ ክርስቲያኒቱ ማእከላዊ መዋቅር እና አሠራር ባፈነገጠ መልኩ በሰሜን አሜሪካ እየተስፋፋ ለመጣው የገለልተኝነት አካሄድ ሽፋን መስጠታቸውን በመጥቀስ ድርጊታቸውን ትክክል አይደሉም ተብለው በቅዱስ ሲኖዶስ ሲገሰፁ እጃቸውን ወደ አቡነ ጳውሎስ ነበር የቀሰሩት፡፡

    በሰሜን አሜሪካ ቨርጂኒያ ግዛት ልዩ ስሙ Baily Cross Road በሚባል አካባቢ አዲስ የገለልተኛ ክርስቲያናትን በመክፈት አገልግሎት እየሰጠን ነው ብለው የሚሉት ሁለት የአሜሪካን ካሕናት ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ውጪ ፤ ያለ ሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ እውቅና ፣ ያለ ሊቀ ጳጳስ ቡራኬ ፤ እንደፈለግን  ቤተክርስትያናትን መክፈት እንችላለን  በአሜሪካን ሀገር ነው ያለነው ማንም ሊከለክለን አይችልም በሚል ቤተ ክርስቲያን በዘፈቀደ ከፍተው ኑ እና እኛ ጋር አስቀድሱ  ብለው ባለፈው ቅዳሜ አገልግሎት መስጠት ጀምረናል  በማለት ሕዝቡን ሲያዋክቡ ሰንብተዋል። በልዩ ስሙ "ቤሊ ክሮስ ሮድ" በሚባለው አካባቢ የከፈቱት  ቤተ ክርስቲያን ከወዲሁ ትልቅ የሕብን ቁጣ ሳያስነሳባቸው እንደማይቀር ተገምቷል። ተከፈተ የተባለው ቤተክርስትያን በቅርብ ቀን አቡነ ፋኑኤል እንደሚባርኩላቸው ይጠበቃል፡፡
    የአሜሪካው የአቡነ ፋኑኤል ቡድን 
    (ሀዋሳ Part 2 ለመስራት የተዘጋጀው ስብስብ)


    ፩ኛ/ ቀሲስ አቡኑ ማሞ
    ፪ኛ/ ቀሲስ ኢስሃቅ 

    እንደሚታወቀው ቀሲስ አቡኑ ከዚህ በፊት በአቡነ ፋኑኤል፣ በአባ ሰረቀ፣ እንዲሁም ኃይለጊዮርጊስ ጥላሁን አስተባባሪነት ለተጠራ የገለልተኛ አስተዳደር ስር ላሉ አብያተ ክርስቲያናት በነበረው ስብሰባ ላይ ቀሲስ አቡኑ ለዚህ ስብስብ "እስከ ሕይወት መሥዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ነን" በማለት የአላማ አንድነታቸውን አሳይተዋል። ከዚህ በተጨማሪ ከዚህ በፊት በሊቀ መምዕራን ቀሲስ አማረ ካሳዪ አማካኝነት ለቅዱስ ሲኖዶስ በተላከ ደብዳቤ ላይ በገለልተኛ አስተዳደር ስር ያሉት ካሕናትን አስተባብረው ፊርማ አስፈርመው በብፁዕ አቡነ አብረሃም ላይ ክስ ካቀረቡት ቀንደኛ የገለልተኛ አቀንቃኞች ዋነኞቹ እነዚህ ካህናት እንደሆኑ ተጠቁሟል። 


    ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እስከ ዛሬ ድረስ ሥርዓቷ፣ ትውፊቷ፣ ቀኖናዋ እና ዶግማዋ ሲጣስ ሲበረዝ እንዲሁም ሲሻር የነበረው በቤተ ክርስቲያኒቷ ሞገስ ባገኙ፣ የክብር ወንበር የተሳበላቸው ለጥቅማቸው እንጂ ለነገው ትውልድ ጨርሶ በማይጨነቁ የጥቅም ሰዎች ካሕናት አገልጋዮቿ ነው፡፡ ለዚህም የመጀመሪያው ምስክሮች እነዚህ ከላይ የምናያቸው ካሕናት ናቸው፣ ቤተ ክርስቲያን አስተምራ ለወግ ለማዕረግ አብቅታ ፤ ድራ ፤ ኩላ ለዚህ ሁሉ ክብር ያበቃቻቸውን ቤተ ክርስቲያን ክደው ሕጓን ወደ ጎን ትተው ከፍቶ ለሌባ እና ለበራዥ መልቀቃቸው እጅግ አሳዛኝ እና ዘግናኝ ድርጊት ነው፣ አሁንም እነዚህ ሰዎች ሥራቸውን እየተከታተልን በቅርብ ባሉ ተወካዮቻቸን ልናቀርብ ቃል እየገባን ለካሕናቱም ልቦና እንዲሰጣቸው እንጸልያለን። በመጨረሻም ይህ ተከፈተ የተባለው ቤተክርስትያን በማን ትዕዛዝ እንደተከፈተ አጣርተን እንነግራችዋለን፡፡


    ለአቡነ ፋኑኤል
    ‹‹እኔስ አሜሪካዊ ነኝ ይብላልኝ ለናንተ ›› አቡነ ፋኑኤል ከሀዋሳ ሲባረሩ የተናገሩት፡፡ ፍትሀ ነገስቱን አንበውታል ብዬ አልጠብቅም እኛ አንብበን ምን እንደሚል እንገርዎ ፡፡ ሠለስቱ ምዕት በቅኖና ቤተ ክርስቲያን እንዲህ ብለው ወስነዋል።
    «በአገሩ መስፋት መጥበብ በሕዝብ ማነስና መብዛት ምክንያት ኤጲስ ቆጶስነት ከተሾመበት አገር ወጥቶ ወደ ሌላ አገር አይሂድ ፤ ከእርስስዋ የተሻለውን ሊፈልግ አይገባም ፤ ይህ ለእርሱ አይገባምና ለሰው ሁሉ ድርሻው ከእግዚአብሔር ተሰጥቶታል እንጂ ፤ ይህ ከሕዝባዊያን ወገን ሚስት ያገቡ ሰዎችን ይመስላል። ያለዝሙት ምክንያት ሰው ከሚስቱ ቢሰነካከል ከእርስዋ በምትበልጥ ቢለውጣትም ቢፈልግ እርሱ በጣም በደለኛ ነው። ከአገራቸው የተሻለ አገርን የሚፈልጉ ኤጲስ ቆጶሳት ካሕናትም እንዲህ ናቸው»። ፍትሐ ነገስት አንቀጽ 5ቁጥር 158 

    በእንደዚህ አይነት ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን በመዳፈር ያለሀገረ ስብከታቸው በሌላ ጳጳሳ ሀገረ ስብከት እየገቡ ሥለጣነ ክህነትን የሚሰጡ ጳጳሳት ሥርዓት በማፈረሳቸውና በመጣሳቸው የእነርሱም ሆነ ክህነት የሰጡት ግለሰብ ሥልጣን የተሻረ ነው። ይህንንም ይኽው ራሱ ፍትሐ ነገስት
    «ባለ ሀገረ ስብከቱ ኤጲስ ቆጶስ ሳይፈቅድለት ከሀገረ ስብከቱ ወጭ ካህንን የሾመ ቢኖር ይሻር,,,በራሱ ፈቃድ ይህንን ቢያደርግ የሾማቸው ሰዎች ክህነት ይቅር ከክህነቱም ይሻር በማለት በአባቶቻችን ውሳኔ ተላልፎል»። ፍት ነገ አንቀጽ 5 ቁጥ 194 በዚህ ሕግ መሰረት ጳጳሱም ሆኑ ከህነት ተቀብለናል ያሉ ግለሰቦች ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ጥሰዋል።
    የቤተ ክርስቲያናችንን ትንሣኤ ያሳየን አሜን 
    ቸር ወሬ ያሰማን

    8 comments:

    1. amen yaseman!!!
      kenanite gena bizu neger enitebikalen.

      ReplyDelete
    2. sent kidusan abatochen yaferach betkristian.....lehodachew baderu mechawecha honech....abatachen teklye,gebremenfeskidus menew zem alachu.....demo zem atelum yegize guday new

      ReplyDelete
    3. betekrstianen lemgedel yetenesachehu hulu leb yestachehu geleltegna nen belchehu yenegerachunten memen ahun men honenal letelut new abune pawlosen enji synodosen ankebelm letelut new mechem yehe memen ferdobetal egziabhern sayhon enanten yemiketelw degmo kesis amare astaraki honew ethiopia hedu alu erso meche tarekuna new aye '' eraswa aktenesach letaquakum hedech alu'' degmos aba mezan erso aydelum yehaymanot hesese alachew belew kemebetachen kerso yegel dergit yabareruachew tadya erso wedeza hedu weyes esachew metu becha enen yemigermegne ber zegtachehu begziaber lay stedoltu menorun enkuan yemetawku ayemeslgenm ,lelit endet enkelf yewsdatual yemot helina kelelachu besteker helina yalew sew aytegnam endihu lefachehu engi betekrstian tebaki alat leb yestachehu emebetachen besmu yeminegduten tagalt

      ReplyDelete
    4. በስመ አብ ወወልድ ወመነፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
      ባለፈው ሳምንት በአንድ አድርገን ብሎግ ያነበብነው ከመንፈሳዊነት የወጣ ቃል ተሰንዝሮአል አረ በተሰቀለው አምላክና ሰለ ቅድስት ቤተ ክርስቲአንያን ብላችሁ የሆነውነ ያልሁነውን አትቅባጥሩ በዚህ ንግግራችሁ ስንት ሰው አንደምታሰናክሉ አልተረዳችሁም ይመስለኛል ያልሰራውና ያላደረጉትን የሰውን ስም እያጠፋችሁ ለምን ስውን ታሳዝናላችሁ ጠላታችን ሰይጣን እኳን እንደዚህ አማኞችን ከሶ አያውቅም ሰይጣን ስመ አምላክ ሲጠሩበት መስቀል ሲያማትቡበት ወደአማኞች አይቀርብም በገዳም ያሉ ቅዱሳን አባቶቻችንም በስባአኤ ጊዜ ለግዜው እየፈተነ ያስቸግራቸዋል ግን ከጥቂት ሳምንታትና ወራት በኋላ ፈተናውን ያቆማል እናንተ ግን ክማህፀን ጀምሮ የተቁራኛችሁት ነው የምትመስሉት አሁንም ስለ ቤት ክርስቲያልን አምላክ እባካችሁ የሰው ስም ማጥፋትና መክሰስ ይቅርባችሁ አምላክ እኮ እንደየ ሥራችን ዋጋን ይሠጠናል ለምንድን ነው የአምላክን ቦታና ፍርዱን የምትወስዱበት አምላክን ሳይቀር ከሥልጣኑ ሻራችሁት ማለት እናንተ ያሰደቃችሁት ጻድቅ ነው እናንተ የኮነናችሁት ኃጥእ ነው እያላችሁ አስቸገራችሁት እኛም እኮ እያወቅናችሁ ዝም ብለን ያለነው ፍርዱን ለአምላክ ሠጥተን ነው እንጂ ማን መሆናችሁን እናቃለን ዲያቆኖቻችሁ፤ካህንቶቻችሁ ፤ መነኮሳቻችሁ፤ ጳጳሶቻችሁ ፈረሶች መሆናቸውን እናቃለን እነሱንም ያሳታችኋቸው እናንተ ናችሁ ከሳቱ በኋላ ንስሐ እንዳይገቡ እናጋልጣችኋለን እያላችሁ እንደምታስፈራሩ ነው ይሀን ስል ማኅበራችሁ ነው አሁንም ይቅርባችሁ እስከ አሁን የምትሠሩትን ይቅር ይላችኋል ከእንግዲህ መልካም ነገር ማሠብ መልካም ነገር መናገር መልካም ሥራ መራት ጀምሩ ለዚም አምላከ አበው ይርዳችሁ
      ሰለ ወላዲተ አምላክ ብዬ እለምናችሁኋለሁ እግዚአብሔር ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እና ተዋህዶን ይጠብቅ አሜን

      ReplyDelete
    5. bseme ab wewelid wemenifes kidus ahadu amilak amen

      KESIHUFU MINIM YEMIYANIS NEGER ALAGENEHUM MINALIBATIM TEHADISO KEMIBALUT YEBASE SEWUN YEIYASENAKIL SIHUF NEW YEMITISIFUT

      ABUNE FANUELIN KONINACHIHU ABUNE ABIRIHAMIN SITAMOGISU TAZEBIKUWACHIHU MINIM BIHON KIRISITIYANOCH KEHONIN EIGIZIABIHERIN TINISHIM BIHON MEFIRAT YASIFELIGAL

      ABUNE ABIRIHAMIM EIKO BEGELELITENA BYTEKIRISITIYAN LEMIGENU DIYAKONAT KIHINET SETEWAL YALEHAGERESIBIKETACHEW BETEKIRISITIYAN BARIKEW KEFITEWAL KEMINIM BELAYI DEGIMO FISUM ZERENA NACHEW KETESHOMU JEMIRO KE20 YEMIBELITU WEGENOCHACHEWUN WEDE AMERICA WESIDEWAL EISACHEWU EIKO BETEKIRISITIYAN YEMIKEFITUT LEZEMEDOCHACHEW YESIRA EIDIL EIYEFETERU NEW ADAME BEMAYAGEBAW ZIM BILO YINICHACHAL EIWUNET LEBETEKIRISITIYAN YEMINASIB KEHONE HULUNIM MEWUKES KALEBIN EINIWUKES

      BENEGERACHIN LAYI ABUNE FANUELIM HONU ABUNE ABIRIHAM EIDIME LEABUNE PAWULOS EINIJI YIHIN TALAK MAEIREG LEMAGINET YEMIYABEKA EIWUKETIM HONE MENIFESAWI TIRUFAT NOROWACHEW AYIDELEM ABUNE FANUELIM KEAMERICA YIZEWUT YEHEDUTIN DOLLAR SETITEW NEW ABUNE ABIRIHAMIM YERAGUEL BIRR NEW LEZIH YABEKACHEW SILEZIH BEMANAWUKEW BECHIFIN YEGILESEBOCH TIFOZO KEMEHON BEEIMINETACHIN SENITEN BININOR YEMISHAL YIMESILENAL

      MILAKE KIDUSAN BEGOWUN ZEMEN YAMITALIN

      ReplyDelete
    6. እናንተ ምን አይነት ሰዎች ናችሁ እረእባካችሁ ገዚአብሄርን ፍሩ አባቶችን አክብሩ እንዲህ አትዝቀጡ ይሄ ዕንቁ መጽሄት የኦርቶዶክስ አማኝ ነው ወይስ ደግሞ ገበያሊያፈላልግና አልሸጥ ለውን መጽሄት እዚህ ሊሸጥ ነው የመጣው የታሪክ ተወቃሽ ከመሆን ያድነን ትልቅ ወንጀል እየተሰራ ነው ማህበሩ ቦታ ተሰቶት እየበጠበጠ ነው ከቤተክርሲቲያኑዋ ላይ እጃችሁን አንሱ ‹‹ እግዚያብሄር ኢትዮጵያን ባርክ››

      ReplyDelete
    7. ያበደ ውሻ ለመናከስ ድንበር የለውም የሚናከሰውም ለመናከስ ፈልጐ ሳይሆን
      በሽታው የፈጠረበት ተጸእኖ ነው ያገኘኝ ሁሉ ይገለኛል ብሎ ስለሚያሰብ ወገኑን እንኳ
      አይለይም ። ማህበራችሁ እንደነ ለእናተም የማየመለስ መሆኑን ዳንኤል ክብረትን መጠየቅ ይቀላል ፡ ማን ያርዳ ማን ያርዳ ማን ያርዳ የነበረ ፣፣፣፣፣፣
      ይህን ካልተቀበላችሁ ከሙታን እንኳ ቢመጡ አታምኑምና ከዛሬ ይልቅ የነጋችሁ ይከፋል ፣፣
      እግዚአብሔር ለጦርነት የሰበሰባችሁትን የሚሰኪን ወጣቶችን ገንዘብ ከእጃችሁ ይረከባል ፡፡፡፡የውድቀታችሁም ዋዜማ አልቆ ወደ በአል አከባበሩ እየገባችሁ ነው

      ReplyDelete
    8. ሀ ሁ ሂ ሃ፡፡፡፡፡፡፡፡ሆ

      ReplyDelete