Tuesday, November 29, 2011

የአለቃ አያሌው ታምሩ መፃህፍት እንዲቃጠሉ ተጠየቀ


  • የሚገርመው መፅሀፉ እንዲቃጠል የተጠየቀው በልጆቻቸው አማካኝነት ነው፡፡

(አንድ አድርገን ፤ ህዳር 18 2004 ዓ.ም) በኢትዮጵያ ኦርዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የሊቃውንት ጉባኤ ሰብሳቢ እና በርቱዕ አንደበታቸው እጅግ ተደማጭና ተወዳጅ የነበሩት የታላቁ ሊቅ አለቃ አያሌው መፃህፍት እንዲቃጠሉ ተጠየቀ፡፡ ለሐገርና ለወገን የሚጠቅሙ አያሌ መፅሀፍትን የተረጎሙ እና ያሳተሙ ሊቁ አለቃ አያሌው ታምሩ ከሶስት ሺህ ዘመናት በላይ ለሀገራችን ኢትዮጵያ ልዕልና ከፍተኛ ስተዋፅኦ ባበረከተችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያ ውስጥ ዛሬ የሚታየውን የአስተዳደርና ሀይማኖታዊ ችግር ከማንም በፊት አስቀድሞ በግልፅ ሲቃወሙና ሲያወግዙ የኖሩ ናቸው፡፡


‹‹ሰማዕት ዘእንበለ ደም -ደም አልባው ሰማዕት›› ሊቁ አለቃ አያሌው ታምሩ ከ50 ዓመታት በላይ ከአገለገሉበት ቤተክርስትያን  እውነት በመናገራቸው ብቻ በግፍ ከተባረሩ በኋላ ይህንኑ ተቃውሟቸውንና ሀዋርያዊ ትምህርታቸውን ለመላው ኢትዮጵያ ህዝብ የሚያደርሱት በልዩ ልዩ መገናኛ ብዙሀን እና በተለይም  በነፃው ፕሬስ በኩል እንደነበረ የሚታወስ ነው፡፡

ከ10 ዓመታት በላይ ባለማቋረጥ በልዩ ልዩ ጋዜጦች እና መጽሄቶች የተላለፉትን የሊቁ አለቃ አያሌውን ቃለ መጠይቆች የያዘ ‹‹ ትምህርተ ሐይማኖት›› መፅሀፍ በመታተሙ ምክንያት በአሳታሚው በአቶ ሳሙኤል ሃይሉ እና በአለቃ አያሌው ልጆች መሀል በተፈጠረው ውዝግብ መፅሀፍቱን ተሰብስበው እንዲቃጠሉ ተጠይቋል፡፡ ይህው ውዝግብም የህግ መፍትሔ ያገኝ ዘንድ ጉዳዩ በፍርድ ቤት እየታየ ሲሆን የመፅሀፉ ‹‹ይቃጠልልን›› ጥያቄም የቀረበው ጉዳዩን አስመልክተው የአለቃ አያሌው ልጆች ፍርድ ቤት ባቀረቡት የክስ ቻርጅ ነው፡፡

‹‹ለሐገርና ለህዝብ የሚጠቅሙ እነዚህ መፃህፍት ሊቃጠሉ አይገባም ምንጭ ጠቅሼ ልጆችና ባለቤታቸውን አስፈቅጄ ነው ያሳተምኩት ›› የሚሉት የመፅሀፉ አሳታሚ አቶ ሳሙኤል ሃይሉ ከመፅሀፍቱም ሽያጭም የተገኝውን ገቢ በሙሉ ለቤተሰቡ ማስረከባቸውንና ለዚህም ህጋዊ ማስረጃ ያላቸው መሆኑን እየገለፁ ይገኛሉ::

ለጥቅምና ለስልጣን ብለው ሳይሆን ለሐገር አንድነት እና ለቤተክርስትያቱ ዶግማ ስርዓት መጠበቅ መስዋትዕነትን ለከፈሉ ሊቁ አለቃ አያሌው እስካሁን ድረስ በስማቸው ምንም አይነት መጠሪያ ባልተሰየመበት በዚህ ጊዜ መፅሀፍቶቻቸው እንዲቃጠሉ በገዛ ልጆቻቸው መጠየቁ ብዙ ኢትዮጵያውያንን በእጅጉ አሳዝኗል፡፡

ፍርድ ቤቱ ግራ ቀኙን አይቶ የሚሰጠውን ፍርድ ወደ ፊት ተከታትለን የምናቀርብ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳልን፡፡

6 comments:

  1. please, who have book scan and post the to the people to disqualify this evil sons and .....

    ReplyDelete
  2. Lemhon yehae hasab kesew new wyes kesetan yehae bertu tselot yasfelegwal

    ReplyDelete
  3. ዜና ስትሰራ በችኮላና ቀድሞ ለመገኘት ብቻ የምትጣደፍ ትመስላለህ። ነገርን ከስሩ ውሃን ከጥሩ የሚለውን የአበውን ተረት አልሰማህም መሰለኝ። ያለፉትን ብዙ ጽሁፎችህን አሁን አንስቼ አልጠይቅህም። በዚህ በአለቃ አያሌው ጽሁፍ ላይ ግን ይህንን ላንሳልህ።
    1/ መጽሐፉን ልጆቹ የተቃወሙበት ምክንያት
    2/ መጽሐፉን የሚቃወሙና የሚደግፉ ልጆች ማንነት
    3/ የመጽሐፉን ገቢ የተቀበሉ ቤተሰብ ማንነትና ምክንያት
    4/ ስለመጽሐፉ ክስ የሚቃወም ወይም የሚደግፍ ቤተሰብ ማንነት
    አልተጠቀሰም። ይህን ሳታሳውቅ ስለፍርድ ቤት ውሳኔ እንነግራችኋለን ማለትህ ዜና መስራት ምን እንደሆነ አለማወቅህን ያሳያል።

    ReplyDelete
    Replies
    1. iwunet new 1 mikniyat ale inji ye irasacew Lijoci indihu yikatel ayilum.

      Delete
  4. ከፕሮቴስታንት አስተምሮ ተከትሎ የሚመጣ መቅሰፍት ነው:: እነሱ እየጨፈኑ ሲጸልዩ እና ሲያለቅሱ ይዉላሉ በተስፋፉባቸው ሀገሮች ግን ይህ ችግር እስከቤተ እምነታቸው ደርሷል:: ጀሪ ፎዉለር የተባለ ቱባ ፓስተራቸው ከሜጋ ቸርቹ ሲሰብክ ይውልና ዴኒቨር ጨላማን ተገን እያደረገ በዴኒቨር ከተማ ካለ የጎዳና ላይ ሰው ጋ የተመሳሳይ ጾታ ወሲብ ይፈጽም እንደነበረ የፓስተሩን የውሽት ስብከት በቴሌቪዥን ላይ የተመለከተው እና የሰማው ግብረ ሰዶማዊ ይህን ሰው አውቀዋለሁ ከሳምንት በፊት እንኳ ከኔ ጋ ነበር ሲል ተናግሯል:: ተመልሶ መምጣት የለም እንጅ ቢቻል ኑሮ ያየውን የደረሰበትን ሁሉ ከሄደበት መጥቶ ይነግረን ነበር:: ነገርግን የለም ወደዋናው ቤቱ ሂዷል:: ዋናው ነገር ስግብግብነት፣ ራስ ወዳድነት፣ ገንዘብ አምላኪነት፣ ግብረሰዶማዊነት እና ሌሎችም ከነሱ መስፋፋት ጋ ጎን ለጎን ይስፋፋሉ:: በጌታ ስም የሚያውኩ የዲያቢሎስ ተላኪዎች ናቸው:: በአሜሪካ አንግሊካኖች የግብረሰዶማዊ ጳጳስ ሁሉ አላቸው:: ጰንጤነት ገና ብዙ ያመጣል::

    ReplyDelete
    Replies
    1. እግዚአብሄር ይባርክህ

      Delete