Thursday, November 3, 2011

አነጋጋሪውን ቪሲዲ ማን ለቀቀው?

"የአሮጊቷ ሳራ ልጆች"
"የአሮጊቷ ሳራ ልጆች"
እርግጥ ነው፤ እገሌ የተሐድሶን አጀንዳ እያስፈጸመ ነው፡፡እሺ እገሌስ? እነ እገሌስ ለይቶላቸዋል፤ እነ እገሌስ?….ይኽ ማን ከማን ወገን እንደሆነ ለማወቅ የሚቀርብ የየአካባቢው ጥያቄ ነው፡፡ ይኽ ጥያቄ ተመልሷል፡፡ መላሹ ክፍል ደግሞ ራሳቸው ተጠርጣሪዎቹ ናቸው፡፡ሌላውን ሰው በጥርጣሬ ዓይን መመልከት ይብቃ የተሐድሶ መናፍቃኑ እኛ እንጂ ሌላ አይደለም ብለውናል ሰሞኑን በተለቀቀ VCD::

ሰሞኑን አንድ VCD ተለቋል፡፡ይኽ VCD ማን እንዳዘጋጀው ባይታወቅም ልክ እንደ አዋሳዎቹ ሁለት ቪሲዲዎች ብዙ እውነታዎችን የያዘ ሲሆን በዋነኛነት ጥቅምት 11 ቀን 2004 ዓ.ም. የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች በአዲስ አበባ መንበረ ፓትርያሪክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በተሐድሶ መናፍቃን ላይ ያደረጉትን የተቃውሞ ሰልፍ ያሳያል፡፡
በዚህ ሰልፍ በአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት ከሚገኙ የ131 ሰንበት ት/ቤት ወጣቶች ያላቸውን የደንብ ልብስ(ዩኒፎርም)እና ነጠላ በመልበስ፣በርካቶች ደግሞ በራሳቸው ልብስ በመውጣት ቅዱስ ሲኖዶስ በጥቅምቱ ጉባዔው በተሐድሶ መናፍቃን ላይ እርምጃ እንዲወስድ አሳስበዋል፡፡

ወጣት የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎቹ ተቃውሞአቸውን በአደባባይ ከማሰማታቸው በፊት ቀደም ባሉት ጊዜያት መዋቅራቸውን ጠብቀው ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤትና ጉዳዩ በቀጥታ ለሚመለከታቸው የቤተ ክርስቲያን አካላት የተሐድሶ መናፍቃንን ማንነት የሚያጋልጥ ባለ 261 ገጽ የጽሑፍ ሰነድና 14 የምስል እና የድምጽ(VCD) ሰነድ በማስረጃነት ማቅረባቸው ቢታወቅም አደባባይ ለመውጣት እነዳላሰቡ ሆኖም ግን እነ በጋሻው፣ትዝታው፣አሰግድ፣ናትናኤል፣ያሬድና ሌሎችም የተሐድሶ ሎሌዎች ስማችን ጠፋ፣ መድረክ ተከለከልን፣ ተሐድሶ የሚባል የለም ፣ወዘተ….በማለት በለመዱት የግራ ዐይን የአዞ እንባቸው ሕዝቡን ለማሳሳት ሰልፍ እንወጣለን ብለው በማወጃቸው ምክንያት ወጥተው ተቃውሞአቸውን እንዳሰሙ ለማወቅ ተችሏል፡፡
              
 ይህ የ54 ደቂቃ ጊዜ የሚወስደው ቪሲዲ፦
  • “የዘማሪ” ትዝታው ሳሙኤልን መደብደብና መዋከብ ኋላም       በድንጋጤ ጥግ ላይ ተደብቆ ጥርሱን እየነከሰ መንቀጥቀጥን፣
  • የተሐድሶ መናፍቅ አሰግድ ሳህሉን ተንኮሳና መንቀዥቀዥ ኋላም መደንገጥና መሸማቀቅን፣
  • የ“ዘማሪት” ቅድስት ምትኩንና “ዘማሪት” የትምወርቅን ድፍረትን፣
  • የመናፍቁ ናትናኤል ታምራት በፍርሃት ታጥሮና ጥግ ይዞ መታየትን፣
  • የ“መምህር” ተረፈን የመሃይም ድፍረትና በኋላም ቅሌትና ውርደት፣
  • የሊቀ ካህናት ኃይለ ሥላሴንና የቅ/ማርያም ገዳም አስተዳዳሪ አላዋቂነትና አድርባይነትን፣
  • የአዲስ አበባን ሰንበት ት/ቤቶች በወኔ የታጀበ ጠንካራና የተደራጀ ተቃውሞን፣
  • የቅዱስ ፓትርያርኩን ብስጭትና ወገንተኛነት፣
  • የአዲስ አበባና የፌዴራል ፖሊሶችን የተረጋጋ፣ሕጋዊና ሰላማዊ የጸጥታ ማስተባበር ሥራን፣
  • የአዲስ አበባ ምዕመናንን እውነተኛ የቤተ ክርስቲያን ቅናት ወዘተ…..በአንጻሩ ደግሞ የተሐድሶ መናፍቃንን ድፍረትና አይን አውጣነት ያሳያል፡፡  
        በፊልሙ ላይ የተሐድሶ መናፍቃኑ ከያዟቸው መፈክሮች ውስጥም፦
  • “የክርስቶስ ወንጌል የአገልጋዮችን ስም በማጥፋት አይሰበክም”
  • “ማኅበረ ቅዱሳን ተሐድሶ በሚል ሰበብ ከተጠያቂነት ማምለጥ አይችልም”
  • “ማኅበረ ቅዱሳን ከመንፈሳዊ ኮሌጆች ላይ እጁን ያንሳ” የሚሉት ይገኙባቸዋል፡፡
በሰንበት ት/ቤት ተማሪዎቹ በኩል ደግሞ፦
  • “በቤተ ክርስቲያን የማይታወቁ የሚዲያ መግለጫዎችና የአዳራሽ ጉባዔያትን ሲኖዶስ አንድ ይበልልን፡፡”
  • “ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አትታደስም” የሚሉት ዋነኞቹ ናቸው፡፡
በዚህ አቋምንና አሰላለፍን ማሳያ በሆነው ትዕይንት ላይ ቤተ ክርስቲያን ትታደሳለች፣ማኅበረ ቅዱሳን አይናገረን፣ተሐድሶ የሚባል የለም፡፡ ከሚሉት ወገኖች የሆኑ በርካቶች ወጥተዋል፡፡ እኔ እንኳን የማውቃቸው፦ ከ“ዘማሪያኑ” ትዝታው ሳሙኤል፣የትምወርቅ፣ቅድስት ምትኩ፣ምርትነሽ ጥላሁን፣ሃብታሙ ሽብሩ፣ሐዋዝ ተገኝ፣…..ከ“መምህራን” ናትናኤል ታምራት፣አሰግድ ሣህሉ፣ተረፈ፣ጋሻዬ መላኩ፣ስንታየሁ፣በፈቃዱ፣ታሪኩ አበራ….ነበሩበት፡፡የአዲስ አበባ ምዕመናን “ፍንዳታ”እያሉ የሚጠሯቸው የመነኩሴ ቆብ ያጠለቁ የተሐድሶ መነኮሳትም ነበሩበት፡፡

እነ በጋሻውና ያሬድ አደመ ከመጋረጃው ጀርባ ሆነው ማስተባበርን መርጠዋል፡፡ማንነታቸው እንዳይታወቅ ፊታቸውን በሰፊ መነጽር ለመሸፈን የሞካክሩ ኮረዳዎችም በሰልፉ እንደነበሩ ፊልሙ ያሳያል፡፡
በአጠቃላይ ፊልሙ የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤት ወጣቶች ቤተ ክርስቲያናችን በተሐድሶ መናፍቃን አትወረርም የሚል አገር አቀፍ ብሎም ዓለም አቀፍ የሆነ አጀንዳ ይዘው የታዩበት፤ በአንጻሩ የተሐድሶ መናፍቃኑ ደግሞ በተወካዮቻቸው በእነ “መምህር” ተረፈ በኩል “ጉዳዩ የነፍስ ሀብታችን የሆነች ሃይማኖታችንን ማኅበረ ቅዱሳን ልንጠቃችሁ በማለቱ አቤት ስለማለት”የሚል ሙግት ይዘው የወጡበትን፤የሰንበት ተማሪዎቹ አቤቱታቸውን ቅዱስ ፓትርያርኩን ጨምሮ ብፁዐን ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት በንባብ ካቀረቡ በኋላ እነበጋሻው በወከሉት በተረፈ በኩል አቤቱታቸውን በንባብ ሊያቀርቡ ሲሞክሩ ግን የሰንበት ተማሪዎቹ ሲቃወሙ ፓትርያሪኩ ግን ካልቀረበ ብለው ሲሞግቱ ተቃውሞው ሲበረታባቸው “እዚህ እንዳይነበብ ብትከለክሉም ጉዳዩን ተቀብለነዋል፡፡”ሲሉም ያሳያል፡፡ እነ በጋሻውና ትዝታው በተለመደው የአየር ሰዓታቸው፣ ፣ተሐድሶ የለም በማለት የቁራ ጩኸት በመጮኽ የሚታወቁት ዲ/ን ታሪኩ አበራና በሰሎቹ በየዐውደ ምህረቱ ያስተባብላሉ ተብሎ ሲጠበቅ አፀፋው ግን ከባድ እንደሚሆን ወጣቶቹ እየተናገሩ ነው፡፡እኛም ይኽንን ቪሲዲ ገብርኄራውያን የሚያገኙበትን ሁኔታ ለማመቻቸት የተቻለንን ሁሉ እናደርጋለን፡፡


ስናገኝው ሙሉውን VCD ፖስት እናደርጋለን
‹‹እግዚአብሔር ቤተክርስቲያናችንን ይጠብቅልን››
በፍቅር ሀለፎም fkrhalefom95@gmail.com

4 comments:

  1. please attached it as soon as possible.Fikre keep on ur writing.

    ReplyDelete
  2. egzio bemeheretehe ande adergen.bertu gobezu ayzoachehu.endew yehe aba selama yembal yenufake temeherete yemizera blog sanebe anjete eyetekatele new.yenanten meselune saye dmo etenanalehu ebakachehu beretulen eje endanesete behayemanotache kelde yelm.yaldengele maryam amalagente alem ayedenem

    ReplyDelete
  3. Please post the vcd soon, I have been waiting till now

    ReplyDelete
  4. pless post the VCd or tell to where to found the VCD? d/n Tariku Abera is among said no Tehadiso i don't expect this.

    ReplyDelete