Thursday, December 1, 2011

የወላዲተ አምላክ ድንቅ ተአምር



(አንድ አድርገን ፤ ህዳር 21 2004 ዓ.ም)፡- ዛሬ ፃድቃኔ ማርያም ሄጄ በአይኔ ያየሁትን ተአምር ልፅፍላችሁ ወደድኩኝ፡፡ ቀኑ ቅዳሜ ነው ፤ ሰዎች አብዛኛውን ጊዜ ወደ ፃድቃኔ ለመሄድ የሚነሱበት ቀን ስለሆነ መጀመሪያ የሚወጣው አውቶቡስ እንዳያመልጠን ከባለቤቴ ጋር በጠዋት ነበር አውቶቡስ ተራ የደረስነው ፤ ነገር ግን ሰው እዛ ያደረ ይመስል 12፡00 ላይ አውቶቡሱ ሞልቶ መንቀሳቀስ ጀምሮ ነበር፡፡ ባለቤቴም ‹‹አይ በዚህም ሰዓት ደርሰን አመለጠን ይገርማል ተወው ባክህ እመቤቴ እንደፈቀደች›› አለችኝና ሁለተኛው አውቶቡስ ላይ ገባን፡፡ ይህኛው ደግሞ ቀጥታ ዘላቂ ሰው ስላጣ የመንገድ ሰዎችንም በመጫን ነበር የሞላው፡፡ ጉዞ ወደ ፃድቃኔ ማርያም ፤ ውዳሴዋን ደግመን ጉዞ ጀመርን፡፡ መኪናው ሲያወርድ ፤ ሲጭን 9፡00 አካባቢ  ደብረ ምጥማቅ ደረስን ፤ እዚህ እንውረድና በአቋራጭ እንሂድ ተባብለን ሰላ ድንጋይ ሳንደርስ ወረድን ፡፡ እቃችንን ለአንድ የሀገሬው ሰው አሸክመን አቋራጩን ተያያዝነው ፡፡ ልጁ እንዲህ አለን ‹‹ ዛሬ ግን ማደሪያ የምታገኙ አይመስለኝም በጣም ብዙ ሰው ነው የመጣው አለን›› :: ‹‹ችግር የለውም ውጪ አንጥፈን እናርፋለን ለመተኛት መች መጣን›› አልነው፡፡



ደጇን ስንረግጥ ልጁ ያለው አልቀረ የወንዶች ማረፊያ ሁለቱም አዳራሽ ከአፍ እስከ ገደቡ ሞልቷል ፤ በረንዳውን ላይ ብናይ የበረንዳው ይብሳል ፡፡ የኔን ማረፊያ ውጭ አነንጠፍንና የእሷን ለማየት ወደ ሴቶች ማረፊያ እያቀናን ሳለ ፤ አንዲት መንፈስ ያደረባት ሴት ፤ እጇም እግሯም በሰንሰለት ታስራ እንዲ እያለች የእመቤታችንን ማዳን ትመሰክራለ‹‹ ዛሬ ደግሞ ኪዳነምህረት ድንቅ ነገር ሰርታለች ሂዱነና እዩ›› እያለች ለሰዎች ስትናገር እንደ አጋጣሚ እኔም ሰማሁ፡፡ እሷ የጠቆመችን ቦታ ላይ ስንሄድ አንዲት የ12 ዓመት ህፃን ልጅ እና እህትየዋ አንድ ላይ ቆመው ተመለከትን ፡፡ ጠጋ ብለን ምን ተደርጎላቸው ነው ስል ስጠይቅ ‹‹ የዚች ህፃን አይኗ በራላት›› ሲሉ ነገሩን፡፡ ለኔ የተደረገልኝን ያህል ደነገጥኩኝ፤ በጣምም ደስ አኘኝ፡፡ እህትየዋ የምትይዘውን የምትጨብጠውን ነገር አጥታ ነበር ፡፡ ታናሽ እህቷ የተደረገላትን ነገር እያየች ከአእምሮዋ በላይ ስለሆነ እና ደስታው ፈንቅሏት ታለቅሳለች  ፤ እኛም ገርሞን ማደሪያችንን ትተን ልጅቷ ጋር ረዥም ደቂቃዎች ስለሁኔታ ለመስማት እዛው አረፍ አልን ፡፡ እህትየዋም ሰዎች ጥያቄዎችን ሲጠይቋት እንዲህ አለች ፡-
‹‹ ቤት ውስጥ ከእኩያዎቿ ጋር ስትጫወት የበረንዳ ብረት አይኗን መታት ፤ ለጊዜው ከማበጥ ውጪ ምንም አልሆነም ነበር ፤ ነገር ግን በጊዜ ሂደት አይኗ እያበጠ መጣ ፤ እይታዋንም ጋረዳት ፤ ትምህርቷንም አቋርጣ ለ6ወር ያህል ህክምና ፍለጋ አሉ የተባሉ የአይን ስፔሻሊስቶች ጋር ብራችንን አውጥተን ሄድን ፤ መፍትሄ ግን ሊመጣ የልጅቷም አይን ማየት ግን አልቻለም ፤ ቤተሰባችን ጭንቅ ውስጥ ገባ ፤ በመጨረሻ እመቤቴ እንዳደረገች ታድርጋት ብይ እዚህ ይዣት መጣሁ ዛሬ ሶስተኛ ቀናችን ነው ፤ ለሶስት ቀን ያህል ፤ ጠዋት ተሸክሜአት ጸበል እወስዳታለሁ ፤ እምነቱን ከፀበል ጋር ደባልቄ አይኗ ዙሪያው ላይ እቀባታለሁ ፤ ይህው እናንተ እንደምታዩት እግዚአብሄር ፈቅዶ ዛሬ አይኗ ሊያይ ችሏል›› ብላ ለቅሶ፡፡
‹ሁሉን የምትገዛ ጌታ አምላክ ሆይ፥ ሥራህ ታላቅና ድንቅ ነው›› ዮሀንስ ራዕይ 15 3-4 ፤ ‹‹ይህች ከእግዚአብሔር ዘንድ ሆነች፥ ለዓይናችንም ድንቅ ናት።›› መዝሙረ ዳዊት11823  ከማለት ውጪ ሌላ ምን ይባላል፡፡አምኖ የመጣ እንዲህ ይደረግለታል ፤ ብዙዎቻችን ግን እግዚአብሔር ቤት ስንሄድ በሁለት ልብ ሆነን ነው ፤ ስንመለስም ከሁለት ያጣ የምንሆነው ለዚህ ይመስለኛል፡፡

ያየነውን ነገር ማመን እስኪያቅተን ድረስ እየተገረምን ማረፊያ ፍለጋ ስንንቀሳቀስ  ሰዎች ተሰብስበው አየን ፡፡ ሁሌ ማታ 11፡00 ላይ በወንዶች ማረፊያ አካባቢ እና በሴቶች ማረፊያ አካባቢ አዲስ ለመጡ ሰዎች የቦታውን ስርዓት ፤ ምን እንደሚደረግ ፤ ምንስ እንደማይደረግ አባቶች ለ30 ደቂቃ ያህል ያስረዳሉ፡፡ ጠጋ ስንል ተረኛው አባት እንዲህ ሲሉ ነገሩን፡-  
‹‹ ይህውላችሁ ልጆች ሀገር አቋርጣችሁ ከተለያየ ቦታ እዚ የመጣችሁት እናንተ ፈልጋችሁ ብቻ አይደለም ፤ እግዚአብሔርም ፈቅዶላችሁ ጭምር ነው፡፡ ስለዚህ እሱ ፈቅዶ እና ወዶ እስካመጣችሁ ድረስ የመጣችሁበትን አላማ የሚያስተጓጉል አንዳች ነገር ማድረግ የለባችሁም ፤ ይህ ቦታ የምህላ ፤ የፀሎት ፤ የሱባኤ ቦታ ነው ፤ እዚህ ቦታ ላይ ከእናንተ የሚጠበቅባችሁ ነገር አለ እርሱም ፡- ወደ ገዳም ስትወርዱ ጫማችሁን አድርጋችሁ መግባት አይቻልም ፤ ሴቶችም ወንዶችም በገዳም ውስጥ ስትመላለሱ ክርስትያናዊ አለባበስ መልበስ አለባችሁ ፤ በማደሪያችሁም ሆነ ገዳም ስትወርዱ ጮክ ብሎ መነጋገር አይቻልም ፤ ብዙ ሰዎች አርምሞ ስለሚይዙ እነሱንም መረበሽ ስለሆነ ይህ አጥብቆ የተከለከለ ነው ፤ የቻለ በቀን ሰባት ጊዜ ፀሎት ማድረስ አለበት፤ ካልቻለህ ግን ሶስቱን ጸሎት ማስተጓጎል የለበትም ፤ ከሰኞ እስከ አርብ ድረስ በሽተኛ ካልሆነ በቀር ምግብ 12 ሰዓት ላይ ነው መብላት የሚቻለው እስከዚያ ሁሌ ጾም ነው(ከበዓለ 50 በቀረ) ፤ የተፈቀዱት ምግቦች ቆሎ ፤ባቄላ ፤ ጥጥሬዎች እና በሶ  ከሰኞ እስከ አርብ ሲሆን ቅዳሜ እና እሁድ ዳቦ መብላት ይፈቀዳል ፤ እንጀራ እና ወጥ ገዳም ውስጥ ባላችሁበት ጊዜ መብላት አይቻልም ፤ ጸበል ጠዋ በ11 ይከፈታል ከዚያ በፊት ጸበል መውረድ አይቻልም  እስከ ሰባትም ስንትም ሰዓት ይቆያል ፤ እዚህ ቦታ ላይ በዓመት 1ጊዜ ብቻ ነው ቅዳሴ ያለው ፤ ጠዋት ሊነጋ ሲል 11 ሰዓት ላይ ኪዳን ማድረስ ፤ ሲነጋ ትምህርተ ወንጌል መሳተፍ ፤ከ ሰዓት ከ9፡40 ጀምሮ ምህላ ማድረስ አለባችሁ የዛኔ ነው የመጣችሁበትን አላማ እና እናንተ የምትገናኙት ›› እያሉ ብዙ ነገር ነገሩን መከሩን፡፡


እኛ እንኳን ለ3 ቀን ነው የመጣነው ገዳም ውስጥ የሚኖሩ መነኮሳት ይህን ሁሉ ችለው ነው የሚኖሩት?  ይገርማል ፤ እግዚአብሔርም አለምን ትተው እሱን ብለው የመጡትን ያስችላቸዋል:: በመጨረሻም ፀሎት አድርገውልን ወደ ማደሪያችን ሸኙን፡፡ ይህን ስመለከት ብዙ ቦታዎች ስንሄድ የቦታውን ስርዓት ሳናውቅ የምናጠፋ ሰዎች እንበዛለን ፤ ልክ እንደ ፃድቃኔ ማርያም ገዳም  ቀን በቀን ሳይሰለቹ እንደዚህ አይነት ነገሮች ሁሉም ቦታ ቢለመድ ጥሩ የሚል ሀሳብ አለኝ፡፡

የሚቀጥለው ቀን ጠዋት
ለሊት ኪዳን አድርሰን ወረፋው እንዳይበዛ ፀበል ወረድን ፤ ፀበል ተጠምቀን ስናበቃ ለመጠጣት አንዱ ልጅ ጋር ጠጋ ብዬ ቁጭ አልኩ ፤ ጎንበስ ብዬ ሳየው አንዳች ነገር ጉልበቱ ላይ ትልቅ እጢ ቋጥሮ ተመለከትኩኝ ፤‹‹ወንድሜ ምን ሆነህ ነው›› አልኩት፡፡ እሱም ‹‹ ተወኝ ባክህ ልቤ ደንድኖ አልሰማ ብዬ ነው እንዲ የሆንኩት አለኝ››፡፡ አልገባኝም አልኩት ‹‹ሰው ንስሀ ገብቶ ወደ በፊቱ ምግባሩ ከተመለሰ የባሰውን ነው የሚሸከመው አለኝ››  ይባስ ግራ አጋባኝ፡፡  ቀስ ብለህ ልታስረዳኝ ትችላለህ አልኩት፡፡ እርሱም፡-
   ‹‹ ትውልዴ አዲስ አበባ ነው የ22 አካባቢ ልጅ ነኝ ፡፡ይህውልህ የዛሬ 2 ዓመት በፊት እጠጣለሁ ፤አጨሳለሁ ፤ እጨፍራለሁ ብቻ ምንም ከሀጢያት የቀረኝ ነገር የለም ሁሉን አደርጋለሁ ፡፡ በዚህ ሁኔታ ላይ ሳለሁ የዚያን ጊዜ ጉልበቴ ላይ ከዚህ በፊት ሆኖ በማያውቅ በልክ ትልቅ እጢ ወጣብኝ ፤ ብዙ ቦታ ብሄድ ኦፕራሲዮን መሆንን ነበር እንደ መፍትሄ ያስቀመጡልኝ ፤ እሱን ደግሞ እኔ አልፈልገውም ፡፡ እናቴ እስኪ ፃድቃኔ ሂድ አለችኝ ፤ ‹‹ምን ማለትሽ ነው ዶክተሮች ኦፕራሲዮን እያሉ እዛ ምን ልሰራ ነው የምሄደው›› ብዬ ከእሷ ጋር ተጣላን ፤ ውዬ አድሬ ሳስበው መሄድ እንዳለብኝ ውስጤ ነገረኝ ፡፡ ከአዲስ አበባ ተነስቼ በሶ እና ቆሎ ብቻ በመያዘ ቀጥታ እዚህ ቦታ መጣሁ ፤ አንድን አባት አግኝቼ ችግሬን ስነግራቸው በደንብ አደመጡኝና ‹‹በል አሁን ጸበል እንዳትጀምር ፤ ንስሀ ግባ፤  ቀኖናህን ስትጨርስ መጠመቅ ትችላለህ›› አሉኝ፡፡  እሺ ብዬ ንስሀዬን ከራሴ ላይ አወረድኩኝ ፤ ቀኖናዬን ጨረስኩ ፤ከዚያ ጸበል መጠመቅ ስጀምር ሰዎች እምነት ሲቀቡ ተመለከትኩኝ ፤ ለምን እኔስ አልቀባም ብዬ ጸበሉን ከእምነት ጋር እየደባለኩ ቁስሉን መቀባት በጀመርኩኝ በሶስተኛው ቀን ተሸክሜ የመጣሁትን እጢ በመግል መልክ ከሰውነቴ ወጥቶ አለቀ ፤ ተሸሎኝ ወደቤቴ ስመለስ እማዬ ስታየኝ ማመን አልቻለችም ነበር ፤ አለቀሰች ፤ እመቤቴን ወላዲተ አምላክን ማመስገኛ ቃላት አጣች ፤ እኔም ለአንድ ዓመት ያህል ከቤተክርስትያን አልራኩም ነበር ፡፡ የሆነ ጊዜ ላይ ግን ከቤቱ ጠፋሁ ፤ ወደ ቀደመ ምግባሬ ቀስ እያልኩ ገባሁበት ፤ የተደረገልኝን ነገር ዘነጋሁ ፤ ይህው አሁን ደግሜ የዛሬ ሁለት ዓመት ይዥው የመጣሁትን እጢ አሁን ተመልሶ መጣብኝ ›› ብሎ ሲነግረኝ ሰውነቴን አንዳች ነገር አራደኝ፡፡


ስንቶቻችን ነን ገብተን የወጣን ፤ ውለታውን የዘነጋን ፤ የተደረገልንን ነገር የረሳን ፤ ከሞት አፋፍ ከጠላት ወጥመድ ጠብቆ አሳልፎን ዛሬ ላይ ከቤቱ ሸርተት ያልን? ቤት ይቁጠረው ፡፡ እኔ አይኔ የልጁ እጢ ላይ ነው ፤ ልጁ ደግሞ አይኑ እኔ ላይ ነው ፡፡ ‹‹ አሁን አኮ ቀንሶ ነው ያየህው›› አለኝ ፡፡ ‹‹ሳይቀንስ ባየው የቱን ያህል ነበር?›› ብዬ ራሴን ጠየኩኝ፡፡እንዲህ ሲል ቀጠለልኝ ‹‹ ትላንት ምልክት አይቻለሁ በጥቂት ቀናት ውስጥ አፍስሳ ትጨርስልኛለች ፤ በአውራ ጣቴ በኩል በቢጫ ፈሳሽ መልክ ትንሽ ትንሽ ሲወጣ ተመልክቻለሁ ፤ ከአሁን በኋላ ግን ወደ በፊቱ ማንነቴ እንዳልመለስ እግዚአብሔር ይጠብቀኝ ፤ እርግጠኛ ነኝ አሁን እድናለሁ አለኝ፡፡››  የልጁ እምነት ገረመኝ፡፡ ስንቶቻችን ነን አፋችንን ሞልተን በእምነት ‹‹እድናለሁ›› ማለት የምንችል ፤ እንዲህ ለማለትም ፍጹም እምነት ያስፈልጋል፡፡ የመጣሁበትን ጉዳዬ እረስቼ ቁጭ ብለን ስለራሱ ፤ አዛው ቦታ ላይ ስላየው ተዓምር ሲነግረኝ ሰዓቱ መዝለቁን አላስተዋልኩም ነበር፡፡ መጨረሻ ላይ ‹‹በል እመብርሀን ወላዲተ አምላክ ትርዳህ ፤እግዚአብሔር በምህረቱ ይጎብኝህ›› ብዬው ወደ ማረፊያየ ለመሄድ ብድግ አልኩ ፡፡መሬት መሬት አቀርቅሬ ፤ የነገረኝን ታሪክ ከራሴ ጋር እያቆራኝውት  እንደ ውሻ የተፋሁትን ነገር ደግሜ የላስኩበትን ሁኔታዎች ሳወጣ ሳወርድ ምንም ሳላውቀው ማረፊያዬ ጋር ደረስኩኝ፡፡

ኡራኤል ቤተክርስትያ

ከወራት በፊት ነው አዲስ አበባ ኡራኤል እለቱ እሁድ ፤ ቀኑ ደግሞ 22 ላይ ውሎ ለማስቀደስ ወደዚያው አቀናሁ፡፡ ሁሉም ነገር ደስ በሚል ሁኔታ ተጠናቅቆ ወደ ቤት ለመሄድ እግሬን ሳነሳ ፤ ቆይ አንድ ጊዜ ዛሬ ድንቅ ተዓምር ትሰማላችሁ ትንሽ ቆዩ አሉን ፡፡ ለመሄድ የተነሳሁት ልጅ ደግሜ ቁጭ አልኩ፡፡

ልጅቷ ከሲሜሲ አካባቢ ሰው እየመራት ነበር ቅዳሴ ለማቀደስ ኡራኤል የተገኝችው ፡፡ ቅዳሴ አልቆ ጸሎት አድርሳ የቅዳሴ ፀበል ለመጠጣት ትፈልግና ትሄዳለች ፤ እግዚአብሔር ፈቅዶ የቅዳሴ ጸበል በጠጣች ፤ ፊቷን አይኗን በደባበሰች ፤ በጥቂት ደቂቃ ውስጥ የአይን ብርሀኗ መመለሱን ሲነግሩን ‹‹ ስራህ ድንቅ ነው›› ከማለት ውጪ አሁንም ዝምታን ነበር የመረጥኩት፡፡ ሰው እየመራ የመጣችው ልጅ እያየች ወደቤቷ ልትመለስ ችላለች ፤ በማታው ጉባኤ ላይ አንደምትገኝ እና ተዓምራቱን ለሰዎች እንደምትመሰክር ቃል ገብታ ወደ ቤቷ እያየች ተመልሳለች፡፡ለካ ይህ ልታሰማኝ ኖሯል 4 ታክሲ አቋርጠር ያመጣህኝ ብዬ እኔም ወደቤቴ ሄድኩኝ፡፡

ሌሎችን ያየሁትን ተአምራት በሌላ ጊዜ እናንተ ጋር ለማድረስ ቃል እገባለሁ  
‹‹ስራህ ድንቅ ነው በሉት››
ቸር ሰንብቱ
‹‹እግዚአብሔር ቤተክርስትያናችንን ይጠብቅ››

44 comments:

  1. such miracle are only from EOTC,we,followers of EOTC,are very lucky.God bless our land.

    ReplyDelete
    Replies
    1. abetu endabedelachen sayihon endcharenate yiker balan

      Delete
  2. awo be'ewinet Egiziabiher hoy sirah dink new
    Kale hiyiwet yasemalin yageligilot zemenihin yarizimilin.

    ReplyDelete
  3. ርብቃ ከጀርመንDecember 1, 2011 at 3:55 AM

    ግሩምክብርከ ከማለት በላይ ለዚህ የቸርነት ስራ ሌላ ቃልከየት ማግኘት ይቻላልያመኑበትን የማያሳፍር የቅዱሳን አምላክ የተመሰገነይሁን እናንተም ለምታቀርቡልንወቅታዊ መረጃ እግዚአብሄር ይስጥልን በርቱ ለኛም በሀጢያት የታወረ ልባችንን ድንግልበምልጃዋ ታብራልን አሜን::

    ReplyDelete
  4. yeembetachen redet berket lehulem kegaa gar yehun

    ReplyDelete
  5. yeembetachem redeate berket ahunem kehulachenem gar yehun

    ReplyDelete
  6. Kale Hiwote Yasemalene.Ye Emebetachen Weladite Amelake Redeate,Amalagenete,Ruruhenete ena Tebeka Kehulachen Gara Yehun.Amen!!!
    Kefyalew,Boston,USA

    ReplyDelete
  7. May God Bless us all with his love

    ReplyDelete
  8. ቃለ፡ሕይወት፡ያሰማልን!!!

    ReplyDelete
  9. አንተን ማመንን የምትሰጠው እኮ አንተ ነህ! እባክህ አንተን ማመንን ስጠን አለማመናችንን እርዳ! ድንቅህንም አሳየን አሜን!
    ወንድሜ ቃለህይወት ያሰማልን!!!
    አብነት ከሆሳዕና
    አንተን ማመንን የምትሰጠው እኮ አንተ ነህ! እባክህ አንተን ማመንን ስጠን አለማመናችንን እርዳ! ድንቅህንም አሳየን አሜን!
    ወንድሜ ቃለህይወት ያሰማልን!!!
    አብነት ከሆሳዕና

    ReplyDelete
  10. Amen Kale Hiwoten Yasemlen! Lengaem Endieu Yedrglen Amen!

    ReplyDelete
  11. Kale hiwoten Yasemalen!!!

    ReplyDelete
  12. Amen Egziabher Betekristianchin Yitebik.lewodajachinim kale hiwet yasemalin.

    ReplyDelete
  13. teameraten eyesemana eyaaye lemayemelesew lebeb hulachehu beselot asebugne Mammen kante new alk ewnethen new lezihem yegziabher erdata asfelagi new yesew lege leb endealet yetenekere selehone , lemanegawem besemanew endenden Egziabher yerdan

    ReplyDelete
  14. egzabher ke egna ayirak

    ReplyDelete
  15. Emebete Anchi Kidist Dingil Mariam Anchin Amno Yafere Manew.

    ReplyDelete
  16. ስራህ ድንቅ ነው!!! embetachenene ameno yehede saydene aymlseme yamene yetxemeke yedenale wendeme kale
    hiwoten yasemalene emebetachene tebarkhe segawene yalbesehe.

    ReplyDelete
  17. ስራህ ድንቅ ነው embetachene dengele maryam hedo saydene emimelse yeleme yamene yetetemeke yedenale wendeme kale hiwotene yasemalene dengele maryame tebarkhe cheru medhani aleme segawene yalbeshe.

    ReplyDelete
  18. ገና ገና ብዙ ታምራቶችን እናያለን፡፡ ለነሱ የደረሰ አምላክ ለኛ ለሁላችንም በቸርነቱ ይድረስልን፡፡

    ReplyDelete
  19. serahe dinke new God is almaighty,i rember b4 seven yrs iwas there tsadekane mariyam himamaten eza nebre yasalfkut ena hiwote yehone bota new selam yalwe bota!embetachen bemlijawa terdan AMEN!

    ReplyDelete
  20. Like the Catholic Church, we should also have specialists to prove such claims. andad gize tenkolegnoch ayitefumna zim bilen te-amr kemaletachin befit , be kefitegna Orthodox experts tetento keteregagete behuala binaworaw yishalal..behuala chigir yemiametaw endezih yalew neger new.

    ReplyDelete
    Replies
    1. Sayayu yemiyamnu bitsuan nachew. Amange enji teteratari atihun. Le Egziabhier yemisanew neger yelem.Minalbatim enga yalsemanew enji yaltederege teamir yelem. Degmom Wendime/ehite hoy Menafikan(catholics) kenga yimaru enji enga kenesu aniwesdim.Egziabhier libona yistih

      Delete
  21. sosina from khartoumDecember 28, 2011 at 3:19 AM

    Kale Hiwot Yasemalin. Yemebetachin Yekidst Dingil Mariam sira etsub dink new. Egnanm Bemihret Tigobgnen. Amen.

    ReplyDelete
  22. ቃለ፡ሕይወት፡ያሰማልን!!!

    ReplyDelete
  23. Ene eyandandachin be hiwotachen weste yatadaragalenen nager mayet becha ke beki belay new manem endiyaregagetelen ayefalegem. Ene enate be tselotua endene Tsadekane Mariyam yaredachew yale sew ale bilugn lemamen eskechager deras denk nagerochen adergalegnalech lasawem setadareg ayechalehu. Ye Emebete fekad yehunena ba safiwe amharic type maderage sechele esfelachehualehu gin Wendemochena ehetoch ene yatemarkut emnet betam telek bota alew yedaregale belachehu mamen kezam ye kalkidan botawa lay mahed wayem yalachehubet bota honachehu basemua mematsene becha. Ene hiwoten be Tselotewanaeyamerachegn yalechiw esu nech chigirin becha matefat ayedalam wadafit min endamihone hulu yametetakum denk enat nat ena enetakamebate esuanem yaseten Kidus azagne yahonewen Amlakem zaweter enamasegenew lahulum sayehone lamiwadew nawena yasetat ba maskel ser!!! Amlak fakedo andachen kalelaw lememar yabekan erse ba ersachenem lamemar yabekan!!! Amen Sebehat le Egziabehere, wale weladitu dengel wele maskelu kebur!!!! Amen, Amen, Amen!!!

    ReplyDelete
  24. kalhiwot yasemalen wendmachin ebkhi legnam setlign God endredan!

    ReplyDelete
  25. I have a plan to go to Tsadkane Mariam very soon, please my brothers and sister pray for me. I am a little bit mentaly affected person due to ignorant peoples falsfication, I will go there and I hope our lady will give me a cure. Tsadkane Mariam teamerishen lemenager yabkagn.

    ReplyDelete
  26. amen kale hiywet yasemalen serah denk new amlake! ante talak nehe negus hoy temesgen

    ReplyDelete
  27. Qale hiwoten YASEMALEN. ....YEmebetachen tegawa be hulachenm lai yegeletse ,,etsube denekenew seraw ye Amelakachen ,,gena bezu tamere ale ewnet andi hayimanote nate tewahido...beretu ye EGZIABHER cherenet yetebekachu !!!

    ReplyDelete
  28. ቃለ፡ሕይወት፡ያሰማልን!!!

    ReplyDelete
  29. የአንድ አድርገን ብሎግ ጸሐፊዎች እግዚአብሔር ይስጣችሁ ይህንን መልካም ዜና ስላሰማችሁን ቃል ህይወት ያሰማልን ............እባካችሁ አንድ ነገር ልጠይቃችሁ .....አንድ ሰው ስልቱ ደርሶለት ወይም እንዲደርስለት ወይም በረከት ለመውሰድ ታቦት በሚቆምበት ቦታ ነጠላውን በማንጠፍ ታቦቱ ረግጦት እንዲያልፍ ቢያደርግ ....ስህተት አለው ? እባካችሁ ከሰዎች ጋር ስለተከራከርኩበት ነው እግዜር ይስጥልኝ

    ReplyDelete
  30. ‹‹ስራህ ድንቅ ነው በሉት››

    ReplyDelete
  31. ከአዘዞ ወለተ ስላሴNovember 3, 2014 at 10:59 PM

    እግዚአብሔርን ስራህ ድንቅ ነው በሉት

    ReplyDelete
  32. እኛማ አንደበት የለን
    ዝም ካልሆነ ምን እንላለን።

    ReplyDelete
  33. እኛማ አንደበት የለን
    ዝም ካልሆነ ምን እንላለን።

    ReplyDelete
  34. እኛማ አንደበት የለን
    ዝም ካልሆነ ምን እንላለን።

    ReplyDelete
  35. እኛማ አንደበት የለን
    ዝም ካልሆነ ምን እንላለን።

    ReplyDelete
  36. ቃለ ሕይወት ያሰማልን። እኛንም ሰምቶ ከመጥፋት ያድነን።
    ውዳሴና አምልኮ ክብርና ምስጋና ቸር እና ይቅር ባይ ለሆነው አምላካችን ከምድር እስከ አርያም ለዘልአለሙ ይሁን።

    ReplyDelete
  37. ከቤቱ አያርቀን ገብተን ከመውጣት ያድነን

    ReplyDelete
  38. ከቤቱ አያርቀን ገብተን ከመውጣት ያድነን

    ReplyDelete