Monday, December 26, 2011

የሀዋሳን ህዝብ ያስለቀሱ ሰው ለአየር ጤና አንቀጸ ብርሃን ኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ተደርገው ተሾሙ

  • አባ” ናትናኤል ለአየር ጤና አንቀጸ ብርሃን ኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ተደርገው  ተሾሙ፡፡

(አንድ አድርገን ፤ ታህሳስ ኪዳነ ምህረት ፤2004 ዓ.ም)፡ አሁንስ እኛም ጆሯችን ጥሩ ነገር ናፈቀው ፤ ባለፈው ዓመት የሀዋሳን ህዝብ ሲያስለቅሱት የነበሩት  ደብረ ገነት ቅድስት ስላሴ ቤተክርስትያን  አስተዳዳሪ ከቀናት በፊት አየር ጤና አንቀጸ ብርሃን ኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ተደርገው ከቤተክህነት ተሾሙው ነበር ፤  ነገር ግን ህዝቡ እኝን አባት አስተዳዳሪ አድርገን አንቀበልም ብሎ እሳቸው በእግራቸው ቢመጡም በኮንትራት ታክሲ ከቤተክርስያን እንዳባረሯቸው ከቀናት በፊት ዘግበን ነበር፡፡  የበፊቱን ዘገባ ለማንበብ ይህን ይጫኑ

ቅዳሜ 14/04/2004 ዓ.ም  የተሰማው ወሬ ግን የተፈራው እንደደረሰ ነው ፡፡ የቤተክርስያኗ አባቶች ተሰብስበው ቤተክህነት ድረስ በመሄድ አባት ሹሙልን ያለ አስተዳዳሪ ወራት ቆጠርን ብለው በአንድነት ቤተክህነት ድረስ ሄደው ጥያቄያቸውን አቅርበው ነበር፡፡ ከአባ ጳውሎስ የተሰጣቸው መልስ ግን ‹የተሸመላችሁን አባት ለምን አልተቀበላችሁም› የሚል ነበር ፡፡ ያልተቀበሉበትን ምክንያት አስረግጠው በመነጋገር በቃ እሺ ይሾምላቿል ብሏቸወ በሰላም ወደ ደብራቸው ሊመለሱ ችለዋል፡፡ ከቀናት በኋላ የሆነው ነገር ግን ‹‹ማነው ደግሞ አልቀበልም ያለው›› ብለው በፊት የሾሟቸውን የተሀድሶ አቀንቃኝ አባ ናትናኤልን ደግመው ሾሟቸዋል፡፡

ባለፉት ሁለት ቀናት ክቡር ሰላመ መላከ ሰላም አባ ናትናኤል እያሉ ቅዳሴ ላይ ስሙን ሲጠሩት ሰንብተዋል ፤ የቤተክርስያኗ አባቶች ከአባ ጳውሎስ የተሰጣቸው መልስ አባት እንደሚሾምላቸው እንጂ እሱ መሆኑን አላወቁም ነበር፡፡ ለፈተናችን መብዛት የአንበሳውን ድርሻ  አቡነ ጳውሎስ ይዘውታል ፤ እኛ ስራቸውን እግር በእግር እየተከታተልን ማውጣታችንን ወደ ኋላ አንልም ፤ እግዚአብሔር እጁን እስኪዘረጋ መፍትሄ ከእሱ እንሻለን እንጂ ከሰው አንጠብቅም ፤ ሲኖዶሱ እንዳያስተምሩ በጉባኤ ሲወስን አባ ጳውሎስ በማን አለብኝነት የተወሰነውን ውሳኔ እየጣሱ ህዝብ ክርስትያኑን እያሳዘኑት ይገኛሉ፡፡እኝህ ሰው ስራቸውን አዋሳ ላይ ሄዳችሁ መጠየቅ ትችላላችሁ ፤ ምን አይነት ስራ ሲሰሩ እንደነበር ፋይላቸውን ከፍተው ይነግሯችዋል ፤


አባ ናትናኤል(የሀዋሳ ደብረ ገነት ቅድስት ስላሴ ቤተክርስትያን አስተዳዳሪ የነበሩ) በፊት በተሐድሶ እና ከፕሮቴስታንት አራማጆች(ተስፋኪዳነምህረት ማህበር እና ከመሰሎቻቸው )ጋር በመሆን የእግዚአብሔርን አውደ ምህረት እንዲፈነጩበት ካደረጉ ሰዎች መካከል ግንባር ቀደሙን የሚይዙ ሰው ናቸው ፡፡ በጊዜው ገንዘብ አይናቸውን አሳውሯቸው ፤ ለአውደምህረት የማይመጥኑ ፤ ትምህርቱ የሌላቸው ሰዎችን በመጋበዝ ህዝቡን እዚህ ደረጃ እንዲደርስ ካደረኩ ሰዎች ዋናዎቹ ሲሆኑ አሁንም በሰሩት ስራ ንስሀ እንደመግባት ከእኩይ ስራቸው ሊማሩ ባለመቻላቸው አሁንም ከአቡነ ጳውሎስ ተልከው ለአስተዳዳሪነት በአየር ጤና አንቀጸ ብርሃን ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን  ሊያስተዳድሩ መጥተዋል፡፡

ህዝበ ክርስትያኑ የተሀድሶን እንቅስቃሴ በተቻለው መጠን እየተከታተለ ራሱንም ቤተክርስያንንም ለመጠበቅ ንቁ ተሳትፎ እያደረገ በሚገኝበት በአሁኑ ሰዓት እንዲህ አይነት ስርአት አልበኛ አባት ለቤተክርስትያን መሾም ምን ይሉታል? እኝህ ሰው በከፍተኛ ገንዘብ ምዝበራ የተከሰሱ ሰው ናቸው ፤ አቡነ ጳውሎስ  የሚወስኑትን ውሳኔ ሁሌ አወዛጋቢ እየሆነ ነው፡፡ እኛንም ሌላ ጥርጣሬ ውስጥ ከከተቱን ሰንበትበት ብለዋል ‹‹ ጠርጥር ከገንፎ አይጠፋም ስንጥር›› ይላል የሀገሬ ሰው ፤ ሲኖዶስ የላከው አጣሪ ኮሚቴ ስራቸውን መዝኖ ከሀዋሳ  ደብረ ገነት ቅድስት ስላሴ ቤተክርስትያን  ያነሳቸውን ሰው ፤ በየትኛው መመዘኛ ነው ፤ ለአየር ጤና ኪዳነ ምህረት ቤተክርስያን በመመጠን የተሾሙት ? ጥያቄያችን ይመለስልን ፤ አቡነ ጳውሎስ ደህና ደብሮችን የማዳከም ስራቸውን ከጋሻ ጃግሬዎቻቸው ጋር ቤተክርስትያን የቁልቁል ለመስደድ እየሰሩ ይገኛሉ፡፡

‹‹አሁንስ እግዚአብሔር ይታረቀን ፤ 
ለቤተክርስትያን ግድ የሚላቸውን አባቶች አያሳጣን››


7 comments:

  1. አቡነ ጰዉሎስ ሆን ብለው ቤተክርስቲያንን እያተወጉና ተርከዊ ስህተት እያፈጸሙ እንደሆነ ግልፅ ነው፤
    አዚህ ዲላ ላይ በለፈው ሰምንት እናንተም በድህራ ገጸችሁ እንደገለፃችሁ የእድር ሀለፊዎች በጥቅም አሁን ከለው ሰበካ ጋር ግንባር በመፍጠር ሀ/ስብካት አየዘንም ሰበካው ተ ጠርነቱ ለእኛ ነው ከህን መቅጠርም ሆና ማበረር እንችለለን እኛም አልጠመጠምንም እንጂ ከህን ናን አስኬማ አልደፈንም እንጂ ጰጰስ ነን ሲሉ ለነበሩት የቤተክርስቲያን መወቅር በልጠበቀ መልኩ ወ/ቤተክህነትን፤ሀ/ስብከትን አልፎ በአቡነ ጰውሎስ ጠሪነት አ.አ በመሄድ የሀ/ስብከቱን ውሰኔ የሚየሽር ተሰቷቸው ምዕመኑን ግራ በመጋበት ላይ ይገኛሉ፡፡
    ስለዚህ አቡኑ በየትኛውም አቅጣጨ ቢሆን ምዕመናንን አንገት የሚያስደፈ ድርጊት ስራዬ ብለው የተያያዙት ይመስላል
    እግዚአብሔር አምለክ በቸርነቱ ይተረቀን
    ድንግል በሚልጃዋ ትታደገን
    አሜን!!!!
    J.M.T Z DILLA

    ReplyDelete
  2. Whose resposiblity is this? Aba Pawlos or The respective Papas? Would you explain it? Why don't the people asked their respective papas?

    ReplyDelete
  3. I am happy about Abune paulos, because he is doing well but all of you are YE WETET ZINB; please be clam and live your life. Who are you who blame him? He is head of our church and he became father of our church over the world by willing of GOD.

    ReplyDelete
  4. እኛ እንዲህም እንዲያም እናስባለን እግዚአብሔር ደግሞ ምክንያት አለዉ! የሀዋሳ ምእመናን የተወጡትን ፈተና ለአዲሰ አባዎች መጥቶለናል እንዴት እንወታው ይሆን? ይመስለኛል በፈሊጥ ወይም በፍልጥ! ነገሮች ወደ ፊት በፍልጥ መሆናቸዉ አይቀሬ ይመስላል:: የደበረ አሚን ተክለ ሃይማኖት ትእይንትን እናስታውስ................

    ReplyDelete
  5. hahahahah....your are the protestant. one. hahah. betam taskaleh....enkalen this is your early vision to distrub our church.....haahahahahha....protestor. y amalaken hayle y nakachehu y kadachehu........

    ReplyDelete
  6. መቼም ቢሆን ጆሮአችሁ ከዚህ የተለየ ወሬ አይሰማም፡፡ እየባሰ ይሄዳል እንጂ አይቀንስም፡፡

    ReplyDelete
  7. Sewen atkonenu enedihum atekesesu ategefafu neger gen ewenetegnawen wongelune sebeku. Mekeneyatume fered yefetari new enanete maderege yalebachehu Baible yemilewene enedegebachehu metene astemeru!! Manem sew tsadik new malet ayechalem!!! Yemiyatsedeke Yemikonene EGZIABHER new!!!!!!!!!!

    ReplyDelete