Thursday, April 3, 2014

ለነሱ የተሰጠው ስም ለእኔም ይገባኛል

የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ ማሩ
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል
(አንድ አድርገን መጋቢት 25 2006 ዓ.ም)፡- መንግሥት በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ዘመቻ ጀመረ በሚል እሰጥ አገባ እንደበዛ አውቃለሁ፡፡ በሌለኝ መረጃ የእኔን ስም እየጠቀሱ ሰዎች ፖስት እንደሚያደርጉ ከሰዎች ብሰማም የእኔ ፌስ ቡክ ይህን አልገለፀልኝም፡፡ ለማንኛውም መንግሥት በእምነት ላይ ዘመቻ ሲጀምር በኦርቶዶክስ ላይ በማህበረ ቅዱሳን መስመር እንደነበር ትዝ ይለኛል፡፡ ሟቹ ጠቅላይ ሚኒሰትር አቶ መለስ ይህን አሰመልክተው ለሰጡት አሰተያየት የሰጠሁትን ምላሽ በድጋሚ ላጋራችሁ፡፡ ይህ ነው የእኔ አቋም፡፡ ይህ ከማህበረ ቅዱሳን ጋር ከገጠመ እሰየው ነው፡፡ ለነሱ የተሰጠው ስም ለእኔም ይገባኛል፡፡ የሰጠሁት ምላሽ እንደወረደ ይህን ይመስል ነበር፡፡


ብዙ ጉዳዮች እንደተርጓሚው እንደሚሆን መገመት ይቻላል ነገር ግን ‹‹አንድ እምነት አንድ ሀገር›› ማለት ግን ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እንተረጎሙት ሳይሆን ፤ አንድ ሰው ሊኖረው የሚገባው አንድ ዕምነት ብቻ ነው (ሰኞ፤ ዕሮብና አርብ ሙስሊም ማክሰኞ፤ ሀሙስና ቅዳሚ ክርስቲያን፤ ወዘተ መሆን አይቻልም) ይህ ደግሞ አምላካዊ ቃል ነው (እኔ ቀናተኛ አምላክ ነኝ ሲል) ይህ አምላካዊ ቃል ደግም የሚሰራው ለሚያምኑበት ነው፡፡ ቃልቻ ቤት እየሄዳችሁ ቤተክርስቲያን አትምጡ ማለት ነው፡፡ ሊኖረን የሚገባው አንድ እምነት ነው፡፡ በእርግጠኝነት ሙስሊም ሆኖም ክርስቲያን መሆን አይቻልም ስለዚህ ይህ ለአንድ እምነት የመገዛት ፍልስፍና የሁለም የእምነት ዘርፎች መለያ ነው፡፡ ጥንቆላ ብቻ ነው ይህንን የሚፈቅደው - ይህ ደግም በሁሉም እምነቶች የተወገዘ የመጥፎ መንፈስ ስራ ነው፡፡ ሰለዚህ እኔ ያለኝ አንድ እምነት ብቻ ነው፡፡ መፈክሬም ይኽው ነው፡፡


ከአንድ እምነት ጋር ተያይዛ የመጣችው የአንድ ሀገር ጉዳይ ነው፡፡ ይህ በእርግጥ አከራካሪ ነው፡፡ አንድ አንድ ሀገሮች ጥምር ዜግነትን የሚፈቅዱ አሉ ፡፡ ይህም ሆኖ እኔ በግሌ ኢትዮጵያ ከምትባል ሀገር በስተቀር ሌላ ሀገር የለኝም- እንዲኖረኝም አልፈልግም ይህን አቋሜን ሰገልፅ ግን እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ ስል ሌሎች ኢትዮጵያዊ አይደላችሁም አለ ተብሎ ልከሰስ አይገባም፡፡ አንድ የእስልምና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያዊ ሊሆን እንደሚችል ብዥታ ኖሮብኝ አያውቅም ወይም የሌላ ክርስትና እምነት ተከታዮች ኢትዮጵያዊ አንደሆኑ አልጠራጠርም፡፡ ኢ-አማኒያንም ቢሆኑ፡፡ አንድ ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር አለችኝ ብዬ ነው ለዚህች ሀገር እድገት (ሁሉ አቀፍ እድገት ማለቴ ነው) የሚከፈል መሰዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ የሆኑኩት፡፡ ሌላ አማራጭ የለኝም - አማራጭ ያለው ግን ካልተመቸው ወደዛኛው ሊሄድ ይችላል፡፡ ሁለት ጉርጓድ ያላት አይጥ› እንደሚባለው፡፡ እኔ ግን ሀገሬ አንድ እና አንድ ነች፡፡ ኢትዮጵያ፡፡ ይህ ማለት ግን በምንም መመዘኛ ይህች ሀገር የኔ ብቻ ነች ማለት አይቻልም፡፡ አይሆንምም፡፡ እኔ የአንድ እምነት እና አንድ ሀገር ባለቤት ነኝ፡፡

5 comments:

  1. ልዑል እግዚአብሂር እዉነት ተናጋሪዎችን ያብዛልን!

    ReplyDelete
  2. yihe new Girma ..Bravo bilenal!! For a person who has working brain..your stements are enough to be convinced. As to be ande hager and hayimanot kezieh yezelele tirgum yalew ayimeselegmn. However, denkoro cadre min yigebawal bileh new

    ReplyDelete
  3. ሁለት ጉርጓድ ያላት አይጥ›

    ReplyDelete
  4. ይህ ማለት ግን በምንም መመዘኛ ይህች ሀገር የኔ ብቻ ነች ማለት አይቻልም፡፡ አይሆንምም፡፡ እኔ የአንድ እምነት እና አንድ ሀገር ባለቤት ነኝ፡፡

    ReplyDelete
  5. አንተን የፈለጉትን ሊሉህ ይችላሉ ፖለቲከኛ ስለሆንክ እኛ ግን አንዲት እምነት አንዲት ጥምቀት እንላለን ስለሃይማኖታችን ፡፡ ቃሉ የማይሻር ስለሆነ

    ReplyDelete