Tuesday, April 22, 2014

የኢፌድሪ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሙላቱና ቤተሰቦቻቸው በሰንበት በቤተመንግሥት ግቢ በምትገኝው ቤተ ክርስቲያን እንደሚስቀድሱና ከቤተሰቦቻቸው ጋርም እንደሚቆርቡ ተገለጸ


  • ፓትርያርኩ ተገኝተው ፀሎተ ቅዳሴውን መርተው አገልግለውበታል፡፡ 
በብሔራዊ ቤተመንግሥት ቅጽ ውስጥ በምትገኝውና በደብረ ገነት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን ፕሬዝዳንቱ እና ቤተሰቦቻቸው በእለተ እሑድ በሚከናወነው ፀሎተ ቅዳሴ  እየተሳተፉ ቅዱስ ቁርባን እንደሚቀበሉ ተገለፀ፡፡


የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በሚመድብላቸው አምስት መነኮሳት ካህናትና በአንድ ዲያቆን ልኡክነት ፀሎተ ኪዳንና ሥርዓተ ቅዳሴ በቤተ ክርስቲያኒቱ በመፈጸም ላይ ይገኛል ፡፡አገልጋዮቹም ከመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ፤ ከመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ፤ ከታዕካ ነገስት ባዕታ ለማርያም ገዳም ፤ ከመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል እና ከቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን በሀገረ  ስብከቱ አማካኝነት የተወጣጡ እና የተመረጡ መሆናቸው ታውቋል፡፡ በዚህም ኦርቶዶክሳዊ ስርዓተ አምልኮ ላይም ፕሬዝዳንቱ ከነቤተሰቦቻቸው ፤ የቤተመንግሥቱ ሰራኞችና የግቢ ጥበቃ አባላት እንዲሁም ህጻናትን ጨምሮ በርካታ ምዕመናን ይገኙበታል፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱ በብሔራዊ ቤተ መግሥት ተሰርታ  የተደራጀችው በዐጼ ኃይለ ሥላሴ ሲሆን በደርግ ዘመነ መንግሥት የተለያዩ እቃ ማስቀመጫ መጋዘን ነበረች፡፡አገልግሎቱን የጀመረችው በቀድሞ ፕሬዝዳንት በክቡር ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ መልካም ፍቃድ በተጨማሪ በቤተመንግሥቱ ዋና አስተዳዳሪ ብርጋዴል ጀነራል ወልደ ሰንበት አምዴ ጥረት ነበር፡፡


የቤተክርስያኒቱ ጥገናና ማስተካከል ሥራ ከተጠናቀቀ በኋላ የቀድው ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በስፍራ ተገኝተው የቅድስ ልደታ ለማርያም ታቦ-ሕግ ከመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም መጥቶ እንዲገባ አገልጋይ ካህናትም እንዲሟሉለት በሰጡት ትዕዛዝ መሰረት ልዑካን ተመድበው ስርዓተ ቅዳሴንና ጸሎተ ኪዳኑ በአግባቡ እየተከናወነ ከመቆየቱም ባሻገር  ፓትርያርኩ በታላቁ ቤተ መንግሥት በመገኝት ከሁለት ጊዜ በላይ ጸሎተ ቅዳሴውን በመምራት አገልግሎት ሰጥተውበታል፡፡
 
ያለፈው ያ ዘመን አይደለም የመንግሥት ባለስልጣን ይቅርና አንድ ምዕመን ነጠላ አገልድሞ ወደ ቤተክርስያን ለመሄድ የሚሳቀቅበት ዘመን አልፎ የሀገር ፕሬዝዳንት ቤተ መንግሥቱ ውስጥ ስርዓተ አምልኮውን የሚፈጽምበት ዘመን መምጣቱ ደስ ያሰኛል፡፡ በአሁንም ሰዓትም የምንገኝ አማኞች ለራሳችን ፤ ለቤተሰባችንና ለቤተክርስቲያን ሰው መሆን የሚገባን ጊዜ ላይ እንገኛለን፡፡ እያንዳንዱ ምዕመን የሚፈለግበትን መንፈሳዊ አገልግሎት በተቻለው አቅም ጊዜው በፈቀደ መጠን ማድረግ ከ እንደ እግዚአብሔር መልካም ፍቃድ አይኖቻችን መልካም የሚያዩበት ፤ ጆሮቿችን ጥሩ የሚሰሙበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም፡፡ ሃይማኖትና ሃይማኖተኝነት እነደኋላ ቀርነት በሚታይበት ዘመን አልፎና ርዕዩቱ ተሸሮ ፤ በበለጸጉ ሀገራት መሪዎች በአማኙ መካከል እየተገኙ  ሥርዓተ እምነታቸው ሲፈጽሙ እና አንዳንዶቹ የብሔራዊ ማንነታቸው መለያ አድርገው ሲመለከቱ ይታያል፡፡

የተከበሩ የኢፌድሪ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ከነቤተሰቦቻቸው እንደ ሩሲያው መሪ ቭላድሚር ፑቲን ዋና ዋና የቤተ ክርስቲያት በዓላት ላይ በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እናያቸው ይሆን? 
From AfroTimes

ስለ ሁሉም ነገር እግዚአብሔር ይመስገን

9 comments:

  1. እግዚአብሔር ይመስገን። ለአቦይ ስብሐሀትም ሳይርቅ በቅርብ ልቦና ይስጥልን ።አሜን!!!

    ReplyDelete
    Replies
    1. ኣስመሳይ ነሀ
      ስብሃት እኮ ፈለገ ሂወት ተምሮ የጨረሰ ነዉ

      Delete
  2. Egziabher yetemesgene yehun Dr. Mulatu and his families Egziabhr tibekawinena tigatun yestachew

    ReplyDelete
  3. እግዚአብሔር ይመስገን።

    ReplyDelete
  4. great!!!!!!!!!!!!!!!

    ReplyDelete
  5. Egeziabhere yemesgen

    ReplyDelete
  6. እግዚአብሔር ይመስገን!!

    ReplyDelete