Friday, April 18, 2014

የመዝሙር ጥራዝ ፤ የበዓል ስጦታ


አንድ አድርገን ሚያዚያ 5 2006 ዓ.ም) ፡- በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስተ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሥርዓት በየወቅቱ የሚዘመሩ መዝሙራት መኖራቸው ይታወቃል፡፡ እነዚህ መዝሙራትም በመጽሐፍ መልክ ተዘጋጅተው የሰንበት ተማሪዎች እና ምዕመኑ ዘንድ ለማድረስ ተሞክሯል ፡፡ እነዚህ ከስድስት መቶ የሚበልጡ መዝሙራት በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጪ ለሚኖሩ የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች እና ምዕመናን ተደራሽ ለማድረግ ያስችል ዘንድ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን የጠበቁትን  በመስቀል ፤ በልደት ፤ በጥምቀት ፤ በስቅለት ፤ በትንሳኤ ፤ በጰራቅሊጦስ  እና መሰል የቤተክርስቲያን ዋና ዋና በዓላት በተጨማሪ ስለ ድንግል ማርያም ፤ ስለ ቅዱሳን ፤ ስለ ንስሃ ስለ ጾም ወቅቶችን መሰረት አድርገው የሚዘመሩ ከ237 በላይ መዝሙራትን በpdf ብሎጋችን ላይ ለጥፈንልዎታል፡፡
መልካም የትንሳኤ በዓል ይሁንላችሁ

3 comments:

  1. እግዚአብሔር አብዝቶ፣አትረፍርፎ ይስጥልን።

    ReplyDelete
  2. እግዚአብሔር ይስጥልን።

    ReplyDelete
  3. May GOD bless your work.Keep it up.

    ReplyDelete