Tuesday, April 8, 2014

ሰላ ድንጋይ

ከሪፖርተር ጋዜጣ የተወሰደ

(አንድ አድርገን መጋቢት 30 2006 ዓ.ም)፡-በሰሜን ሸዋ ዞን .. ከደጋማው የመንዝ ምድር .. ተፈጥሮው በብዙ ከሚተርክበት መልከአ  ምድር መሃል በዚያ ንጹህ አየር በሚሳብበት  ውብ ምድር የሚገኝ ጥንታዊና ታሪካዊ ስፍራ  ነው::  ሰላ ድንጋይ የዚህ ድንቅ ስፍራ መጠሪያ  ነው:: ከሰሜን ሸዋ ዞን መዲና ከደብረ ብርሃን  ከተማ 75 .ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው  ሰላ ድንጋይ ኢትዮጵያን 38 ዓመታት  በፓትሪያሪክነት ያገለገሉት አባት የአቡነ ማቴዎስ  የመንበር ጵጵስናቸው መቀመጫ ነበረች::  ግብጻዊው ፓትሪያሪክ አቡነ ማቴዎስ በዚሁ  ስፍራ 1875 .. የማርቆስ ቤተ ክርስቲያንን  አሠርተዋል:: 


በአቡነ ማቴዎስ የተሰራው የማርቆስ ቤተ- ክርስቲያን ህንፃ በተሰራ 25 ዓመቱ በመብረቅ  አደጋ ፈርሷል:: እንደ ብዙ የቅርስ አጥኚ  ባለሙያዎች አስተያየት ቀድሞ የተሰራ  የማርቆስ ቤተ-ክርስቲያን ህንፃ አሰራር ጥበቡ  ድንቅ ነበር የሚል ሲሆን በመብረቅ ከመውደሙ  ጋር ተያዞ 1900 .. ነበር በድጋሚ በንጉስ  ምኒሊክ ትዕዛዝ በድጋሜ የታነፃው::  ለሁለተኛ ግዜ በንጉሥ ምኒልክ አማካይነት  የታነፀው የማርቆስ ቤተ ክርስቲያን ህንጻ በንጉሡ  ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት ስለ ነበር በድንቅ ሁኔታ  ተሰርቶ ለመጠናቀቅ ግማሽ መንፈቅ ብቻ  ፈጅቶበታል:: ይኸው ደብር የሚያዝያ ማርቆስ  ዕለት (ሚያዚያ 30) ንጉሱና አቡኑ በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተባርኳል:: 

የሰላ ድንጋይ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን  ከህንፃው የአስተናነፅ ጥበብ ህንፃውን ለመስራት  ከተጠቀሙበት ቁሳቁስና በየዘመናቱ በነበሩት  ታሪኮች ስፍራው የተለየ ቦታ እንዲሰጠው  አድርገውታል::  ለመንበረ ጵጵስናቸው መቀመጫ አድርገው  የመረጡት አቡነ ማቴዎስ ለመቀመጫነት ከግብፅ  አስመጥተውት የነበረው ወንበራቸው ዛሬም  ድረስ አለ:: በቀደመው የሸዋ ነገስታት ዘመን  የወይዘሮዎች መዲና በመባል የምትታወቀው  እና በታሪክ ጉልህ ስም ያላት የሰላ ድንጋይ  የሸዋው ንጉስ የንጉስ ሣህለ ስላሴ እናት ስም የምትጠራው ሰገነት በራሳቸው በወይዘሮ  ዘነበወርቅ እንደተሰራች ይነገርል:: አቡነ ማቴዎስ  በዚህች ሰገነት ላይ ይቀመጡባት ነበር::  አብዛኛዎቹ የሸዋ ነገስታት ቆነጃጅት ሚስቶቻቸውን ያስቀምጡባት የነበረች ስፍራ በመሆኗ የወይዘሮዎች ከተማ የሚል ስያሜ ቢሰጣትም ሰላ ድንጋይ የእምነትና የፖለቲካ ማዕከል ነበረች:: በዚሁ ስፍራ የምትገኘው የደብረ ምጥማቅ ጽላት ተሰውሮባታል ፃድቃኔ ማርያም የስፍራውን የቅርስ ማዕከልነት ከሚያሳዩ ማስረጃዎች አንዷ ናት:: አፄ ዘርዓያቆብ ወደ ሸዋ በወረዱ ግዜ ለማረፊያነት የሚጠቀሙበት ቤተ መንግስታቸውም በዚሁ በሰላ ድንጋይ ይገኛል:: 

አፄ ዘርዓያቆብ ቤተ መንግስታቸውን ቀልሰው በነበረበት ስፍራ አቅራቢያ የምትገኘው ጥንታዊቷ ደብረ ምጥማቅ 1426 እስከ 1460 ባለው ጊዜ የተመሰረተች ታሪካዊ ስፍራ ናት:: ሰላ ድንጋይ የሃይማኖታዊ ጉባኤዎች ማዕከልም ሆና አገልግላለች:: 1442 .. የተደረገውና ከመቶ ዓመት በላይ በቅዳሜ ሰንበትነት ዙሪያ ይደረግ የነበረው ክርክር በአፄ ዘርዓያቆብ አማካይነት የሃገሪቱ ሊቃውንት በተገኙበት በደብረ ምጥማቅ  የተካሄደ ጉባኤ ነበር:: 

1276 .. ጀምሮ ይነሳ የነበረውን ይከን የቅዳሜ ሰንበትነት ጉዳይ ለመጨረሻ ግዜ እልባት እንዲያገኝ ያስቻለው ጉባኤ የተካሄደበት ደብረ ምጥማቅ የያኔው ህንፃዋ ፈራርሶ ፍርስራሹ ዛሬም ይታያል::

No comments:

Post a Comment