Tuesday, April 22, 2014

ኢሕአዴግ አደረጃጀቶቹ ስለ አክራሪነትና ጽንፈኝነት ያላቸውን ግንዛቤና አቋም የሚያዳምጥበትን ውይይት እያካሔደ ነው

  • በማኅበረ ቅዱሳን ላይ የተሰነዘረውን አክራሪነትን ፍረጃ ተሳታፊዎቹን አስቆጣ
  • ፍረጃው ለውይይቱ አካሄድ ከተቀመጠው አቅጣጫ ውጪ ነው ተብሏል፡፡
  • ‹‹ መንግሥት ማኅበረ ቅዱሳን አክራሪ ለመሆኑ አስገራሚ አስገራሚ ማስረጃዎች አሉት›› በስብሰባው ላይ የተነሳ ፍረጃ እና ክስ
  • ጠባብነት በሙስሊሞች አካባቢ ፤ ትምክህተኝነት በኦርቶዶክሶች አካባቢ የመዳበር ባህሪ አለው ተብሏል፡፡

(አፍሮ ታይምስ ሚያዚያ 14 2006 ዓ.ም)፡-  ገዥው ግንባር ኢሕአዴግ በሃይማኖት ይሁን በማንኛውም ሽፋን የሚደረግን የፖለቲካ ግጭት ለመመከት በሚል በአዲስ አበባ በተለያዩ በደረጃጀቶች ውስጥ ከታቀፉ አባሎቹ ጋር ውይይት በማካሄድ ላይ መሆኑ ተገለጸ፡፡  በአዲስ አበባ 116 ወረዳዎች ካሉት ሰባት የግንሩ አደረጃጀቶች ማለትም የሴቶች ፤ ወጣቶች ፤ መምህራን ፤ መንግሥታዊና መንግታዊ ያልሆኑ ድጅቶች ፤ የአነስተኛ እና ጥቃቅን ተቋማት ከእያንዳንዳቸው 60 አባላት ያሳተፈ ውይይት ባለፈው ሳምንት መጨረሻ እንስቶ በመካሔድ ላይ ይገኛል፡፡

‹‹የሃይማኖት ተቋማትና ተከታዮች በሰላም አብሮ የመኖር ወርቃማ ተመክሮን የማስቀጠል ፋይዳው›› ‹‹አዲስቷ ኢትዮጵያና የሃይማኖት ብዝሃነት አያያዝ›› ‹‹አክራሪነት ጽፈኝነት  ከሕገ መንግሥታችን  ጋር ያለው የማይታረቅ መሠረታዊ ቅራኔና መፍትሔር›› የሚሉ ርእሶች በቀረቡት ጽሑፎች ላይ የተመሰረተው ውይይቱ ለአራት ተከታታይ ዙሮች እንደሚካሄድ ተመልክቷል፡፡


‹‹የመደማመጥ መድረክ›› የተሰኙ የመጀመሪያዎቹ  ሁለት ዙሮች ከቀረቡ ጽሑፎች ጋር በተያያዘ  የተዘጋጁ የመወያያ ነጥቦች አስመልክቶ የተሳታፊዎች ግንዛቤና አቋም ምንድነው ? የሚለው ለማወቅ ጥያቄዎች ፤ አስተያየቶችና አቋሞች በስፋት እንዲነሱና በዚህ ስልት በአባላት ውስጥ ያለው ስሜት በቀጥታ ለማድመጥ የታቀደበት መሆኑ ተገልጧል፡፡

በዚህ ሳምንት ከተከናወኑ ውይይቶች በአወያይነት በተመደቡበት ወረዳ ጸ/ቤት ሓላፊዎች አማካይነት በየፈርጁ ተጠቃለው ለበላይ አመራር (ለፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር) ቀርበዋል ለተባሉት የተሳታፊዎች ጥያቄዎች ፤ አስያየቶችና አቋሞች የግንባሩ እና የመንግሥት አቋሞች ፤ መረጃዎችና እቅዶች ምላሽነት እንደተሰጠባቸው ታውቋል፡፡

በጠቅላይ ከሚካሄዱት ሁለት ዙሮች ፤ በተናጠል ሲወያዩ የቆዩት የሰባቱ አደረጃጀቶች ስድሳ ስድሳ ተሳታፊዎች በጋራ በመገናኝት በሥልጠና አመለካከታቸውንና ግንዛቤያቸውን ያስተካክሉበታል ተብሎ የሚጠበቅ የማጥራትና የመግባባት መድረክ እንደሚሆን ተጠቁሟል፡፡በሰላም አብሮ የመኖር እሴቶችን  ሕገ-መንግሥታዊ ድንጋጌዎችን ይሸረሽራል የተባለው የአክራሪነትና ጽንፈኝነት ዝንባሌ ከቁጥር ውጪ ነው ባይባልም  ተገቢ ትኩተር እንደሚያሻው የተጠቆመ ሲሆን  የአክራሪነት የጽፈኝነት ምንጩን የማድረቅ ሥራ እየተሰራ የሕግ የበላይነትን የማክበር ሥራም ጎን ለጎን መፈጸም እንዳለበት አሳቧል፡፡

የሕዝብን ህልውና የሚፈታተንና የሀገሪቱን ልማት እድገት የሚያደናቅፍ ነቀርሳ ነው ለተባለው አክራሪነት ጽንፈኝነት ችግር ትክክለኛውን መፍትሄ ለመለየትና ለመረዳት  ያስችላል የተባለው በዚህ ተከታታይ ዙር  የኢህአዴግ  የአዲስ አበባ  አደረጃጀት ውይይት  ፤ የሃይማኖት ተቋማት ልኡካንም የተሳተፉ ሲሆን ይህም በየደረጃው የሚገኙ የሕዝብ አደረጃጀቶች  የተሟላ ግልጽት ይዘው ሁሉንም ዜጋ በተደራጀ ሁኔታ  በማሰለፍ የጸረ-አክራሪነቱን ትግል ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር አስፈላጊ መሆኑን በቀረቡ ጽሁፎች ተጠቅሷል፡፡ የሰዓቱ አደጋ ነው የተባለው ኪራይ ሰብሳነት የመጨረሻ መደበቂ ዋሻ ብሔርና ሃይማኖት መሆናቸው የተመለከተ ሲሆን  በኪራይ ሰብሳዎች መካከል የሚደረግ የሞት ሽረት ፍልሚያ  በሂደት በብሔረሰቦችና በሃይማኖቶች መካከል ወደሚካሄድ ፍትጊያ ሊሻገር እንደሚችል ፤ ይህም የስር ነቀሉን  ለውጥ መስመር መበታተንና  በሕዝቦች መካከል የሚፈጠረው ቁርሾና መናቆር እንደሚያፋጥን ያስጠነቅቃል፡፡

በተለይ የሃይማኖት አክራሪነት እንደነገሩ ሁኔታ ከጠባብነት በሙስሊሞች አካባቢ ፤ በትምክህተኝነት በኦርቶዶክሶች አካባቢ የመዳበር ባህሪ እንዳለው በማስረዳት  ፤ በጠባነት በትምክህት ሃይማኖታዊ ርእዮት ላይ የተመሠረተ ሽብርተኝነት ሃይማኖታዊ ግጭት ሊፈጠር እንደሚቻል ታሳቢ አድርጎ ርእዮቱን በትምህርትና በስልጠና በዲሞክራሲያዊ አኳኋን መታገል የለዘብተኝነትና የመቻቻል ባህል እንዲዳብር የተጠናከረ ስራ መስራት እንዳለበት ያሳስባሉ፡፡

በሌላ በኩል የመድረክ አወያዮች ለስሰባው አካሄድ  ተቀምጧል የተባለው ድርጅታዊና መንግስታዊ አቋምና አቅጣጫ በተጻራሪ በማኀበረ ቅዱሳን ላይ ያሰሙት ገለጻ ፤ የውንጀላና የፍረጃ መንፈስ የተጠናወተው ከመሆኑም በላይ ያልተፈለገ አደገኛ ውጤት ሊያስከትል እንደሚችል አስጠንቅቀዋል፡፡በስብሰባው ላይ ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን መዋቅሩን አጥንቶ ፋይናንሱን እኔ ካልያዝሁትና ካተቆጣጠርኩት ብሏል ፤ ስለዚህ አክራሪ ነው›› ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን ቤተክርስቲያቱ ከሰጠችው ደንብ ውጪ ይንቀሳቀሳል ፤ ስለዚህ አክራሪ ነው›› ‹‹ መንግሥት ማኅበረ ቅዱሳን አክራሪ ለመሆኑ አስገራሚ አስገራሚ ማስረጃዎች አሉት›› የሚሉና የመሳሰሉት ክሶችና ፍረጃዎች በስብሰባው ላይ ተሰንዝረዋል፡፡

የት/ቤት(መምህራን) አደረጃጀት አባላት እንዲሁም የተሰብሳው ተሳታፊዎች በበኩላቸው በቅርበት ጠንቅቀው የሚያውቋቸው በርካታ የማኅበሩ አባላት መኖራቸውንና ፍረጃውና ክሱ በማስረጃ መደገፍ እንዳለበት አለበለዚያ ማኅበሩን ይሁን አባላቱን ይገልጻቸዋል ለማለት እንደሚያዳግት በመጥቀስ ተቃውመዋል፡፡አወያዮቹ ማስረጃ እንዲያቀርቡ እና አነጋገራቸው እንዲያርሙ በጥብቅ ያስጠነቀቁት ተሳታፊዎች ፤ ውይይቱ በዚህ መንፈስ የሚካሄድ ከሆነ በተሳትፎ ለመቀጠል እንደሚቸገሩ በማሳወቅ ስብሰባው ጥለው ለመውጣት  ተነሳተው እንደነበርና አወያዩ አካል የመድረኩን መሪዎች በሌሎች በመተካት አስቸኳይ እርማት በማድረግ  በተሳትፏው ለመቀጠል እንደቻሉ ተጠቁሟል፡፡

ሌሎች ተሳታፊዎች በበኩላቸው ፤ ማኅበሩ ቤተክርስቲያቱ አጽድቃ በሰጠችው መተዳሪያ ደንብ መሠረት እንደሚንቀሳቀስና የፈጸማቸውም አበይት ማኅበራዊ የልማት ተግባራት ፤ የአገልግሎቱ እሴቶችና ትሩፋቶች ያስገኙትን አገራዊ ጠቀሜታዎች በመሰንዘር አስረድተዋል ፤ በተሰነዘሩት ፍረጃዎችና  ክሦች አንጻርም እውነታው በመግለጽ  ፍረጃውንና ክሱን ሕገ መንግሥታዊውን ሃይማኖት ነክ ድንጋጌ የሚጥስ ጣልቃ ገብነት ነው በሚል ኮንነውታል ፡፡ በሕግ አውጪነት ሉአላዊ ስልጣኗ አገልግሎቱን የፈቀደችለት  ቤተ ክርስቲያን እንኳን  ያላለችውን  ሕዝብን ሰብስቦ ማኅበሩን በአክራሪነት  መወንጀል የማኅበሩን ገጽታ ማጠልሸት ከሕዝቡ ለመነጠልና ሕዝቡን በማኅበሩ ላይ በማዝመት ተይዟል ብለው የጠረጠሩትን ዘመቻ  አካል ነው ብለው እንደሚዩትም አመልተዋል፡፡

የመድረኩ አወያዮች በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ለሰነዘሯቸው ክሶችና ፍረጃዎች ቅሬታ አቅራቢ ተሳታፊዎችን በግልጽ ይቅርታ መጠየቃቸው  ተገልጧል፡፡  ፍረጃው ክሱ ለውይይቱ ከተሰጣቸው ተሰብሳው የማድመጥ አቅጣጫ አልፈው የተናገሩት መሆኑን በማመን መሳሳታቸውን የገለጹት ‹‹ማንንም እንዳፈርጁ specific አታድርጉ ተብለናል ፤ የመላእክት ስብስብ አይደለንም ፤ ሰዎች ነንና እንሳሳታለን›› በማለት ነበር፡፡

ይሁንና ይህ ነው የተባለ ማረጃ ባይጠቅሱም  መንግሥት በሕግ የሚጠይቃቸው አንዳንድ ግለሰቦች ሊኖሩ እንደሚችሉ ሳይጠቁሙ አላለፉም፡፡  መንግሥትን በልዩነትና በግጭት ወቅት ሰላምና ፀጥታን ለማጠበቅ በሚል ካልሆነ በቀር በሃይማኖት ጣልቃ እንደመግባት ተደርጎ የቀረበውን አስተያየት አልተቀበሉትም፡፡

የውይይቱ አላማ  ኢሕአዴግ መራሹ መንግሥት ከአባሉና ከአጠቃላይ  ሕዝቡ አቋምና  ግንዛቤ  በመነሳት  በትምህክትና ጠባብነት የሃማት አክራሪነት ርዕዮት አራማጅነት በሚፈርጃቸው ወገኖች ላይ  በቀጣይ የሚዚው አሰላለፍና የምት አቅጣጫ ለመወሰንና  ይሁንታ ለማግኝት  የሚጠቀምበት ሊሆን እንደሚችል ብዙዎች ያምናሉ፡፡

  

6 comments:

  1. ibakachu mahiberu le ortodox bicha sayihon le hagerachinm tilik astewatsio alw silezi bakachihu atinekakut.......e/r mahiberu yibark amen........(D/N Endreas Tadele ke moyale)

    ReplyDelete
  2. እግዚአብሔር ከማህበሩ እጁን አያንሳ።

    ReplyDelete
  3. lebaw mengestachen menem biyawera borthodox kelede yelem ...... eneberta kerstiyanoche yemenafek meri new yemichaweteben

    ReplyDelete
  4. menafkan orthodoxen lematfat yemisrut sera new

    ReplyDelete
  5. “ሲነቅፉአችሁና ሲያሳድዱአችሁ በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብፁዓን ናችሁ”።(ማቴ 5:11)

    ReplyDelete
  6. ሲነቅፉአችሁና ሲያሳድዱአችሁ በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብፁዓን ናችሁ።

    ReplyDelete