Friday, April 25, 2014

‹‹ይህ የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራና የእነዚያ አባቶች በረከት መሆኑን እናምናለን››



  • ቀድሞ አፍሮ አይገባም መስቀልና እንዲሁም የጣና ቂርቆስ ገዳም የቅዱስ ያሬድ መስቀል  ወደ ኢትዮጵያ መመለሳቸው ይታወቃል፡፡
ቪዲዮውን በዚህ ይመልከቱ
(አንድ አድርገን ሚያዚያ 18 2006 ዓ.ም)፡-19ኛው ምእት ዓመት አካባቢ ከሰሜን ሸዋ እንደተወሰደ የሚነገርለት የመድኃኔዓለም ታቦት ዓርብ ሚያዝያ 17 ቀን 2006 .. ከጂቡቲ ወደ ኢትዮጵያ እንደገባ ለማወቅ ተችሏል፡፡በርግጥ ታቦቱ መቼ እንደተወሰደ፣ በማን እንደተወሰደና እንዴት እንደተወሰደ እየተጣራ ቢሆንም ወደ ኢትዮጵያ ሲመለስ ቦሌ አየር ማረፊያ ላይ አቀባበል ተደርጐለታል ጠቅላይ ቤተ ክህነት ሙዚየም ውስጥ የሚቀመጥ ይሆናል፡፡

(መምህር ሰሎሞን ለሪፖርተር)

በጂቡቲ ምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አለን፤ ጥቆማው የደረሰን ከዚያ ነው፤ በጂቡቲ የሚገኝ ግለሰብ ይሁን ምዕመን ባይገለጽልንም እርሱ ‹‹ቤቴ ውስጥ እጅግ ጥንታዊ ታቦት አለ፤ መጥታችሁ ውሰዱልኝ›› ይላል፡፡ እዚያ ያለው የቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ታቦቱን ወስደው በቤተ ክርስቲያን አስቀምጠውታል፡፡ ታቦቱ ከአገር አኳያ ወደ ክብሩ መመለስ አለበት በሚል እዚያ ካሉ አባቶች ለፓትሪያርኩ መግለጫ ቀርቦ እኛ ነገሩን በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል ስንጻጻፍ ቆይተን ዓርብ ሚያዝያ 17 ቀን 2006 .. ይገባል ብለን እየጠበቅን ነው፡፡ ከየት ቦታ እንደሄደ በግልጽ አላወቅንም፡፡ ከሰሜን ሸዋ አካባቢ እንደተወሰደ መረጃዎች አሉ፡፡ ቅርሱ ታቦተ መድኃኔዓለም ነው፤ ቅርሱ እጅግ ጥንታዊ ነው፡፡ 19ኛው ምእት ዓመት የነበረ ነው፡፡ ቅርሱ በመንበረ ፓትርያርክ ካረፈ በኋላ በትክክል ከየት ነው የሄደው የሚለው የማጣራት ሥራ ይካሄዳል፡፡ ጠያቂዎች በቂ መረጃ ይዘው ሲገኙ ሲኖዶሱ ወስኖ ወደ ቦታው የሚሄድ ይሆናል፡፡ በርካታ አባቶች ከጠላት ለማሸሽ የቀበሯቸውና ጠላት ከሄደ በኋላ የወጡ፣ አባቶች ሞተው የተረሱ ቅርሶችም አሉ፡፡ ቤተ ክርሰቲያኒቷ በቅርሶቿ ብዙ የመከራ ዘመናትን አሳልፋለች፡፡ እንዲያም ሆኖ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን በቂ የአገር ቅርሶች አሉ፤ የወጡትም በተለያየ ምክንያት እየተመለሱ ነው፡፡ ይህ ደግሞ የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራና የእነዚያ አባቶች በረከት መሆኑን እናምናለን፡፡ አፍሮ አይገባም መስቀልም ከስምንት ዓመታት በፊት፣ እንዲሁም ከዓመት በፊት የጣና ቂርቆስ ገዳም የቅዱስ ያሬድ መስቀል ከፈረንሳይ መጥቶ እዚህ ከተቀመጠ በኋላ ወደየገዳማቱ ተመልሰዋል፡፡ 

4 comments:

  1. Hi guys, would you please post in pdf format? therefore we can easilyr read from our phones.

    ReplyDelete
  2. Tewahido Hayal Kidus Nitsihit

    ReplyDelete
  3. /መቼስ መገኘቱ፣ እንዲሁም ወደ አገር ቤት መመለሱ እጅግ መልካም ነው። ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል ማደሪያ የሆነው ይህ ቅዱስ ታቦት፣ ...... ሲሆን ሲሆን ከየት እንደተወሰደ ተጣርቶ ባስቸኳይ ወደ ቦታው እንዲመለስ፣ ካልሆነም ሌላ ቤተክርስቲያን በማነጽ፣ ይህም ካልተቻለ አንዱ አብያተ-ክርስቲያን ውስጥ ተዳብሎ እንዲቀመጥ መደረግ ሲገባው፣ ያለስፍራው ሙዝየም ውስጥ ይቀመጣል መባሉ በእጅግ አስገርሞኛል። ወዴት እየሄድን ነው ጎበዝ?

    ReplyDelete