- ‹‹ማኅበረ ወይንዬ›› የተባለው የንግድ ተቋም የታገደበት ደብዳቤ ከቤተክህነት መዝገብ ቤት ሊገኝ አልቻለም፡፡
- ጸረ-ግብረሰዶማውያን ሀገራዊ ንቅናቄ ሃሳብ የተነሳው ከቤተክህነቱ ሆኖ ሳለ አቶ ደረጀ የራሱ በማስመሰል ሕጋዊ በመምሰል ከመስተዳደሩ ጋር ስራ ሲሰራ ነበር፡፡
(አንድ አድርገን ሚያዚያ 13 2006ዓ.ም
)፡-
የቀለም ቀንዱ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ እንደተረጎሙት ማኅበር ማለት ‹‹በቁሙ አንድነት ፤ ሸንጎ ፤ ብዙ ሰው ›› ማለት ነው
፡፡ በሌላም አተረጓጎም ‹‹ወገን ፤ ነገድ ፤ ቤተሰብ ፤ ጭፍራ ፤ ሰራዊት›› የሚል ትርጓሜ ተሰጥቶታል ፡፡ ጠቅለል ባለ
መንገድ ማኅበር አንድነትና ህብረትን የሚያመላክት ነገር ነው፡፡ ቤተክርስትያናችንም ወጣቶች በሰንበት ትምህርት ቤት ፤
አዛውንቶች ደግሞ በሰንበቴ ማኅበራት በመታቀፍ አንድነታቸውን የሚፈጽሙበት ሁኔታ አመቻችታላችዋለች ፡፡በዚህም ከ50 ዓመት በላይ
ስትሰራበት ቆይታለች ነገር ግን ከ1980 ወዲህ ቤተክርስትያኗ አስቀድማ ካስቀመጠችው አወቃቀር የተለየ በተለየ በ1990 ዎቹ
መጨረሻ የማኅበራት ቁጥር እጅግ እየበዛ መጥቷል፡፡
መልካም
ስራ ያላቸው ማኅበራ ቢኖሩም በብዛት በቤተክርስትያኗ መዋቅር ስር አይደሉም ፤ መልካም ስራቸውንም በአደባባይ ማሳየት አልቻሉም
፤ ቅዱስ ሲኖዶስም አያውቃቸውም ፡፡
ስለሆነም ከስሜቶቻቸው ጋር የሚጣጣም ማንኛውንም ነገር ተቀብሎ ለማስተናገድ የሚከለክላቸው ምንም
ነገር የለም፡፡ ለምን? ቢባል የቤተክርስትያን አስተምህሮ በአባላቶቹ ዘንድ በጠለቀ መጠን ስለማይታወቅ ነው፡፡ ስለሆነም
ቤተክርስቲያን የወጣቱን መንፈሳዊ ስሜትን ተረድታ ጉድለታቸውን ሞልታ በበሳል አመራር ለመልካም ነገር ልትጠቀምበት ይገባል ፡፡
በተለይ ጥምቀትንና የመስቀል በዓልን በደመቀ ሁኔታ ለማክበር ከተለያዩ ደብሮች የተሰበሰቡ ወጣቶች የላቀ ትኩረት
ያስፈልጋቸዋል፡፡ ቤተክርስቲያኒቱ በብዙ ድካም ልትሰበስባቸው ሲገባ ያለምንም ጥረት በፈቃደ እግዚአብሔር ተሰባስበዋልና ፤ እነዚህ
ወጣቶች የነገይቱን የቤተክርስቲያን ተረካቢ በመሆናቸው ቤተክርስቲያን ይህን መልካም አጋጣሚ ተጠቅማና ስሜታቸውን ጠብቃ
መሰረታዊውን የሀይማኖት ትምህርት በማስተማር ወደሚፈለገው ደረጃ ልታደርሳቸው ይገባል፡፡
በመላ ሀገሪቱ ማኅበራት አሁን ባሉበት ሁኔታ ልቅ ሆነው የተወሰነ መንገድ ከሄዱ ቀጣዩን ትውልድ
በቤተክርስትያን አቅፍ ውስጥ ለመምራት እና የቤተክርስቲያንን ቀኖና እና ዶግማ ጠንቅቀው እንዲያውቁ ለማድረግ እጅግ ያስቸግራል
፤ ነገ ይህን በብዙ ሺህ የሚቆጠር ማኅበር ለመቆጣጠርና ለመምራት ማጠፊያው እንዳያጥረን የብዙዎቻችን ስጋት ነው፡፡
በአሁኑ ሰዓት ለቁጥጥር በማያመች መልኩ በየቦታው በጥቂት
ሰዎች ፍቃደኝነት ላይ የሚመሰረቱ ማኅበራ ከጥቅማቸው ይልቅ ጉዳታቸው ሊያመዝን ይችላል ፡፡ ማኅበራት በአግባቡ በቅዱስ ሲኖዶስ
ስር የሚያደራጃቸው እና መንገዳቸውን የሚከታተል አካል ከሌለ ከቤተክርስቲያኗ ይልቅ የሀገርና የህዝብን ሰላም ሊያናጉ ይችላሉ
የሚል ስጋት አለ፡፡ እንደ ማኅበረ ማርያም የተሀድሶያውያን ማኅበር በጥቂት ሰዎች መዘውር ውስጥ ከገባ በኋላ ሀዋሳ ቅዱስ
ገብርኤል ላይ የፈጠሩትን ችግር እንደ ማሳያ መውሰድ ይቻላል፡፡ እነዚህ ማኅበራት ጉዳታቸው መናፍቃንን እና ከቤተክርስትያን
የታገዱ ሰዎችን በማካተት በማር የተለወሰ ውስጡ መርዝ የሆነ ስብከት ለምዕመኑ ይዘው መቅረባቸው ነው፡፡ ባለፉት ዓመታት በነዚህ
ማኅበራት አማካኝነት አጥንታቸው በወንጌል ያልጠነከሩ ወገኖቻችንን በየአዳራሹ እየሰበሰቡ ከመናፍቃን ዘንድ እንዲቀላቀሉ በማድረግ
የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳሉ ፡፡ አሁን ለማሰየት የፈለግነው በየጊዜው የተቋቋሙ መንፈሳዊ ማኅበራት ለቤተክርስትያን ያመጡትን
ጥቅምና ጉዳታቸውን ከወደፊት ስጋቶች ጋር ለማቅረብ ነው፡፡
በቤተክርስትያኒቷ ስር ያሉትን ማኅበራት በ5 ከፍለን ለማየት ወደድን
1. ክፍተትን ለመሙላት የተቋቋሙ
እነዚህ ማኅበራት ቤተክርስትያን በነበራት መዋቅር ልትሸፍነው ያልቻለችውን ክፍተት ለመሙላት
የተቋቋሙ ማህኅበራት ናቸው ፤ ክፍተትን ተረድተው ለመሙላት የሚቋቋሙ ናቸው እነዚህ ማኅበራት የአጭር እኛ የረዥም ጊዜ እቅድ
ይዘው የሚንቀሳቀሱ ሲሆኑ ለምሳሌ ህንጻ ቤተክርስትያን ለማሰራት ፤ እድሳት ለማከናወን ፤ ቤተክርስትያኒቷ የራሷ ተቋም
እንዲኖራት የሚሰሩ ፤ የተዘጉ ቤተክርስትያናትን ለማስከፈት ..እና መሰል አላማን ይዘው የሚንቀሳቀሱ ናቸው ፡፡ ዛሬ ማኅበራቱ
በመሰረቷቸው መልካም ሰዎች አማካኝነት ጠንካራ ማንነት ቢኖራቸውም እንኳን ነገ እነርሱን የሚተኳው ሰዎች ዓላማቸው ሊለወጥ የሚችልበት
ሁኔታ ከተፈጠረ የቤተክርስትያን ስጋት ከመሆን አያልፉም፡፡
2. የገጠሪቱን ቤተክርስትያን ለመርዳት በሚል የተዋቀሩ ማኅበራት
በገጠሯ ቤተክርስትያን ያሉ አገልጋዮች ያለባቸው ፈተና በጣም ብዙ ነው፡፡ የእለት ጉርሳቸውን
ለማግኝት ቀን ቀን ከእርሻ ጀምሮ በልዩ ልዩ ስራዎች ተጠምደው ይውላሉ ፡፡ ማታ ማታ ደግሞ በትግሀ ሌሊት እግዚአብሔርን
ሲያገለግሉ ያድራሉ፡፡ በብዙ መዋተት ያገለግላሉ ፤ በዚያ ላይ አልሞላ ብሏቸው ይኖራሉ ፡ ይህን ችግር ለመቅረፍ የሚቋቋሙ ማኅበራት
አሉ፡፡
እነዚህ ማኅበራት የሚያዩትን ችግር አቅማቸው በፈቀደላቸው መጠን ለመፍታት ብለው ተመሳሳይ ስሜትና
መንፈስ ያላቸውን ወንድሞችንና እህቶችን በማሰባሰብ በግለሰቦች ቅንነት የተመሰረቱ ማኅበራት ናቸው፡፡ አላማቸው እና ምልከታቸው
የሚደነቅ ነው ፤ ቤተክርስትያናት በጎደላት ጊዜ ደርሳችሁላታል ፤ ልትመሰገኑ ይገባል ፤ ነገር ግን ሩጫችሁን በድል ለማጠናቀቅ
ስለሚቀጥሉት ነገሮች ተወያይቶ መፍትሄ ማስቀመጥ ያስፈልጋል
ü ማኅበራቱ
የሚዋቀሩት በሰዎች ማንነት ላይ ተመስርተው ነው፡፡ ስለሆነም ግለሰቦች እንቅፋት በገጠማቸው ጊዜ በርካታ ተከታዮቻቸው የስብስቡን
አላማ ከግብ ለማድረስ ሊሳናቸው ይችላል ፡፡ በወንጌል ትምህርት ያልበሰሉ ከሆኑ ደግሞ ዓላማቸውን በጥቂት መሰሪ ሰዎች ቀይረው
መስመራቸውን ሊያስቷቸው ይችላሉ ፤
ü ማኅበራ
አቅማቸው በፈቀደ መጠን ገንዘብ አሰባስበው ወደ ገጠሯ ቤተክርስትያን በመውሰድ አገልጋዮች ካህናትንና ዲያቆናትን የተወሰነም
ቢባል ደመወዝ በመክፈልና ንዋያተ ቅድሳትን በሟሟላት የተቋረጠውን አገልግሎት እንዲቀጥል የተዘጋችዋን ቤተክርስትያን እንድትከፈት
፤ የተዳከመው እንዲበረታ በማድረግ ፤ የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው፡፡ በዚህ ጉልህ ድርሻ ጎን ለጎን ግን ስራው
ተጠንቶና ዘላቂነቱ ተረጋግጦ የተጀመረ ባለመሆኑ በየወሩ የሚያወጡት ገንዘብ ከጊዜው የኑሮ ሁኔታ ጋር እየከበዳቸው ይሄዳል ፤
እንቅስቃሴያቸውም በጊዜያት ሂደት እየቀዘቀዘ ይመጣል ፤ በመሆኑም አባላት ወርሐዊ ክፍያቸውን ድንገት ሲያቋርጡ ማኅበራቱ
የሚያቀርቡት ገንዘብ ያጡና የጀመሩት ስራ ይቋረጣል፡፡ ይህን የመሰለ ችግር ወደፊት ለስራቸው እንቅፋት እንደማይሆንባቸው
አውቀውት ቢገቡበት መልካም ነው፡፡
3. ቁጭት የመሰረታቸው ማኅበራት
አህዛባዊ ግብር ባላቸው አካላት በቤተክርስትያን ላይ በደረሰው ጉዳት አንገብግቧቸው በቁጭት
የተመሰረቱ ማኅበራትን ይመለከታል ፤ ከአህዛብያውያን አኩይ ግብር የተነሳ አብያተክርስያናት በእሳት እንዲጋዩ ፤ ካህናትና
ምዕመናንም በቤተ መቅደሳቸው በሰይፍ ሲታረዱ ፤ ቤተክርስትያን ላይ እሳት ሲሎከስባት ፤ በየቦታው የሚገኙ ክርስትያኖች ላይ
ክርስትያን በመሆናቸው ብቻ ችግር ሲደርስባቸው ባዩ እና በሰሙ ጊዜ አዝነው መፍትሄ ለማምጣት ብለው ወጣቶችን በማሰባሰብ
የመሰረቸቷው ማኅበራት ናቸው ፡፡ የማኅበሩ አባላት በቤተክርስትያን ባላቸው ጥልቅ ፍቅርና ተቆርቋሪነት የተሰባሰቡ ናቸው፡፡ ስለ
ቤተክርስያን ስርዓት አስተምህሮ ዶግማ እና ቀኖና ያላቸው እውቀት አናሳ ቢሆንም ፍቅራቸውና መቆርቆራቸው ግን በጣም ጥልቅ
ነው፡፡
ቤተክርስያኗ ላይ አንድ ፈተና ቢመጣ እንኳን ከሁላችንም ይልቅ ቀድመው ከፊት የሚቆሙ ናቸው፡፡
እንዲህ አይነት ቅናትና መቆርቆር ይዞ የመጣን ሰው ደግሞ በአግባቡ ተቀብሎ ማስተናገድ የቤተክርስያኒቱ ተግባርና ሀላፊነት
ይመስለናል ፡፡ መንፈሳዊ ከመሆን ጋር የሚመጣውን ፈተናና የቅዱሳንንም ሕይወት በውል ስለማያውቁ ትከሻቸው መከራንና መገፋትን
ለመሸከም አይችልም፡፡ ስለዚህ በጥሞና እያስረዱ መስመር እንዲገቡ ቅንነታቸውና መቆርቆራቸው ወደ ተስፋ መቁረጥ እንዳይቀየር
መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡
እንደዚሁም አብዛኛው እንቅስቃሴያቸው ስሜት የተቀላቀለበት ስለሆነ ቀስ በቀስ ጉዳት እንዳያደርስ
ቤተክርስትያን ብርቱ ጥንቃቄ ማድረግ ይጠበቅባታል ፡፡ አንዳንድ ተምረው ምግባረ ብልሹ የሆኑ ግለሰቦች ተቀላቅለው መስመር
እንዳያስቷቸው ፤ ቤተክርስትያኗ ባላት መዋቅር ውስጥ ገብተው እንዲማሩ እና እንዲያገለግሉ በለዘበ ቋንቋ እስከሚገባቸው ድረስ
ማስረዳት ይኖርባታል፡፡
ያላቸው ጥልቅ ስሜትና ተቆርቋሩነት ለቤተክርስትያን ስርአት አስተምህሮ ካላቸው እንግድነት ጋር
በድምር ተጠቅመው የቤተክርስትያኒቱን ጉዞ ለማደናቀፍ እንቅልፍ አልባ የሆኑ ቡድኖች ወደ አልሆነ አቅጣጫ እንዳይመራቸው መጠበቅ
ያስፈልጋል፡፡ የወቅቱ ስልታቸው እቅዳቸው ይህው መሆኑን የተለያዩ የመረጃ ምንጮች ይጠቁማሉና፡፡
4. የንግድና የኑፋቄ ስራን ለመስራት የተቋቋሙ ማኅበራት
በዚህ መስመር ያሉ ማኅበራት የሚያንጹና የሚያስተምሩ ሳይሆኑ ስሜት የሚነኩ የተለያዩ ስራዎችን
በመስራትና ንግዱ በዚህ መስመር ያዋጣል ብለው ሲያምኑ የቤተክርስትያኒቱን ሃላፊዎች ሳይቀር ስድብ በመሳደብና በማዋረድ ወደ
ሕዝብ የሚገቡ ፤ አላዋጣ ሲላቸው ደግሞ እያወቁ ያዋጣናል ብለው የገቡበትን መስመር ጥለው ያለ ጥቂት ሀፍረት እንደ እባባ
አቅጣጫ ቀይረው የሚጠመዘዙ ናቸው፡፡
በኑፋቄ ተልእኮታቸውና ስሜት የሚነኩና ልቅ የሆኑ ትምህርቶቻቸውና መዝሙሮቻቸው ምዕመናን
ለቤተክርስያኗ ስርአት የነበራቸው ጥብቀት እንዲላላ ፤ ተቆርቆሪነታቸውም ደረጃ በደረጃ እየተሸረሸረ እንዲሄድ የሚሰሩ ተቋማት
ናቸው፡፡ በትኩረት ከተመለከትነው የዘወትር ስራቸው ምእመናን ቤተክርስትያኒቷን እንዲከተሉ ፤ ቅዱሳንን እንዲወዱ ፤ ፈሪሀ
እግዚአብሔር እንዲኖራቸው ፤ እግዚአብሔርን እንዲያመልኩ እና ለጽድቅ የሚያበቃ ስራ እንዲሰሩ ሳይሆን የእነሱ ደጋፊዎችና የንግድ
አጋሮቻቸው እንዲሆኑ ማድረግ ተቀዳሚ አላማቸው ነው ፡፡ አንድ ጊዜ አውደምህረት ላይ አንዱ አሁን ከአውደ ምህረት የታገደ ሰው
ፕሮግራሙ ካለቀ በኋላ ህዝቡን እስኪ አንድ ጊዜ እጃችሁን ወደ ላይ አለ ፤ ምዕመኑም እጁን ወደ ላይ በማውጣት ተባበረው ፤
ከዚያ ቃል ግቡልኝ ካለ በኋላ ‹‹በማርያም ይህን ካሴት አንድ አንድ ግዙኝ›› ብሎ አረፈው …ይህ ሰው መጀመሪያም የመጣው
የእግዚአብሔርን ቃል ለመስበክ ሳይሆን ካሴት ለመሸጥ ነው፡፡
እነዚህ ማኅበራት ምዕመናን ወደ ቤተክርስትያን የእግዚአብሔር ጉባኤ ሳይሆን የእገሌ ጉባኤ አለ
ብለው እንዲመጡ በማድረገስ ስራዎችን ቀድሞ ሱሰሩ ነበር፡፡ ለእነዚህ አይነት ቡድኖች ማኅበራት ቤተክርስትያን ልዩ አይን ሊኖራት
ይገባል፡፡ ሲመች የሚሰሩ ሳይመች ምድር ቀደው የሚገቡ ቢሆኑም ቤተክርስትን ያላት ህጋዊ መብት ተጠቅማ ቢያንስ ይፋዊ
እንቅስቃሴያቸውን መግታት ይኖርባታል፡፡
በአዲስ አበባ ውስጥ ‹‹ወይንዬ ተክለሀይማኖት›› በሚል ስም የተቋቋመ ማኅበር ስሙ የማያውቅ
ምዕመን አለ ብለን አንገምትም፡፡ ይህ ማኅበር ከደብረብርሀን በ5 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝው የአባታችን የአቡነ
ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያንን ለመርዳት መሰረት አድርጎ የተመሰረተ መንፈሳዊ ማኅበር ነበር ፡፡ በገዳሙያለውን ችግር መሰረት አድርጎ ለመርዳት በማለት በአቶ ደረጀ
አማካኝነት ከ10 ዓመት በፊት ማኅበሩ ተቋቋመ፡፡ መጀመሪያ አካባቢ ጥቂት ብሮችን እያመጣ ለቤተክርስቲያኑ ይሰጥ ነበር፡፡ ከዚያ
ግን ስሙን በመጠቀም ብቻ በርካታ መቶ ሺህ ብሮችን ቢሰበስብም ይህ ነው የተባለ ለውጥ ቦታው ላይ ማየት አልተቻለም፡፡ ከዓመታት
በፊት ስለ ወይንዬ ተክለሀይማኖት በሰራው የቪሲዲ ስራ በምድረ አሜሪካ የሚገኙ አንድ አባት በሱ የባንክ አካውንት 50ሺህ ብር
ልከውለት ነበር፡፡ እኝህ አባት ቤተሰብ ለመጠየቅ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ፤ የተጀመረው ቤተክርስቲያን ያለበትን ሁኔታ ለመመልከት
ወደ ቦታው ሄደው የሰበካ ጉባኤውን ሲያናግሩ ምንም አይነት ብር እንዳልደረሳቸው ይገልጹላቸዋል ፡፡ እኝህ አባት በጊዜው በጣም
ተናደው ፤ ገንዘባቸው ለቤተክርስቲያኒቷ እንዳልደረሰ ተገነዘቡ ፤ ብራቸውም ጅብ እንደበላው አውቀው ፤ አቶ ደረጀን ፍርድ ቤት
በዚህ ጉዳይ አቁመውት ነበር ፤ አቶ ደረጀም በጊዜው በወሎ ላስታ አካባቢ የማይታወቅ ቦታ በመጥራት እዛ ላለው ተክለኃይማኖት
ቤተክርስትያን ነው የሰበሰብኩት በማለት መልስ ሰጥቷል ፡፡
ü ይህ
ሰው ‹‹ወይንዬ ተክለሃይማኖት››የሚለውን ስም አሁን እንኳን መልስ ቢባል ፍቃደኛ አልሆነም ፤ በማኅበሩ ስም የሚያገኝው ገንዘብ
ስለሚቋረጥ የእሱም እስትንፋስ የማኅበሩ ስም ስለሆነ ለሚመለከተው አካል የማኅበሩን ስም መመለስ አልፈለገም፡፡ ቤተክህነቱ በማኅበሩ ስም ያካበትከውን ሀብትና የሚሰራበትን ማህተብ
አስረክብ የሚል ደብዳቤ ቢያደርሰውም የማኅበሩን ንብረት ብሎ
የመዘገባቸውን ንብረቶች ለመመለስ ፍቃደኛ አልሆነም፡፡ አሁንም ቤተክህነቱ ይህን ተቋም ቢያግደውም ‹‹ወይንዬ ተክለኃይማኖት››
የሚለውን ስም እንደ Trade Mark እየተጠቀመበት ይገኛል፡፡ ከቀናት በፊት ሪፖርተር ጋዜጣ ላይ ወጥቶ የነበረው ጸረ ግብረሰዶማውያን
ስብሰባን በማስተባበር ማኅበረ ወይንዬ ስሙ ተነስቶ ነበር ፤ ይህን ሕገወጥ የመጠቀሚያ ስም የቤተክህነቱ
ጽ/ቤት ህጋዊ እንዳልሆነ እና በቤተክርስቲያኒቱ መዋቅር ስር ያልሆነ ተቋም መሆኑን ገልጾ ለአዲስ አበባ መስተዳደር ደብዳቤ ጽፎ
ነበር ፤ ደብዳቤው በሚጻፍበት ወቅት ማኅበሩ የታገደበትን ደብዳቤ ከቤተክህነት መዝገብ ክፍል ላይ ማግኝት አልተቻለም ነበር፡፡ አቶ
ደረጀ በረዥም እጁ እሱን የሚከሱ ከእሱ ጋር የተያያዙ ሰነዶችን ሁላ ከቤተክህነት መዝገብ ቤት ጠራርጎ ማስወጣት ችሎ ነበር፡፡ ይህ
የተገነዘቡት የቤተክህነት ሃላፊዎች ዋናውንና ደብዳቤ ጉዳዩ ከሚመለከተው ሀገረ ስብከት በማስመጣት የታገደበትን ምክንያት እና የታገደበትን
ሁኔታ በመግለጽ ለአዲስ አበባ መስተዳደር የተጻፈውን ደብዳቤ አጋዥ
በማድረግ ችለዋል፡፡ አቶ ደረጀ የታገደበትን ደብዳቤ ደብዛውን በማጥፋት ሂደት ከቤተክህነቱ መዝገብ ቤት በተጨማሪ የሰሜን ሸዋ ሀገረ
ስብከት መዝገብ ቤት ያለውን ሰነድ ለማጥፋትም ሞክሮ ነበር ፤ ባይሳካለትም ፡፡
በቅርቡ የፀረ ግብረ ሰዶማዊነት ሰላማዊ ሠልፍ ሃሳብ የተሰረዘው በቤተ ክህነት ጥያቄ ቢሆንም
ይህን በሚመለከት ቪሲዲ ያሳተመው አቶ ደረጀ የሱ ሃሳብ እንደሆነ
በማስመልከት ከአዲስ አበባ መስተዳደር ጋር ሥራዎቹን በሕገወጥ ማኅበሩ አማካኝነት ሲሰራም ነበር፡፡
ከጀርመን ሀገር እሱ የሰራውን
የወይንዬ ተክለሀይማኖት ሲዲን የተመለከቱ ከ10 በላይ ሰዎች በጣም በርካታ ብር በመላክ በአቶ ደረጀ አካውንት ተልኮለት
ነበር፡፡ ከላኩት ሰዎች አንዱ ሰው ወደ ኢትዮጵያ ሲመጣ የላክነው ብር የተጀመረውን ቤተክርስትያን ምን ያህል ደረጃ ላይ
እንዳደረሰው ቦታው ላይ ሄደው ሲመለከቱ ቪሲዲ ላይ ካዩት ምንም ሳይቀየር ያገኙታል ፤ ከዛ በጊዜው የነበሩት የህንጻ አሰሪ
ኮሚቴ አባላት ምንም እንዳልደረሳቸው ያስረዷቸው ፤ ምን ያህል ብር እንደላኩ ሲጠየቁ ፤ ‹‹ተውት በቃ ልጆቼ ያልደረሰ ብር
ብነግራችሁ ምን ይሰራላችኋል ትርፉ መናደድ ነው›› ብለው ቅስማቸው ተሰብሮ ወደ መጡበት ወደ ጀርመን ሊመለሱ ችለዋል፡፡
ሌላ አስገራሚ ነገር ደግሞ የዚህው ግለሰብ ሚስት ኑሯቸውን የሚገፉበት ፤ ልጆቻቸውን የሚያስተምሩበት በጠቅላላው የሚተዳደሩበት ብር የቤተክርስትያን ብር መሆኑን ስለምታውቅ ነገሩ ለጭንቅላቷ እረፍት ስለነሳት ብጹእ አቡነ ኤፍሬም ጋር በመሄድ ፤ ‹‹ከዚህ ሰው ጋር አብሬ መኖር አልፈልግም አፋቱኝ›› ስትላቸው ፤ እሳቸውም ለምን ልጄ ? በተክሊል ተጋብታችሁ እንዴት እንዲህ ትያለሽ ? ይህ ተገቢ አይደለም ብለው ሀሳቧን እንድትቀይር የአባትነት ምክር ሲመክሯት ፤ እርሷም አባታችን ‹‹እኛ እስከ አሁን የምንኖረው ለወይንዬ ተክለሃይማኖት ተብሎ በሚላከው ገንዘብ ነው ፤ ከአሁን በኋላ በዚህ ብር መኖር አልችልም ፤ ውስጤም እየተጨነቀ ነው›› ብላ ተናግራለች ፤ እሳቸውም በጊዜው ምን እንደሚደርጉ ግራ ገብቷቸው ነበር፡፡ አባታችን ምንም ባይሉም እርሷ ይህን ሁሉ እያየች መኖር ስላልቻለች በጊዜው ፍቺ ፈጽማ ነበር፡፡
አባታችን አቡነ ኤፍሬም በየጊዜው የሚሰሙት እሰጣ ገባ ስለሰለቻቸው ‹‹ልጅ ደረጀ እባክህን
የሀገረ ስብከቴን ስም አታበላሽ ፤›› በማለት ተግሳጽ ተናግረውት ነበር ፡፡ አቶ ደረጀ የወይንዬ ተክለኃይማኖት ማኅበር ስራ
አስኪያጅ ብዙ ጊዜ ተመክሮ እና ተዘክሮ እምቢ ስላለ ሰዎች የእርሱን ነገር ለእግዚአብሔር አሳልፈው ሰጥተዋል ፡፡ ሰው ልቡን
እንዳያደነድን መጽሀፉ ያዛል ፤ ልቡን ያደነደነ ደግሞ ሳያስበው እግዚአብሔር ህይወቱን እንደሚቆርጣት ተፅፏል፡፡ ይህ ካሉት
መንፈሳዊ ስምን ከተላበሱ የንግድ ማኅበራት አንዱ ነው
የስብከተ ወንጌል ሰራተኞችና ሰ/ት/ቤቶች ምዕመኑ እገሌን ብሎ ሳይሆን እግዚአብሔርን ብሎ ወደ
ቤተክርስትያን እንዲመጣ ተግተው መስራት ይኖርባቸዋል፡፡‹‹ሀጥያተኛ በሃጥያቱ ይጠፋል ደሙን ግን ካንተ እሻለሁ›› ያለ አምላክ
እግዚአብሔር እንድታገለግሉ በሰጣቸው እድል መጠን ይጠይቃችዋል፡፡ በየትኛውም ደረጃ ላይ የሚያገለግሉ የቤተክርስትያኒቷ መሪዎች
በሚያልፍ ዘመናቸው የማያልፍ መከራ አስቀምጠው እንዳይሄዱ ልጠነቀቁ ያስፈልጋል፡፡
5. የስነ ምግባር ያለባቸው ግለሰቦች የመሰረቷቸው ማኅበራት
በመጨረሻ ደረጃ የምናያቸው ማህራት በተለያዩ ስነ ምግባር ችግሮች ከሰ/ት/ቤት ወይም በድምሩ
ከቤተክርሰትያን አገልግሎት የታገዱና ለቤተክርስትያኗ አስተዳር ከላይ እስከ ታች ጭፍን ጥላቻ ያላቸው ግለሰቦች የሚያቋቁማቸው ማኅበራት
ናቸው፡፡
እነዚህ ማኅበራት በቁጥር እጅግ ብዙ ናቸው፡፡ ስራቸውም በተጨባጭ ይሁን በተፈጠረ ምክንያት
ምዕመናን የቤተክርስትያን አስተዳደር በጥቅሉ እንዲጠሉ ማድረግና ቤተክርስትያን ውስጥ ቢሆኑ ልናገኝ እንችል ነበር ብለው
የሚያስቡትን ማኛውንም ጥቅማ ጥቅም የማስጠበቅ ዓላማን አንግበው የሚንቀሳቀሱ ናቸው፡፡ ግለሰቦች ከቤተክርስትያን አገልግሎት
የታገዱት በፈጠሩት የስነ ምግባር ችግር አማካኝነት ሆኑን ማሰብ አይፈልጉም፡፡
እኛ ምዕመናን ስለ ማኅበራት ያለንን አመለካከት አሁን እናስተካክል ፤ እኛው ተሰናክለን ሌላውን
አናሰናክል ፤ ሳናውቅ ለቤተክርስትያን የእግር እሳት አንሁንባት ፤ ይህን የማኅበራት ችግር አሁን መፍታት ካልቻልን ነገ ከዚህ
የባሰ ነገር ስለሚፈጠር መጀመሪያ ራሳችን የቆምንበትንና ያለንበትን ማኅበር እንመርምር ፤ እንደ በግ ከመነዳት ራሳችንን
እንጠብቅ ፤
‹‹ነገን ለማስተካከል ዛሬን ተግተን እንስራ››
We told you several times not to accuse individuals. This person is not hertic as far as I know. In fact his earlier VCD was opposing Menfkan. The VCD on sodomites underworld in Ethiopia is appreciable work even if the producer gains from it financially. If he has weakness we shall pray for him and advise hm. You are committing great sin by exposing sins of individuals! The so called MK self appointed supporter website, you are sentimental and you make many enemies for MK!
ReplyDeleteAmen
This is one of MK supporters behaviour. We all know how MK is good for our church. But the web site like this kills MK. MK is not for hate. MK is not for fight back. MK is not selfesh. So I beg MK true members to stop some extrimist like this web site.
ReplyDeleteyeh hulu sihone abeageritu west heg yelem woy.አቡነ ኤፍሬም yen yakil yemiyawkut kehone lemin kemehaberu merinet yesiltan derega alweredutim. mekniyatum sew temekro, tegesesto kaltemelese lebetekristyan dehininet sibal ermiga mewesed neberebet. MK degmo yehulu merega kalew eskahun mineyesera neber.Ahun chegeru ketefetere bewale were kemarageb askedimo minsera.yehmale degmo MK endelelaw yealem mediyawoch were manafes new. yealem mediyawoch chigeru kemefeteru befit yemefteh hasab kemafelaleg yilk chigeru sifeter lezigijitachew demket,leadimach sabinet video mekirest new sirachew.ene bizu gize bendi aynet melku yemiwetu hitmetoch lay tekawimo alegn.lemin akerebachew yemil hasab yelegnm neger gin yechigirun sir kawekachew lemin askedimachew yetechalachewn atadergum?...Adrigachewm kehone lemin yederesachewbetn derega lehizb ataswikum? minalbatim negeroch keakimachew belay kehone askedimachew silehunetaw lemin lehizbu ataswiku?....alebeliziyama yekushina were amelalash sira new yemitiserut....I am sorry for every thin happening to my church...
ReplyDelete