Wednesday, February 1, 2012

300ሺህ ብሩ የት ገባ ?

  • በዝግ ሂሳብ ባንክ ገብቷል - ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኢጲፋንዮስ

(አንድ አድርገን ጥር 23 ፤ 2004ዓ.ም)፡-  በምዕራብ ሸዋ ሐገረ ስብከት (ዞን) የሚገኙ ምዕመናን ለገጠር አብያተክርስትያናት ተብሎ የተዋጣ 300 ብር በላይ የት እንደገባ እንደማያውቁና ሳይመዘበር እንዳልቀረ ሰሞኑን ተናገሩ፡፡ ገንዘቡ የተዋጣበት የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በዞኑ ዋና ከተማ በአምቦ አለመከናወኑ ጥርጣሬ አሳድሮብናል ብለዋል - ምዕመናኑ፡፡ በምዕራብ ሸዋ ሐገረ ስብከት (ዞን) የአስተዳደር ችግር እንዳለ የጠቆሙት ምዕመናኑ፤ ሥራቸውን በአግባቡ ሲወጡ የነበሩት ከሃላፊነት ተነስተው መሾም የማይገባቸው ተሹመዋል እንዲሁም አምቦ አካባቢ የሚገኘው የአዋሮ ቅዱስ ሚካኤል መሬት ተሸንሽኖ ለግለሰቦች እየተሸጠ ነው ሲሉ ቅሬታቸውን ገልፀዋል፡፡

የምዕራብ ሸዋ ሀገረስብከት ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኢጲፋንዮስ ስለተነሱት ቅሬታዎች  በሰጡት ምላሽ፤ ለገጠር አብያተክርስትያናት ተብሎ 450 ብር መዋጣቱንና 300 ብሩ በዝግ ሂሳብ ሐገረ ሕይወት ቅርንጫፍ አምቦ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መግባቱን ገልፀው፤ 150 ብሩ ግን ገና ገቢ እንዳልተደረገና ቃል የገቡ ግለሰቦችን በማነጋገር ላይ እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡ ሊቀጳጳሱ የአዋሮ ቅዱስ ሚካኤል መሬትን ጉዳይ በተመለከተም መሬት የመንግስት በመሆኑ መሸጥ መለወጥ እንደማይቻል ጠቁመው የቤተክርስቲያኑ መሬት አላግባብ ተሸጠ ስለሚባለው ጉዳይ መረጃ እንደሌላቸው ገልፀዋል፡፡ ጳጳሱ ከሃላፊነት ያለ አግባብ ተነሱ ስለተባሉ ሰዎች በሰጡት አስተያየት፤ ሁሉም ሹምሽሮች በቤተክርስትያኒቱ ሥርአት መከናወናቸውን ተናግረዋል፡፡

1 comment: