Monday, March 24, 2014

ቤተ ክርስቲያንን የማፈራረስ የቀደመ ሴራ ሲያገረሽ



(አንድ አድርገን መጋቢት 15 2006 ዓ.ም )፡- አሁን መንግሥት በቤተክህነት ጥቂት ደጋፊዎችና በቆየ የውስጥ አላማው አማካኝነት ሊሰራ አስቧል የተባለው ማኅበረ ቅዱሳንን አመራሮች እና ቀጥሎም ማኅበሩን የሚከስ ዘጋቢ ፊልም ነገሩን ከአንድ ማኅበር ጋር ብቻ የሚያያይዙት አልጠፉም ፤ ነገር ግን ማኅበረ ቅዱሳን እና ቤተክርስቲያን የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ መሆናቸው እስከ አሁን የገባቸው አይመስልም ፡፡ ባሳለፍናቸው 20 ዓመታት በርካታ ሥራዎችን በቤተክርስቲያኒቱ የእዝ ሰንሰለት ስር በመሆን ማኅበረ ቅዱሳን መስራቱ በአይን የሚታይ በእጅ የሚዳሰስ እውነት ነው፡፡ ጠላት ግን የሚታየው የባለፈው መልካም ሥራ ሳይሆን የወደፊቱ የእንቅፋት መንገድ ስለሆነ ዛሬ ላይ ይህን እግዚአብሔር የሚገኝበትን ረዥም ጉዞ ለማደናቀፍ በይፋ ሃይማኖተኞችም ፖለቲከኞችም ሳይሆኑ አንድን አላማ ለማሳካት በአንድ ጉባኤ ተሰብስበዋል ፡፡ ይህ ፊልም እንደተባለው ተሰርቶ ለእይታ የሚቀርብ ከሆነ ቀጥሎ ምን ሊከሰት እንደሚችል ለመገመት ነብይነትን አይጠይቅም ፤ ቤተ ክርስቲያኒቱ እንዲህ ባለበት አንድም ሰው ባጣችበት ጊዜ ላይ ፤ ሲኖዶሷ ለሁለት በተከፈለበት ፤ ሙሰኝነትና ዘረኝነቱ ጣራ የደረሰበት ፤ ሁሉም ሰሚ እንጂ ተናጋሪ አንደበት የሌለው ይመስል ዝም ባለበት ጊዜ የቤተክርስያኒቱ እምነት ፤ ሥርዓትና ትውፊት ትውልድ እንዲያውቅ ፤ አብነት ትምህርት ቤቶቿ ከመዘጋትና ከተማሪ ድርቅ ከመመታታቸው በፊት የቻለውን ያህል እያደረገ ዘለቄታዊ ካህናትና ዲያቆናት መሰል አገልጋዮች እንዲወጡ የበኩሉን ትንሽ የማይባል ሥራ እየሰራ የሚገኝውን ማኅበር በቤተክህነቱ ውስጥ የቀድሞ ስርዓት ርዝራዥ በሆኑ ሰዎች አማካኝነት ይሰራበታል የተባለው ዘጋቢ ፊልም የሚዘጋጅ ከሆነ ውድቀቱ ከአንድ ማኅበር ይልቅ የቤተክርስቲያኒቱ መሆኑን ልንገነዘብ ይገባናል፡፡


ከዓመት በፊት የአቡነ ጳውሎስ  ዜና እረፍተ ከተሰማ በኋላ ሃዘን ለመድረስ የመጡት የህወሀት የቀድሞ ከፍተኛ አመራር  ቤተ ክርስቲያኒቱ ሃገራዊ ግዴታዋን ስትወጣ የነበረች፣ ለወደፊቱ ታላቅ ሚና ሊኖራት የሚችል ስለኾነች አሁን የት አለች ብለን እናስብ በማለት በቤተክህነት አዳራሽ በተቀመጠው ደብተር ላይ ማስፈራቸው ይታወቃል፡፡ አዎን በቤተክርስቲያን ላይ የሚደረጉ ሴራዎችን የሚመሩት የሚያሳልጡትና መነሻ እና መድረሻቸውን አስልተው የሚጓዙት ፖለቲከኞች በአደባባይ እንዲ ይሉናል ፤ ዘወር ብለው ደግሞ ቤተክርስቲያኒቱ ሀገራዊ ያላትን ተሰሚነት ለመቀነስ በፖለቲከኞች የእዝ ሰንሰለት እንድትወድቅ እና አድራጊ እና ፈጣሪዋን እንድትለይ የኮሜዲ ድራማ ስክሪፕት ሃሳብ ያመነጫሉ ፡፡ አንዳንዴ የሚያገኙት ጥቅም አይናቸውን ያሳወራቸው የውስጥ እና የውጭ ጠላቶች ደግሞ በትህምክት ባህር ውስጥ የሰመጡ ትህምክተኛ ሆነው ሳለ የ“ትምክተኞች” መሰብሰቢያ ብለው ሲናገሩ ይስተዋላል፡፡


ቀድሞ በቤተክርስትያናችን አባቶች ላይ የተከፈተው የስም ማጥፋት ዘመቻ የምናስታውሰው ነገር ነው ፤ አባቶች ሲሰደቡ ቤተክርስቲያን መሰደቧን ጭምር የምናውቅ ሰዎች ጥቂት ብንሆንም ፤ አሁን ደግሞ አንድ ላይ መስደቡ የማያዋጣ ስለመሰላቸው በተናጥል የመምታት ዘመቻ ውስጥ ሊገቡ እንደሆነ የሚሰሙትና የሚታዩት ነገሮች እያመላከቱ ይገኛሉ፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ ፍቃድ ሰጥቶት በተሰጠው ፍቃድ የሚንቀሳቀስን መንፈሳዊ ማኅበር አንደበት አውጥተው ሲሳደቡ ለሰማቸውና ጽሁፋቸውንም ላነበበ ሰው ቢዘገይም የሚደገስ ታላቅ የተንኮል ድግስ መኖሩ የማይቀር መሆኑ ይገባዋል፡፡ ጠላት የቤተክርስቲያኒቱን መሰረት ለመናድ ጥልቅ ጉድጓድ ቢቆፍርም መሰረቷን ሊያገኝው በሰውኛ ሃሳቢ ሊበታትናት ግን አይቻለውም፡፡ ቅዱስ መጽሀፉ ጠባቂዋ አያንቀላፋም ብሎላታልና፡፡
  
እስኪ ህወሀት(ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ) በቤተክርስትያን ላይ ያለውን አቋም ቀድሞ ምን እንደሚመስልና አሁን ሀገሪቱን እያስተዳደራት የሚገኝው የብሔር ተኮር ፓርቲዎች ስብስብ(ኢህአዴግ) እዚች አንዲት ቤተክርስቲያን ላይ እቅዱ ምን ነበር? የሚለውን የሚታወቅ ታሪክ ዘወር ብለን ለመመልከት እንሞክር፡፡

የህወሀት( ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ) መስራችና ኮማንደር የነበሩት ያያኔው ታጋይ ያሁኑ ዶክተር አረጋዊ በርሄ A Political History of the Tigray People’s Liberation Front ( 1975-1991) የተሰኘ መጽሐፍ ማሳተማቸው ይታወቃል። መጽሐፉ አስራ ሁለት ምእራፎችና 355 ገጽ ያሉት ሲሆን በይዘቱም በርካታ ጉዳዮችን ይዳስሳል።

የመጽሐፉ ደራሲ ደግሞ የህወሀት የፖሊት ቢሮ አባልና ከህወሀት ጥንሥስ ጀምሮ ፖሊሲ አውጪ አመራር ስጭና አዋጊ ስለነበሩ በተራ አባላቶቸ የማይታወቁ በርካታ ሚስጥሮችን በመጽሐፋቸው ይፋ አድርገዋል። መጽሀፉ ስለ ብሔር ፓለቲካ አደገኛነት ስለ ማሌሊት ማኒፌስቶ 1976 አና ትግራይን ስለመገንጠል የነበረውን ውዝግብ ስለ ስብሀት ነጋና መለስ ሚስጥራዊ ሰንስለቶች ስለ ጦርነቱ ከኤርትራው ኢሳያስ ጋር ስለነበረው ፍቅርና ጠብና አሁን ድረስ እያዋጉ ስላሉት መሰረታዊ ምክንያቶችና ሌሎች ብዙ አስገራሚ ሚስጥሮችን ይተነትናል።

እኔን ግን የሳበኝ ህወሀት ወይም ወያኔ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስቤተ ክርስቲያንላይ ከበረሀ ጀምሮ የሰራውን ደባ የሚያትተው ክፍል ነው።ዶክተር አረጋዊ በዚሁ መጽሀፋቸው ምእራፍ አስር ላይ “Neutralizing the Church and Mobilizing Muslims “ በሚለው ንኡስ ርእስ ስር ህወሀት የኢትዮጵያ ተዋሕዶቤተ ክርስትያንን እንዴት እንደተዋጋትና አሁን ቤተ ክርስትያና ውስጥ የሚታዩት አበይት ችግሮች በሙሉ ህወሀት ከበረሀ ጀምሮ ያቀዳቸው መሆኑን በዝርዝር አስቀምጠውታል።




ወያኔ ቤተ ክርስቲያንን መታገል ለምን ፈለገ?
ይህን መጽሀፍ ሳነብ ዋናው ጥያቄዬ የነበረው ወያኔ ቤተ ክርስቲያንን መታገል ለምን ፈለገ? “ የሚለው ነበር። ወያኔ በወቅቱ ቤተክርስትያንን አምርሮ መታገልና ማዳከም የፈለገበትን ምክንያቶች ዶክተር አረጋዊ አንድ ባንድ አስቀምጠውታል።በሚገርም ሁኔታ አንዱና ዋናው ምክንያት የቤተክርስቲያኗ ብሔራዊ አስተምህሮ መገንጠልን መቃወምና የሀገሪቱን አንድነት ደጋፊ መሆንና በባንዲራና መሰል ኢትዮጲያዊ መገለጫዎች ላይ የነበራት አስተምህሮ እንደሆነ እንዲህ ሲሉ አስቀምጠውታል።

“A combination of factors made relations between TPLF and the EOTC church difficult …the church taught its followers to respect their allegiance to the Ethiopian state and was, in effect , a school for national consciousness, using national symbols such as the flag in all religious and social events. No church ever conducted major ceremonies without hoisting the Ethiopian flag – an act also regularly observed …’ page 244

“The pragmatic TPLF understood the church’s role in village social life and its support for the unity of the country .It also understood a possible alliance between the Church with its forces that stood against socialism and nationalization of the land as well as separatism .The church was viewed as a force standing in the way of TPLF. …there was no doubt that it wanted to subordinate the church to its cause” page 245


የኢትዮጵያ ተዋሕዶቤተክርስቲያን በህዝቡ ውስጥ ያላት ተቀባይነትና ቤተ ክርስቲያና በሀገር አንድነት ላይ ያላት ጽኑ አቋም  እግዚአብሔር  የለም ብሎ የሚያስተምረውን ሶሺያሊዝምን መቃወሟና በባንዲራ ላይ ያላት ጽኑ አስተምህሮናና የመገንጠል ተቃዋሚ መሆኗ በወያኔ ጥርስ ውስጥ እንድትገባ ምክንያት እንደሆነ ዶክተር አረጋዊ እማኝነታችውን ከገለጡ በሁዋላ ወያኔ ቤተ ክርስቲያኗ ላይ ያሳረፈውን በትር እንዲህ ሲሉ ጠቅሰውታል።

የኢትዮጵያ ተዋሕዶቤተክርስቲያንን ማደንዝዝና መቆጣጠር በብሔራዊ ማንነትና በሀገር አንድነት ላይ ቤተክርስቲያኗ የያዘችው ጽኑ አቁዋም ያበሳጨው ህወሀት ቤተ ክርስቲያኗን ለማደንዘዝና ለመቆጣጠር የለኮሰውን ባለ ሶስት ዘርፍ የጥቃት ዘመቻ እንዲህ ሲሉ ይዘረዝሩታል

አንደኛ ቤተክርስቲያኗ በህዝቡ ዘንድ ያላትን ማህበራዊ ተሰሚነት ማዳከምና የቤተ ክርስቲያኗ መንፈሳዊ ጉዳዮች ሳይቀሩ በካድሬ በሚመሩ ህዝባዊ ጉባኤዎች እንዲወሰኑ ማድረግ

“the second step was to try and move the socio economic focus of life from the church to the peoples assemblies. All administrative and social activities were taken over by the associations and the baitos and even church affair such as the rights and obligations of the church and its followers fell under the jurisdiction of the assemblies. The capacity of the church to mobilize and influence waned. The church lost its status as mediator in conflicts, rights over spiritual and familiar issues because the new political authorities….”

የሚገርመው ቤተክርስቲያኗ በራሷዋ መንፈሳዊ ጉዳዮች ላይ እንኳን ለመወሰን መብቱን አሳጥቷታል። 1970ዎቹ እና ሰማነያዎቹ ህወሀት ነጻ አወጣሁዋችው በሚላቸው ቦታዎች በሙሉ የቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ ውሳኔዎች በካድሬና በካድሬ በሚመሩ ስብሰባዎች መወሰን ጀመሩ።
ሁለተኛው ደግሞ የቤተ ክርስቲያኗን አመራር በሙሉ በህወሀት ካድሬዎች ማስያዝና የቤተክርስቲያኗን አመራረ ሙሉ በሙሉ ግእዝ በሚናገሩ ካድሬዎች መተካት እንደነበረ እንዲህ ሲሉ ይገልጹታል

“thirdly , the TPLF launched a series of conferences or seminars for selected parish priests in 1970 to win them over. The underlying motive of the seminars was to isolate the church in Tigray from the wider Ethiopian Church in order to foster Tigraian nationalism along the lines of the TPLF strategic objective. Suppressed Tigraian nationalism was invoked to challenge the dominant Ethiopian Orthodox Church. The initial wereda seminars for the priests were conducted by an eloquent TPLF fighter,Gebre Kidan Desta, a graduate of the theological College at Addis Ababa university .The themes of the seminars were to replace the Ethiopian Church authority by TPLF – minded church and the language in the church with Tigrigna and ultimately, to further Tigraian nationalism and identity ‘ page 246

የቤተ ክርስቲያኗን ኋይል ለማዳከምና ለመቆጣጠር መነኮሳት በማስመሰል ትልልቅ ገዳማት ውስጥ ካድሬዎችን በማስረግና በማስሾም በስብሐት ነጋ የሚመራ የስለላ ቡድን ለዚሁ ጉዳይ ሲባል መዋቀሩን እንዲህ ይገልጹታል

“this process involved the mobilization of parish priests and ordinary Christians to isolate them from the church national hierarchy. To weaken church authority, an intelligence group was formed under Sibhat Nega to infiltrate the wel-established monasteries in Tigrai, such as Debre Damo , by planting TPLF members’ camouflaged as monks and influencing church activities in the interests of TPLF”

ሌላውና አደገኛው ደግሞ የቤተ ክርስቲያኗን አመራር ለሁለት የመክፈል ጉዳይ ነው
1987 እና 1989 (እኤአ) ትግራይ ያለውን የኢትዮጵያ ተዋሕዶቤተ ክርስቲያን ሀገረ ስብከት ከማእከላዊው የቤተክርስቲያን ሲኖዶስ መለየትና የቤተ ክርስቲያኗንም አስተዳደር ለሁለት መክፈል ከበረሀ ጀምሮ የታሰበበትና የተተገበረ ጉዳይ መሆኑን በማያወላዳ ሁኔታ እንዲህ ገልጸውታል

“ in 1987 and 1989 ,regional and national conference for priests were organized by the TPLF in liberated territories to reshape the Tigray Church in line with the TPLF program . A separate secretariat of the Orthodox Church was formed in the liberated areas of Tigray and was supposed to operate under TPLF guidelines. Practically, the Ethiopian Church was divided in to two secretariats…’

አራት ኪሎ ቤተ ክህነት
ዶክተር አረጋዊ በርሄ የጻፉት ይሄ ሁሉ ሴራ የተጎነጎነውና የተተገበረው ገና ወያኔ አዲስ አበባ ሳይገባ በረሀ ላይ እያለ ነበር። ወያኔ አዲስ አበባን ከተቆጣጠረ በኋላ በቤተ ክህነቱ ዙርያ ምን ተፈጸመ የሚለውን ጥያቄ ለመመለስና በበረሀ ታቅደው መተግበር ከጀመሩት ሴራዎች አንጻር ለመመልከት ውሳኔዎቹንና እቅዶቹን ደግመን እንያቸው

1. ቤተክርስቲያኗ ያላትን ማህበራዊ ተሰሚነት ማዳከምና የቤተ ከርስቲያኗ መንፈሳዊ ጉዳዮች ሳይቀሩ በካድሬና በካድሬ በሚመሩ ህዝባዊ ጉባአኤዎች እንዲወሰኑ ማድረግ

2. የቤተ ክርስቲያኗን ሀይል ለማዳከምና ለመቆጣጠር መነኮሳት በማስመሰል ትልልቅ ገዳማት ውስጥ ካድሬዎችን በማስረግና ማስሾም
3. የቤተ ክርስቲያኗን አመራር በሙሉ በህወሀት ካድሬዎች ማስያዝና የቤተክርስቲያኗን አመራር ሙሉ በሙሉ ግእዝ በሚናገሩ ካድሬዎች ማስያዝ

4. የኢትዮጵያ ተዋሕዶቤተ ክርስቲያን ሀገረ ስብከት ከማእከላዊው የቤተክርስቲያን ሲኖዶስ መለየትና የቤተ ክርስቲያኗንም አስተዳደር ለሁለት መክፈል ይገኙበታል፡፡ ያልተፈጸምው የቱ ይሆን? የኢትዮጵያ ተዋሕዶቤተ ክርስቲያን በሁለት ሺህ አመት ታሪኳ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ሲኖዶሷ ለሁለት ተከፍሏል። የቀድሞው የሀገሪቷ ጠቅላይ ሚኒስትር ታምራት ላይኔም ለአሜሪካው አምባሳደር ዶናልድ ያማሙቶ እንደገለጹት አባ መርቆሬዎስ ከሀገር የወጡት በፖለቲካ ውሳኔና በጠቅላይ ሚኒስትሩ ፊርማ መሆኑን ገልጸዋል። እኚህም ሰው ከዓመታት እስር በኋላ ከእስር ሲለቀቁም በዚህ  ሥራቸው መጸጸታቸውንና የፈሰሰውን ውሃ ለማቅናት ፍላጎት እንዳላቸው ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡ ከዚህ ሥራ ጋር ተያይዞም የቤተ ክርስትያኗ ሲኖዶስ ለሁለት ተከፍሏል።

የቤተ ክርስቲያን ጉዳዮች በቤተ ክርስትያን ሲኖዶስ ሳይሆን በሌሎች አካላት እንደሚወሰን የአባ ጳወሎስ ሀውልት ህያው ምስክር ነው።ሲኖዶሱ ይፍረስ ብሎ ቢወስንምየማይፈርሰው ሀውልት” ብለው የወሰኑትምእመናንውሳኔ እንደጸና የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው። ከዚህም በተጨማሪ ከዋልድባ ገዳም ጋር በተያያዘ የመንግሥትን አቋም በመደገፍ ሙሉ ይሁንታውን በአባቶች የሲኖዶስ ጉባኤ ሳይሆን ከበስተኋላ ሆነው በሚሾፍሩ ሰዎች የስምነት አጀንዳውን ላይ እንዴት ለማስገባት እንደሞከሩ የምናውቀው ነገር ነው፡፡

ከክርስቶስ ወንጌል ይልቅ ፖለቲካ የሚሰብኩ ጥቁር ራስ መነኮሳትና ነጭ ለባሽ ካህናት በየቤተ ክርስቲያኑ ማየትና ማድመጥ የተለምደ ከሆነ በርካታ አመታትን ተቆጠሩ።ሌሎቸም ብዙ ጉዳዮች ሆኑ። ለጊዜው ሁሉም እቅድ የተሳካ ይመስላል።የመውጊያው ብረት ላይ መቆም ተቸሏል። ለማን እንደሚብስ ግን ወደፊት የምናየው ይሆናል።የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ላንተ ይብስብሀልየሐዋርያት ስራ 9 5 የእግዚአብሔርን ለቄሳር አሳልፈው የሰጡሐዋርያትምስለሰፈሩት ሰልሳና መቶ ከግብር አባታቸው ዋጋቸውን ይቀበላሉ።

አሁን ነገ ቤተክርስቲያን ላይ ስለሚደርሰው ነገር በመመልከት ስለ አንዲት እምነታችንና እና ስለ አንዲት ቤተ ክርስቲያናችን ብለን በጋራ የምንቆምበት ጊዜ ላይ ደርሰናል፡፡   “አመልህን በጉያ ስንቅህ በአህያ” እንዲሉ አባቻችን በአንዲት ሀገራቸው ኢትዮጵያ ፤ በአንዲት  እምነታቸው ተዋሕዶተዋሕዶ ላይ የመጣባቸውን ነገር ለመመለስ “ክተት ሰራዊት ምታ ነጋሪት” በማለት አንድነታቸውን ያሳዩ ነበር ፤ አሁንም ይሰራል የተባለውን የቅድመ ክስ ዶክመንተሪ ቀጣይ ዳፋውን ከአንድ ማኅበር በላይ በማየት አሁን ላይ ስለ አንዲት እምነታችን ዘብ ልንቆም ይገባል፡፡

የቤተ ክርስቲያን አምላክም ቤተ ክርስቲያንን ይጠብቅልን፡፡


17 comments:

  1. this is true. this is the serious issue for Ethiopia and Ethiopian orthodox tewahedo church bad situation. it needs deep pray.

    ReplyDelete
  2. በዚህ ጉዳይ ላይ መንግሥት ደጋግሞ ቢያስብበት ይመረጣል። ይህን የሚያራግቡ ግለሰቦች ለሙስና የተጋለጡ፣ ሀገራዊ ፍቅርና ታሪካዊ ድርሻ ያልገባቸዉ፣ የቤተ ክርስቲያንና የሀገር አንድነት ትዉስብ የሌላቸዉ እንደሆኑ ማጤን ይጠይቃል። በ ሃይማኖት የሚመጣ አደጋ ወዴት ሊያመራ እንደሚችል መንግሥት ሳያዉቅ የቀረ አይመስልም። የፖለቲካዉ ጨዋታ ከፖለቲካዉ እድምተኞች ጋር ቢሆን ጉዳዩን ያቀለዋልና ዘጋቢዎቹም ሆኑ ተዋናኞቹ ከእሣት መጫወት ቢያቆሙ። ሀገራዊ ፍቅርና በስነ ምግባር የታነጸ ትዉልድ የማይፈልጉ መሪዎች ብሎም ሙሰኞችን የሚበረታቱ ከሆኑ የመንግሥት አከላት ትብብሩን ይቀጥሉ።

    ReplyDelete
    Replies
    1. betikikil kale hiwetn yasemaln. mengst ejun ke betekrstiyanachinlay yanesa.

      Delete
  3. Focusing on what practical measures we should take is an issue of paramount importance.The above mentioned intrigues of TPLF were being told and and retold long time ago,for no avail.HOW we can stop the intervention of the party in the affairs of our Church is the point that we should contemplate on and discuss anew.

    ReplyDelete
  4. @ሐዋርያዉ What if the government is not willing to hear you? Does previous experiences witness our government is capable of heeding? Are we not living in Ethiopia where dissenting voices are stifled? Rather,is it not fitting to prepare ourselves for what is to come after we doing what is ESSENTIAL at this critical moment in history?

    ReplyDelete
  5. Egna Tsenten wede Egziabeher abzeten entseliy Enji you will see sidenefa endemeta akerkero yimelesal tez kalachihu endihu sidafer neber ye 97 mircha gize denberberu yewetaw. Hizkiel abatachen endaderegew bebetemekedesu gebeten yihenen Egziabheren ena Hizbun yetegedaderewen tigab ena Tebit Libun Yasabetewen yemetabeten yasresawen hulu yetsafewen debedabe yizen befitu benkom ye senakremen serawit besifu belichta demetmatun yatefaw Egziabher zarem siran yiseral:: Abetu Cher Fetariache Beante Yemiamnu hulu begna Ayeferu "Anse haileke wenea adehenene"

    ReplyDelete
  6. አሁንም ይሰራል የተባለውን የቅድመ ክስ ዶክመንተሪ ቀጣይ ዳፋውን ከአንድ ማኅበር በላይ በማየት አሁን ላይ ስለ አንዲት እምነታችን ዘብ ልንቆም ይገባል፡፡

    ReplyDelete
  7. የቤተ ክርስቲያን አምላክም ቤተ ክርስቲያንን ይጠብቅልን፡፡

    ReplyDelete
  8. “የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ላንተ ይብስብሀል”

    ReplyDelete
  9. ሕወኃት/ወያኔ በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን ላይ አቀድሞ በበረሃ ያቀደችው ሴራ ፡-
    1. ቤተክርስቲያኗ ያላትን ማህበራዊ ተሰሚነት ማዳከምና የቤተክርስቲያኗ መንፈሳዊ ጉዳዮች ሳይቀሩ በካድሬና በካድሬ በሚመሩ ህዝባዊ ጉባአኤዎች እንዲወሰኑ ማድረግ፡- ተጨባጭ ማስረጃ፡- መንፈሳዊ በዓላትን በኮንፈረንስ መሻር
    2. የቤተክርስቲያኗን ሀይል ለማዳከምና ለመቆጣጠር መነኮሳት በማስመሰል ትልልቅ ገዳማት ውስጥ ካድሬዎችን በማስረግና በማስሾም ቁልፍ ቦታዎችን መያዝ፤ ተጨባጭ ማስረጃ፡- አባ ገ/መድህን፣ በርካታ የደብር አስተዳዳሪዎች
    3. የቤተክርስቲያኗን አመራር በሙሉ በህወሀት ካድሬዎች ማስያዝና የቤተክርስቲያኗን አመራር ሙሉ በሙሉ ግእዝ በሚናገሩ ካድሬዎች ማስያዝ፤ ማስረጃ፡- ተጨባጭ ማስረጃ፡- እነ አቡኖሙ ጳውሎስ እና እነ ንቡረ ዕደ-መንግስት ኤልያስ አብርሃ የሕወሃት መረጃ አቀባይና የደህንነት አባላት መሆናቸው ግልጽ ነው፡፡
    4. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሀገረ-ስብከት ከማእከላዊው የቤተክርስቲያን ሲኖዶስ መለየትና የቤተክርስቲያኗንም አስተዳደር ለሁለት መክፈል፤ ተጨባጭ ማስረጃ፡- በተለያዬ መሰናክል እርቅ እንዳይፈጽሙ የተደረጉት ሁለቱ ሲኖዶሶች፣ በ3 አስተዳደራዊ መዋቅር የሚመሩ አብያተ ክርስቲያናት (ኢትዮጵያ ውስጥ ባለው ሲኖዶስ ፣ አሜሪካ ባለው ሲኖዶስ፣ ከሁለቱም ውጭ በቦርድ)፣ በከፍተኛ የመንግስት ባለሥልጣናትና እንደነ አቡኖሙ ፋኑኤል እና “አባ” ሰረቀ-ብርሃን ባሉ የውስጥ ባንዳዎች የሚደገፉ የተሃድሶ አራማጆች ቤተክርስቲያንን ለመከፋፈል እየተሯሯጡ መሆናቸው፡፡

    ሕወሃቶች ለዚህ አሰራራቸው አልመቻቸው ያለውንና በቤተክርስቲያን አንድነትና ሕልውና ላይ ጠንካራ አቋም ያለውን አባትም ሆነ ልጅ (ጳጳስም ሆነ ምዕመን)፣ ድርጅትም ሆነ ማኅበር ከተቻለ ማፈራረስ ካልሆነ ደግሞ ማዳከም እንደ ስልት ተነድፎ እየተተገበረ ያለ የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡

    ለተጨባጭ ማስረጃም ጠንካራ አቋም ያላቸው ሊቃነ ጳጳሳት ማደሪያ ቤት ከመደብደብ ጀምሮ እስከ ማስፈራራት ተደርሷል፡፡ በዋልድባ ገዳም ይዞታ ጉዳይ ሲከራከሩ የነበሩ ሁሉ ጸረ-ልማት ተብለው ተሸማቅቀው እና ተሳቅቀው አርፈው እንዲቀመጡ ተደርገዋል፡፡

    ReplyDelete
  10. አውሬው የስድብ አፍ ተሰጠው በማንም አንፍረድ እኛኮነን ቤተክርስቲያናችንን ያሰደብናት በጥቂቱም ቢሆን መስዋእትነት መክፈል አለብን

    ReplyDelete
  11. አሁን መንግሥት በቤተክህነት ጥቂት ደጋፊዎችና በቆየ የውስጥ አላማው አማካኝነት ሊሰራ አስቧል የተባለው የማኅበረ ቅዱሳንን አመራሮች እና ቀጥሎም ማኅበሩን የሚከስ ዘጋቢ ፊልም ነገሩን ከአንድ ማኅበር ጋር ብቻ የሚያያይዙት አልጠፉም ፤ ነገር ግን ማኅበረ ቅዱሳን እና ቤተክርስቲያን የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ መሆናቸው እስከ አሁን የገባቸው አይመስልም ፡፡ ባሳለፍናቸው 20 ዓመታት በርካታ ሥራዎችን በቤተክርስቲያኒቱ የእዝ ሰንሰለት ስር በመሆን ማኅበረ ቅዱሳን መስራቱ በአይን የሚታይ በእጅ የሚዳሰስ እውነት ነው፡፡ ጠላት ግን የሚታየው የባለፈው መልካም ሥራ ሳይሆን የወደፊቱ የእንቅፋት መንገድ ስለሆነ ዛሬ ላይ ይህን እግዚአብሔር የሚገኝበትን ረዥም ጉዞ ለማደናቀፍ በይፋ ሃይማኖተኞችም ፖለቲከኞችም ሳይሆኑ አንድን አላማ ለማሳካት በአንድ ጉባኤ ተሰብስበዋል ፡፡ ይህ ፊልም እንደተባለው ተሰርቶ ለእይታ የሚቀርብ ከሆነ ቀጥሎ ምን ሊከሰት እንደሚችል ለመገመት ነብይነትን አይጠይቅም ፤ ቤተ ክርስቲያኒቱ እንዲህ ባለበት አንድም ሰው ባጣችበት ጊዜ ላይ ፤ ሲኖዶሷ ለሁለት በተከፈለበት ፤ ሙሰኝነትና ዘረኝነቱ ጣራ የደረሰበት ፤ ሁሉም ሰሚ እንጂ ተናጋሪ አንደበት የሌለው ይመስል ዝም ባለበት ጊዜ የቤተክርስያኒቱ እምነት ፤ ሥርዓትና ትውፊት ትውልድ እንዲያውቅ ፤ አብነት ትምህርት ቤቶቿ ከመዘጋትና ከተማሪ ድርቅ ከመመታታቸው በፊት የቻለውን ያህል እያደረገ ዘለቄታዊ ካህናትና ዲያቆናት መሰል አገልጋዮች እንዲወጡ የበኩሉን ትንሽ የማይባል ሥራ እየሰራ የሚገኝውን ማኅበር በቤተክህነቱ ውስጥ የቀድሞ ስርዓት ርዝራዥ በሆኑ ሰዎች አማካኝነት ይሰራበታል የተባለው ዘጋቢ ፊልም የሚዘጋጅ ከሆነ ውድቀቱ ከአንድ ማኅበር ይልቅ የቤተክርስቲያኒቱ መሆኑን ልንገነዘብ ይገባናል፡፡

    ReplyDelete
  12. አሁንም ይሰራል የተባለውን የቅድመ ክስ ዶክመንተሪ ቀጣይ ዳፋውን ከአንድ ማኅበር በላይ በማየት አሁን ላይ ስለ አንዲት እምነታችን ዘብ ልንቆም ይገባል፡፡

    ReplyDelete
  13. Inhidig MahibereneMarch 26, 2014 at 4:16 AM

    The government needs to be ware that religion is the only place where almost all of the Ethiopian people are going to rest to escape all these suppression of the government and all these manifestly excessive maladministration. If it is also challenging religion, I think doomsday is coming to the government. I totally agree with the contention of the writer of this article that we orthodox Christians have to look over the matter beyond a campaign targeting Mahibere Kiduasan.

    After all, Let us pray and hope that God will not left us alone.

    ReplyDelete
  14. Let the Government focus on it development work and keeping the security of the country and shall not interfere on GOD's domain!

    ReplyDelete
  15. besmeab wewekd wemenfes kudus ahadu amlak amem, yih yemibalew ewnet kehone mengist degmo degagmo liyaten yigebal. mikniatum mengist halafinet alebet yih mahber bet kristiann min lilak .min lagelgil bilo beabatoch sir yemitazez yebetkristian mahber new.yelijinetu dirsha yemiweta mahber silehone sihtet kalebetm abatoch weyin kudus sinodos kebtsu abatachin gar bemehon sihtetu liyrmu yegbal enji endihu betelatnet meferej lehulum aybejim mahberum besigawim bemenfesawi timhrt yegolemese silhone saychekul bemeregagat hulun endemitebabek ergtegna negn, mengistm halafinet betemelabet akahed bihed tiru new elalah , kemahbere kudusan yemibet bemehal yemiyaragibut tikm felagiwoch bechimtnet liyayache yigebal,egziabher mastewalun yadlen amen,

    ReplyDelete