Wednesday, March 27, 2013

የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀ መዛሙርት የመብት ጥያቄ በተሃድሶ መናፍቃን አጀንዳ ተጠለፈ

  • የደቀመዛሙርቱ አካዳሚክ፣ አስተዳደራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄ ወደ ግለሰቦች ኃላፊነት ማስነሳት በሚል ቅድመ ሁኔታ ተቀይሯል፡፡
  • “ተቃውሞውን አስተባብረሃል” በሚል ታስሮ የነበረው ደቀመዝሙር ከእስር ትናንት ተፈትቷል፡፡
  • የተሃድሶ ኑፋቄ አራማጅ የሆኑ ተማሪዎች ተቃውሞውን ኦርቶዶክሳውያንን ከኮሌጆ ቁልፍ ቦታ በማስወገድ በመናፍቃን ለመተካት በኅቡዕ እየተንቀሳቀሱ ነው፡፡

(አንድ አድርገን መጋቢት 19 2005 ዓ.ም)፡- የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀ መዛሙርት በኮሌጁ ስላለው የአስተዳደር ጉድለት ፣ የትምህርት ጥራት ማነስና የምግብ አቅርቦት ጥራት መጓደል ተቃውሟቸውን በትምህርት ማቆምና የረሃብ አድማ በማድረግ እየገለጹ ነው፡፡ በርካታ መገፋት ቤተክህነቱ  እያደረሰባቸው የሚገኙት የነገረ መለኮት ምሩቃንና ደቀ መዛሙርት ያቀረቡት ተቃውሞ የቤተክህነቱን አስተዳደረዊና መንፈሳዊ ድቀት ርቀት እንደ ማሳያ ተደርጎ ተወስዶአል፡፡

ደቀ መዛሙርቱ በኮሌጅ ቆይታቸው ጥራቱ የተጓደለ ምግብ ፣ ፍታሃዊ ያልሆነ የውጤት ምዘና ሥርዓት ፣ የአስተማሪዎች ንቀትና ስድብ ፣ በተሃድሶ መናፍቃን ቡድን ቅሰጣና በአስተማሪዎች የአቅም ማነስ ይማረራሉ፡፡ ከኮሌጅ ተመርቀው ሲወጡ የሚከፈላቸው ደመወዝ ለዕለት ኑሮ አለመብቃትና በጥቂት መናፍቃን ምክንያት በምእመናን ዘንድ ለደቀ መዛሙርቱ ያለው አመለካከት የተዛባ መሆኑ ቤተክርስቲያን ከምሩቃኑ ልታገኝ የሚገባትን አገልግሎት እንዳታገኝ እያደረጋት ነው፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ያቀረቡት የመብትና የአስተዳደራዊ ለውጥ ጥያቄ ሁሉንም የኮሌጁ ደቀ መዛሙርት ባሳተፈ መልኩ እያቀረቡ ሲሆን ተቃውሞውን ከሚመሩት የደቀ መዛሙርት ተወካዮች (ካውንስል  አመራር አባላት መካከል የተሃድሶ ኑፋቄ አራማጆች መሆናቸው ማስረጃ የቀረበባቸው) አጋጣሚውን ተጠቅመው የኮሌጁን አስተዳደር ቁልፍ መዋቅር ኦርቶዶክሳውያንን በማስነሳት አዝማቾቻቸው በሆኑት ሁለት መምህራን ለመተካት እንቅስቃሴ ላይ መሆናቸው ተመልክቶአል፡፡



መናፍቁን አሰግድ ሣህሉን እስከ ሰበር ሰሚ ችሎት ድረስ ተከራክሮ ድግሪውን ያስነጠቀውን የኮሌጁን አካዳሚክ ምክትል ዲን መምህር ፍስሐጽዮንና የተሃድሶ ኑፋቄ ከሚያራምዱ አራት መምህራን አንዱ የሆነውን መምህር ዘለዓለም ረድኤትን ከቀን ተማሪዎች አስተባባሪነት ኃላፊነታቸው ካልተነሱ ትምህርት አንቀጥልም፤ ከአስተዳደሩ ጋርም አንደራደርም ወደ ሚል ቅድመ ሁኔታ ተቀይሮአል፡፡ 

ደቀመዛሙርቱ በመምህር ፍስሐጽዮን ላይ ያቀረቡት ክስ “የአስተዳደር ሥራ ስለሚበዛበት በአንድ ሴሚስተር የሚያሰተምራቸው አራት ኮርሶችን የሚያስተምረው ሳይዘጋጅ ነው”  የሚል ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ ብቸኛ መፍትሔ ያደረጉት ከሓላፊነቱ ማንሳት መሆኑ፣ መምህር ፍስሐጽዮን አጎደለ ያሉት በአስተዳደር ካልሆነ ኮርስ መቀነሱን ተወካዮቹ እንደ አማራጭ ማቅረብ አለመቻላቸው ጥያቄ አስነስቷል፡፡
አንድ አድርገን ምንጮች እንደገለጹት የተማሪዎች ካውንስል ጸሐፊ የሆነው ዲያቆን አሳምነው አብዩና ዲያቆን ሙሉቀን አማረ የተሃድሶ ኑፋቄ አራማጅ መሆናቸውን ደቀ መዛሙርቱ ማስረጃ ለኮሌጁ አስተዳደር ቢያቀርቡም በተለይ እርምጃ ሊወስደባቸው የሚችለውን መምህር ፍስሐጽዮንን “ማኅበረ ቅዱሳን” ነው የሚል ወሬ በማስወራት እርሱን ለመቆጣጠር በምክትል ዲን ማዕረግ ንቡረእድ ኤልያስ አብርሃ ተመድቦ ስለነበር እርምጃ ሳይወሰድባቸው ቀርቶአል፡፡ ዲያቆን ሙሉቀን አማረ ባለፈው ዓመት ተመርቆ በአሁኑ ሰዓት ካዛንቺስ ቶታል አካባቢ በሚገኘው የአሸናፊ መኮንን የተሃድሶ መናፍቃንን ማስልጠኛ ውስጥ በአሰልጣኝነት እየሰራ  ይገኛል፡፡ 

ዲያቆን ሙሉቀን ከአሸናፊ መኮንን እና ከአሰግድ ሣህሉ “ቡራኬ” እየተቀበለ ደቀ መዛሙርቱን ወደ መናፍቃን ጎራ እንዲቀላቀሉ ከውጭ ሆኖ እነ ዲያቆን አሳምነው አቢዩን ግቢ ውስጥ በማዝመት የተሃድሶ መናፍቃንን ቅሰጣ ይመራል፡፡ የተማሪዎች ካውንስል ፀሐፊነት ቦታውን ተቅጠሞ ግቢ ውስጥ የሚራመደውን የተሃድሶ እንቅስቃሴን ይቃወማል ፣ የሚመች አጋጣሚ ቢያገኝ የማያዳግም እርምጃ ይወስድብናል ብለው የሰጉትን መምህር ፍስሐጽዮንን ማስወገድና እነርሱን ከሚያዘምቷቸው ሁለት መምህራን አንዱን ለማድረግ እየጣሩ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

በኦርቶዶክሳውያን ዘንድ ቅሬታ እንዳይቀርብ የተሃድሶ ኑፋቄ አራማጁ መምህር ዘለዓለም ረድኤትንም ከመደበኛ ተማሪዎች አስተባባሪነት እንዲነሳ በመጠየቅ ለማደናገር ሞክረዋል፡፡ መምህር ዘለዓለም ረድኤት በወር ከሚያገኘው 3000 ብር በላይ ቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ህንጻ ላይ በወር 4500 ብር አፓርታማ ተከራይቶ የሚኖር ሲሆን ፣ በቀንና በማታ ተማሪዎች የተሃድሶ ሰራዊት በመመልመል ልደታ አካባቢ በሚገኘው ማሰልጠኛቸውና ዩጎ ሲቲ ቸርች ማክሰኞ ምሽት አምልኮ ላይ ተማሪዎች እንዲሳተፉ በማስተባበር እንዲሁም የኮሌጁ አስተዳደር በተሃድሶ መናፍቃን ላይ እርምጃ ለመውሰድ ሲወስን መረጃዎች እንዲያሸሹ ቀድሞ በማሳወቅና ለእነ አሰግድ ዓይነቶች ደግሞ ህጋዊ ሽፋን በመስጠት በኮሌጁ ማኅበረሰብ ዘንድ ይታወቃል፡፡ በተለይ ደግሞ ለረጅም ዓመታት የኮሌጁ የስነ ምግባር (Christian Ethics) መምህር የሆኑትን መምህር ተሾመ የሚያነሷቸው መሰረታዊ የግብረገብነትና የምግባር ጥያቄዎች እረፍት ስለነሱት መምህሩን በአደባባይ በመደብደቡ ደቀ መዛሙርቱ ማዘናቸውን ገልጠዋል፡፡

ይህንን የደቀ መዛሙርቱን ተቃውሞ ከሚመሩትና እንቅስቃሴውን ለተሃድሶ መናፍቃን አጀንዳ መጠቀሚያነት ካስጠለፉት መካከል ዲያቆን አሳምነው ዐቢዩን በሚመለከት ደቀ መዛሙርቱ ለኮሌጁ ያቀረቡት ማስረጃ የሚከተሉትን ጉዳዮች ይዳስሳል፡፡

 በምዕራብ ሸዋ ሀገረስብከት የጀልዱ ወረዳ ደብረ መንከራት ቅዱስ ጊዮርጊስና ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን በቀን 27/06/2003 ዓ.ም የደብሩ ሰበካ ጉባኤ ፣ የወረዳ ቤተክህነት ፣ የሀገር ሽማግሌዎች ፣ ጠቅላላ ሕዝበ ክርስቲያን ፣ ማኅበረ ዲያቆናት በመሰብስብ “የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነታችን በመናድ ወይም ለማጥፋት እና ተሃድሶ እምነትን ለማስፋፋት የተነሳሱ የውስጥ የቤተክርስቲያን ዲያቆናት ሆነው ከዚሁ ቤተክርስቲያን በወጡትና አድራሻቸውን አዲስ አበባ ማድረግ የጥፋት ተልዕኮቸውን የሚፈጽሙ
1.    ዲ/ን አሳምነው ዐቢዩ       አድራሻ       አዲስ አበባ
2.    ዲ/ን ሙሉቀን አማረ      አድራሻ       አዲስ አበባ       
3.    ዲ/ን ዋሲሁን አማረ       አድራሻ         ያልታወቀ
እነዚህ ሰዎች አድራሻቸውን የተለያየ ቦታ በማድረግ የተዋህዶ እምነታችንን ወደ ምንፍቅና እምነት ለመቀየር ስውር ደባ ትምህርትና ለግል ጥቅማቸው በመገዛት በተለያዩ ጊዜ በጀልዱ  ወረዳ አብያተ ክርስቲያናት አገልጋይ ዲያቆናትና የሰ/ት/ቤት ተማሪዎች እንዲሁም በወንድሞቻቸው በመጠቀም የምንፍቅና ትምህርት ለማስተላለፍና የተለያዩ መጽሔቶችን በማደል ፤ በደብሩ አገልጋይ ዲያቆናት አማካኝነት ተልዕኮአቸውን ለማሳካት ቢሞክሩም በመረጃ ስለተደረሰባቸው ተልዕኳቸው ሳይሳካ ቀርቷል፡፡…..” በማለት የሚገልጸው ቃለ ጉባኤ አክሎም እነ ዲ/ን አሳምነው ያሰማሯቸው ዲያቆናት ቤተክርስቲያንና ምእመናን ይቅርታ ጠይቀዋል፡፡ ያሳሳቷቸው የዲ/ን አሳምነው ዐቢዩ ወንድም እነ ዲ/ን አንድነት ዐቢዩ መሆናቸውን መመስከራቸውን ይገልጻል፡፡

ቤተክርስቲያንን ክፉኛ ውስጥ ሆኖ እየወጋት ያለው የተሃድሶ ክንፍ በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተላላኪ የሆነው ዲ/ን አሳምነው ዐቢዩ  በተመለከተ ካለን መረጃ  ከፍለን አቅርበንላችኋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ላዩን የሚነሳ ጥያቄ እና ተቃውሞውን አራማጆች ውስጥ ውስጡን የሚሰሩት ስራ ተለያይቷል ፡፡ አሁን ላይ ትንሽ ቆም በማለት ጥያቄ አቅራቢዎችም ሆኑ ጥያቄው የቀረበለት አካል ነገሩን ከስር መሰረቱ ይረዳው ዘንድ መልዕክታችን ነው ፤ አንድ አድርገን ለማስረጃ ይሆን ዘንድ ይህን አቅርባላችኋለች……. 



2 comments:

  1. Good flip. How much did they pay you. Believe me this is the 11th hour. They can't win!! you wil loose too.

    ReplyDelete
  2. ye'kedemut ye'ortodox abatoch hasaben eko new eydereg yalew enanet tehadeso yemetelut eko ende enanet bewegen belemed ayenorem ye'geta kal yefetsem eyalu slezeh atedekemu awo ke'geta zened yedel akilil tezegagetolenal enamenalen. enate gen ye'geta yehonuten eyasadedachu newena neseha gebu.geta yemetal'" Amen Geta eyesus hoy tolo na"

    ReplyDelete