Saturday, April 19, 2014

በቅዱሳን ስም ፤ የእግር ኳስ ክለቦችና ቢራ ፋብሪካዎች


  • ‹‹ቅዱስ ቂርቆስ›› የስፖርት ክለብ የሚል ቡድን ተቋቁሞ በአዲስ አበባ ሊግ ውድድሩን እያደረገ ይገኛል፡፡
(አንድ አድርገን ሚያዚያ 10 2006 ዓ.ም) ፡- በ1915 ዓ.ም የቅዱስ ጊዮርጊስ ቢራ ፋብሪካ ስራ መጀመሩንናቀጥሎ ከ77 ዓመት በፊት ኢጣልያ ኢትዮጵያን በወረረችበት ወቅት በ1928 ዓ.ም አራዳ(ፒያሳ) አካባቢ ባሉ ወጣቶችና ጥቂት በጎ አድራጊዎች አማካኝነት የቅዱስ ጊዮርጊስ የስፖርት ክለብ እነደተመሰረተ የኋላ ታሪኩ ይናገራል፡፡ 

አሁን እኛ የክለቡን የኋላ ታሪክ ለአንባቢያን ለማስተዋወቅ ሳይሆን በቅዱሳን ስም የቢራ ፋብሪካ እና የእግርኳስ ክለቦች ቀድሞ መኖር እና አሁንም መፈጠር መቻል ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት አኳያ እንዴት ይታያል የሚለውን ለማመላከት ነው፡፡ ከጥቂት አመታት በፊት በ‹‹ቅዱስ ጊዮርጊስ›› ስም ቢራ ማምረት መቻልን የተቃወሙ ጥቂት ወጣቶች ይህን ስም የማስቀየር ዘመቻ ጀምረው ነበር ፤ ወጣቶቹ አላማቸው ለተዋህዶ እምነት ጤዛ ልሰው ድንጋይ ተንተርሰው ፤ እንደ ሻማ ቀልጠው ወንጌልን ለአለም ለማድረስ በርካታ መስዋእትነትን የከፈሉ በጻድቃን ሰማዕታት ስም የእምነቱ አስተምህሮ የማይደግፈውን የረከሰ ተግባር ለቢራ ማሻሻጫነት ስማቸውን መጠቀም መቻል የለበትም የሚል ጥቅል ሃሳብ ነበረው ፤ ቀጥለውም ስማቸው ቤተክርስቲያኒቱ ከማክበሯ በላይ በሕግ አግባብ ማንም እንዳይጠቀምበት ከማድረግ በተጨማሪም ‹‹ቅዱስ ጊዮርጊስ›› የሚለውን ለቢራ መጠሪያ የሚጠቀመውን ፋብሪካ ስሙን እስከማስቀየር የሚያስችል ዘመቻ ነበር፡፡

ይህ ትልቅ ዘመቻ ተጀመረ እንጂ አልተጨረሰም ፤ አሁን ላይ ሁላችንም እንደምናውቀው ‹‹ቅዱስ ጊዮርጊስ›› የሚለው የሰማዕቱ መጠሪያ ስም ለቢራ ፋብሪካ እና ለእግር ኳስ ክለብ መጠሪያነት እያገለገለ ይገኛል፡፡ በዚህ አመት የአዲስ አበባ ክልል መስተዳደር የሚያደርገው ዓመታዊ የሊግ ጨዋታ ውስጥ ‹‹ቅዱስ ቂርቆስ›› የስፖርት ክለብ የሚል ቡድን ተቋቁሞ ውድድሩን እያደረገ ይገኛል፡፡ ለዚህም ቡድን የ‹‹ቅዱስ ጊዮርጊስ›› ቢራ ፋብሪካ የገንዘብ እርዳታ እንዳደረገለት ለማወቅ ተችሏል፡፡ 

የስፖርት ክለቦች አይኑሩ የሚል አመለካከት ባኖረንም ክለቦቹ ሲመሰረቱ ግን ባልጠፋ መጠሪያ እና ስም የቅዱሳንን ፤ የጻድቃንና የሰማዕታትን ስም ባይጠቀሙ የሚል አመለካከከት አለን፡፡ ወደፊት እንደዚሁ ተክለ ሃይማኖት አካባቢ ያሉ ወጣቶች ተነስተው ‹‹አቡነ ተክለ ሃይማኖት›› የስፖርት ክለብ ብለው ቢመሰርቱ እነዚህ ክለቦች በአንድ ሊግ ቢወዳደሩ የእግር ኳስ ጋዜጠኛው ማንን ከማን እያወዳደረ እንደሚዘግብ እናስተውል …… ቤተክርስቲያኒቷ የከበሩ ስሞችን ለንግድ መጠሪያ ፤ ለእግር ኳስ ክለብ መጠሪያ ፤  እና መሰል ከስሞቹ ጋር በምንም ለማይመሳሰሉ መጠሪያነት ልትጠብቃቸው ለሚመለከተው አካልም አቤት ልትል ይገባታል እንላለን፡፡   
መልካም የትንሣኤ በዓል ይሁንላችሁ

2 comments:

  1. ውድ ወንድሞቸ
    ቅዱሳንን በማክበር የቃልኪዳናቸው ተጠቃሚ ለመሆን እንድንችል አግዚአብሔር የሰጠን የመዳን መንገድ ሆኖ እያለ ከላይ እንደተጠቀሰው ስማቸውን ባልሆነ መልኩ ቤተክርስቲያን ከምትፈቅደዉ ውጭ መጠቀም እየበዛ መጥቷል። ሌሎች ደግሞ ለልጆቻቸው ሚካኤል፤ገብርኤል፤ኢየሱስ ወዘተ የሚል ስም የሚሰጡ በዝተዋልና እነዚህንም ማስተማርና ማስተካከል ሌላው የሚታሰብበት ትልቅ ችግር ነው።
    ገብረ ሚካኤል፤ ወልደ አማኑኤል፣ ወዘተ ነው ክርስቲያናዊ ስያሜ።

    ReplyDelete
  2. this is what extremism is all about. Extremists always want to control all public life. They want to dictate all activities. They want to draw a line to tell others that they are the only owners of the claimed mark, brand....etc. We need to stop dictating the public life.

    ReplyDelete