- አራት አመት ሙሉ ቁርስ በልተው አያውቁም
- “ ከረሀብ ሰይፍ ይሻላል” ምክንያቱም ሰይፍ አንዴ ሊገል ይችላል ረሀብ ግን እያሰቃየ ነው የሚገለው እና እኛንም ረሀቡ እያሰቃየን ሊገለን ነው … የመንፈሳዊ ተቋሙ አንድ ተማሪ
(አንድ አድገን ጥቅምት 30 2005 ዓ.ም)፡-የታእካ ነገስት በአታ ለማርያም የዳግማዊ ምኒሊክ መታሰቢያ ትምህርት ቤት
ቤተክርስትያኒቱ ካሏት ቀደምት ማሰልጠኛዎች አንዱ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በዚህ ታሪካዊ መንፈሳዊ ትምህርት ቤት ውስጥ 70 ወጣቶች ትምህርት
እያገኙ ቢሆንም ካለፈው አርብ ጀምሮ በትምህርት ቤት ውስጥ የሚላስ የሚቀመስ በማጣታቸው ረሀብ የጎዳቸው ከአልጋቸው ሲውሉ ብርታት
ያገኙት ደግሞ ትላንት ለሸገር ሬዲዮ “በረሀብ ማለቃችን ነው” በማለት አቤቱታቸውን አቅርበዋል፡፡ ወጣት በትረ ሳሙኤል እና ሲራክ
አሰፋ የተባሉ ወጣት ተማሪዎች እነርሱን ጨምሮ ቀሪ 68 ተማሪዎች ያጋጠማቸውን ችግር እንዲህ በማለት አቅርበዋል፡፡
በትረ ሳሙኤል እንዳለው “የተበጀተልን በጀት በአሁኑ ሰዓት ለአንድ ሰው 300 ብር ነው ፤ ለአንድ ሰው በቀን 10 ብር ሂሳብ ማለት ነው ፤ ይህ ደግሞ ለአንድ ሰው በቀን ሶስት ጊዜ ሊመግብ ቀርቶ አንድ ጊዜ እንኳን ሊመግበን አይችልም ፤ ይህ ብር ቁርስ ምሳ እራት እንድንመገብበት የተበጀተ በጀት ቢሆንም በቂ አለመሆኑንና እንዲስተካከል በየጊዜው አቤቱታችንን ለጠቅላይ ቤተክህነት አቅርበናል ፤ ይህ ብር በቀን ሶስት ጊዜ ስለማይመግበን ቁርስ ሳንበላ ምሳ እና እራት እየበላን እስከ ባለፈው አርብ 23/02/2005 ዓ.ም ድረስ ቆይተናል ፤ አርብ ቀን ራሱ እራት አልበላንም ፤ በተበጀተልን በጀት ከባለፈው አርብ ጀምሮ ምግብ አላገኝንም ፤ አባቶች እንደሚሉት “ ከረሀብ ሰይፍ ይሻላል” ነው ፤ ምክንያቱም ሰይፍ አንዴ ሊገል ይችላል ረሀብ ግን እያሰቃየ ነው የሚገለው እና እኛንም ረሀቡ እያሰቃየን ሊገለን ነው ፤ በርትተው መምጣት ያልቻሉ ረሀቡ የጸናባቸው ጓደኞቻችን አሉ” በማለት ተናግሯል፡፡
ወጣት ሲራክ አሰፋ እንዳለው “የሚያስተዳድረን ቤተክህነት ነው ፤ ባለፈው አርብ ቀን ምግብ እንደሌለ ስናውቅ አባቶቻችን ጋር ሄደን ጠይቀን ነበር ፤ ‹ረሀብ ሊጨርሰን ነው ምን እንብላ እናንተ አባቶቻችን እንደመሆናችሁ መጠን ችግሮቻችንን አውቃችሁ ልትፈቱልን ይገባል› ብለን ጥያቄ አቀረብን ያገኝነው መልስ ግን አመርቂ አይደለም ፤ በዚህ ምክንያት ረሀብ ጸንቶብናል መማርም አልቻልንም” ብሏል፡፡
ሸገር ሬዲዮም የመንፈሳዊ ትምህርት ቤቱ አስተዳዳሪ ሲያነጋግር “ ልክ ነው ችግሩ ተፈጥሯል ፤ ተማሪዎቻችንም በረሀብ
አለንጋ እየተጠበሱ ነው ፤ ሁሉንም ነገር እንደ ተማሪዎቹ በሰልፍ ባይሆንም በተማሪዎቹ ዙሪያ ብቻ በ5 ገጽ በደብዳቤ ጠይቀናል ፤
ከቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠን ምላሽ የለም” የሚል መልስ አግኝቷል፡፡ የትምህርት ቤቱ ጸሀፊ እንደተናገሩት “በበጀት ምክንያት ላለፉት
4 ዓመታት ተማሪዎቹ ቁርስ በልተው አያውቁም ፡፡ አንሶላ ፤ ፍራሽና ብርድልብስ የሚቀይርላቸው አጥተው እየተማሩ ነው” ብለዋል
ለእነዚህ ደቀ ማዛሙርት በጀት የሚመድብላቸው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት መሆኑ ይታወቃል ፤ የሀገረ ስብከቱን ሊቀ ጳጳስ
አቡነ ቆዎስጦስን ያጋጠማቸውን ችግር ሰምተው እንደሆነ ተጠይቀው እስከ አሁን አለመስማታቸውን ተናረዋል ፤ ለ70 ተማሪዎቹ የሚቆረጠው
በጀት በምን ምክንያት እንደዘገየ ተጠይቀው እንዲህ ብለዋል “ይህ ጉዳይ የሚመለከታቸው ስራ አስኪያጅ በአዲስ አበባ እንደማይገኙ
እና ለስራ ወደ አክሱም ስለሄዱ እርሳቸው እንደመጡ ይላክላቸዋል ፤ ከድሮ የተቀየረ ነገር የለም ፤ የሰራተኛው ደመወዝ ሲወጣ በጀቱ
አብሮ ይላክላቸዋል ፤ ሰራተኛውም ደመወዙ አልተከፈለውም ስራ አስኪያጁን
እየጠበቀ ነው” ብለዋል፡፡
ባሳለፍነው ሳምንት የተጠናቀቅ ሲኖዶስ ለካህናት ማሠልጠኛ፣ ለገዳማት፣ ለአብነት ት/ቤቶች 10 ሚልዮን እና ለሌሎችም የልማት ዕቅዶች ማስፈጸሚያ ከብር 128 ሚልዮን
በላይ በጀት መመደቡ ይታወቃል ፤ ይህ ብር ያለ ስትራቴጂክ ፕላን ወደ ስራ የሚገባ ከሆነ ብሩ በቋሚነት የካህናት ማሠልጠኛዎችን
፣ የገዳማትንና የአብነት ት/ቤቶች ችግር ፈቺ ይሆናል ብሎ ማሰብ
የሚከብድ ይሆናል፡፡
ትምህርት የአንድ ሀገር እድገት በመሆኑ በትምህርት ገበታ አሉ አስፈላጊወን እውቀትና ሀገራዊ ኃላፊነት ለመሸከም የሚችሉት በረሃብ አለንጋ ሳይሆን በተመጣጠነ ምግብና የሞራልና ስነልባዊ ተግባር ሲታከልበት ነው፡ የሀገር ስብከቱ ጳጳስ ገንዘቡን ተሸክመውት አይሄዱም የሳቸውን የሚፈጸም ከፊርማ በስተቀር የሂሳብ ክፍሉ ተጠያቂ ያደርጋል;ለምሆኑ 300 ር ላንድ ተማሪ ተብሎ ከሚመደብ ትምህርት ቤቱ ባጀቱን ለማስተካከል የሚያስችለው እቅድ ባለመንደፉ ነውንጂ በማህበር የምግብ መዘጋጃ አድርጎ ከወር እስከወር ያለችግር የተማሪዎቹን የምግብ ፍላጎት ለምሟላት ባላቃተው ነበር ስለዚህም ሆን ተብሎ ትምሕርትቤቱን ተማሪዎቹን ተስፋ ለማስቆረ የተግመደ ተንኮል ብዮ አስባለሁ
ReplyDeleteewnet bilewal lela minim aydelem siwir deba new. Abetu firedilin
Delete