Friday, November 16, 2012

ብጹዕነታቸው በመደበኛ የአቃቤ መንበረ ፓትሪያሪክ ተግባራቸውን እያከናወኑ ነው

  •   ብጹዕ አቡነ ናትናኤል ቅዳሴ ቤት ለማክበር ወደ አገር ስብታቸው ሄደው መንበረ ፓትሪያሪክ ባለፈው እሁድ ተመልሰው የአቃቤ መንበረፓትሪያሪክ አገልግሎታቸውን እየተወጡ ይገኛሉ።
  •  በተሃድሶ መናፍቅነት የሚጠረጠረው መምህር አእመረ አሸብር ከስብከተ ወንጌልና ሃዋሪያዊ መምሪያ  ኃላፊነቱ ተነስቷል
  •  የቤተክረስቲያኒቱን ተቋማዊ ሰላም በማያናጋና ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ ቤተክርስቲያኒቱ ለማደረግ ያሰበቸውን አስተዳደራዊ ለውጥ የሚያደናቅፉና ቤተክርስቲያኒቱን በከፍተኛ ሁኔታእየጎዱ የሚገኙ ሓላፊዎች ላይ ተመሳሳይ እርምጃ መውሰድ እንደሚቀጥል ይጠበቃል።
ዝርዝሩ፡-
በተሃድሶ መናፍቅነት የሚጠረጠረው መምህር አእመረ አሸብር ከስብከተ ወንጌልና ሃዋሪያዊ መምሪያ  ኃላፊነቱ ተነስቶ  የሊቃውንት ጉባኤ ሰብሳቢ መልዓከ ሰላም አምደ ብርሀን ተመድበዋል። በተለይ ባለፈው ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ “ ያሬድ ድጓ የደረሰው ወንጌል ተምሮ ነው፣ ለወንጌል አገልግሎት ቅድሚያ መሰጠት አለበት፣ ወንጌል ትኩረት አልተሰጠውም ……” በተለይ ደግሞ ሰባኪያን በተመለከተ በተናገረው ንግግር ህገወጥና ተሃድሶ የሚባሉትን በመምሪያው ስር ከሆኑ ፈቃድ በመስጠት ወደ ህጋዊ መስመር የማስገባት ሥራ እንደስራና ወደ ፊትም አጠናቅሮ እንደሚቀጥልበት ብጹዓን ሊቃነጳጳሳት ባሉበት መናገሩ አሰላለፉ ከማን ጎን እንደሆነ ግልጽ እንዳደረገ ተነግሮለታል። በተለይም እንደ አሰግድ ሳህሉ ዓይነት የሙሉ ወንጌል እምነት ድርጅት አባል ህጋዊ ከለላ በመስጠትና ኦርቶዶክሳውያን ደግሞ በማጉላላት የሚታወቀው መ/ር አእመር አሸብር ችግሩ ጎልቶ ስለወጣ ከኃላፊነቱ እንዲነሳ ተደርጎል።
አቃቤ መንበረ ፓትሪያሪክ አባ ናትናኤል ወደ አገረስብከታቸው አርሲ - አሰላ አዲስ ቅዳሴ ቤት ለማክበር መሄዳቸውን ባለፈው ሳምንት በአዲስ አበባ አኅጉረስብከት ሥራአስኪያጆች ምደባ ወቅት በአቃቤ መንበረፓትሪያሪኩና ሥራአስፈጻሚ ኮሞቴው መካከል ተፈጥሮ የነበውንና መጨረሻ ላይ ስምነት የደረሱበትን መጠነኛ የሃሳብ ልዩነት በማስታከክ የተሃድሶ መናፍቃን ልሳን የሆኑት እነ አባሰላማ ድረገጽ ብጹነታቸው “ስራአስፈጻሚ ኮሚቴውን አልሰበስብም” ብለው ወደ አገስብከታቸው ሄዱ በማለት ያለቸውን ተምኔት ጽፏል። ብጹነታቸው ወደ አገስብከታቸው የሄዱት አዲስ ቅዳሴ ቤት ለማክበር እንዲሁም የማኅበረቅዱሳን አሰላ ማዕከል ጠቅላላ ጉባኤ ለመገኝት እንደሆነ ምንጮቻን ተናግረዋል። ከባለፈው እሁድ ጀምሮ ብጹዕነታቸው በመደበኛ የአቃቤ መንበረ ፓትሪያሪክ ተግባራቸውን እያከናወኑ ይገኛሉ።
የቤተክርስቲያኒቱን ወቅታዊ ሁኔታ የሚከታተሉ ወገኖች ብጹዓን አባቶች ቤተክርስቲያን የቆመችው መስቀለኛ መንገድ መሆኑን መላልሰው እንዲያስቡ እየጠየቁ ነው። ብጹዓን አባቶች የሌላ ሦስተኛ አካልን ጣልቃ ላለማስገባት እየከፈሉት ያለው ሰማዕትነትና እያሳዩት ያለው ጥብዓት ልብ የሚነካ ቢሆንም የሚኖሩ የሃሳብ ልዩነቶች በሃይማኖትና በመካከር ለመፍታት ካልተቻለ ወደ መከፋፈል ሊወስዱ የሚችሉ ምልክቶች እየታዩ መሆናቸው ጉዳዩን አሳሳቢ ያደርገዋል። ቤተክርስቲያን ባለፉት ሃያ ዓመታት የገጠሟትን ችግሮች ለመፍታት የተገኘውን ይህን ወርቃማ ጊዜ በአግባቡ አለመጠቀም በእግዚአብሔርም በታሪክ ፊት ተወቃሽ ያደርጋል። ለዚህም በ2001 ዓ.ም ቤተክርስቲያን ገጥሟት የነበረውን መልካም አጋጣሚ የጨለማው ሲኖዶስ አባላት አባቶችን በመከፋፈል መንግስት ጣልቃ የሚገባበት እድል አግኝቶ ፈንጥቆ የነበረው ተስፋ እንዲሁ እንደጠፋ የምናስታውሰው ነው።
ዛሬም በቤተክርሰቲያናችን የቆመችበት መስቀለኛ መንገድ ብጹዓን አባቶች በማስታወስ፣ ለመንጋው የሚጨነቅ ትጉህ እረኛ ለመውለድ ምጥ ላይ የምትገኘውን ቤተክርስቲያን ደገኛ ሀኪም በመሆን ሊያገላግሏት ይገባል። ለምጣዱ ሲባል ችግሮችን በጽናትና በስፍሐ ልቦና ማለፍ ይጠይቃል። በተለይም በአሁኑ ሰዓት የቤተክርስቲያኒቱ ተቋማዊና መንፈሳዊ ውድቀት እንዲፋጠን የሚፈልጉት ከውስጥም ከውጭ ያሉ አጽራረ ቤተክርስቲያን በአባቶች ዙሪያ ማንጃበባቸው ፣ የምትፈጠር ጥቂት ክፍተት ወደ አልተፈለገ ግርግር በማምራት የሚገባበት ቀዳዳ ያጣውን መንግስትን እድል እንዳይሠጠው ተፈርቷል። 
ለዚህ ማሳያ የሚሆነው በብጹዕ አቡነ ሣሙኤል ሰብሳቢነት የሚመራው ህገ ቤተክርስቲያን ማሻሻያና የፓትሪያሪክ መምረጫ ቋሚ ህግ አጥንቶ እንዲያቀርብ በቅዱስ ሲኖዶስ የተቋቋመው ኮሚቴ ስራ ቢጀምርም አንድ ሊቀ ጳጳስና የማኅበረቅዱሳን  የህግ ባለሞያዎች እየተሳተፉ እንዳልሆነ ምንጮቻችን ዘግበዋል። ቅዱስ ሲኖዶስ ለኮሚቴው በአባልነት የመረጣቸው አንድ ሊቀጳጳስና የማኅበረቅዱሳን ህግ ባለሙያዎች ለምን መሳተፍ እንዳልፈጉ ለጊዜው ባይታወቅም ኮሚቴው  በተቀመጠለት የጊዜ ገድብ የተሰጠውን ስራ ማጠናቀቁ የሚያሰጋ ሲሆን ሁሉም የኮሚቴው አባላት ባልተሟሉበት የሚሰራውን ስራ ታማኝነት ጥያቄ ውስጥ ያስገባዋል። ይህንን ችግርም አቃቤ መንበረ ፓትሪያሪኩ ከሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ጋር በመሆን እንደሚፈቱት ይጠበቃል።

3 comments:

  1. mimihr aemere yanesaw hasab ejig wesagn hasab new. ejigim asfelagi new. betekirstian ke wengel betam eyerakech new. be fewdal siriat tewuten papasatun mamlekina menekosatin mamlek wust gebtenal. betekirstian wust musina, sedom, sigawi fukikir bestowal. yih degmo yebasew papasatu ena menekosat lay new. enersun yaye sew betekirstian ke wengel enderakech yiredal. let us put efforts spreading our gospel in truly God's way. still confusion continues to the end of this church. aemere has mentioned very strong points and he should have honored for it.

    ReplyDelete
    Replies
    1. kebete menafeqe nehe yalekewen hulu yemiyaderegute yetesegesegu menekose mesaye menafeqanena ante nachehu!!!!

      Delete
  2. Let's help our fathers by pray to get the job done . if we pray with faith we can tell the mountain to move from here to there .so do you wanna move this mountain ? let's use the spiritual instruments (pray,faith,fasting)then nothing will be impossible for us . Matthew 17 -:- 14-21 . GOD BLESS ETHIOPIA&ETHIOPIAN ORTHODOX CHURCH !

    ReplyDelete