Friday, November 23, 2012

ታሪክን የኋሊት “የኢትዮጵያ ጥቁር ጠባሳ”




(አንድ አድርገን ህዳር 13 ፤ 2005 ዓ.ም)፡- “የእናት ምጥና አብዮት ምን ይዞ እደሚመጣ አይታወቅም” ይባላል ፤ አንድ ወዳጄ “የእናት ምጥና የአገር አብዮት አንድ ናቸው ፤ ሁለቱም ምን እንደሚያወልዱና ምን እንደሚያመጡ በርግጠኝነት መናገር አይቻልምና” ይላል ፤ እናቲቱ በድሮ ዘመን ወንድ ትውለድ ሴት ፤ ጤነኛ ልጅ ትውለድ በሽተኛ ፤ ተመራማሪ ትውለድ አማራሪ ፤ ጻድቅ ትውለድ ርኩስ ፤ መሪ ትውለድ ተመሪ ፤ መልካም ሰው ትውለድ ክፉ ሰው ከአንድ አምላክ በቀር ማንም አያውቅም፤ ሁሉም ነገር የሚገለጠው በጊዜ ሂደት ውስጥ ነው፡፡
ዘመኑ የዘውድ አገዛዙን ለመገርሰስ ብዙ ወጣቶች ሆ ብለው የተነሱበትና ለአንዲት ሀገራቸው የወደፊት እጣ ፈንታ ብዙ የሚወያዩበት ፤ ብዙ የሚከራከሩበት ፤ ብዙ ርቀት ለመሄድ አንድ ብለው የጀመሩበት ወቅት ነበር ፤ ነገር ግን ሁሉም ወደ ጫፍ ሲደርስ “ደርግ” የሚባል ቡድን ማንም ያላሰበውን የስልጣን ወንበሩን ተቆናጥጦ ያዘ ፤ ብዙም ጊዜ ሳይወስድ ለሀገሪቱ ጥቁር ጠባሳ ጥሎ ያለፈ ታሪክ ፤ ማንም ሊረሳውና ሊዘነጋው በማይችል መልኩ ህዳር 14 1967 ዓ.ም እና ሐምሌ 1971 ዓ.ም  ከ68 በላይ የሀገሪቱ ከፍተኛ አመራሮችን በመረሸን ስራውን ጀመረ፡፡ ይህ ከሆነ በኋላ የእምነት ተቋማት ከእነ አማኞቻቸው የእምነት ነጻነታቸው መሬት ተቆፍሮ ተቀበረባቸው ፤ ከአንድ ትውልድ በላይ በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ሰውን በ17 የስልጣን ዘመን በተለያዩ ምክንያቶች ገደለ ፤ ሀገሪቱን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር በተነሳው አብዮት በ17 ዓመት የደርግ አገዛዝ ውስጥ በሁሉም ነገር 170 ዓመት ወደ ኋላ ወሰዳት ፤ እነዚህ በግፍ የተገደሉ ሰዎችን 38 ዓመታቸውን በማሰብ ዛሬ ህዳር 14 2005 ዓ.ም በጸሎት በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስትያን ታስበው ውለዋል፡፡ “የእናት ምጥና አብዮት ምን ይዞ እደሚመጣ አይታወቅም”……….



                      የ68 ባለስልጣናት የሞት ደብዳቤ
 


በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን  ውስጥ የተሰራላቸው መታሰቢያ

                           (ይህን ቦታ ፎቶ ማንሳት ካሜራ ያስነጥቃል)


No comments:

Post a Comment