Wednesday, November 7, 2012

በመጨረሻም አባ ናትናኤል ከአስተዳዳሪነታቸው ተወገዱ


(አንድ አድርገን ጥቅምት 28 2005 ዓ.ም)፡- ከአመት በፊት የሀዋሳን ምዕመን ሲያስለቅሱ ከነበሩት አንዱ መላከ ገነት አባ ናትናኤል መላኩ አየር ጤና አንቀጸ ብርሃን ኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን  አስተዳዳሪ ተደርገው  ከቤተክህነት  ተሾሙው እስከ አሁን ሲያስተዳድሩ እንደነበር ይታወቃል ፤ በየጊዜው ቀድሞ በሰሩት ስራ የተለያዩ ክሶች እየቀረበባቸው ከአዲስ አበባ ሀዋሳ በፖሊስ ተይዘው ታስረው ፍርድ ቤት ሲቀርቡ የነበሩት አባ ናትናኤል በስተመጨረሻ ከአየር ጤና  አንቀጸ ብርሃን  ኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን ከአስተዳዳሪነታቸው መነሳታቸው ታውቋል ፡፡ በእርሳቸው መነሳት ምዕመኑ ከፍተኛ እፎይታ ተሰምቶታል ፤ ባሳለፍነው እሁድ 25/02/2005 . ከቅዳሴ በኋላ ለመጨረሻ ጊዜ ያስተማሩት አባ ናትናኤል “ከዚህ የትም አልሄድም” ሲሉ የነበሩት እና በአውደ ምህረት ላይ ብጥብጥ አስነስተው ለመቆየት ያደረጉት ሙከራ ሳይሳካላቸው መቅረቱ ታውቋል፡፡
በአውደ ምህረት ላይ የእግዚአብሔርን ቃል እንደማስተማር ራሳቸውን ነጻ ለማድረግና በመጣር “ ኢንተርኔት ላይ አንድ አድርገን የሚባል ድረ-ገጽ ስሜን እያጠፋ ነው ፤ ባልሰራሁት ስራ እየወነጀለኝ ነው” በማለት ተናረዋል ፤ “አንድ አድርገን” ከዚህ በፊት ያደረጉትን ነገር ከመዘገብ ውጪ ስማቸውን አላጠፋችም ፤ አባ ናትናኤል ከተሃድሶያውያን ጋር በማበር ለአውደ ምህረት በማይመጥኑ ሰዎች አማካኝነት ሲያስፈነጩበት ነበር ፡፡
ምዕመኑ እኝህን በመሰሉ ሰዎች መታወክ መቻል የለበትም የሚል አቋም አለን ፤ “አንድ አድርገን” ፍርድ ቤት በሰሩት ስራ በወንጀል ተከሰውና በፖሊስ ተይዘው ወደ ሀዋሳ ሲሄዱ የሆነውን ነገር ተናግራለች ፤ ፤ ምግባራቸውን እና ስራቸውን አደባባይ ላይ አስቀምጣለች ፤ ወደፊትም በሄዱበት ሁላ ከእኩይ ስራቸው ካልተመለሱ የሰሩትን ፤ ለመስራት ያሰቡትን በመከታተል ሰዎች ዘንድ መረጃ ታደርሳለች ፤ ቤተክርስትያኒቱን እንደ ምስጥ ሆነው ከውስጥ የሚቦረቡሯን ሰዎች አይታ ዝም ማለት አይቻላትም ፤ እኛን መስለው ነገር ግን ከእኛ ያልሆኑትንም ሰዎች በመከታተል ሚስጥር ስራቸውን በአደባባይ ታሰጣለች፡፡ 

የዛሬ አመት እኝህን አባት አንቀበልም ያለው ምዕመናን በግድ እንዲቀበል ተደርጎ ነበር ፤ መላከ ገነት አባ ናትናኤል መላኩ አሁን ደግሞ የትኛው ቤተክርስቲያን  ይመድቧቸው ይሆን ? እኛ እንደ ቀድሞ ወደ ቦታቸው እንዳይመልሷው እንሰጋለን፡፡ 
 ቸር ሰንብቱ

1 comment:

  1. yih zegeba ewnet silemohunu min mereja ale? please if there is any?

    ReplyDelete