Wednesday, November 14, 2012

ጸሎቱ የተሰማለት ሰው




(አንድ አድርገን ህዳር 5 2005 ዓ.ም)፡- ቀኑ የጽጌ ጾም የመጨረሻው እሁድ  ቀን ነበር ፤ ማህሌተ ጽጌ የተፈጸመበት ዕለት ፤  የመጨረሻውን ማህሌተ ጽጌ በዚች ቤተክርስትያን ነበርኩበጣም በጠዋት ቅዳሴው ተጀምሮ ደስ በሚል ሁኔታ ተጠናቅቋል ፤ከቅዳሴው መጠናቀቅ በኋላ የእመቤታችን ተዓምር ተነበበ ፤ ቤተክርስትያን ውስጥ ያስቀደሰው ምዕመን ከውስጥ ሲወጣ ደጅ ያሉት ደግሞ ወደ አውደ ምህረቱ በመቅረብ ቀጣይ መርሀ ግብሩን ተካፍሎ ለመሄድ አረፍ አረፍ ብለዋል ፤ በየሳምንቱ ምዕመናን ተስለው የተሳካለትን ነገር በአውደ ምህረት ላይ እየተናገረ የተሳለውን ብርም ይሁን የቤተክርስትያን መገልገያዎችን መስጠት በየሳምንቱ የተለመደ ነገር ነው ፤  አንድ አባት በአውደ ምህረት ላይ እንዲህ በማለት የቀኑን ስዕለት የተሰማለት ሰው ነገሩን መናገር ጀመሩ “ዛሬ ደግሞ የተነገረኝ ስዕለት እንደ እስከዛሬው ካለው ለየት ይላል ፤ ይህን የነገረኝ ወጣት እንዴት ለጓደኞቻችን  ማሰብ እንዳለብን ያስተምረናል ፤ ለአንድ ክርስትያን ምን ያህል ማሰብ እንዳለብን ያስገነዝበናል” አሉ፡፡


ጉዳዩ እንዲህ ነው “ በጣም የሚወደው ጓደኛው ከአንዲት ሙስሊም ጋር ፍቅር ይዞት ነበር ፤ ይህንን ጉዳይ  ሲያማክረኝ ‹ሁሉም ነገር ይቅር እንጂ ይህ ነገር መሆን መቻል የለበትም› ብዬ የወንድምነቴን ቁጭ አድርጌ መከርኩት ፤ ልጁ ምን እንደነካው አላውቅም ምክሬን ሊሰማኝ ፍቃደኛ አልሆነም ፤ እነዚህ በእምነት የማይመሳሰሉ ሁለት ጓደኛሞች  በስተመጨረሻ ለመጋባት ወስነው ልጁ እምነቱን ለእሷ ብሎ እንደሚቀይር ነገረኝ ፤ ይህን ነገር ሲነገረኝ የሰማውን ጆሮዬን ማመን ተሳነኝ ፤ በዚህ ሰዓትም እጅጉን አዘንኩኝ ምንም ማድረግ ስላልቻልኩኝ በቀጥታ አዲስ አበባ አውጉስታ አካባቢ የምትገኝው ጽዮን ማርያም ቤተክርስትያን በመሄድ ይህ ነገር እንዳይሆን አልቅሼ ነገርኳትኝ ፤ ከተቻለ እሷ ወደ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ተቀይራ እምነቱንና ስርአቱን ተምራ እንዲጋቡ ፤ ያለበለዚያ ደግሞ ጓደኛዬ እምነቱን እንዳይቀይር እንድትረዳው ነበር ጸሎቴ ፤ እመቤቴም አላሳፈረችኝም ሀይማኖቱን ሊቀይር የነበረውን ጓደኛዬን ልቦናውን መልሳለት በቀድሞ እምነቱ ሊጸና ችሏል ፤ ከዚህ በላይም እንደ እግዚአብሔር መልካም ፍቃድና እንደ እመቤታችን አማላጅነት ልጅቷን በማሳመንና የእምነቱን ስርዓትና ትምህርተ ሃይማኖቱን በማስተማር እሷ ወደ ኦርቶዶክስ መመለስ ችላለች ፤ ባለፈው ወር ላይም ሁለቱም ገጠር ቤተሰቦቻቸው በመሄድ በስርአተ ቤተክርስትያን ጋብቻቸውን ፈጽመዋል ፤ እኔም የተሳልኩትን ዣንጥላ ቃሌን በመጠበቅ ይዤ መጥቻለሁ ፤ ስለዚህ እኔን የሰማች እናንተንም ትስማችሁ ፤ ሁላችሁም በእልልታ እመቤቴን አመስግኑልኝ” ብሏል በማለት ተዓምሩን ሲናገሩ በቦታ የነበረው ምዕመን ታቦት የወጣ እስኪመስ ድረስ ግቢውን በእልልታ በአንድ እግሩ አቋመው፡፡


ለወንድማችን የተለመነች ለኛም ትለመነን..አሜን


5 comments:

  1. I don't know what the problem with the church is... but Ethiopian churches are designed to be made as a circle... why like this ... This is not a church...

    ReplyDelete
  2. እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን! በጣም የተባረከ ወንድም ነዉ። ስለጓደኛ፤ ወንድምና እህት ብሎም ወገን ግድ የሚለዉ ዛሬ ላይ መታየቱ እፁብ አስብሎኛል።

    እባካችሁ ወገኖቼ እኔም እንዲሁ በዚህ የጽጌ ፆም ወራት እመቤቴን ስለምን የቆየሁት የአንዲት ጓደኛዬ ልጅ ወደእስልምና እምነት ከገባ ዓመታት መቆጠሩን በመስማቴ እጅግ አዝኜ ነዉ። እባካችሁ በፀሎታችሁ አስቡት፤ ስሙን አልጠቅስም እመቤቴ ከነልጇ ያዉቁታል። አዉቆና ተራቆ እምነቱን የለወጠ ሳይሆን ስለዕምነቱ ሳያዉቅ የተጠለፈ ነዉና አስቡት።
    ድንቅ ተዓምራቱን ለመመስከር ወደኋላ አልልም። አዘክሪ ድንግል በሉልኝ!
    የእመብርሃን ፍቅር በያለንበት ይብዛልን!
    እንኳን ለቁስቋም ማርያም በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!

    ReplyDelete
    Replies
    1. Amen.emebete libonawun timelsew.

      Delete
  3. amen!john 2:1-11 "--jesus' mother said to him,'They have no more wine' ---

    ReplyDelete
  4. yet bota ?
    Where is the name of the church & the address? PLS mentoin.

    ReplyDelete