Thursday, November 22, 2012

የሰማዕቱ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ሃውልት ሊፈርስ ነው

  • የእምዬ ሚኒሊክ ሐውልትም ሊፈርስ ይችላል


(አንድ አድርገን ህዳር 13 2005 ዓ.ም)፡-  የግብፅ ቤተ ክርስቲያን ከአንድ ሺ ስድስት መቶ ዓመታት በኋላ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዕውቀት መንፈሳዊ ከእርሷ ተወልደው በእቅፏ ውስጥ ባደጉ ኢትዮጵያውያን ጳጳሳት እንድትመራ ፈቃዷን ስትገልጽ ከተመረጡት አባቶች አንዱ በመሆን ግንቦት 18 ቀን 1921 ዓ.ም. በእስክንድርያው መንበረ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን ማዕረገ ጵጵስናን ተቀበሉ። ከዓመት በኋላም “አቡነ ጴጥሮስ ጳጳስ ዘምሥራቅ ኢትዮጵያ ተላዌ አሠሩ ለአቡነ ኢየሱስ ሞዓ” ተብለው ተሾሙ።



በ1928 ዓ.ም. አረመኔው የኢጣልያ ፋሺስት በግፍ አገራችንን ለመውረር ክተት ሠራዊት ምታ ነጋሪት በማለት ውቅያኖስ አቋርጦ በመምጣት ኢትዮጵያን ሲወርና ሕዝቧን፣ ሊቃውንቷን፣ ገዳማቷንና አድባራቷን በግፍ ሲጨፈጭፍ ያዩት ብፁዕነታቸው ወራሪውን ኃይል ከኢትዮጵያውያኑ አርበኞች ጋር በመሆን በጸሎት ሊዋጉት ቆረጡ። የወቅቱ የአገሪቱ መሪ ግርማዊ ንጉሠ ነገሥት በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል ከአረመኔው ፋሺስት ጦር ጋር በመፋለም ላይ የነበረውን አርበኛ ለማበረታታት ወደ ማይጨው በሔዱ ጊዜ ብፁዕነታቸው ተከትለው ሔዱ። ከዚያ እንደ ተመለሱም በታላቁ የደብረ ሊባኖስ ገዳም ተሰባስበው የቤተ ክርስቲያን አምላክ በኢትዮጵያውያን ላይ የመጣውን ችግር እንዲያስታግሥ በጸሎት እየተጉ ወደነበሩት አባቶችና አርበኞች በመሔድ ለአገርና ለነጻነት መሞት ቅዱስ ተግባር መሆኑን በመስበክ ሁሉም እንዲጋደሉ ማሳሰብ እና ማትጋት ጀመሩ። ኋላም የገዳሙ መነኮሳትና የሰላሌ አርበኞች ይባሉ የነበሩት አርበኞች ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ተሳታፊ ሆኑ። ከዚያም አርበኞቹ የቻሉትን ሁሉ አድርገው ወደ ሰላሌ ሲመለሱ ብፁዕነታቸው አዲስ አበባ ቀሩ። ብዙም ሳይቆዩ በጠላት እጅ ተያዙ። ከጥቂት ጊዜ በኋላ በስምንት ጥይት አሁን ሃውልታቸው ከሚገኝበት ቦታ ዝቅ ብሎ ባለው ቦታ ላይ ሰማዕትነትን ተቀበሉ፡፡

በአሁኑ ሰዓት የአዲስ አበባ የባቡር መንገድ ስራ ከተማዋን ከጊዮርጊስ ፤ በአትክልት ተራ በመርካቶ በኩል አድርጎ በአብነት  ኮካ ኮላ ጋር ይገጥማት ተብሎ የታሰበው የመጀመሪያው ምዕራፍ  የባቡር መንገድ ምክንያት የአቡነ ጴጥሮስ ሃውልት ሙሉ በሙሉ ከቦታው እንደሚነሳ ታውቋል ፤ በመሰረቱ የመንገድ እና የተለያዩ መሰረተ ልማቶች በማንኛውም ሃገር በሚደረጉበት ጊዜ የእምነት ተቋማትንና እና ለሀገር እና ለህዝብ ትልቅ ውለታ የዋሉትን ለስማቸው መታሰቢያ የተሰየሙ ሃውልቶችን መነካት እንደሌለባቸው ይታወቃል ፤  የአገራቸው በጠላት መወረር፣ የሕዝባቸው መገደልና መታሰር፣ የቤተ ክርስቲያናቸው መደፈር እስከ ሞት ያደረሳቸው እኒህ እውነተኛ ጳጳስ መታሰቢያቸውን ለማንሳት በስመ የባቡር ፕሮጀክት ለዚች ሃገር የዋሉት ውለታ ፤ ለአርበኞች ያሳዩት ተጋድሎ ፤ ህዝቡ በእምነቱ አንድ በመሆን ጠላትን እንዴት መመከለት እንዳለበት ያስተላለፉት መልዕክት ከግምት ውስጥ ሳይገባ እንደ ተራ ሃውልት ለማንሳት ሃውልቱ የቀናት እድሜ በቦታው ላይ እንደሚቀረው የባቡር ስራ ፕሮጀክት ስራን በበላይነት የሚመራው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዛሬ በሸገር ሬዲዮ  ተናግሯል፡፡

በአሁኑ ጊዜ የሚሰሩ ትላልቅ ፕሮጀክቶች የእምነት ተቋማትንና ታሪካዊ ሃውልቶችን በጥናት ወቅት ለምን ግምት ውስጥ አስገብተው እንደማይሰሩ መነጋገሪያ ነጥብ ሆኗል ፤ ባልጠፋ ቦታ ዋልድባ ላይ ስኳር ልማት ማቋቋም እና ባልጠፋ መንገድ ሃውልቶችን እያነሱ መንገድ መስራት የሃገሪቱን ታሪክ ጥላሸት ከመቀባት በላይ ሃገሪቱ አለኝ የምትላቸውን ቅርሶች ከማጥፋት የማይተናነስ ስራ መስሎ ይታየናል፡፡  ከዚህ ጋር በተያያዘ ስለ ሚኒሊክ ሐውልት ከተማ መስተዳድሩ ያለው ነገር ባይኖር ስለ አጼ ሚኒሊክ ሐውልት ባለሙያዎች እንደሚሉት የባቡር መንገዱ ዲዛይን ካልተቀየረ በቀር የሚኒሊክንም ሐውልት እንደሚነካው አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡




እኛ እያልን ያለነው ሀገሪቱ ላይ የሚሰሩ ፕሮጀክቶች ለምን ቅድመ ጥናት ሲካሄድ የእምነትና የሐውልት ቦታዎች ፤ የአባቶቻችን ለቤተክርስቲያንም ሆነ ለኢትዮጵያ አሻራቸውን ያስቀመጡበት ቦታ ከግምት ውስጥ አይገባም ? ወይስ ከበስተጀርባ ሌላ ነገር አለ……?..

“አይጥ ለሞቷ የድመትን አፍንጫ ታሸታለች” ይላል ያገሬ ሰው


የታሪክ ምንጭ፡- ዲያቆን መልአኩ እዘዘው

14 comments:

  1. እፉፉፉ pleas be open mined አሁን አዲስአበባ ነዉ ባልጠፋ ቦታ የሚባለዉ ባይሆን ከተነሳ የትነዉ የክብር ቦታ የሚሰጠዉ ቤ/ክ ምንድርነዉ የሚጠበክባት በመሰረቱ የአቡነ ጴጥሮስ ሀዉልት እዛ እንደተራ ነገር ብቻዉን መቆም ነበረበት ወይ በሌሎች ህገርም ቢሆን በሀይማኖታዊም ሆነ በሀገራዊ ጉዳይ ታሪካዊ ስራ ያላቸዉ ሰዎች የሚመለከተዉ አካል ሙዝየም አሰርቶ ስርቸዉ ለትዉልድ መማርያ እንዲሆን ያደርጋል የእነ ማርቲንሉተር ሙዝየም የእነ ጆርጅ ዋሽንግተን የእነ ጂሚካርተር ሴንተር ታድያ ለምንድነዉ ቤ/ክ ሙዝየም አስርታ እንዲህ በቤተከርስትያንም በህገርም ሊዘከሩ የሚገባቸዉ ቅዱሳን ለትዉልድ መማርያ እንዲሆኑ ዘመኑን የዋጀ ስራ ለምን አይሰራም ከማለት ይልቅ ጽንፍ ይዛችሁ አትጻፉ ለዚህ እነ ኢሳት ይበቃሉ ወይስ መንፈሳዊ ኢሳት ናችሁ

    ReplyDelete
    Replies
    1. አንተ የፈረንጅ ተላላኪ ደደብ የት ይገባሐል በቁምህ እስክቀብሩህ ነዉ የምትጠብቀው ወይም ቀንድኛ የተሃድሶ ተላላክ አለበለዚያም ካድሬ መሆን አለብህ::እውነት አይዋጥልህም

      Delete
  2. ሐውልቱ ከዛ ሥፍራ ተነስቶ ፣ ዳግም ሌላ ጊዜም እናፍርስ እንዳይባል ፣ የወቅቱን ማስተር ኘላን ተከትሎ በሌላ አመች ቦታ የሚተከል ከሆነ ምንም ማለት አይደለም ፡፡ የማይገባኝ በመሃከላቸው የሚገኙትን የመዘጋጃ ቤቱንና የጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያንን እንዴት ሊያደርጉት ይሆን ፡፡ ወይንስ አብረው ሊፈርሱ ነው ፡፡ እንዲህ የሚያውድም ዕቅድ ከሆነ ያላቸው በሰላም በአህዮቻችን ብናጓጉዝ ይሻለናል ፡፡

    ReplyDelete
    Replies
    1. ሲጀመር ለምን ይነሳል?ወያኔ የፈረንጅ ተላላኪ ስለሆነ ታሪካችንን አጥፍቶ በነጭ ታሪክ መተካት እንደሚፈለግ ተናገሯል ይህንንም ከ ኅርማን ኮል ከተባለ አሜሪካዊ አይሁድ ጋር በ 1982 ዓ ም እንዴት ማጥፋት እንደሚችሉ ሲመክሩ እንደነበር የታሪክ ትዉስታ ነዉ

      Delete
    2. ሲጀመር ለምን ይነሳል?
      እጅግ ትልቅና ሰፊ ጥያቄ ነው ፡፡ መልሴ ግን በአጭሩ የዘንድሮዋ አዲስ አበባ ከመቶ ዓመት በፊት ከነበረችዋ ትንሽ መንደር በብዙ መልኳና ባህርይዋ ስለምትለይ ነው ፡፡ አዲስ አበባ የህዝብ ቁጥሯ ጨምሯል ፤ ይህ የሰው ቁጥር መጨመር ደግሞ የመሠረታዊ ፍላጐቶችን (ውኃ ፣ መጠለያ ፣ መጸዳጃ ፣ መጓጓዣ …)የአቅርቦት ጥያቄ በእጅጉ ያንራቸዋል ፡፡ የመኪናው ቁጥር ጉኗል ፤ ይህን በሥርዓቱ የሚያስተናግድ መንገድ መዘርጋት ግድ ይላል ፤ የውሃ መስመሮችም በየጊዜው መስፋፋትና መዘርጋት አለባቸው ፤ የፍሳሽና ቆሻሻ የማስወገጃ ቦዮች መከፈት ይገባቸዋል ፤ መገበያያ ቦታዎችም በየአማካይ ቦታዎች መዘጋጀት ይኖርባቸዋል ….፡፡ ስለዚህም በየጊዜው ቢያንስ ለሃምሳና ለመቶ ዓመት የሚያገለግል ማስተር ኘላን እየተዘጋጀ ፤ ለውጥና ማሻሻያ ይደረጋል ፡፡ እነዚህ የማሻሻያ ለውጦች ሲደረጉ ደግሞ አንዳንድ የታሪክ አሻራ የሆኑትን ነገሮች መነካካቱ አይቀርምና ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል ፡፡ እኔን አስደንግጦኝ የነበረው አሮጌ ግንብ ቤት ለህይወት አደጋ ስለሆነ ሊፈርስ ነው ተብሎ እንደሚዘገበው ዓይነት ሆኖ መቅረቡ ነው ፡፡ ለጊዜው ከቦታው ማንሳትና መልሶ እንደነበረ ማስቀመጥ ማፍረስ አይባልም ፡፡ ለዚሁም ሲባል ብዙ ገንዘብ ተከፍሎ የውጭ ልምድ ያላቸው ሙያተኞች እንደሚሰሩ ፣ ጉዳዩን ለማጣራት ያነበብኩት መግለጫ ያስረዳል ፡፡ ችግሩ የዳግማዊ ምኒልክን ሐውልት ጨርሶ አይመለከተውም ፡፡ የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ለጊዜው በጥንቃቄ ተነስቶ ፣ መተላለፊያ ፉካው (underground tunnel) ከተዘጋጀ በኋላ ከነበረበት ተመልሶ ይተከላል ይላል ፡፡ ዝም ብለው ማፍረስ ቢፈልጉ እኮ ለአንድ ሰካራም አንድ ከባድ መኪና መስጠት ብቻ በቂአቸው ነው ፤ ምን መሥራት እንደሚችሉ ሁላችንም እናውቃለን ፤ ብዙ ሃተታ ሳይሰጥበት ፈረሰ ተብሎ ምራቅ ይመጠጥ ነበር ፡፡ የተንኰል ሥራዎችን በጥንቃቄ ለመለየትና ለመተቸት ፣ ሃሳብ ለመስጠትም እንሞክር ፡፡ ሁሉ መጥፎ ሊባል አይችልም ፡፡

      Delete
  3. ETHIOPIA SEW ATACH MALET NEW?ENEZIH LIBACHEW YABETEBACHEWUN TEWU MILACHEW YELEM ENDE?AND LIB YALEW HALAFINET MISEMAW SEW ALEMENORU YETARIK TEWEKASH KEMEHON AYADINENIM!ESKEMECHE GIN????

    ReplyDelete
  4. The historic enemy of ETHIOPIA IS NOT ONLY THE GROUP THAT IS DOING ITS BEST TO DEMOLISH Ethiopia.
    there are some behind the group who provides hands
    to weaken our belief,orthodox.now should be the time to say no strongly.timidity leads to intimidation .God will never leave us alone if we stand against this devil sent act. may God help our
    effort to save our countrys history.may God save us. may God send angel for these notrious
    hitoric enemies of the generation.

    ReplyDelete
  5. ጣሊያን የሹምባሽ አስረስ አለቃ አቡነ ጴጥሮስን ገደለ፡ የሹምባሽ የልጅልጅ የብጹ ጰጰስ አቡነ ጴጥሮስን ሀውልትን አፈረሰ፡፡ ነገ ደግሞ ጣሊያንን እና ሹምባሽ ወይም ሙንጣዥ አስረስን የርበደበደውን የዕምዪ ምኒልክን ህውልት የሙንጣዥ የልጅልጅ የፈርሰዎል፡፡ ይህ ነው ደመላሽ የሙንጣዥ ልጅ ማለት፡፡

    ReplyDelete
  6. what do you expect for the new prime minster,you should remeber around 1920s i am not exactly sure about the year that he was the king of ethiopia ,what legi eyasu (did he built mosque) in addis ababa so the same thing to hailmariam desalgneGOD be with Ethiopia.

    ReplyDelete
  7. SO WHAT? OUR COUNTRY NEED DEVELOPMENT FOR ALL STREETS OR ROAD TO CONNECT EACH OTHER. WE HAVE TO ENCOURAGE FOR GOOD CHANGE. WHEN YOU DO SOMETHING IT CREATE SOME SIDE EFFECT AND WE COME TOGETHER FIND A SOLUTION NOT BY STUPID CRITICIZED. IF REALLY EVERYONE GOOD VISION FOR OUR GREAT COUNTRY DEVELOPMENT, LETS US SUPPORT THEM. NO BODY DENIED ABUNE PETROSSE DIED FOR OUR COUNTRY. PLEASE LETS US ASK OUR SELVES, DO I HAVE A GREAT VISION FOR MY COUNTRY ? HOW CAN I APPLY MY POSITIVE VISION TO ETHIOPIA AND PEOPLES? THE ANSWER IS JUST TRY LITTLE BIT YOUR PART ANY PLACE AND ANY TIME. THE REST OUR LORD GOD WILL TAKE CARE IT.

    ReplyDelete
  8. እባካችሁ መልካም ነገር ለሀገር እናስብ. ለሀገራችን እድገት ሁላችንም የራሰችን ጥረት ልናደርግ ይገባናል። ዛሬ ሥራው እየተሰራ ያለው በዚህች ቅድስት ሀገር ላይ ነው። በአሜርካና በአውሮጳ የራስን ህይወትና ኑሮ እያመቻቹ ደሀው የሀገራችን ህዝም ለምን እድገት ያገኛል ብሎ መተቸት አዋቅነት አይደለም። ለምን ብባል ዛሬ በውጪው አለም ያሉት ኢትዮጵያውያን በመንገድ እንኻን ስገናኙ ሰላም አይባባሉም ለዝያው የቤተ ክርስቲያን ሰዎች ነን የሚሉት። ከአገልጋዮችን ጨምሮ። ታድያ እንድህ በሰው ሀገር አብሮ መኖር ያልቻለው ሰው እንዴት አድርጎ ለሀገር እድገት ያስባል። ከጥፋት በስተቀር። የአቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ለሀገር እድገት ለተሻለ ነገር ተብሎ ቦታ ተቀይሮ ብስራ ምን ጉዳት አለው? ጠነኛ አእምሮ ያለው ሰው እንድህ አይተነቱን የሀገር ለውጥ መሻሻል ለምን ይጠላል? ጉድ ነው .......ስለ እውነት እንነጋገር ካልን ለምን በውጪ ያሉትን ኢትዮጵያዊን አንድ አታደርጉም? ለማትኖሩባት ኢትዮጵያ ምድር አትጨነቁ እግዚአብሔር አምላክና ቅድስት ድንግል ማርያም አሉላት። ይልቁን ስለ ሀውልት ከምትቆረቆሩ ዛሬ በሀጢአቱ እየሞተ ላላው ወንድሞቻችን ተጨነቁ ይህ አይነት የቅድስና ሥራ ለሰማያዊ ታላቅ መንግስት ያበቃናል። ብዙ ኢትዮጵያዊያን ዛሬ በውጪው አለም በረዳ አደራር ሆነዋል። ያሳዝናል። እድገት ከዚህ ዓይነቱ መረዳዳት ይጀምራል። ቅዱስ ቀሉም በአጠገብህ ያለውን በዓይነህ የሚታየውን ወንድምህ ሳትውድ እንደት አድርገህ የማታየውን አምላክህን ልትወደው ትችላል ይል የለም 1ኛ ዮሀ ም 3።

    ReplyDelete
  9. wendem ye ethiopianen hewet yeyazew eko bewuch yalew diaspora mehonun aseb:let teqen sertew eko new lebetesebochachew bemelak lehagerem le ethiopiawuyan hulu mesesowoch nachew:kemengest kadriwoch bemusena ketechemalequt weym andand investeroch besteqer:diasporaw eko new lerasu sayaseb lewegenechu eyesera yemigebr:yihenen yemiresa dengay ras bicha new

    ReplyDelete
  10. SOME MEEK INDIVIDUALS ALWAYS SEE ONE SIDE OF A COIN AND CRY ABOUT THE DEVELOPMENT OF THE CITY OF ADDIS ABABA.THEY NEVER SEE WHAT IS IN THE NAME OF
    DEVELOPMENT.WHERE DOES IN THE WORLD SUCH ANNIHILATION HAPPEN.GOD KNOWS THE
    HIDDEN PURPOSE IN THE TRANSFORMATION PLAN.HE WILL PAY WHAT THEY SHOULD
    DESERVE AS HE HAS PAID FOR SOME RECENTLY.WAIT AND SEE.


    ReplyDelete
  11. Mnew andargnoch yfersal tebsle blachu endetsafachu Hulu mengst bekbr tendto bekbr wede botaw ymelesal blua blachu atzegbum yh tkkl aydelem nestsa honacu lemzegb mokru

    ReplyDelete