Tuesday, November 27, 2012

“እኛ የክርስቶስን መስቀል በመካከላችን አድርገን መወያየት አለመቻላችን ያስተዛዝባል፡፡” መጋቢ ሀዲስ እሸቱ አለማየሁ


  • በሁሉ ነገር ላይ እኛ ቤተክርስቲያናችን እናስቀድም ፤ እኛ ከመነቃቀፍ ይልቅ ተከባብረን ፤ ከመራራቅ ይልቅ ተቀራርበን አንድ ሆነን ብንነጋገር የማይፈታ  ችግር የለም” አቡነ መርቆርዮስ ለሰላም ኮሚቴው የተናገሩት
  • አቡነ መርቆርዮስን ለማውረድ ቅዱስ ሲኖዶስ በተሰበሰበበት ወቅት የተጻፈውን ቃለ ጉባኤ እንዳየሁት    “እኔ ከዚህ አልስማማም ፤ የኔ ድምጽ በልዩነት ይያዝልኝ” ያሉ አቡነ በርናናስ ብቻ ነበሩ...... ዲ/ን ዳንኤል ክብረት
  • ትልቁ ነገር ሁለቱም ሲኖዶሶች ተገናኝተው ቤተክርስቲያኒቱን ማዕከል አድርገው የሚነጋሩ ከሆነ የማይፈታ ችግር አይኖርም፡፡” ሊቀ ካህናት ኃ/ሥላሴ
  • “ቤተክርስቲያን ያለ ፓትርያርክ የቅርብ አመራር ለብዙ ዘመን የቆየች ቤተክርስቲያን ናት ፤ ያለ አንድነቷ ግን መኖር ከባድ መሆኑን በተለያየ ጊዜ አይተዋለች፡፡” ዲ/ን ዳንኤል ክብረት
  • “አሜሪካ ሆነው ስንት ጆሮ በተከፈተበት ፤ ምላስ በበዛበት ፤ የዜና ማሰራጫዎች በበዙበት ቦታ ቁጭ ብለው ምንም አይነት ነገር ባለመናገራቸው በዘመኑ ቋንቋ እጅግ በጣም  አድናቂ ነኝ፡፡ የእስከ  ዛሬ ዝምታቸው ተገቢ ነው ፤ የአሁኑ ዝምታቸው ግን ይህን ያህል አስፈላጊ ነው ብዬ አላስብም ፡፡” መጋቢ ሀዲስ እሸቱ አለማየሁ

(አንድ አድርገን ህዳር 18 2005 ዓ.ም)፡የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ እሁድ 15/03/2004 ዓ.ም  ከአዲስ አበባ መጋቢ ሀዲስ እሸቱ አለማየሁ እና  ዲያቆን ዳኤል ክብረትን ከአሜሪካ ደግሞ ከሰላምና የእርቅ ኮሚቴ ሊቀ ካህናት ኃ/ሥላሴ አለማየሁ ከዴንቨር እና ጉዳዩ የማይመለከታቸው በቅዱስ ሲኖዶስ ስለ ምፍቅናቸው ተጠይቀው መልስ መስጠት ያልቻሉት አባ ሰረቀ ብርሀንን በማቅረብ አወያይቷል ፡፡ በዚህ ውይይት ቀሲስ ዘበነ ተገኝተው ሃሳባቸውን ይሰጣሉ ተብሎ ቢጠበቅም በውይይቱ ወቅት ሳይመቻቸው በመቅረቱ ውይይቱን ሊካፈሉ አልቻሉም ፡፡ 


የአባ ሰረቀን አስተያየት በማስቀረት ውይይቱ ጥሩ እና አስተማሪ ሆኖ ስላገኝነው ውይይቱን ወደ ጽሁፍ በመቀየር እንዲህ አቅርበነዋል፡፡ ፡፡ (የአባ ሰረቀን በእርቀ ሰላሙ ላይ የሰጡትን አስተያየት በሚዲያና በድረ ገጽ ማቅረብ በቤተክርስቲያናችን ወቅታዊ ጉዳይ ላይ እውቅና እንደመስጠት ስለቆጠርነው ትተነዋል ፤ “ይቺ ጠጋ ጠጋ ……” ፡፡)


ጥያቄ፡- በኢትዮጵያው ያለው ቅዱስ ሲኖዶስ ቀን አይቁረጥ እንጂ ፓትርያርክ ለመምረጥ በዝግጅት ላይ ይገኛል ፤ አራተኛውን ፓትርያርክ ወደ መንበራቸው ለመመለስ እንደማይታሰብ ቅዱስ ሲኖዶስ በጸሀፊው አማካኝነት ገልጿል ፤ ይህ ከሆነ ዘንዳ ሰላሙ እንደምን ይመጣል? የሚሉ ሰዎች አሉ ፤ በእርስዎ በኩል ምን ይላሉ ሊቀ ካህናት?

ሊቀ ካህናት ኃ/ሥላሴ፡- እግዚአብሔር ይስጥልኝ አመሰግናለሁ ፤ ስለ ቤተክርስቲያን ስንነጋገር ቤተክርስቲያኒቱ ባለቤት አላት ፤ ባለቤቷም እግዚአብሔር ነው ፤  የኮሚቴያችን የመጀመሪያ ጥረት እግዚአብሔር ይችን ቤተክርስቲያን ሰላም እንዲያደርግልን ፤ የአባቶቻችንን ልቦና አንድ እንዲያደርግ ፤ የራሳቸውን አስተሳሰብ ለውጠው ቤተክርስቲያኒቱን ማዕከል እንዲያደርጉ ነው ትልቁ ጥረታችን፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ሁለቱን ወገኖች በፍጹም ማገናኝት አይታሰብም ተብሎ የነበረ ቢሆን እኛ በአሜሪካ አሪዞና ላይ ተገናኝተው አይተነዋል ፡፡  በአባቶች ዘንድ በእርቀ ሰላሙ ጉዳይ ምን አይነት ፍላጎትና ምን አይነት ስሜት እንደነበረ እናውቃለን ፡፡ አሁን እንደተነገረው በአዲስ አበባ ያለው ቅዱስ ሲኖዶስ የራሱ የሆነ ሃሳብና ውሳኔ ሊኖረው ይችላል ፡፡ እዚህ ያለው ሲኖዶስ ደግሞ የራሱ የሆነ ሃሳብና ውሳኔ ሊኖረው ይችላል ፤ ትልቁ ነገር ሁለቱም ሲኖዶሶች ተገናኝተው ቤተክርስቲያኒቱን ማዕከል አድርገው የሚነጋሩ ከሆነ የማይፈታ ችግር አይኖርም ፡፡  ኮሚቴው ተነጋግረውና ተወያይተው ችግሩን ሊፈቱ ይችላሉ የሚል እምነት ነው ያለው  ፤ ኮሚቴው እገሌ እንዲህ መሆን አለበት ፤ እገሌ እንዲ መሆን የለበትም ብሎ ውሳኔ መስጠት አይችልም ፤ ሁለቱንም አገናኝቶ እና አቀራርቦ ቤተክርስቲያኒቱን ማዕከል ያደረገ  ፤ የነገውን ትውልድ ታሳቢ ያደረገ ፤ ቤተክርስቲያኒቱ ከመለያየት ፤ ትውልዱ ከመጥፎ ታሪክ እንዲድን ፤ ዛሬ እንደ ቀላል ነገር የምናየው ነገር ነገ ከባድ ሆኖ መፍትሄ ወደሌለው ችግር እንዳይሸጋገር የሚያስችል ውይይት ያደርጋሉ ስምምነት ላይ ይደርሳሉ ብለን ተስፋ እናደርጋለን፡፡

አዲሱ፡- በአሁን ሰዓት የተያዘው የፓትርያርክ ምርጫ መሰናዶ በአንድ በኩል ደግሞ ሁለቱን ሲኖዶሶች ለማስታረቅ የተጀመረው  የእርቀ ሰላም ድርድር ሁለቱ የሚጣጣም ሂደት ያለው አይመስለኝም ፤ እርቁ እንዲቀድም የአዲስ አበባው ሲኖዶስ ወስኗል ፤ ነገር ግን እርቁ በስደት ያሉትን ፓትርያርክ ወደ መንበራቸው ያልመለሰ እርቅ ምን እርቅ ይሆናል ? የሚሉ አሉ::  ዲ/ን ዳንኤል ያንተን አስተያየት በዚህ ላይ ብትሰጠን፡፡


ዲ/ን ዳንኤል ፡- የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ከሚያስፈልጓት ዋንኛ ጉዳዮች አንዱ ከፓትርያርኩም በላይ የቤተክርስቲያኒቱ አንድነት ነው ፡፡ ቤተክርስቲያን ያለ ፓትርያርክ የቅርብ አመራር ለብዙ ዘመን የቆየች ቤተክርስቲያን ናት ፤ ያለ አንድነቷ ግን መኖር ከባድ መሆኑን በተለያየ ጊዜ አይተዋለች ፤ ሁለት ሶስት ጊዜ ይህ ነገር ተፈትኗል ፤ ማን ፓትርያርክ ይሁን? የሚለው ጥያቄ አይደለም ለዚች ቤተክርስቲያን ከባዱ ፤ ዋናው ነገር የአቡነ መርቆርዮስ መኖር ወይም አዲስ አበባ ያለው ሲኖዶስ አዲስ ፓትርያር መምረጥ ላይ አይደለም ፤ ይህ ጉዳይ ቢቀርና ስለ ቤተክርስቲያኒቱ አንድነት ብቻ ብንነጋገር መልካም ነው ፤ አንድ ከሆንን በኋላ ፓትርያርኩን መምረጥ የምንችል ይመስለኛል፡፡


አዲሱ ፡አዲስ አበባ ምንም ይሁን ምን ፓትርያርክ ለመምረጥ ዝግጅት ላይ እንዳሉ ስለምናውቅ ያ ዝግጅት ተግባራዊ ከሆነ የሰላሙና የአንድነቱ ጉዳይ ይመጣል ወይ ?


ዲ/ን ዳኤል ፡- እኔ ሁለቱም ቦታ ላይ የማየው ነገር አለ ፤ እዚህ ፍጥነት አለ ፤ ቤተክርስቲያኒቱ ወደ ኋላ መሄድ አለባት ብዬ አላምንም ፤ ወደፊት መቀጠል አለባት ፤ ግን ይህ እንዴት ነው የሚሆነው? ሲባል ይህ በራሱ ሁለተኛ ጥያቄ ነው የሚሆነው ፤ እዚህ 6ተኛ ፓትርያርክ የመምረጥ ሂደቱን ገታ አድርገነው እዚያም ደግሞ አቡነ መርቆርዮስ ወደ መንበራቸው ካልተመለሱ በስተቀር የሚለውን ትተነው ሁለቱም ቁጭ ብለው ምንድነው መደረግ ያለበት? ብለው መወያየት አለባቸው፡፡ ሁሉም ቦታ እየታየ ያለው ያለፈውን ማን አጠፋው ነው ፤ እንደ እኔ ባለፈው ያላጠፋ የለም ፤ መንፈሳውያንና እውነትም ክርስትያኖች  ከሆንን እኛ በደለኞች ነን ብለን ፤ ይችን ቤተክርስትያን በድለናል ማለት መቻል አለብን ፡፡ የተበደለውም ደግሞ በመዝሙር 50 ላይ እንደሚለው እግዚአብሔር ነው ፤ ቅዱስ ዳዊት “አንተን ብቻ በደልኩ ነው ያለው” ፡፡  የተበደለው እግዚአብሔር ብቻ ነው ፤ ሁላችንም እግዚአብሔርን በድለናል ብለን የሚያስማማንን መንገድ ካልፈለግን በቀር እኔ የሁለቱም አቋም የሚያዋጣ ነው ወይም ለቤተክርስቲያኒቱ የሚጠቅም ነው ብዬ አላምንም፡፡

ሰሞኑን ዜና ቤተክርስቲያን ያወጣው አንቀጽ አለ “ወደ ፓትርያርክ ምርጫ መቅደም የለብንም ፤ ጊዜ ሰጥተን ተረጋግተን እንየው ” የሚል ነበር ርዕሰ አንቀጹ ፤ እኔም በዚህ እስማማለሁ ጊዜ ሰጥቶ ማየት ያስፈልጋል ፤ ከዚህ የሚሄዱትም ከዚያ የሚመጡትም ይህን እንደፈተና ብቻ ማየት አለባቸው፡፡

መጋቢ ሀዲስ እሸቱ ፡- እርቅ ሲባል ዋጋ ያስከፍላል ፤ አለም ዛሬ ኃያላን መንግሥታት እንደሚታውቀው ብዙ የኒውክለር መሳሪያዎችን አምርተው አከማችተዋል ፡፡ ምን አልባት በዚያ መሳሪያ አለምን እናጥፋ ቢሉ ራሳቸው እንደሚጠፉ ስላወቁና ስላላዋጣቸው መሳሪያውን በመጋዘን ቆልፈው አሁን ያለው ብቸኛ መንገድ በጠረጴዛ ዙሪያ መወያየት ሆኗል፡፡ እነርሱ ኒውክሌርን ያህል አጥፊ መሳሪያ ይዘው በጠረጴዛ ዙሪያ በመወያየት ሲነጋገሩ እኛ የክርስቶስን መስቀል በመካከላችን አድርገን መወያየት አለመቻላችን ያስተዛዝባል ፤ ይህ ቀላል ነገርም አይደለም፡፡  ስለዚህ ዋጋ ቢከፈልና ለጊዜው ሹመቱን ፤ ስልጣኑንና  ወንበሩን ዘወር አድርገው ስለ ቤተክርስቲያን በቀናነት መነጋገር ቢችሉ ጥሩ ነው ፡፡ በወዲያም በኩል ያሉት መጥፎ ከመቀመጥና ከማሰብ ይልቅ በመጀመሪያ ፍቅር ለመመስረት ፤ በወዲህም ያሉት መርጦ ሹሞ ለማስቀመጥ ከመጣጣር ይልቅ መጀመሪያ ወደ እርቅ የሚወስዱ መንገዶች ቢጠረጉ  መልካም ነው የሚል አስተያየት አለኝ፡፡

አባቶቻችን መከፈል ያለበትን ዋጋ አሁንም መክፈል አለባቸው ፤ 21 ዓመት ቀላል አይደለም ፤ በጣም ብዙ ስህተቶች አሉ ፤ ሁሉንም አለባብሰን እንትና ደስ እንዲለው ወይም እነ እንትና ደስ እንዲላቸው ብለን አለባብሰን የምንተወው ነገር የለም ፡፡

ዲ/ን ዳንኤል ፤- አሁን ጥፋቶችን ብንዘረዝር ሁሉም ነው ያሉበት ፤ ለምሳሌ አቡነ መርቆርዮስ ሲወርዱ እዚያ ያሉትም አባቶች ነበሩ እዚህም የነበሩ ሽማግሌ አባቶች ነበሩ ፤ ያኔ ሰማእትነትን ለመክፈል እሞታለሁ እንጂ አይሆንም ያለ አባት አልነበረም ፤  አቡነ መርቆርዮስን ለማውረድ ቅዱስ ሲኖዶስ በተሰበሰበበት ወቅት የተጻፈውን ቃለ ጉባኤ እንዳየሁት  አቡነ በርናናስ ብቻ ናቸው “እኔ ከዚህ አልስማማም ፤ የኔ ድምጽ በልዩነት ይያዝልኝ” ያሉ አባት እሳቸው ብቻ ነበሩ ፤ ግማሾቹ አንፈርምም አሉ እንጂ ሰማዕትነትን ለመቀበል የቆረጠ አባት በጊዜው ማንም አልነበረም ፤ ሁሉም ፈርቶ ነው የተወው ፤ ከዚያ በኋላ የተፈጸመው ነገር ሁለቱም ጳጳሳትን ሾመዋል ፤ ችግሮቹ ላይ ብቻ በመነጋገር … ፤ “እኔ” የሚለውን ትተን ሁላችን አጥፍተናል እንበል ፤ ጳጳስ ንስሀ አይገባም ያለው ማነው ? ጳጳስ አያጠፋም ያለው ማነው ? እናንተም አጥፍታችኋል እኛን ይቅርታ ጠይቁ ፤ እኛም አጥፍተናል እናተን ይቅርታ እንጠይቅ መባባል አለባቸው ፡፡ እርቀ ሰላሙ ቢፈጸም እንኳን ብዙ የሚቀሩን ጉዳዮች አሉ ፤ የሀገሪቱ ነባራዊ ሁኔታ ተቀይሯል ፤ ፖለቲካ ሲስሙ ተቀይሯል ፤ እሳቸው ወደ አሜሪካ ሲሄዱ ክፍለ ሀገር ነበር የሚባለው  አሁን ክልል ሆኗል ፤ በጣም ብዙ ነገር ተቀያይሯል ፤ እኘህ አባት መጥተው አሁን ሀገሪቱ ባለችበት  ሶሾዮ-ፖለቲካል ኩነት መስራት የሚያስችላቸው ነባራዊ ሁኔታ  አለ ብዬ በራሴ አላስብም ፤  አሁን ካለው የኢትዮጵያ መንግሥት ጋር በአንድም በሌላም በኩል አልተግባቡም ፤ ወደፊት በአዲስ አመት መንግስት ፓርላማ ሲከፈት ሲጠሩ ይሄዳሉ ፤ ስለዚህ ለሁላችን ይሄ ጉዳይ ስለማይሆን እንተወው ፤ አሁን እኛ የማንከራከርበት ሰው እንዴት እናምጣ ? እንዲህ አድርጎን ነበር  ፤ እንዲህ በድሎን ነበር የማልበትን ሰው እናምጣ፡፡



 ሊቀ ካህናት ኃ/ሥላሴ፡- አሜሪካ ያሉትም "አቡነ መርቆርዮስ ስልጣናቸውን መረከብ አለባቸው" የሚለውን ሃሳብ ገታ እንዲያደርጉ ፤ አዲስ አበባም ያሉትም ፓትርያርክ መሾም አለበት የሚሉትን ሃሳብ ገታ እንዲያደርጉ እና ሁለቱም ተገናኝተው እዲነጋገሩና እንዲወያዩ ነው ኮሚቴው ጥረት እያደረገ ያለው ፤ ግንኙነቱ ከተጀመረ ስምምነቱ ይኖራል ብለን ተስፋ እናደርጋለን ፤ አሁን እኛ እንዲህ ብላችሁ ነው መስማማት ያለባችሁ አንላቸውም ፤ የሚስማሙት እነርሱ ናቸው፡፡ አሁን እንደ ቁልፍ ነገር አድርገን የምንወስደው መገናኘቱ እና መወያየቱ ነው፡፡አንድ የመሆኑ ጉዳይ ፤ ውግዘቱ የሚፈታበት ጉዳይና ጥቃቅን ነገሮች የሚፈቱበት ጉዳይ ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገባቸው ነገሮች ናቸው ፡፡ አሜሪካ ያሉትም ቢሆኑ "ፓትርያርኩ ወደ መንበራቸው ይመለሱ" ለማለት አይቸኩሉበት ፤ አዲስ አበባ ያሉትም ቢሆኑ "6ተኛ ፓትርያርክ እንሾማለን" የሚሉትን ነገር አይቸኩሉበት ፤ አሁን ችግሩ መሰረታዊ መፍትሄ እንዲያገኝ ውይይት ያስቀድሙ ነው እያልን ያለነው ፡፡


አዲሱ ፡- ለመሆኑ እሳቸው ምን ይላሉ? ብለው ጥያቄ የሚያነሱ አሉ ፡፡ ራሳቸው አቡነ መርቆርዮስ ተናግረው አያውቁም ለምን አይናገሩም? ፤ እስከ አሁን ድረስ ከብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ የሰላም ኮሚቴው በቃል ያገኘው ነገር አለ?


ሊቀ ካህናት ኃ/ሥላሴ፡-  አዎ ፤ ብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስን ሄደን በአካል አነጋግረናቸዋል፡፡  እሳቸው ያሉት ነገር “ በሁሉ ነገር ላይ እኛ ቤተክርስቲያናችን እናስቀድም ፤ እኛ ከመነቃቀፍ ይልቅ ተከባብረን ፤ ከመራራቅ ይልቅ ተቀራርበን አንድ ሆነን ብንነጋገር የማይፈታ ችግር የለም” ነው ያሉት፡፡ “እርስዎ ወደ መንበርዎ ይመለሳሉ” ብሎ የሰላም ኮሚቴው አይጠይቃቸውም አልጠየቃቸውም ፤ እኛ ከእሳቸው እንደተረዳነው ተቀራርቦ የመነጋገሩና የመወያየቱ ፍላጎቱ አላቸው ፡፡


አዲሱ ፡- በዳላሱ ጉባኤ ፓትርያርኩ በመካከላችሁ የመገኘቱ ነገር ይኖር ይሆን ?

ሊቀ ካህናት ኃ/ሥላሴ፡- የለም ፤ የሰላም ጉባኤው ፓትርያርኩንና አቃቢ መንበሩን ለተወሰነ ጊዜ ተገናኘተው እንዲወያዩ ፕሮግራም አውጥቶ የነበረ ቢሆንም  አቃቢ መንበሩ ለመምጣት የሚችሉበት እድል  አይኖርም የሚል ውሳኔ ስለተላለፈ ግንኙነቱ አይኖርም፡፡ ብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስን ከአቡነ ናትናኤል ተገናኘተው እንዲወያዬ አስፈቅደን ነበር፡፡


አዲሱ ፡- ቀደም ሲል እንዳነሳሁት የአቡነ መርቆርዮስን እስከ አሁን አለመናገር ሁኔታ እናንተ እንዴት ነው የምታዩት ?


መጋቢ ሀዲስ እሸቱ ፡- ሁለት አይነት አስተያየት ነው ያለኝ እዚህ ላይ፡፡ እሳቸው እስከዛሬ አሜሪካ ሆነው ስንት ጆሮ በተከፈተበት ፤ ምላስ በበዛበት ፤ የዜና ማሰራጫዎች በበዙበት ቦታ ቁጭ ብለው ምንም አይነት ነገር ባለመናገራቸው በዘመኑ ቋንቋ እጅግ በጣም  አድናቂ ነኝ፡፡ ለሁላችንም በተርጓሚ እና በስማ በለው በወኪል ከሚናገሩ ይልቅ በአደባባይ ወጥተው አቋሜ ይሄ ነው ቢሉ ጥሩ ነው ፡፡ የእስከ ዛሬ ዝምታቸው ተገቢ ነው የአሁኑ ዝምታቸው ግን ይህን ያህል አስፈላጊ ነው ብዬ አላስብም ፡፡

 ሁላችሁንም በጣም አመሰግናለሁ፡፡


ቀጣይ ዘገባ፡-በጀርመን ድምጽ ሬዲዮ ላይ ዲ/ን ዳንኤል ክብረት ፤ መምህር ደጉ ፤ ዶ/ር ኃ/ማርያም ያደረጉትን ቃለ ምልልስ ይጠብቁን

8 comments:

  1. Mefiratachew aygermim

    ReplyDelete
  2. WE CHILDREN OF GOD SHOULD NEED TO THINK TWICE
    BEFORE WE DECIDE.JESUS CAME TO THE WORLD TO SAVE US.WE PREACH THE GOSPEL TO THE THE PEOPLE.WE ALWAYS
    SAY WE ARE COMMITTED TO THE GOSPEL.BUT WHEN OUR SOURCE OF INCOME IS IN DANGER,WE MOVE TWO STEPS
    BACKWARD.NOW IS THE TIME FOR ALL CHILDREN OF TEWAHIDO TO COMPROMISE.GOD READS OUR HEARTS.

    ReplyDelete
  3. WE CHILDREN OF GOD SHOULD NEED TO THINK TWICE
    BEFORE WE DECIDE.JESUS CAME TO THE WORLD TO SAVE US.WE PREACH THE GOSPEL TO THE THE PEOPLE.WE ALWAYS
    SAY WE ARE COMMITTED TO THE GOSPEL.BUT WHEN OUR SOURCE OF INCOME IS IN DANGER,WE MOVE TWO STEPS
    BACKWARD.NOW IS THE TIME FOR ALL CHILDREN OF TEWAHIDO TO COMPROMISE.GOD READS OUR HEARTS.

    ReplyDelete

  4. We do know you very well. You revealed yourself by yourself. Do not worry a lot about Aba Serekebirhan Woldesamuel, we do know him much better then you do know him. For you, yes he is very tough and he cannot allow you destroying the holy church, but for us he is our beloved father. He is committed him to the church and he is very dedicated person, that's why you and your supporters always stand against him. So, shame on you by doing this and posting like this. By the way, this is a very good opportunity for us. We know you now very well why you are doing this.

    ReplyDelete
  5. 1 2 3 4 5 then 6
    not 1 2 3 4 5 then 4

    ReplyDelete
    Replies
    1. ፬ተኛው ፍጹም ይለያል

      Delete
  6. D daniel,are you a politician? if not, you would have not given a decision like
    that.There are several options to solve the existing problems between the two
    synodoses.Hopefully,you would be ashamed if both agree and accept Abune
    Merkorios.May God who looks into your heart,and those who planted hatred in their hearts help bless those who pray and exert much effort to go in between.
    You have taught so many times about spiritual encouraging words citing from
    the Bible.Then,why do discourage the hope in the heart of diaspora synodose?

    ReplyDelete
  7. If some one desiгes expert view conсeгnіng blogging аftеr
    that i propose him/her to visit thіѕ weblog, Кeeр
    up the fastidious job.

    Here is my ωеbpagе :: Paydayloanst3.Com
    My page ... Payday Loan

    ReplyDelete