Tuesday, November 27, 2012

በእንተ ሐውልት

From :- Abel Wabella

ለአንዳንድ ኦርቶዶክሳውያን
(አንድ አድርገን ህዳር 19 ፤ 2005 ዓ.ም)፡- የሰማዕቱ አቡነ ጴጥሮስን ሐውልት መነሳት አስመልክቶ ጥቂት ያሳዘኑኝ ጉዳዮች አሉ፡፡ የመጀመሪያውሐውልቱ መነሳቱ ካልቀረ ቢነሳ ችግር የለውም” የሚለው ነው፡፡ ለኔ እንደሚገባኝ እንዲህ ማለት አቡኑ የከፈሉትን መስዋዕትነት ማቃለል እና ዋጋ ማሳጣት ነው ፡፡ ይህን የምልበት ምክንያት መጀመሪያ ስርዓቱ (ሕወሓት መር) ቤተ ክርስቲያኒቷን ሆን ብሎ ከስሯ ለመንቀል እንደሚንቀሳቀስ የታወቀ ነው፡፡ ከትጥቅ ትግል እስካሁን ድረስ ይህ አቋሙ አልተለወጠም ፤ ትላንት ደብረ ዳሞ ገብተው ቤተ ክርስቲያኒቷን እንዲሰልሉና እንዲሰነጥቁ የሐሰት መነኮሳት እያሰለጠነ ሲያሰርግ የነበረው ስብሐት ነጋ ዛሬ ደግሞ ትልቁ ስኬታቸው የኦርቶዶክስ እና የአማራ(አማራ የሚባል ነገር?) “የበላይነት”(quote unquote ) ማስቀረት እንደሆነ በድፍረት ተናግሯል፡፡ ይህ የሚያሳየው ስርዓቱ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ የጠነከረውን በትር ቤተ ክርስቲያኒቷ ላይ እንደሚያሳርፍ ነው፡፡ ስኳር ፋብሪካ ሲባል ተነስቶ ዋልድባ ላይ መንገድ ሲባል ደግሞ ተነስቶ የሰማዕቱ ሐውልት የሚታይ ከሆነ ለምን ? ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል፡፡ በሰለጠነው አለም የአንድ ግለሰብ መኖሪያ አከባቢ አዲስ ነገር ሲሰራ  የሚሰራው ነገር በሰውዬው የወትሮ እንቅስቃሴ፣ አስተሰሳሰብ ልማድ ላይ ያለው ተጽእኖ ታይቶ በንድፍና በሞዴል ቀርቦለት የግል አስተያየቱን እንዲሰጥ ይጠየቃል፡፡ የአንድ ግለሰብ፣ የአንድ ነፍስ፣ የአንድ ንፋስ መብት! እኛ ግን ብዙ ሚሊዮኖች ሳለን እንደማንኛውም ተራ ዜና፣ እንደ ማንኛውም የሐማስ ሮኬት ከሬዲዮ መስማታችን እጅግ ያሳዝናል፡፡ እውነታው ይህ ሆኖ ሐውልቱ እንደማንኛውም ድንጋይ እናነሳዋልን ሲሉን ተሸቀዳድመንየሚመለስ ከሆነ” ብለን እሺ ማለታችን  እጅግ የሚያሳፍር ነው፡፡


ሌላው ይህን ንድፍ የሰሩት ሰዎች እኛም የተማርነውን ምህንድስና የተማሩ ከሆነ አንድን ነገር ለመስራት አንድ አንድ መንገዶች ይኖሩታል፡፡ ከነዚህ ውስጥ ያለውን ፋይናንስ እና ሌሎች አስገዳጅ ሁኔታዎች ግምት ውስጥ ስናስገባ እጅግ ብዙ አማራጮች ይቀሩናል፡፡ መቼም ቦታውን የምታውቁ እና ለሙያው ቅርብ የሆናችኹ ሰዎች ታውቁታላችኹየአቡኑን ሐውልት ሳይነካ የሚያልፍ የባቡር መስመር መዘርጋት ይቻላል፡፡ ለባለታሪኩ ተገቢውን ዋጋ ከሰጡከልብ ካለቀሱ እንባ አይገድም” አንዲሉ አበው ያለ ጥርጥር ይቻላል፡፡ ከቤተ ክርስቲያኒቷ እና ስርዓቱ ተራክቦና የኋላ ታሪክ በመነሳት ምን እየተሰራ ነው? ከዚህ ፕሮጀክት ጀርባ እነማን አሉ? ብሎ አጥበቆ እንደመጠየቅ ዝም ማለት ወይምተመልሶ በቦታው ከቆመ ችግር የለውም” ማለት ተገቢ አይደለም፡፡ አባቶቻችን እነ አቡነ ጴጥሮስም ይህን አላስተማሩንም፡፡እሳቸውም  እሺ ብለው አጎንብሰው ለጣልያን አድረው መኖር ይችሉ ነበር፡፡ ነገር ግን በመንፈስ ከፍ ያሉ በመሆናቸው የበለጠውን መረጡ፡፡ ጉባኤ ዘርግተው፤ አበ ነፍስ ሆነው ካስተማሩት በገነተ ልዑል በፈሰሰው ደማቸው ያስተማሩት በለጠ፡፡ ይህንን አስቤ የአባቶቻችን ልጆች ባለመሆናችን እጅግ ሀዘን ገባኝ፡፡ ከዚህ ሐዘኔ ምን ይነጥለኝ ይሆን? እንጃ! አላውቅም ምንአልባት የሎሬት ፀጋዬን ጴጥሮስ ያችን ሰዓት ደጋግሞ ማዳመጡ ትንሽ ሳይረዳኝ አልቀረም፡፡ ምነዋ! እመብርሃን No comment!!!

ለአንዳንድ ኢትዮጵያውያን
በብዙ ሀገራዊ ጉዳዮች ከጥላቻ የጸዳ ዐሳቦችን ስናቀርብ ስንወያይ መቆየታችን ይታወሳል፡፡ የነገዋ ኢትዮጵያ እጣ ፈንታም ያገባናል ብለን ትንንሽ መስዋዕትነትን ልናዋጣ ተዘጋጅተናል፡፡ ይሁንና ከወትሮ በተለየ የብዙዎቹ ወዳጆቼን የሰላ ምልከታ (critical) ሐውልቱንም በተመለከተ አላየሁኝም፡፡ ይህ በእያንዳንዳችን ውስጥ ያለችው ኢትዮጵያ እጅግ የተለያየች እንደሆነች ነግሮኛል፡፡ በጽዕኑ የማምንበትን የኔን ትውልድን ጤነኛነትም እንደገና እንዳስተውለው አድርጎኛል፡፡ ሐውልት ትክል ነው የማይነሳ:: እንኳን በጎ አርአያ የሆነ ሰው ይቅርና የነሳዳም ሲፈርስአይ! ይህ እንኳን አግባብ አይደለም ትውልድ እየተመለከተ ያለፈውን ይማርበት ዘንድ ይጠበቅብለናል፡፡ የበቀል ጥማት ሁለንተናቸውን ከተቆጣጠረው በቀር፡፡ ምናዋ እንዲህ ያለ አይን ያወጣ የመብት ጥሰት significant ቁጥር ባለው ወገናችን እሴት ላይ ሲደርስ ዝምታን መምረጣችን? ወይስ ባለቤት ካልጮኸ ጎረቤት አይረዳም በሚል ቀመር ነው? የሰማዕቱ ደም ቅኝ ያልተገዛች ሀገር ዜጎች እንድንሆን ያበረከተው አስተዋጽኦ የለምን? የአቡነ ጵጥሮስ ገድል የበጎው ታሪካችን አካል አይደለምን? ባለጊዜውን ጀብራሬ የሚያቆመው የለም እንደፎከረው ሐውልቱን ያነሳዋል፡፡ እኔም ፖለቲካ የብቻ ስራ አይደለም የምትለውን የጋሽ መስፍን(ፕሮፍ) ምክር ልቤን እያመመኝ ስለዋጥኩኝ ምንም የምለውጠው ነገር የለኝም እንደው በሆዴ እንዳይቀር ብቻ ይህን አልኩኝ፡፡ No comment!!!

10 comments:

  1. አልፎ አይቼውNovember 28, 2012 at 2:48 PM

    ውድ ወገኖቼ
    አሁንስ ምን እንሁን? መከራው ስደቱ ግፉ በዛ!!!
    እግዚዖ!እግዚዖ!እግዚዖ!
    እግዚዖ!እግዚዖ!እግዚዖ!
    እግዚዖ!እግዚዖ!እግዚዖ!
    እግዚዖ!እግዚዖ!እግዚዖ!

    ReplyDelete
  2. ዳንኤል ክብረት መርዶ እያረዳን ለወያኔ ጥፋት ቤተክርስቲያናችንን ሲያመቻች በተደጋጋሚ ታዝቤዋለሁ ከዚህ በፊት ያማህበረ ቅዱሳንን ስም ሰድቦ ላሰዳቢ/ ለመናፍቃን /አሳልፎ መስጠቱ ሳያንሰው በተለያየ ጊዜ ከሚያወጣቸው" እይታዋች"መካከል ለመጥቀስ ያህል 1ኛ በዋልድባ ለስኳር ፋብሪካ 14 ቤተክርስቲያኖችና ስለሴሎችም ስለሚፈርሱ ገዳማት አርድቶን ለወያኔም መንገስት ከቤተ ክህነት ጋር መምከር እንዳለበት መክሮ እኛንም አርድቶን ጠፋ 2ኛ የሰላምና የአንድነት ጉባኤን በተመለከተ እኛ የሌሌለንበት አይነት እና የአንድነትና የሰላሙንም አባላት ብቃት ጥያቄ ውስጥ ለማስገባት ሞክሯል:: 3ኛ አሁን ደግሞ ሀውልቱ አይፍረስ እንጂ “ሐውልቱ መነሳቱ ካልቀረ ቢነሳ ችግር የለውም” ተመልሶ በክብር ካስቀመጡት ወዘተ እያለ እሱን የሚሰሙ ክርስቲያኖችን ምንም ማለት አይደለም አይነት የወያኔን የቤተክርስቲያናችንንና የታሪክን የማጥፋት ዘመቻ አስቀድሞ አለሳልሶ በማሳወቅ ህዝቡ ለምን ብሎ እንዳይጠይቅ የሰላም አምባሳደርነቱን ስራ በመስራት ላይ ይገኛል:: በነገራችን ላይ ለቤተክርስቲያናችን መከፋፈል እንዲሰፋን በምእራቡ አለም በማህበሩ ስም በመዞር ቤተክርስቲያን እንድትከፋፈል በስደት ያሉትን አበው ከፍተኛ የጥላቻና የመዘርጠጥ ስብከት በመስበክ የተከበረውን ማህበረ ቅዱሳን በክፉ ስም እስከማስነሳት የጥፋቱን ዘመቻ ተያይዞት እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው :: እንግዲህ በጣም ሲበዛና የሀገርና የሀይማኖት ጉዳይ በመሆኑ እንደ ዳንኤል ክብረት አይነቱ ለምን? ተብሎ ሊጠየቅ ይገባል :: የሰው ስም ጠቅሶ መናገር የሚከብድ ቢሆንም ይሄ ሰው እንደ ልደቱ ሌላ አላማ ያለው ስለሆነ ማንኛውም የተዋህዶ ለጆች የዚህን ሰውየ ማንነት ተከታተሉልን አንዴ አውተር አንዴ የስነ መለኮት ተመራማሪ አንዴ ዲያቆን የመለኮት ሚስጢር ተካፋይ አንዴ በነፍሰ ገዳዩ ወያኔ የሰላም አምባሳደር አንዴ ሰባኪ ወንጌል ወዘተ

    ReplyDelete
    Replies
    1. asteyayet or Danielen mesadeb tefelgo new .Hulem ewenet tenagare ayewededem weyyyyyyyyyyyyyyyyy ken amelekaket alemenore

      Delete
    2. Danin yaqimun sertual wedefitm bemeselew menged yiseral. Ebakachihu Danin tewut. Ersu mebt yelewim ende? lemin atewutm. Yisrabet, yitsafibet please please. KE ERSU ANAT LAY WIREDU.Dani be gilts photown letifo eyetsafe new ante anononymous bileh tsifeh hageren ewedalehu atibelegn. Ahun yeminidebeqibet gize neber? Dani andi gileseb new. Yemeselewin yemetsaf mebt alew. MEBTU NEW. Esu eskinagerilih atebiq. Ante ke Anonymous wita ena tsaf.

      Delete
    3. Egziabher lehulum lebyestlen! betkerstianenm balbetu yetbkelen
      Yehulum sew asteyayet waga alew ena enastwel

      Delete
  3. ልክ የዚህ ኃውልት ነገር ሲነሳ መቼም ኢጣሊያንን የማያስታውስ ሀበሻ የለም:: በዕድሜ የገፋው በዓይኑ ካየውና በወቅቱ ከተከሰቱት ዘግናኝ ነገሮች እየተነሳ በአብዛኛው በአፈ-ታሪክ ደረጃ: በከፊል ደግሞ ገጠመኙንና ምልከታውን እንደ እነ ፊታውራሪ አመዴ ለማ: እንደ እነ አብዲሳ አጋ ወይም እንደ ጃጋማ ኬሎ ጽፎ ያስቀምጣል:: የቤተክርስቲያን ምሁራንም እንደየዕውቀታቸው በቁስም ይሁን በቅርስ ለዚህ ትዉልድ ያዩትን ከማስተላለፍ አልተቆጠቡም፤ እናም የአቡነ ጴጥሮስን ኃውልት ከእነዚህ ውስጥ እንደ አንዱ ልናየው እንችላለን::

    የእህል ውሃ ነገር ሆኖ ዛሬ ኢጣሊያን ላይ ሆኜ ይህንን ስሰማ ብዙ ጥያቄዎች ውስጤ ይመላለሳሉ፤ ዋናውና ነገር ግን አንድ ሥራ ሲታቀድ ወይም ንድፍና ቅየሳ ሲሰራ (design ማለቴ ነው)የቀብር ቦታዎች: መስጊዶች: ታሪካዊ ሥራ የተሠራባቸው አደባባዮች: ትላልቅ አገልግሎት የሚሰጡና መልሶ ለመተካት ወጪአቸው ከባድ የሆኑ ግንባታዎች ወዘተ መነካት እንደሌለባቸው ትምህርቱም ይጠቅሳል:: በተለይ ወደ ኢትዮጵያ ህግ ስንመጣ ለሙታን መታሰቢያ የሚሠሩ ሥራዎች ትልቅ አክብሮት የሚቸራቸው እንደሆነ የሚካድ አይደለም:: ስለ ኢጣሊያን ሲነሳ መቼም ኮሎሰዮም የሚባለውን ጥንታዊ የሮማዊያንን ግንብ የማያውቅ ጥቂት ነው፤ ወይም ዘ-ግላድያተር ፊልምን ያላየ ጥቂት ነው:: የሆነው ሆኖ ይህ ግንብ የተሠራው ከክርስቶስ ልደት በኋላ በአንደኛው መቶ ክፍለ ዘመን እንደሆነ ይናገራሉ ኢጣሊያኖች:: ከዚያ ወዲህ ከ1930 እ.ኤ.አ አዲስ የባቡር መንገድ ከመሬት ውስጥ ለውስጥ ሲዘረጉ በዚህ በኮለሰዮም ግንብ ሥር ማለፍ ግድ ሆነባቸውና አንዳች ነገር ግንቡን ሳይነኩ ከስር ቆፍረው ለማለፍ ችለዋል:: ዛሬ የሜትሮ አግልግሎት በሰፊው ከሚሰጠው መስመር አንዱ ይሄው ሜትሮ-ቢ (LINEA B) የሚባለው ነው::

    እንግዲህ የእኔ ጥያቄ እዚህ ላይ ነው:: ከውጪ ባለሙያ አስመጥተናል ካሉ የኢጣሊያኑ ሳሊኒ (የሕዳሴን ግድብ እየገነባ ያለው)አጠገባቸው ነው:: ሁለተኛ የየትኛውም ሀገር ሜትሮ ሲሰራ በመሬት ሥር የሚያልፍ ከሆነ 30-40 ሜትሮች ወደላይ የተንጣለለ ሕንጻ እንኳን እያለ ግንባታ ያካሄዳሉ ከሥር ግን በፍጹም አያነሱትም:: ምድር ላይ የሚያልፍ ከሆነ ደግሞ ከላይ በጠቀስኳቸው ምክንያቶች ይሄ ኃውልት መነካት አልነበረበትም:: ብቻ የእኔ ጥያቄ መንግሥት አጠፋ መንግሥት አለማ ከሚለው ጋ ሳይሆን ባለሙያ የተባሉት እንዴት ይሄንን ጉዳይ በዝምታ ማለፍን መረጡ?

    ReplyDelete
  4. devil had been thrown into garbage since the advent of our lord jesus christ.
    even though he is dead and thrown,he has still made us his servants.emancipation
    from his grip may not be easy unless we clean our hearts.tongues say many words.
    nothing is impossible for a tongue.but looking around is very important.devils
    servants are ready from in and outside to dismantle the nation.saying yes some times may help.being peaceful and patient is the lesson we have learned from
    our God.He will never leave us alone.we will be free soon to say a word for

    ReplyDelete
  5. ወገን እርስ በርስ ከመወቃቀስ እውነት የኦርቶዶክስ እምነታችንን ለመጠበቅ የሀገራችን ታሪክና ቅርስ ለመታደግ የሚያስችለን ቆራጥ የሆነ ተግባእር ለማድረግ መነሳት መቋቋም እንጂ ለታሪክ ጥፋት የተነሱብንን የወገን ጠላቶች አሉ አደረጉ እያልን እንሱም እስቲ የምታደርጉትን አሳዩን እያሉ የልብ ልብ አግኝተው በቁማችን ለመቅበር የተነሱት የዛሬ ሃያ ዓመት በመሆኑ ዛሬ ከመጨረሻው የታሪክ ውድመት በመድረስ የታላቁን ገዳም ዋልድባን አሁን የታልቁ አባታችን ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ቤዛ ሆነው ያለፉትን አቡነ ጴጥሮስን ታሪካዊ ዝክረ ሀወልት ለማፍረስ የሚደረገው ጥረት የለም ብለን ባንድነት ተነስተን የታሪክ ተምውጋቾች ሆነን ስንቆምና በተግባር ስናሳይ ብቻ ነው፡

    ReplyDelete
  6. Howdy! This is my first visit to your blog! We are a group of volunteers and starting a new initiative in
    a community in the same niche. Your blog provided us valuable information to work on.
    You have done a outstanding job!
    Review my web-site :: acne relief

    ReplyDelete
  7. Hello, I want to subscribe for this webpage to obtain
    most recent updates, therefore where can i do it please
    help.
    Feel free to visit my homepage ; immobilier

    ReplyDelete