Monday, November 9, 2015

ዛሬም በመተት ወይም ከጋኔን በመዛመድ ተአምራት የሚያደርግ ስለተገኘ ብቻ የእግዚአብሔር ነው ከማለት ልንታቀብ ይገባናል

ዲ/ን አባይነህ ካሴ
(አንድ አድርገን ጥቅምት 30 2008 ዓ.ም)፡-ከዘመነ ብሉይ ጀምሮ ጋኔንን በመዛመድ የማሳሳት እና የማምታት ድርጊት የሚፈጽሙ እንዳሉ መጽሐፍ ቅዱስ ምስክር ነው፡፡ ከመጽሐፍ ቅዱስ በላይ ሌላ ምስክር አያሻንምና እንደዚህ ያሉ ሰዎች ዛሬም በመኖራቸው ልንጠራጠር አይገባንም፡፡ ስልታቸውም ያው ተመሳሳይ እና ያልተለወጠ በመኾኑ እንግድነት አይሰማንም፡፡ ተመሳስሎ ማጭበርበር!


ጊዜው ከምንም በላይ አምርረን የምንዋጋው ሐራጥቃ ተሐድሶን የመዋጋት በመኾኑ በመምህራነ ወንጌል በኩል ይኽኛው ጉዳይ ችላ የተባለ የሚመስላቸው አልታጡም፡፡ ነገር ግን እናጠምቃለን እና አጋንንትን እናስወጣለን በሽታም እናድናለን ስለሚሉ ሰዎች በየጦማረ ገጹ (facebook) በተለያየ ጎራ ወግኖ መወራወር ይታያል፡፡ አንዳንዶች ቤተ ክርስቲያንን ትተው ለምን ሰውን የመከተል አዝማሚያ እንደሚታይባቸው ግራ ያጋባል፡፡ ለቅዱሳን የሰዎች ጥብቅና ረድቶ አያውቅም፡፡ ከብቃት የተገኘ ጉዳይ ከኾነ እግዚአብሔር መልስ ስላለው ብዙ መጨነቅ ባልተጋባ ነበር፡፡ ግን ምን ያደርጋል በድቡሽት ላይ ሲገነቡ ስለኖሩ ጥቂት ነፋስ ሲነካቸው ወልከፍከፍ ማለት ጀመሩ፡፡ ገና ሳይነኩ በጩኸታቸው ዓለምን አደነቆሩ፡፡ አንዲትም ዘለላ እውነት ስለ አጥማቂ ነን ባዮች የሚያውቁት ሳይኖር ሊከራከሩላቸው ፈቀዱ፡፡

ትኩረት ሊደረግ የሚገባውም ስለ አንድ ግለሰብ ጉዳይ ሳይኾን ተመሳሳዮች ብዙ አሉና ድርጊታቸው ከትምህርተ ቤተ ክርስቲያን አንጻር እንዴት ይታያል? የሚለው መኾን ይገባዋል፡፡ ስለዚህም ይህ የተጻፈው እገሌን ለማጥቃት ነው ከሚል ቁንጽል አስተሳሰብ ፈንጠር ብለን ከቃለ እግዚአብሔር ለመማር ራሳችንን እናቀርብ ዘንድ በትህትና እጠይቃለሁ፡፡ በእገሌ በኩል ተአምራት ተደርጎልናል ብላችሁ የምታስቡ ሰዎችም ብትኾኑ ሰከን ባለ ስሜት ውስጥ ገብታችሁ ከቃለ እግዚአብሔር እንድትማሩ እግዚአብሐየር ይርዳችሁ፡፡

ተአምር አድራጊነት የእግዚአብሔር ሰው የመኾን ማስረጃ ነውን?
ገቢረ ተአምራትን መፈጸም ብቻውን የእግዚአብሔር ሰው ለመኾን ማረጋገጫ አይደለም፡፡ ለዚህም ማስረጃ ይኾን ዘንድ የሚከተሉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች እንመልከት፡፡

. ሊቀ ነቢያት ሙሴን ለመገዳደር የሚከሩ የግብጽ ጠንቋዮች (መተተኞች)
ሊቀ ነቢያት ሙሴ የእግዚአብሔር መልእከተኛ መኾኑን ለፈርዖን ለማስረዳት በፊቱ በቆመ ጊዜ እርሱ የሚያደርገውን ገቢረ ተአምራት በማድረግ ለማናናቅ ጥረት ያደረጉ ግን ያልተሳካለቸው ሰዎች ነበሩ፡፡ ሊቀ ነቢያት ሙሴ በትረ አሮንን መሬት ላይ ቢጥላት እባብ ኾነች፡፡ ፈርዖን የጠራቸውም መተተኞች በትራቸውን ሲጥሉ እባቦች ኾኑ፡፡ ነገር ግን በትረ አሮንን የጠንቋዮችን እባቦች ሙሉ በሙሉ ጨረሰቻቸው፡፡ ዘጸ ፯፥፲-፲፪።

ደግሞም ሊቀ ነቢያት ሙሴ በግብጽ አገር ያለው ውኃ ሁሉ ደም እንዲኾን ሲያደርግ መተተኞችም እንዲሁ አደረጉ፡፡ እንዲሁም ወንዙም ጓጕንቸሮችን ያፈላል ብሎ ሲያዝዝ ነቢዩ እነርሱም ይኽንኑ አደረጉ፡፡ ዘጸ ፯፥፲፭-፰፥፯። ለአራተኛ ጊዜ ሊቀ ነቢያት ሙሴ የምድሩን ትቢያ በበትሩ ሲመታ አገር ምድሩ ቅማል በሚባል ተባይ ሲመታ የግብጽ ጠንቋዮች እንደቀድሞው ማድረግ ተሳናቸው፡፡ "ጠንቋዮችም በአስማታቸው ያወጡ ዘንድ እንዲሁ አደረጉ፥ ነገር ግን አልቻሉም" እንዲል፡፡ዘጸ ፰፥፲፰።

ይኸንን ያዩ የግብጽ ጠንቋዮች ራሳቸው ከአቅም በላይ እንደኾነ ተናገሩ፡፡ "ጠንቋዮችም ፈርዖንን፦ ይህስ የእግዚአብሔር ጣት ነው አሉት፤ የፈርዖን ልብ ግን ጸና፥ እግዚአብሔርም እንደ ተናገረ አልሰማቸውም።" ዘጸ ፰፥፲፱። ዛሬም ብዙ ሰዎች በእነ እገሌ "ገቢረ ተአምራት" ተለክፈው እነ እገሌ ራሰቻው ነገር ዓለሙን ትተው ሲኖሩ እያዩ ፈርዖን እምቢ እንዳለው እምቢ ብለው ይኖራሉ፡፡ መሸነፋቸውን በግልጥ እያዩ ካፈርሁ አይመልሰኝ ብለው ለያዥ ለገራዥ የሚያስቸግሩት ብዙ ናቸው፡፡ ይህ ግን ፈርዖናዊ ጠባይ ነው፡፡

ሊቀ ነቢያት ሙሴ ገቢረ ተአምራቱን ቀጥሎ ሻህኝ የሚባል ቁስል በሰው እና በእንስሳ ላይ እንዲኾን በእግዚአብሔር ታዘዘና አደረገ፡፡ እንዲህ ተብሎ እንደተጻፈ፡- "እግዚአብሔርም ሙሴንና አሮንን፦ እጃችሁን ሞልታችሁ ከምድጃ አመድ ውሰዱ፥ ሙሴም በፈርዖን ፊት ወደ ሰማይ ይበትነው። እርሱም በግብፅ አገር ሁሉ ትቢያ ይሆናል፥ በግብፅም አገር ሁሉ በሰውና በእንስሳ ላይ ሻህኝ የሚያመጣ ቍስል ይሆናል አላቸው። ከምድጃውም አመድ ወስደው በፈርዖን ፊት ቆሙ፤ ሙሴም ወደ ሰማይ በተነው፥ በሰውና በእንስሳም ላይ ሻህኝ የሚያወጣ ቍስል ሆነ። ጠንቋዮችም ቍስል ስለ ነበረባቸው በሙሴ ፊት መቆም አልቻሉም፤ ቍስል በጠንቋዮችና በግብፃያን ሁሉ ላይ ነበረና። እግዚአብሔርም የፈርዖንን ልብ አጸና፤ እግዚአብሔር ለሙሴ እንደተናገረው አልሰማቸውም።" ዘጸ ፱፥፰-፲፪።

አሁን ራሳቸውም ተዋረዱ፣ በቁስል ተመቱ፡፡ ራሳቸውን ማዳን የማይችሉ ግን ተአምራትን የሚያደርጉ አቅመ ቢስ መኾናቸውን ማየት ይቻላል፡፡ ጋኔናዊ ሥራቸው ውሎ አድሮ የሚመልስላቸው ብድራት ራስን መቅሰፍ ነው፡፡ የሰይጣን ውለታው ከዚህ በላይ ሊኾን አይችልምና አጋልጦ ሰጥቶ እርሱ ዘወር አለ፣ ብቻቸውን ቀሩ ራሳቸውም በቁስል መቅሰፍት ተበላሹ፡፡ ስለዚህ ዛሬም በመተት ወይም ከጋኔን በመዛመድ ተአምራት የሚያደርግ ስለተገኘ ብቻ የእግዚአብሔር ነው ከማለት ልንታቀብ ይገባናል፡፡
በሊቀ ነቢያት ፊት ለመቆም ያላፈረ ሰይጣን ዛሬ በእኛ ፊት በየጠበል ቦታው በቤተ እግዚአብሔር በማስመሰል ሂሳብ ለመቆም የሚገድደው ይመስላችኋልን? ሰይጣን እኮ እግዚአብሔር በሚመራው በቅዱሳን መላእክትም ጉባኤ ታድሞ ነበር፡፡ ኢዮ ፩፥፮። ልዩነቱ ቅዱሳን መላእክት ለይተው ስለሚያውቁት ስህተት አይፈጽሙም፡፡ እኛ ግን በማስመሰል ጥበቡ ለመደነቃቀፍ ቅርቦች ነንና "መንፈስን ሁሉ አትመኑ" ተባልን፡፡ ፩ኛ ዮሐ ፬፥፩።

ፈርዖንን ያሳሳቱ መተተኞች ዛሬም እኛን እንዳያሳስቱን መጠንቀቅ አለብን፡፡ ተአምራት አድርገውም ቢኾን እንኳ በማድረጋቸው ብቻ የቅድስና ቆብ ከመጫናችን በፊት ደግመን ደጋግመን እናስብ፡፡ የምንናገረው ስለአንድ ሰው አይደለም፡፡ በዚህ ተወስነን ዋናውን ጉዳይ ከማየት እንዳንታጎል መንፈሳችንን ወደቀናው በመምራት እናስተውል፡፡ ለሰዎች ሲባል መጽሐፍ ቅዱስ ሊቆነጻጸል አይችልምና፡፡


6 comments:

  1. ወንድሜ ስለምክርህ ቃለ-ሕይወት ያሰማልን፡፡ ብዙዎች እየተቃወማችሁ ነው፡፡ ተቃውሟችሁ የቤተክርስቲያንን ድምጽ ለማሰማት እያደረጋችሁ ያለውን ነገር ሳላደንቅ አላልፍም፡፡ በዚህ በአውሬው ዘመን ግድ ማስተዋል ያለብንን ነገር እየነገራችሁን ነው መልካም ነው ልትመሰገኑ ይገባል፡፡ ነገር ግን ወንድሜ እስኪ ምእመኑ እያሉ ያሉትንም እንስማ፣ እንደማመጥ፣ አንዳንዴ እናንተም ስሜታዊ እየሆናችሁ የምእመኑን ችግር ማዳመጥ አልቻላችሁም፡፡ ክርስትና በአንድ ልብ የሚጓዝበት መንገድ ነው፡፡ ከአባቶቻችን የተማርነው ይህንን እውነት ነው፡፡ እናንተ ዛሬ ቴክኖሎጂው ቅርብ ነው ብዙ ድካም አይፈልግም፡፡ ለምሳሌ ብናነሳ የመምህር ግርማ ትምህርትና የሌሎችም የፈውስ ጉባኤ በኢንተርኔት ላይ ቁጭ ብሏል፡፡ ድብቅ አይደለም፡፡ እንመልከተው፡፡ መርምሩትና አስተያየት ስጡበት፡፡ በዚህ መንገድ ደግሞ ተመልከቱት፡፡ የእናንተ የወንድሞቼ ትልቁ ችግር የምእመኑን ችግር መረዳትና ማዳመጥ አልቻላችሁም፡፡ እስኪ በዚህ ጉዳይ ጥናት ስሩበት፡፡ ልክ ተሀድሶን እንደሰራችሁበት ይህንንም ጉዳይ ስሩ፡፡ አለበለዚያ ቀጥታ ድፍንፍን ባለ መንገድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ እየጠቀሳችሁ ብቻ የምታስተላልፉት መንገድ በእውነት ምእመኑን ግራ ያጋባል፡፡ ለመናፍቃንና ለተሀድሶም መሳቂያ አታድርጉን፡፡ እኛ አህዛብን ማስተማር ያለብን መሆን ሲገባው ግን በመከፋፈልና በመሰዳደብ ቤተክርስቲያንን የቅዱሳን ሐይማኖት መሆኗ ቀርቶ የመሰዳደቢያ መድረክ አድርገነዋልና፡፡ እባካችሁ መደማመጥና፣ መናበብ እንቻል፡፡ የምእመኖቻችንንም ችግር እንመልከተው፡፡ በሕይወታቸው ያለውን ለውጥ እንመልከት፡፡ ብዙዎች ከተለያየ የሀጢያት ስፍራ ተነስተው እግዚአብሔርን ማምለክ ችለናል እያሉን ነው፡፡ ይህ ደግሞ የሚያስደስት ነገር ነው፡፡ አንድ ሰው እንኳን መመለስ በሰማይ ምን ያህል ደስታ እንደሆነ ወንጌል ታስተምራለች፡፡ ብዙዎች ግን እያሉን ያሉት ከነበሩበት የኃጢያት ስፍራ ተነስተናል እያሉን ነው፡፡ እናንተ የምትሉትና እነርሱ የሚሉት ጭራሽ አይገናኝም፡፡ ይህንን ሀሳብ ማስታረቅ ያለባችሁ ደግሞ እናንተው የቤተክርስቲያንን ድምጽ የምታስተላልፉ አገልጋየች የቤት ስራ ይመስለኛል፡፡ በደፈናው ምንም መረጃ በሌለው ነገር ተነስተን ደባብቀን የምናየውን ነገር ሁሉ የሰይጣን ነው የምትሉን ከሆን ካዲያ እግዚአብሔርን ስራ የት ነው የምንመለከተው????????????? ስለዚህ እንደእኔ እንደእኔ ስድቡንና ነቀፋውን ትተን መደማመጥ በምንችልበት መንገድ ግልጽና መረጃ ባለው ነገር ማስረዳትና ማስተማር ብትችሉ መልካም ነው የሚል አስተያየት አለኝ፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ማስተዋሉን ይስጠን፡፡

    ReplyDelete
  2. ewent blhale lega egezab her amlak ewntwen lhulachen eskgalslen dres mnkakefun ttan ewntwen endgalslenn wad lebanachen endenmals kaganent tsenow nsa endywatan atbkan ensaley! ydengle Maryam yasrat legwech bmulew? sytan ytafale thedes ytafal orthodox twhedow yabbale bkerb kan aman!!

    ReplyDelete
  3. man u have to see who u are before u right down about memhire girma.

    ReplyDelete
  4. this is a matter of fighting for his own livelihhod .Live him alone he is preaching for his worldly desires :Abba Girma is serving God & the laty of EOTC

    I guess he is a memeber of MK

    damn

    ReplyDelete
  5. ቤተ ክህነት ራሱ ያልደፈረውን የመተተኛ መሪጌቶችና ደብተሮች ጉድ መምሕር ግልጥልጥ አድርገው አፍረጠረጡት እኮ! እኮ የትኛው ሰባኪያነ ወንጌል ነው ዐውደ ነገስቱን በዐውደ ምሕረት ያቃጠለው??? ሁሉም ለራሱና ለቤተሰቡ እየፈራ ይህችን ጉዳይ ንክች አያደርጋትም። በመምሕርማ ጸጋ ከዲያብሎስ እስራት ተፈትተን በንስሐ ታጥበን ለቅዱስ ሥጋው ለክቡር ደሙ በቃን። እና እኛን የመሳሰሉ ሕያው ምስክሮችንስ ምን ልትሉን ነው? አልተፈጠሩም? Hallucination ነው??? ለሰይጣን አሰራር ይህን ያህል ቦታ መስጠት ከተካናችሁ ምነው ለመድኃኒዓለም ፈውስ ጥቂትዋን እንኳን ማመን ተሳናችሁ???!!!!

    ReplyDelete
  6. Dn. Ante erashe lemenkef aydel zare beerehin yanesahaw? Antena meselochih Egziabeher beseweyew laye adro seladane minew kire alachuhu? Esu endehon yemadan mengedu bizu new tastemirum yeneberew endezihe aleneber?

    ReplyDelete